TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ የሃይማኖት
ተቋማት ጉባዔ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶች እና ስርዓት አልበኝነት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ኤፍሬም ወልደኪዳን በጊዜያዊነት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ሁከት ለተፈናቀሉ እና #በቀብሪደሃር ለሚገኙ ሕፃናት አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ #ዛሬ ረፋድ እንደተላከ ተሰምቷል፡፡ በሌላ በኩል #በደገሃቡር ላሉ ተፈናቃዮችና የችግሩ ተጠቂዎች ግን እስካሁን በመንግሥት በኩል የተደረገ ምንም አይነት ድጋፍ እንደሌለ ለመስማት ተችሏል፡፡

©Sheger 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቴፒ⬆️

በቴፒ ከተማ በተፈጠረ አለመረጋጋት የንግድ ተቋማት እደተዘጉ እንዲሁም ከተማው ውስጥ ውጥረት መንገሱን በቴፒ የሚገኙ የቻናላችን ቤተሰቦች ተናግረዋል። የፀጥታ ሀይሎችም ሁኔታውን ለማርገብ ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ገልፀዋል።

*ለተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት በሆነው ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማጣራት አድርጌ ትክክለኛ መረጃ አቀርባለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍት የስራ ቦታ⬆️የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ እየገነባ ያለውን ሆስፒታል ስራ ለማስጀመር ባሉት ክፍት የስራ መደቦች ላይ የሰው ሀይል ለመቅጠር ይፈልጋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update⬆️የኢትዮጵያ ኳስ ዛሬም ጉድ እያሰማን ነው። ዛሬ ከፍተኛ ሊጉ 28ኛ ሳምንት ቡታጅራ ላይ ጅማ አባቡናን ከቡታጅራ ከተማ አገናኝቶ ነበር በጫወታውም መጨረሻ ላይ የቡታጅራ ደጋፊዎች የጅማ አባቡናን ተጫዋቾች ደብድበዋል ይለናል የጅማ ማህበረሰብ ራድዮ።

በሌላ በኩል ከደጋፊዎች እና ከራድዮ ጣቢያው እንደተሰማው⬇️

◾️አምበሉ ጀሚል ተደብድቦ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ኦዚልም በደጋፊዎች ተፈንክትዋል ሌሎቹ በፖሊስ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው ይላል ራድዮ ጣቢያው።

በሌላ በኩል ዳኞች ላይ ማስፈራሪያ ደርሷል ተብሏል። ቡታጅራ 2-1 ጫወታውን እየመራ እንደነበር እና በ79ኛ ደቂቃ ይህ እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል።

©የጅማ ማህበረሰብ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሳሪስ ዘንባባ አካባቢ በአብስራ ግሮሰሪ አስተባባሪነት "አንድ ውሀ ለአንድ ወገኔ" በሚል በጅግጅጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መልካም ስራ እየተሰራ ይገኛል።

©ዮኒ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጊብሰን አካዳሚ⬆️

"ሰላም ፀግሽ የጊብሰን ዩዝ አካዳሚ አስተማሪዎች በዛሚ 90.7 FM እና Ahadu FM ላይ በት/ቤቱ የሚደረሸስባቸውን በደል እና በትምህርት ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎች የሀገራቸውን ባህል እንዳያውቁ እየተደረጉ መሆናቸውን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ ይህንንም ተከትሎ አስተያየት የሰጡ መምህራንን ት/ቤቱ ያለ ምንም የህግ አግባብ እያባረረ ይገኛል፡፡ ስሜ ለጊዜው አይገለፅ፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዳህላክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች። ኤርትራ ፕሬስ እንደዘገበው #ዳህላክ ደሴት 4.8 ሬክታር ስኬል በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታለች። እስካሁን በሰውም ላይም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም።

©Yirgu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መጪው አዲስ ዓመትን ለማክበር ወደ ሀገራቸው ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የ25 በመቶ የዋጋ ቅናሽ እና የተለያዩ ማበረታቻዎችን ለማድረግ አየር መንገዱ፣ ሆቴሎች፣ አስጎብኚዎች እና ሌሎች የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቃል ገብተዋል።

📌ይፋ የተደረገው ቅናሽ ከነሀሴ 9 እስከ መስከረም 20 ድረስ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

የ25 በመቶ ቅናሹ፦
◾️የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ በረራዎች የትኬት ሽያጭ ላይ፣
◾️ሆቴሎች በመኝታ አገልግሎት
◾️አስጎብኚዎች ደግሞ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ሕወሐት⬇️

ሕወሐት ከቀናት በኋላ በሚያካሂደው ድርጅታዊ ጉባዔ በርካታ አንጋፋ አመራሮችን በማሰናበት ወጣቶችን ወደ ኃላፊነት ለማምጣት መወሰኑ ተገልጿል፡፡ በምንገኝበት ነሐሴ ወር በሚካሄደው 13ኛው የሕወሐት ድርጅታዊ ጉባዔ የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የማዕከላዊ ኮሚቴ ተመራጭ በኃላፊነት የሚቆየው ለአራት ጠቅላላ ጉባዔ ማለትም ለስምንት ዓመት ብቻ ሲሆን፣ ዕድሜው ከ65 በላይ የሆነ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መመረጥ አይችልም፡፡ የሕወሐት ሊቀ መንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ትናንት በሰጡት መግለጫ “ሕወሐት ሕገ መንግሥትን መሰረት ላደረገ የለውጥ ጉዞ ደጋፊ እንጂ እንቅፋት አይሆንም” ብለዋል፡፡

©WazemaRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ እና የአፋር አክቲቪስቶች አቶ ጋአዝ አህመድን ጨምሮ ሌሎች ነገ ጧት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይገባሉ።

©BBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰማያዊ፣ ኢራፓ፣ መኢአድና ሌሎች ፓርቲዎችን ያሰባሰበው “የብሔራዊ መግባባትና ዕርቀ ሠላም ኮሚቴ” በአዲስ አበባ ፓርቲዎችን
ለምክክር ጠርቷል፡፡ ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት መላኩ መሰለ “በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ችግር በተናጠል ወይም በቡድን መፍትሔ ከሚሰጥበት አቅም በላይ በመሆኑ ተሰባስቦ መፍትሔ መፈለግ ይገባል” ነው ያሉት፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች የሠላም ጥሪ ቢያደርግም በየቦታው የሚታዩ ግጭቶች አስነዋሪና #ዘግናኝ ባሕሪያትን እየያዙ በመምጣታቸው ስብሰባው በአስቸኳይ መጠራቱን አስተባባሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡

©ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia