TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.5K photos
1.59K videos
216 files
4.34K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ምን ያህል ተቃጥሎ ምን ያህል እንደቀረ አላወቅንም። እሳቱ ከባድ ነበር። ኮሚቴ ተልኳል ” - የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በበደሌ ከተማ የሚገኝ ከተሰራ አመት የሆነው መስጂድ ምክንያቱ እስካሁን ባልታወቀ ሁኔታ በእሳት መቃጠሉ ተሰምቷል። “ ቡልቲ አዳ” የተሰኘው መስጂድ “ሙሉ ለሙሉ በእሳት” መቃጠሉን የተመለከተ መረጃም በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል። …
#Update

“ መስጂዱ ሙሉ ለሙሉ ነው የተቃጠለው። ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገ ነው ” - ኮሚቴው

በቡኖ በደሌ ዞን የበደሌ ከተማ “ቡልቲ አዳ” መስጂድ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰበት፣ የቃጠሎውን ምክንያትና መጠኑን ለማረጋገጥ ወደ ስፍራው ኮሚቴ ተልኮ እንደነበር የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጾ ነበር።

በዚህም ምክር ቤቱ በወቅቱ በሰጠን ቃል፣ ቃጠሎው መፈጸሙን ገልጾ፣ “ ምን ያህል ተቃጥሎ ምን ያህል እንደቀረ አላወቅንም። እሳቱ ከባድ ነበር። ኮሚቴ ተልኳል ” ነበር ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የመስጂዱ ቃጠሎ ምክንያት ታወቀ ? መስጂዱ ሙሉ በሙሉ ነው የተቃጠለው ? ሲል ዛሬ ወደ ስፍራው የተላከውን ኮሚቴ ጠይቋል።

ኮሚቴው ምን መለሰ ?

“ በቃጠሎው ተጠርጥረው በቀጥጥር ስር የዋሉ አሉ። እስካሁን ምርመራ ላይ ናቸው። ከቃጠሎው ጀርባ ያለው ምክንያት አልታወቀም። ምናልባት ግን ‘ሰዎቹ የአእምሮ ችግር ያለባቸው ናቸው’ እያሉ ነው።

‘እኔ ነኝ ጉዳዩን የፈጸምኩት’ ብሎ የተያዘ ሰው አለ። አንድ ሁለት ሰዎች ተይዘዋል። አሁን ተረጋግቷል። ተማሪዎቹም ወደ ትምህርታቸው ተመልሰዋል። ከክልልም ከዞንም ዛሬ መጥተው ልጆቹን አወያይተዋል።

መስጂዱ ሙሉ ለሙሉ ነው የተቃጠለው። ይህ መስጂድ ተትቶ ሌላ መስጂድ እንዲሰራ የመንግስት አካል ፈቅዷል። የተቃጠለው መስጂድ ተሰርቶ ያለቀ ነበር። አሁን ሌላ መስጂድ መስራት ሊጀመር ነው ” ብሏል።

የመስጂዱ የአዳሪ ትምህርት ቤት ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጪ ስለሆነ እንዳልተቃጠለ፣ በዚህም ወደ 300 የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ ኮሚቴው ገልጿል።

መስጂዱ ከመሰራቱ በፊት የአሁኑን ጥቃት ሊያደርስ የሚችል የተፈጠረ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር ? ስንል ለኮሚቴው ጥያቄ አቅርበናል።

ኮሚቴው፣ “ አሁን እኛም ጠይቀን ነበር። ችግር እንዳልነበር ነው የተነገረን። እንደዛ የሆነ ነገር አልነበረም። ግን አሁን ሙሉ ለሙሉ እንደዚህ ነው ብለን ለማብራራት ምርመራው ገና እየቀጠለ በመሆኑ ማረጋጠጥ የቻልነው ነገር የለም ” ሲል መልሷል።

በወቅቱ ሲሰራ ከዞን አስተዳደር ተፈቅዶ እንደሆነ መረዳቱንም ገልጿል።

መስጂዱ ሲሰራ ምን ያህል ወጪ እንደጨረሰ ላቀረብነው ጥያቄ ኮሜቴው በሰጠን ምላሽ፣ የወጪውን መጠን እንዳልጠየቀ፣ ሆኖም በተማሪዎች መዋጭ ከተጀመረ በኋላ ህብረተሰቡ ተጨምሮበት ተውጣጥቶ የተሰራ እንደነበር ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
💔561517😭106😡54👏48🕊29🤔21🥰10😢9🙏8
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሜክሲኮ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፖሊሲ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚወስዱት የፈዴራል ፖሊሶች ነግረውን ወደዚያ እየሄድን ነው" - ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ። የቀድሞ ሰላም ሚንስትር ደኤታ አቶ ታዬ ዳንዳዓ ዛሬ ጠዋት ከችሎት በኃላ ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ገለፁ። የአቶ ታዬ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ከጠዋት የችሎት ቀጠሯቸውን ተከታትለው…
#Update

አቶ ታዬ ደንዳዓ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነፃ የተባሉባቸው ሁለት የክስ ጭብጦች ተሻረ።

የአቶ ታዬ ዳንዳዓ የህግ ጥበቃ አበራ ንጉሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት " የፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ታዬ ነፃ የተባሉባቸው ክሶችን በመሻር እንዲከላከሉ ትዛዝ ሰጥቷል " ብለዋል።

" የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀር ሽብር እና ህግ መንግስት ጉዳዮች ችሎት 30/12/2016 ዓ/ም አቶ ታዬ ከተከሰሱባቸው ሶስት ክሶች ውስጥ አንደኛው ፤ ' በመንግስት ሀላፊነት ላይ እያሉ የህዝብ እና የመንግስት የተሰጣቸውን ሀላፊነት ወደ ጎን በመተው የፀር ሰላም ሀይሎች ሀሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማሰብ በግል ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የታጠቁ ሃይሎችን የሚደግፍ መልዕክት አስተላልፈዋል ' የሚለውን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነፃ ተብለው ነበር " ብለዋል ጠበቃቸው።

አክለውም የዋስትና መብታቸው በሰበር ሰሚ ችሎት ከተጠበቀላቸው በኃላ ከህግ ፍቃድ ውጭ የጦር መሳሪያ ይዘው መገኘት የሚለው አንዱን የክስ ጭብጥ እንዲከላከሉ በተሰጠው ብይን መሰረት በከፍተኛ ፍርድ ቤት እየተከታተሉ ነበር።

ሆኖም ዛሬ አቶ ታዬ ነፃ በተባሉበት ክስ ጭብጦች ላይ ቅሬታ እንዳለው የገለፀው አቃቤ ህግ " ተከሳሹ በቂ ማስረጃ ቀርቦባቸው መከላከል ሲገባቸው ነፃ መባላቸው አግባብነት የለውም " በማለት ለፈዴራል ጠቅላይ  ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ወንጀል ህግ አንቀጽ 251/ሐ ጠቅሶ ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ነፃ የተባሉበትን ክሶች ብይን ሽሮ እንዲከላከሉ አዟል።

ጠቃቸው አቶ አበራ ንጉሱ ፤ ለውሳኔ ብቻ ዛሬ በአምስተኛ ተለዋጭ ቀጠሮ መገኘታቸውን ጠቅሰው ችሎቱ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮ እንዲከላከሉ ብይን በመስጠቱ ቅሬታ እንዳላቸው ገልፀው በቀጣይ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ እንደሚሉ ገልፀዋል።

ይሁንና ደንበኛቸው ችሎት ተከታትለው ከተለያዩ ከቀትር በኃላ 10:00 በፌደራል ፖሊስ መወሰዳቸውን ከአቶ ታየ ባለቤት በስልክ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
792😡336😭66🤔40😢33🕊18👏15💔13😱9🙏8🥰6
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ታዬ ደንዳዓ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነፃ የተባሉባቸው ሁለት የክስ ጭብጦች ተሻረ። የአቶ ታዬ ዳንዳዓ የህግ ጥበቃ አበራ ንጉሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት " የፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ታዬ ነፃ የተባሉባቸው ክሶችን በመሻር እንዲከላከሉ ትዛዝ ሰጥቷል " ብለዋል። " የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀር ሽብር እና ህግ መንግስት…
#Update

አቶ ታዬ ደንደአ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤት አዘዘ።

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው እንዲከታተሉ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፖሊስ አቶ ታዬን ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም የተዘጉ ሁለት ክሶችን ጨምሮ መዝገቡ በፍርድ ቤቱ እንዲቀሳቀስ ጠይቋል።

አቶ ታየ ደንደአ ለፍርድ ቤቱ " ትናንት የተያዝኩበት መንገድ ልክ አይደለም የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቼ ተይዘዋል፤ ከጠበቃዬ ጋር ተማክሬ መቅረብ ነበረብኝ " በማለት ተከራክረዋል።

የግራና ቀኙ ክርክር የመረመረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት የተከሳሹ የዋስትና መብት እንዲነሳ ወስኗል።

ተከሳሹ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ በመስጠት የመከላከያ ምስክርን ለመስማት ለሰኔ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

የአቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ምን አሉ ?

" ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ነግሮኛል " - ወይዘሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

አቶ ታዬ ደንዳዓ ዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ባለቤታቸው ወይዘሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ስንታየሁ እንደተናገሩት አቶ ታዬን ዛሬ ጠዋት ለመጠየቅ ወደ ፈዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዳመሩና ለሰዓታት ጠብቀው እንዳገኙዋቸው ገልፀዋል።

አቶ ታዬም ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበሩና የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው በማረምያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ መደረጉን ነግሮኛል ብለዋል።

ወ/ሮ ስንታየሁ አክለውም ባለቤታቸውን አቶ ታየን ለምን እንደታሰረ ሲጠይቁት ዛሬ ፍርድ ቤት በነበረው ችሎት ፖሊስ ለፍርድ ቤት ሲያስረዳ " አቶ ታየ እየሸሹ እያሉ በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ " ማለቱን ነግሮኛል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ዛሬ ያለ ህግ ጠበቃቸው ፍርድ ቤት እንደ ቀረቡ እና እስካሁንም ከጠበቃቸው ጋር እንዳልተገናኙ ባለቤታቸው ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
559😢501😡137😭40🤔36👏19🕊15🙏8😱5🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፍትሕ " አያንቱ ላይ የግብረ-ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በፖሊስ አዛዥ ተባባሪነት እንዲሸሽ ተደርጓል " - የአያንቱ ታላቅ ወንድም 🚨 " ፖሊስ አዛዡን ከኃላፊነት ከማዉረድ የዘለለ ደፋሪዉን ለሕግ አቅርቦ ዉሳኔ የማሰጠት ስራ አልተሰራም !! " በሲዳማ ክልል፤ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሻፋሞ ወረዳ ሹሮ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በእንጀራ አባቷ ቤት እያደገች የነበረች የ13 ዓመቷ ታዳጊ አያንቱ…
#Update

የ13 ዓመቷ አያንቱ ቱና ላይ የግብረስጋ ድፍረት በፈጸም የተጠረጠረውና ከአካባቢው ተሰውሮ የቆየው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ቤተሰቦቿ " ድምፅ ስለሆናችሁን እናመሰግናለን ! " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሲዳማ ክልል፤ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን፤ ሻፋሞ ወረዳ አያንቱ ቱና የተባለችን የ13 ዓመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረው ወጣት በወቅቱ የወረዳዉ ፖሊስ አዛዥ በነበረ ግለሰብ አማካኝነት ከአከባቢው እንዲሰወር መደረጉን መረጃ አጋርቶ ነበር።

አያንቱም አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ደርሶባት ከትምህርት ገበታዋ ተለይታ በጣሊታ የህፃናት ማቆያ ከ1 ዓመት በላይ እንድትቀመጥ መደረጉ ቅር እንዳሰኛቸው ቤተሰቦቿ ድምጻቸውን አሰምተው ነበር።

ከአንድ ዓመት በላይ ዱካው ጠፍቶ የሰነበተዉ ተጠርጣሪ በትናትናዉ ዕለት ፖሊስ ባደረገዉ ክትትል ከኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ አርሲ ዞን፤ ኮኮሳ ወረዳ " ሀንገሳ " ተብሎ ከሚጠራዉ አከባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሻፋሞ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሙሴ አወል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ተጠሪጣሪዉን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ በትብብር መስራታቸዉን የገለፁት አዛዡ የተጠርጣሪውን ወላጅ አባት ጨምሮ ተባባሪና ልጁን በመሸሸግ ሂደት ተሳታፊ የነበሩ የቤተሰቡ አባላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ገልፀዋል።

" ብቸኛዋ እህቴ በግድ ተደፍራ ፍትህ ሳታገኝ ከ1 ዓመት በላይ በየቆችበት ወቅት ተረጋግቼ ትምህርቴን እየተማርኩ አልነበረም " ያለን ወንድሟ ጴጥሮስ ቱና " በልጁ መያዝ እኔም ሆነ ቤተሰቦቼ ደስተኛ ሆነናል፤ ከዚህ በኋላ ሙሉ ትኩረቴን ወደ ትምህርቴ አደርጋልሁ " ሲል ተናግሯል።

በቤተሰቡ ስምም " ድምጽ ስለሆናችሁን አመሰግናለሁ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.99K👏471🙏97😭74💔57😡31😢22🥰21🕊21
TIKVAH-ETHIOPIA
" የደረሰው ጉዳት ከባድ በመሆኑ ገና እያጣራን ነው " - የቡለን ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ➡️ " የባንክ ቤቱን ስራ አስኪያጁን ከቤቱ ይዘውት መጥተው ቢሮውን አስከፍተው ባንኩን ዘረፉት ፤ ባለሀብቶችንም በስም እየጠሩ ውጣ እያሉ ሲጠሩ ሰምቻለሁ የዘረፉትን ንብረት በኤፍ ኤሳር መኪናና በሞተር እየጫኑ ዘና ብለው ነው ወጥተው የሄዱት "  - የአይን እማኝ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን፤ ቡለን…
#Update

" ታጣቂዎቹ አሁንም እያስፈራሩን ነው " - የቡለን ከተማ ነዋሪዎች

የቡለን ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸውን ገለፁ።

አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ነዋሪዎቹ " ከከተማው በቅርብ ርቀት የሚገኙት የሸኔ  ታጣቂዎች አሁንም ማስፈራሪያ እየላኩ ነው "  ብለዋል።

ትላንት ግንቦት 29/2017 ዓ.ም ከማለዳው እስከ ረፋዱ ድረስ ወደ ከተማው ዘልቀው የገቡት ታጣቂዎች  በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሱ በኃላ የዘረፉትን ንብረት በመኪና ጭነው ወስደዋል ብለዋል።

" ታጣቂዎቹ ይህንን ያህል ጥቃት ሲፈፅሙ በቂ የመንግስት የፀጥታ ሀይል በከተማው አልነበረም " ያሉት ነዋሪዎቹ " ከጥቃቱ በኃላ ግን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከተማውን ተቆጣጥሮታል " ብለዋል።

" ከዋና ከተማው ቡለን በእግር የ2 ሰዓት መንገድ በሚወስድ ርቀት ' ጎንጎ ' በተባለ ቦታ ላይ ታጣቂዎቹ ይገኛሉ " ሲሉ የገለፁት ነዋሪዎቹ  " አሁንም በማህበርዊ ሚዲያ ' በቅርቡ እንመለሳለን ' እያሉ መልዕክት እያስተላለፉ ነው መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃ ያድርግልን " ሲሉ ተማፅነዋል።

" ባለፈው ሳምንትም ተመሳሳይ የማስፈራሪያ መልዕክት ሲልኩ ሰምተን ለመንግስት አመራሮች ተናግረን ነበር " የሚሉት ነዋሪዎቹ  " ' ተራ አሉባልታ ነው ' በማለት የተቀበለን አልነበረም አሁንም ጥቃቱ  እንዳይደገም " ሲሉ ጠይቀዋል።

በቡለን ከተማ ትላንት ስለተፈፀመው ጥቃት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሩን ዑመር የእጅ ስልካቸው ላይ ደውለን ብንጠይቃቸውም ምርመራ ላይ መሆናቸውንና አሁን ላይ ምንም መናገር እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
571😢177😭67😡37🕊24🙏11🥰7😱6👏4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

“ የሊቀ መንበሩን ባለቤት ጨምሮ ሦስት የታገቱ ሰዎች የደረሱበት አይታወቅም። 11ዱን ለቀዋቸዋል። ከታጋቾች አንዱ አጎቴ ነው። ይኑር ይሙት የምናውቀው ነገር የለም” - ነዋሪና የታጋች ቤተሰብ

➡️ “ በዞኑ ሽርካ ወረዳ 2016 ዓ/ም ጀምሮ ካህናትን ጨምሮ 113 ንጹሐን ተጨፍጭፈዋል። ከ30 በላይ ታፍነው ተወስደው የደረሱበት አልታወቀም ” - እናት ፓርቲ


በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ/ም በተፈጸመው ጥቃት ከሟቾች ባሻገር ታግተው የተወሰዱ የቀበሌው ሊቀ መንበር ባለቤትና እህትን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎችና የታጋች ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የስፍራው ነዋሪ በሰጡን ቃል፣ “ የሊቀ መንበሩን ባለቤት ጨምሮ ሦስት ያታገቱ ሰዎች የት እንደደረሱ አይታወቅም። ከታገቱት መካከል 11 ሰዎች ተለቀዋል” ብለዋል።

በሰሞንኛው ጥቃት ታግተው ተወስደው የነበሩ 11 ሰዎች መለቀቃቸውን ገልጸው፣ “የአንጎዴቼ ቀበሌን ሊቀመንበር ስልጠና ብለው ወስደውት ስልጠና ላይ እያለ ነው ቤቱን አቃጥለው፣ ከብቱን ነድተው የወሰዷቸው” ሲሉም አስረድተዋል።

ሌላኛው ነዋሪና የታጋች ቤተሰብ፣ “አንደኛው ተጎጂ እኔ ነኝ። አካባቢያችንን ለቀን ወደ አጎራባች ቦታ ሂደናል። ያለው ችግር በጣም አስጊና ነው። መከላከያ ቢኖርም ህዝቡ በደረሰው ሰቆቃ ምክንያት በጣም ተደናግጧል” ብለዋል።

“ከታጋቾች አንዱ አጎቴ ነው። አቶ ሳህሌ ሙሉጌታ ይባላል። እስካሁን ድረስ ድምጹ የለም። ይኑር ይሙት የምናውቀው ነገር የለም” ያሉት ነዋሪው፣ የታገቱት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ/ም መሆኑን አስታውሰዋል።

በእለቱ 11 ሰዓት ከ20 ተኩሱ እንደተከፈተ አስታውሰው፣ “ቀን የዋለው ሚሊሻ ከአዳሪ ሚሊሻዎች ጋር እየተቀያየረ ባለበት ሰዓት ነው ጥቃት አድራሾቹ ቀበሌዋን ከዳር እስከ ዳር ነበር የያዟት” ብለዋል።

“አንድ ሚሊሻ ‘ተበላህ፣ ተበላህ ሰዎቹ እዚጋ ደርሰዋል’ አለኝ። ሮጠን ነው ያመለጥነው። ታጣቂው ቀድሞኝም ነበር፤ እላዬ ላይ አውቶማቲክ ነው የከፈተብኝ፤ ከማሰሮ ውስጥ እንደሚወጣ ባቄላ ነው የተረፍኩት” ሲሉም አስረድተዋል።

ሥጋት ያደረባቸው የሥፍራው ነዋሪዎች እቃቸውን እየጫኑ ወደ አቅራቢያ ከተሞች እየተፈናቀሉ መሆኑን፣ ሰሞኑን በአካባቢው መከላከያ ቢኖርም ቁጥራቸው አስተኛ እንደሆነ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ “መንግስት ይየን፤ አሁንስ ዋስትናችን ምንድን ነው?” ሲሉ ጠይቀዋል።

እናት ፓርቲ ስለጥቃቱ ባወጣውና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ምን አለ?

በጀጁ ወረዳ አንጎዴቼ ቀበሌ ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ/'ም “ሸኔ” በደረሰው ጥቃት “ተገደሉ” ስለተባሉት ንጹሐን የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፣ “ታፍነው የተወሰዱ ንጹሐን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን” ብሏል። 

በጥቃቱ ካህኑን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች እንደተገደሉ ጠቅሶ፣ “ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው በሕክምና ላይ ሲሆኑ፣ ሌሎች 5 ሰዎች ታፍነው እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም” ሲል ገልጿል።

ስለሰሞኑ ግድያም፣ “የካህኑና ምዕመናኑ ግድያ የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ፕሮጀክቱ አካልም ነው” ብሏል። 

በዞኑ ጥቃት በተደጋሚ መፈጸሙ እንደሚታወቅ ጠቅሶ፣ “በዞኑ ሽርካ ወረዳ 2016 ዓ/ም መስከረም ጀምሮ ካህናትን ጨምሮ 113 ንጹሐን በግፍ ተጨፍጭፈዋል። ከ30 በላይ ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን የደረሱበት አልታወቀም” ሲልም ፓርቲው በመግለጫው አትቷል። (የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
 
ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
484😭472😡36🕊11🙏10👏5😱5😢5🥰3🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ከ564 በላይ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ከእስር ተፈተዋል " - የወላይታ ዞን ፖሊስ

➡️ " የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ በወቅቱ የወሰዱት እርምጃ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል ! "

በአዲስ አበባ ፖሊስ በእስር ላይ የነበሩ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች መለቀቃቸውን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል።
 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰኔ 01/2017 ዓ/ም የድቻ ደጋፊዎች በከተማ ውስጥ ተዘዋዉረዉ በፈጠሩት አለመግባባት ምክንያት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው የድቻ ደጋፊዎች መካከል፦
- በቂርቆስ ክፍሌ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፑፑላሬ ፖሊስ ጣቢያ 245 ፣
- ቦሌ ቡልቡላ 68 ፣
- በየካ ክፍለ ከተማ 50፣
- ልደታ ክፍለ ከተማ 201 የተጠረጠሩ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር በመነጋገር ከእስር እንዲፈቱ መደረጋቸው ተገልጿል።

አጠቃላይ በተለያየ ክፍለ ከተማ የታሰሩ  ከ564 በላይ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ናቸው ከእስር የተፈቱት።

የዞኑ ፖሊስ " የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ የድቻ ደጋፊዎች በከተማዉ ውስጥ በተለያየ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ የፈጠሩትን ያለመግባባት ለመፍታት በወቅቱ የወሰዱት እርምጃ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ያስቀረ በመሆኑ ያስመሰግናል " ብሏል።

አሁን ላይ ሌሎች የተወሰኑ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው ጉዳዮች በፍርድ ሂደት የሚገኙ መኖራቸው ተጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.22K😡287👏66😭43💔38🕊36🤔27🙏25🥰21😢19😱14
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሕገ ወጥ እስር ማለት እንዲህ አይነት እስር ነው። እስሩ ኢ-ሥነ ስርዓታዊም ነው ፤ ኢ-ሕገ መንግስታዊም ነው " - የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ጠበቃ በፓሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ጠበቃ፣ " ጋዜጠኛው አላግባብ በፖሊስ ኃይል ነው አሁን ታስሮ ያለው እንጂ በህግ ኃይል አይደለም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ጠበቃው ቤተማርያም ኃይሉ በሰጡት ቃል፣ " ይህ ሰው 'ይፈታ'…
#Update

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት ተከብሮ ከእስር እንዲፈታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 5/ 2017 ዓ.ም. ወስኗል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱ በዛሬ ውሎው የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጋዜጠኛው በዋስ ይለቀቅ ውሳኔ ማጽናቱን ጠበቃው አቶ ቤተማሪያም አለማየሁ ገልጸዋል።

ጋዜጠኛው ለሦስተኛ ጊዜ በዋስ ከእስር እንዲፈታ በፍርድ ቤቶች ቢወሰንም ከእስር አለመፈታቱን ጠበቃው ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
368😭129😡56👏20💔17🤔15😢12🙏10🥰5😱3🕊2
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

ዛሬ በህንድ አህመዳባድ በደረሰው የቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሞቱ ሰዎች ወደ 294 እንደሚጠጉ ተነግሯል።

በአውሮፕላሉ ውስጥ ከነበሩ 242 ሰዎች አንድ ሰው በህይወት ሲተርፍ ሌሎች ህይወታቸው አልፏል።

አውሮፕላኑ በተነሳ በትንሽ ደቂቃ የተከሰከሰው በአንድ የህክምና ኮሌጅ ውስጥ ነው። በኮሌጁ በሚገኝ ህንጻ ውስጥ የነበሩ የጤና ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 294 አካባቢ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia
😭1.5K406💔170😢92🙏40🕊38😱21🤔18👏16🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

የሲዳማ ክልል ከሰሞኑ በፀጥታዉ ዘርፍ እየወሰደ እንደሆነ በተገለፀዉ ተቋማዊ ሪፎርም ዛሬ የቀድሞ የክልሉ ኮሚሽነር የነበሩትን ሽመልስ ቶማስ በዛሬዉ ዕለት ከስልጣን ማንሳቱ የተሰማ ሲሆን ማምሻዉን ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟቸዋል።

አዲሱ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ ሲዳማ በዞን መዋቅር ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በልዩ ልዩ ፖሊሳዊ አመራሮች ተቋሙን ያገለገሉና በአሁኑም ወቅትም የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጧል።

ይህ መረጃ በተዘጋጀበት ወቅት ስለ ቀድሞዉ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ከኃላፊነት መነሳት ዙሪያ ይፋ የተደረገ መግለጫ የሌለ ሲሆን የፖሊስ ኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የአዲሱን ኮምሽነር ሹመት ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጎታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
886😭58🤔36🕊33🙏32😢18👏15😡15🥰11😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ ትገባ ይሁን ? እስራኤል በኢራን ላይ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ ስለምትሳተፍበት ሁኔታ ለመወያየት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር አድርገዋል። አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ በቆየው ስብሰባ ላይ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማዕከላት ላይ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ መሳትፍ እንዳለባት…
#Update

እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት እስከ እሁድ ምሽት ድረስ 224 ሰዎች መገደላቸውን 1 ሺህ 277 መጎዳታቸውን ኢራን አስታውቃለች።

እስራኤል በበኩሏ በኢራን ጥቃት 20 ሰዎች እንደተገደሉባት ገልጻለች።

ተባብሶ በቀጠለው የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ምክንያት ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው እንዲወጡ በሁለቱም በኩል መልዕክት እየተላለፈ ነው።

ኢራን የእስራኤሏ ሃይፋ ከተማ በተወሰነው ክፍል ያሉ ነዋሪዎች ለህይወታቸው አደጋ ስለሚኖር አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

እስራኤልም ነዋሪዎች ከተለያዩ የቴህራን ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ እያስጠነቀቅች ነው። በዚህም ሰዎች በቻሉት አቅም ወደ አጎራባች ከተማ እየወጡ እንዳለ ተነግሯል።

መረጃው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
853😭306🕊169😢46👏33🙏22😡22😱19🤔16💔12🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኃይል ተቋርጧል ! " አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል። በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር /ግሪድ/ ባጋጠመ ቴክኒካል ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። የተቋረጠውን የኃይል አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው…
" በተወሰኑ ቦታዎች ኃይል እየተመለሰ ነው " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በከፊል የተቋረጠው ኃይል በተወሰኑ አካባቢዎች መመለስ እንደጀመረ የኢትዮጵያ ኤሌትክሪክ ኃይል አሳውቋል።

" በተቀሩት አካባቢዎችም በየደረጃው መልሶ ኃይል የማገናኘት ስራ እየተሰራ ነው " ብሏል።

#Update : ሙሉ በሙሉ ኃይል ተመልሷል።

@tikvahethiopia
798👏191😭103😡90🙏66🤔41🥰24🕊24😢22😱14💔13
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍቅረኛዉን በቅናት ተነሳስቶ የገደላት ግለሰብ ማምለጥ እንደማይችል ሲያውቅ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል " - የኮንሶ ዞን ከና ወረዳ ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ከና ወረዳ የገዛ ፍቅረኛዉን በስለት በመዉጋት ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ ከሕግ እንደማያመልጥ ሲገባዉ እጁን ለፖሊስ መስጠቱን የከና ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ገዛኸኝ ካራተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ግለሰቡና…
#Update

" የመምህርት ተዋበች ገዳይ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል " - የኮንሶ ዞን ፖሊስ

በኮንሶ ዞን ኬና ወረዳ ፋሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮቶላ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ወር በፊት የገዛ ፍቅረኛዉን መምህርት ተዋበች ኩሲያን ሌላ " የፍቅር አጋራ ይዘሻል " በሚል ጥርጣሬ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደላት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉሎ በተመሰረተበት ከባድ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ በመባል የፍርድ ዉሳኔ እንደተላለፈበት የኮንሶ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን ካማይታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመበት ሁኔታ፣ ሰዓት እና የድርጊቱን አሰቃቂነት ዐቃቤ ህግ በሰዉና ኤግዚቢት እንዲሁም የምርመራ ማስረጃ በማቅረቡ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ኩሻቦ ኩራዎ ጥፋተኛ በማለት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የወንጀል ድርጊቱን በተፈፀመበት ወቅት የኬና ወረዳዉ ፖሊስ ምላሽ አካቶ በጉዳዩ ላይ ዘገባ ማቅረቡ አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
687😡174😭119👏79💔58🙏35🕊26😢18🥰14🤔13
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢራን መገናኛ ብዙኃን በሰሜናዊ ኢራን ፍንዳታዎች በመሰማታቸው " ተኩስ አቁሙ ተጥሷል " አሉ።

በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም መደረጉ ቢነገርም በሰሜናዊ ኢራን ማዛንዳራን ግዛት ውስጥ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ ቅርብ የሆነው 'ፋርስ' የተባለው የዜና ወኪል እንዳለው ከዋና ከተማዋ ቴህራን በስተሰሜን ማዛንዳራን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ባቦልሳር ከተማ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፊል መንግሥታዊ የሆኑት 'መህር' እና 'ኢስና' የተባሉት የዜና ወኪሎች በሰሜናዊ ግዛት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች ፍንዳታዎች መከሰታቸውን እና የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ተኩስ መሳማቱን በመጥቀስ የተኩስ አቁሙ “ተጥሷል” ብለዋል።

