TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅማ⬆️የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለODP ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለፁ ይገኛል።

ከተያዙት መፈክሮች መካከል፦

.Xawalwaallee Kana booda Maqaa Oromoon Wilwill Jeedhuun Siif hin Eeyyamamu!

(ጠወልዋሌ ከአሁን በኋላ በኦሮሞ ስም ውል ውል ማለት አይፈቀድልሽም!)

.Oromoon Biyya ijaara Malee Hindiigu!

(ኦሮሞ ሀገር ይገነባል እንጂ አገር አያፈርስም)

.Oromoon Hammachuu malee Ariyachuu hin beeku!

©ካሱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል በአዲስ አበባ ስላለው የወጣቶች ወደ ጣቢያዎች መወሰድ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ከሰአት #መግለጫ ይሰጣል ብለዋል።

©ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን #በሌብነት እንጂ በአፈሳ ያሰርኩት ወጣት የለም ሲል ተናግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fana Live! የአዲስ አበባ ኮሚሽን መግለጫ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Walta Tv Live! የአዲስ አበባ ኮሚሽን መግለጫ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቢሾፍቱ⬇️

"በመጪው እሁድ መስከረም 20 ለሚከበረው የእሬቻ በአል ከአሁኑ የኦሮሚያ ፖሊስ ዝግጅት እያረገ ይገኛል። በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ ከባድ የሆነ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል። ህብረተሰብም ከኦሮሚያ ፓሊስ ጎን ነው። H.T ነኝ ከቢሾፍቱ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለጋምቤላ‼️

በጋምቤላ ያለውን ጉዳይ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ነዋሪዎች እየጠየቁ ናቸው። ችግሮች ሰፍተው ከፍተኛ ጉዳት እንዳይከሰት የሚመለከተው አካል አፋጣኝ የሆነ መፍትሄ ሊሰጥና ችግሩ ሊፈታ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ⬇️

በሀዋሳ ከተማ ስጋት ለመፍጠር ሙከራዎች እየተደረጉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ አከባቢውን #በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በከተማዋ ከሰሞኑ የተፈጠረውን የፀጥታ ስጋት ችግር ለመቅረፍ የከተው የፀጥታ አካላት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ፖሊስ አክሎ ገልጿል።

የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በሰጡት መግለጫ፥ በሀዋሳ ከተማ ማንነታቸውና አላማቸው ያልታወቁ አካላት የከተማውን ነዋሪ ላይ #ስጋት ለመፍጠር ያልተጨበጠ የስነ-ልቦና ጦርነት ከፍተዋል ብለዋል።

ባለፉት 3 ቀናትም ምሽትን ተገን በማድረግ የተለያዩ ቀለማትን በግለሰቦች በር እና አጥሮች ላይ በመቀባት ነዋሪው ላይ ጥርጣሬን መፍጠሩን ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ተናግረዋል።

ተግባሩም ለውጡን በማደናቀፍ የህዝቦችን በአንድነት የመኖር እሴት ለማፍረስ ሆነ ተብሎ የተደረገ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አረጋግጧል ብለዋል።

ቀለም የሚቀቡትን አካላት ፖሊስ #በቁጥጥር ስር ለማዋል ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ ምንም የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር ግን የጸጥታው መዋቅር አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ እንዳለም ነው የገለጹት።

የተቀቡት ቀለሞች ግን ሁሉም ቤቶች ላይ በመደረጉ #ብሄር ተኮር ባለመሆናቸው ህብረተሰቡ በዚህ ሆነ ተብሎ የከተማውን ሰላም ለማወክና በቀጣይ የሚካሄደውን የደኢህዴን ጉባኤ ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረትን ሊያወግዝና ሊያጋልጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወቂያ📌ኢትዮ ላይፍ ሪል ስቴት(Ethio Life Real Estate)
>የግንባታ ቦታ - ቦሌ(ወሎ ሰፈር)-Bole,Wollo sefer
>0920725945 & 0910931987
>ለቢሮ, ለሱቅ, ለሬስቶራንት, ለሾው ሩም እና የመኖሪያ አፓርታማዎች G+16
>የግንባታ ደረጃ - 15ኛ ፎቅ
>ስራ ተቋራጭ- ባማኮን ኮንስትራክሽን
____ከ8 ካሬ እስከ 180ካሬ አለ_______
በ 510,000ብር ብቻ ቦሌ ላይ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!
አፓርታማ-
ባለ 2 መኝታ-128 ካሬ, 133 ካሬ, 144ካሬ
ባለ 3 መኝታ-166 ካሬ, 186 ካሬ, 187ካሬ
****ቅድመ ክፍያ 30% ብቻ*****
Building Facilities
> 6 Elevators
> Escalators
> Open down
> Circulation area
> 3 floor underground parking
> And many more modern technologies
*Your life time property*
ASTU_.pdf
776.3 KB
AASTU.pdf
830.7 KB
የፈተና ውጤት⬆️በሳይንስ እና ቴልክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመመግባት ፈተና የተፈተናችሁ ውጤታችሁን ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ ከተማ⬆️

በከተማዋ #ብሔር ተኮር መጠራጠር እንዲሰፍን በበሮች ላይ ቀለም በመቀባት የተሰራው ስራ በህብረተሰቡ እና በመንግስት ንቃት መክሸፉን የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ #ስኳሬ_ሹዳ ገለፁ፡፡

ምክትል ከንቲባው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከፊታችን ባለው መስከረም 17 ለሚከበረው የመስቀል ባዓል ለመላው የእምነቱ ተከታዮች #የእንኳን_አደረሳችሁ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

ከመስከረም 18 እስከ 21 በሀዋሳ ከተማ ለሚካሄደው የደኢህዴን 9ኛ ጉባኤ እንዲሁም ከመስከረም 23 እስከ 25 ‹‹በልማታዊ ዴሞክራሲ ማዕቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴያችንን በማስቀጠል የኢትዮጵያን ህዳሴ እናረጋግጥ›› በሚል መሪ ቃል በከተማዋ ለሚካሄደው የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ ለመላው የድርጅቶቹ አባላትና ደጋፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

በከተማችን ባለፉት 3 ቀናት በተለያየ አካባቢ በተለይም በታቦር፣ በምስራቅና በመናህሪያ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ቀለሞችን በመኖሪያ ቤት በሮች ላይ #በመቀባትና ቀለሙን ተከትሎ የብሔር ግጭት ሊኖር እንደሚችል በማስመሰል በተነዛ ወሬ የከተማዋ ህዝብ መጠነኛ ጭንቀት ውስጥ እንደገባ ይታወቃል፡፡

ይህን አአስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ ከክልሉና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ #የፀጥታ ጥበቃና የጥናት ስራ ሲሰራ መቆየቱን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት በከተማው በግለሰቦች መኖሪያ ግቢ በሮች ላይ የተቀባ ቀለም መኖሩን ማረጋገጥ እንደተቻለም አቶ ስኳሬ ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ቀለሞች አንደኛው የከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት የቤቶች ደረጃ ምዝገባ ስራ ክፍል የቀባው ሲሆን ሁለተኛው በከተማዋ በቆሻሻ ማንሳት ስራ የተሰማሩ ማህበራት ገንዘብ የከፈሏቸውን ነዋሪዎች ካልከፈሉት ለመለየት የቀቡት መሆኑን ለመለየት እንደተቻለ ምክትል
ከንቲባው ገልፀዋል፡፡

ከዛ ውጪ የተለየ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ህዝቡን ለማሸበርና የከተማዋን ገፅታ ለማጉደፍ እንዲሁም በህዝቦች መካከል መተማመንና አብሮነት እንዳይኖር በማድረግ ብሔር ተኮር ጥርጣሬ ለማሳደር የቀቡት ቀለም መኖሩንም ለማረጋገጥ ተችሏልም ብለዋል፡፡

በሀገር ደረጃ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳይቀጥል ለማድረግና እንዲቀለበስ ፍላጎት ያላቸው ሀይሎች በተለያየ ጊዜና ቦታ ሲያደርጉት ከነበረው እንቅስቃሴ አንዱ እንደሆነም #ለመረዳት እንደተቻለ አቶ ስኳሬ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም በተደረገው ክትትል ወቅት እኩይ ተግባር ማስፈፀሚያ የሆኑና ገንዘብ የሚከፈላቸው በልመና መስክ የተሰማሩ ጥቂት ግለሰቦች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት መክትል ከንቲባው ከእነርሱ ውጭ ከሌላ አካባቢ በመምጣት አልጋ
በመከራየት ስለት ነገሮችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ፀጉረ ልውጦች መኖራቸውንም በመጠቆም ነው፡፡

ቀለም በበራቸው የተቀባባቸው ነዋሪዎችም ያለምንም ልዩነት አልፎ አልፎ የተቀባባቸው መሆኑም ተረጋግጧል፡፡ በዚህም በከተማው
የሚኖሩ የደቡብ ብሔረሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ በሚገኙ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በር ላይም መቀባቱ ተረጋግጧልም ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡

እነዚህ አካላት ላይ በመደረግ ላይ ያለው ምርመራ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ነው ያሉት አቶ ስኳሬ በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ሀይሉና ህብረተሰቡ በአንድ ላይ በመሆን አከባቢውን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ ከተራ ሽብር እና ወሬ በስተቀር የተከሰተ አንዳችም ችግር አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ከፊታችን ያለው የመስቀል በዓልም ይሁን በጉጉት የሚጠበቀው የደኢህዴንና የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤን በከተማዋ ለማክበር ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንደማይገጥም ገልጸው የከተማው ነዋሪዎችና ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች ስጋት እነዳይገባቸው
አሳስበዋል፡፡

ውበት ለከተማችን፤ ስኬት ለህዝባችን…!

©የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስአበባ ሰሞኑን እየታየ ካለው አፈሳ ጋር ተያይዞ የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽነር ሜጀር ጄኔራል #ደግፌ_በዲ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

▪️በአዲስአበባ በሰሞኑ ግጭቶች 28 ሰዎች ሞተዋል፣

▪️በአብዛኛው ሰዎች የሞቱት ከሆስፒታል በተገኘ መረጃ መሰረት በድብደባ ነው፣

▪️7 ያህሉ በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሲሆን አምስቱ የሞቱት በቂርቆስ አካባቢ ነው፣ አንዱ በስህተት የተገደለ ነው፣ አጥፊው ተይዟል፣

▪️በርካታ ሰዎች ብንይዝም አብዛኛውን እየመከርን፣ እያስተማርን ለቀናል፣በአሁኑ ሰዓት 1 ሺ 204 ሰዎች በጦላይ
በእስር ላይ ይገኛሉ፣

▪️174 ያህሉ በሕግ የሚጠየቁ ናቸው፣ ቀሪዎቹ ተገቢው ትምህርት ተሰጥቷቸው ይለቀቃሉ፣

▪️ባንኮችን ለመዝረፍ ተሞክሯል፣ ቤቶች፣ ሱቆች ተደብድበዋል፣ መኪኖች ተቀጥቅጠዋል፣

▪️1 ሺ 459 ሺሻ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል፣

▪️31 ሰዎች ከቁማር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለዋል፣

▪️94 የማስቃሚያ ቤቶች ተይዘዋል፣

▪️በአ/አ ሕገወጥነት፣ዘረፋ እየተስፋፋ ነው፣ መኪናም ጭምር በጠራራ ጸሐይ ይዘረፋል፣

▪️ከክልል ጭምር የተደራጁ (ከጎንደር፣ ከደሴ፣ ከአርባምንጭ) ቡድኖች አ/አ ውስጥ እየዘረፉ ነው፣

▪️25 ጊዜ የዘረፈ ግለሰብ ተይዟል፣

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ በፒያሳ፣ በለገሐር፣ በአውቶብስ ተራ፣ በሜክሲኮ፣ በችርችል ጎዳና፣ በመገናኛ፣ በ 22፣ በቦሌ፣ በመድሃኒያለም፣ ሸጎሌ፣ አስኮ፣ በጦር ሃይሎች፣ በሶማሌ ተራ፣ ...በርካታ የአዲስ አበባ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ የታክሲ #እጥረት ተከስቶ እንደነበር ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰንደቅ አላማ ቀን⬆️

በዜጎች መካከል ብሄራዊ መግባባት የተደረሰበት ሰንደቅ ዓላማ እንዲኖር ለማድረግ በቀጣይ ሰፊ #የውይይት መድረኮች እንደሚዘጋጁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል።

ምክር ቤቱ ዘንድሮ ለ11ኛ ጊዜ ጥቅምት 6 ቀን 2011 “ሰንደቅ ዓላማችን ለዲሞክራሲያዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ሐሳብ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ተሰጥቷል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia