TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቀለ⬆️ከክልላቸው ውጭ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #የተመደቡ የትግራይ ክልል ተማሪዎች #ደህንነት ያሳስበናል ያሉ የመቀለ ከተማ ነዋሪዎች፣ በሮማናት አደባባይ ሰልፍ አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የርብ መስኖ ግድብ ኘሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ ዛሬ ተመርቋል፡፡ ኘሮጀክቱ 28 ሺህ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ላሊበላ⬆️

በአማራ ክላዊ መንግስት በሰሜና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገፕው: በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የተመራውና ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ክቡር የአማራ ብ/ክ/መ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንድአርጋቸው እና
ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች የሚገኙበት ልዑክ ከስዓት በኃላ ላይ ወደ ላሊ-በላ በማቅናት የላሊ-በላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ጥበቃና ጥገና የሚገኝበትን ሁኔታ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፣

በቅድሚያም ቤተ-መድሃኒዓለም ሲጎበኝ በድንገት ለተሰበው የላሊ-በላ ህዝብ ንግግር ያደረጉት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ: "ላሊ-በላን የሚያክል ድንቅ የዓለምና የአፍሪካ ቅርስ: ለእኛ ደግሞ ከዚያም በላይ መኩሪያችንና መመኪያችንን ስለሆነ ደግመን መገንባት ባንችልም እንኳ መጠበቅ ግን ግዴታችን ነው" ብለዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አርጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬆️

"ዛሬ ማህበረ ቅዱሣን የአቡነ ጎርጎርዮስ ሥልጠና ማዕከል ለ14ተኛ ዙር በበጋው እና በክረምቱ መርኃግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች በቅድስት ሥላሤ አዳራሽ እያስመረቀ ይገኛል። ተማሪዎቹ የተማሩት
👉በገና
👉ማሲንቆ
👉ከበሮ
👉ልሳነ ግዕዝ ነው።
በመርኃግብሩ ላይ ወደ 1000 የሚጠጋ ሰው ተግኝቷል።"

©B ከሥላሤ ካቴድራል አ·አ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጀርባ ያለው አካል⁉️

አሁን አሁን በተደጋጋሚ የምንሰማው ለሚደርሱት ችግሮችና ለሚታዩት #ግጭቶች ማንነቱ #የማይታወቅ፣ በጀርባ #ተደብቆ የሚገፋ ሀይል
መኖሩ ነው፡፡ በግጭቶች ሰው ሲሞት፣ ፀጥታ ሲታወክ፣ አደጋ ሲደርስ፣ ከኋላ ሆነው አቀነባብረዋል የሚባሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች “አሉ” ይባላል እንጂ ማንነታቸው ይፋ ሆኖ ችግር ፈጣሪው አካል የሚታወቀው መቼ ነው ? ሁልጊዜ የማይታወቅ ተጠያቂ ማበጀት እያደር መተማመንን አያጎድልም ወይ ? በዚህ ዙሪያ የሸገር 102.1 ጋዜጠኛ ከባለሙያ ጋር ያደረገውን ቆይታ ከላይ አድምጡት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተገኘ‼️

አደጋ የደረሰበት የነዳጅ ቦቲ ህገ ወጥ መሳሪያ #ተገኘበት። ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ የነበረው የነዳጅ ቦቲ በገንዳውሀ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ኢንዱስትሪ መንደር በሚባል አካባቢ በትናትናው ዕለት ጥቅምት 17/2011 ዓ.ም ፍየል አድናለሁ በሚል ምክኒያት #በመገልበጡ አደጋ ደርሷል። በዛሬው ዕለት ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩና የወረዳው የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ፍተሻ መሰረት 97 ክላሽን ኮፍ 1291 የቱርክ ሽጉጥ እና 3 ብሬን መገኘቱን ከስፍራው ለመዘገብ ተችሏል።

ምንጭ፦ Metema wereda communication affairs office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ዛሬ በተካሄደው አየርላንድ #ደብሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንድም በሴትም ማሸነፍ ችለዋል።

በሴቶች የደብሊኑ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ መስራ ዱቢሶ 2:33:48 ፈጣኑን ሰዓት አስመዝግባ አሸንፋለች።

በወንዶች ፆታ በአውሮፖውያኑ 2015 ና በ2017 ደብሊን ማራቶንን 3ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አሰፋ በቀለ የዛሬውን ውድድር 2:13:23 በመግባት በቀዳሚነት አጠናቋል።

ምንጭ፦ ፋስት ረኒንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia