TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የምስራቅ #ወለጋ ዞን ፀጥታና አስተዳደር ሀላፊ አቶ #ታከለ_ቶሎሶ ለBBC Afaan Oromoo እንደተናገሩት፣ ከካማሸ ዞን የተፈናቀሉ 13 ሺ አባወራዎች በምስ/ወለጋ ዞን በሳስጋና በሃሮሊሞ ወረዳዎች በሚገኙ መጠልያ ጣቢያዎች ሰፍረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር⬆️

የጎንደር ከተማ #እስልምና ዕምነት ተከታዮች #የመስቀል በዓል በከተማዋ በድምቀት እንዲከበር ቀድመው ያደመቁት እነርሱ ናቸው፡፡ የመስቀል በዓል የሚከበርበትን ቦታ ቀድመው በማጽዳት #አንድነታቸው መቼም እንደማይላላ ያሳዩበት ነው፡፡ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትም ለከተማዋ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች #ምስጋናውን ችሯል፡፡ እውቅናም ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአለታ ጩኮ⬆️

"ሀይ ፀግሽ ይሄ የምታየው የኤጄቶ ህብረት በየወረዳው የሚያደርገውን ስብሰባ ላይ ጩኮ ከተማ ነው። የከተማውን ማህበረሰብ ሰብስበው አባቶች እየተወያዩ ነው እናም ትልቁ ሀሳብ ዘረኝነትን ማስቆም እና ነገሮችን በተገቢው መንገድ #ተወያይቶ መፍታት እንዳለባቸው እያወያዩ ነው።"

©Ha(ከጩኮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ #ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ህዝቦች እንኳን በፍቅርና #በአንድነት ለሚከበር የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን ብለዋል፡፡

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አካልና የምስጋና የሰላም ቀን ነው፣ የኦሮሞ ምኞት ፍቅር፣ ብልጽግና፣ ባህሉ ደግሞ አብሮነት ነው፤ ኦሮሞ ለምለም ይዞ ለፈጣሪ #ምስጋና ያቀርባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የሚተዳደርበት #የገዳ ስርዓት ለዘመናዊ ዴሞክራሲ መሰረት የሆነና ታናሽ ታላቅን አክብሮ ከተላቅ የሚመር፣ ታላቅ ደግሞ ታናሽን በማብቃት ስርዓትን የሚያስቀጥል ስርዓት መሆንም ዶ/ር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮን የኢሬቻ በትግል የተገኘውን ለውጥ የሚናስቀጥልበት፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በእኩልነት አገር የሚንመራበትና የገዳ ልምዶችን የሚንቀስምበት ጊዜ በመሆኑ ደስታችንን ድርብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ የዘንድሮ ኢሬቻ ባህላችንንና አንድነታችንን የምናጠናክርበት፣ የአባገዳዎች መልዕክት #የምንሰማበትና የምንተገብርበት ይሆናል የሚል ተስፋም አለን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በፖለቲካ አለላካከት #ልዩነቶቻቸን ሳይገድቡን በፍቅርና በአንድነት አብሮ ለመስራት የሚንመራረቅበት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

አሸናፊ ሀሳብ በመያዝ አንድነታችንን አጠንክረን፣ ለሰላም፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር፣ ለፌዴራሊዝምና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አብረን መስራት አለብን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ሰላማችንን ማስጠበቅ በእጃችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሰላማችንንና ባህላቸን በመጠበቅና በማስጠበቅ አገርን መገንባት አለብን፤ በኢሬቻ በዓል ላይ ሰላማችንን በማስጠበቅ ለዓለም ምሳሌ መሆን አለብንም ብለዋል፡፡

ዘመኑ በፍቅርን አቅፈን ጥላቻን የምናሸንፍበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Gondar University⬇️

Entry Announcement:

The University of Gondar official entry #dates are as follows:

SECOND YEAR STUDENTS & ABOVE: Meskerem 30 and Tikimit 1, 2011 ( e.c)

FIRST YEAR STUDENTS: Entry dates for freshmen will be announced in the near future.

Notice: Those second year and above students will be expected to come on the exact dates mentioned. The University of Gondar would like to remind all students to be on time!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ📌የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጥሪ ቀናችሁን ከተቋማችሁ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ወይም ከድህረገፅ ላይ ካላገኛችሁ እንዲሁም በማህተም የተደገፉ የማስታወቂያ ፅሁፎችን ካላያችሁ ልታምኑ አይገባም። በመሆኑንም የተጠራችሁበትን ቀን ለማወቅ ቀጥታ በዩኒቨርሲታያችሁ የፌስቡክ ገፅ እየገባችሁ አረጋግጡ። እንዲሁም የተማሪ ህብረት ተወካይ ስልክ እና የሬጅስትራር ቢሮ ስልክ ቁጥሮችን መያዝ ባህላችሁ አድርጉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወላይታ ሶዶ⬆️

ዛሬ መስከረም 19/2011 ዓ.ም የወላይታ ብሔር የባህል ታሪክና ቋንቋ #ሲምፖሲየም መካሄድ ጀምሯል። ሲምፖዚየሙ የተጀመረው በ2010 ዓ.ም በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ህይወታቸውን ላጡ የወላይታ ብሔር ተወላጆች የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው፡፡ ሲምፖዚየሙ ከመጀመሩ በፊት በዞኑ በ2010 በጀት ዓመት የተከናወኑ አበይት ክንውን የፎቶ ግራፍ ኤግዝቢሽን በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ መምሪያ ኃላፊ በአቶ #ደገቱ_ኩምቤ ተከፍቷል፡፡

ምንጭ፦የወላይታ ዞን ባህል፣ ቱሪዝም እና መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tivahethiopia
ከኮፈሌ⬆️

"የኦሮሞ ታጋዮች ከ25 አመት በኋላ ወደትውልድ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ኮፈሌ ላይም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። Qabsaa'ota oromoo ejoolle kofelee waggaa 25 booda gara biyya abbaa esaaniitti deebianiiru"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች አባላት እና ደጋፊዎች #ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል። አባላቱ በድሬዳዋ ቆይታቸው ከከተማው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ይደርጋሉ።

©አሰግድ ከድር(Dire Dawa Mass Media Enterprise)
@tsegabwolde @tikvahethiopia