በተጨማሪም የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ፍንዳታዎች መከሰታቸውን እና የግዛቲቱን አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ ክስተቱን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች ገና አለመታወቃቸውን መናጋራቸው ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ " እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም " በማለት ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ  " እስራኤል፤ እነዚያን ቦምቦች አትጣይ። በጥቃቱ የምትቀጥይ ከሆነ ከፍተኛ ጥሰት ነው። የጦር አውሮፕላን አብራሪዎችሽን አሁኑኑ ወደ ቤታቸው መልሺ! " ብለዋል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የመጣው ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም በኢራን እና በእስራኤል መካከል መደረጉን ካስታወቁ በኋላ ነው።

እስራኤል በትራምፕ ሃሳብ መስማማቷን ስታሳውቅ፣ ኢራን ደግሞ ጥቃቱን የምታቆመው እስራኤል ካቆመች ብቻ ነው ብላለች።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
744🕊78😡34🙏23😭12🤔6👏4💔4😱2😢2🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
" የጉዞ ታሪክ በሌላቸው ሁለት ታዳጊዎች ላይ የMpox ምልክት መታየቱ ስጋት ፈጥሮብናል " - የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ➡️ " በኮንሶ ዞን የኤም ፖክስ(Mpox) በሽታ ምልክት በሁለት ሰዎች ላይ ታይቶ ናሙና ተወስዶባቸው ዉጤት እየተጠባበቅን ነዉ " - የዞኑ ጤና መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) በሽታ ምልክቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች…
#Update

" በሰገን ዙሪያ ወረዳ በሁለት ሰዎች ላይ የታየዉ ምልክት የMpox በሽታ ስላልሆነ ሕብረተሰቡ ከስጋት ነፃ ሆኖ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " - የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ


ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ አማራይታ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሁለት እህታማምች ላይ የታየዉን የሰዉነት ላይ ምልክትን ተከትሎ ሕብረተሰቡ " የኤም ፖክስ በሽታ ሊሆን ይችላል " በሚል ስጋት ዉስጥ መግባቱንና የዞኑ ጤና መምሪያ በበኩሉ ከተጠረጠሩት ሁለት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ናሙና ወስዶ ለምርመራ መላኩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳቆ ነበር።

የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ በሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሁሉቱ እህታማሞች የተወሰደዉ ናሙና ዉጤት ከአዲስ አበባ መምጣቱንና በዉጤቱ መሰረት ምልክቱ MPox (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) አለመሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

አቶ ግርማ ሕብረተሰቡ በሽታዉን መጠንቀቁ አግባብ ቢሆንም ልጆቹንና ቤተሰቦቻቸውን ያገለለበት መንገድ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።

ዉጤቱን ተከትሎም ስለ በሽታው የግንዛቤ ማስፋትና የጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ልጆቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉንም አስታውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
373🙏57😭14🤔6😱6🕊5🥰4😢4👏2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከጎንደር መተማ በሚወስደው መንገድ በአንድ ቀን ልዩነት በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ላይና በንፁሀን ላይ " ዘግናኝ " ሲል የጠራው ጭፍጨፋ መፈጸሙን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ለጥቃቱ " ፅንፈኛው ቅማንት " ሲል የጠራውን ታጣቂ ኃይል ተጠያቂ አድርጓል።

ዞኑ ሰኔ 19 ባወጣው መግለጫ በቀን ሰኔ 16/2017 ዓ.ም 11:00 ገደማ  ከጎንደር ገንዳ ዉሃ በሚወስደው መንገድ " መቃ " በተባለ ቦታ ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጿል።

በቀን 16/10/2017 ዓ/ም ከቀኑ11:30 ገደማ ለአርሶ አደሩ እና በአካባቢው በእርሻ ስራ በኢንቨስትመት ለተሰማሩ የሚከፋፈፍል የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ተሽከርካሪ እና ሌሎች የህዝብ መጓጓዣዎችን አጅበው የነበሩ  መከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስና የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት እንዲሁም አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን " ዘግናኝ በሆነ ጭካኔ ጨፍጭፏቸዋል " ሲል ገልጿል።

" ታጅበዉ እና ማዳበሪያ ጭነዉ ሲመጡ የነበሩ 16 ሹፌሮችን ከመኪና እያስወረደ ዘግናኝ በሆነ ጭካኔ ጨፍጭፏቸዋል። የተወሠኑትንም አግቶ በመውሠድ አድራሻቸውን አጥፍቷል " ሲል መግለጫው ይጠቅሳል።

አክሎሞ " ይህው ታጣቂ ኃይል በቀን 18/10/2017 ዓ/ም ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊታችን አመራሮችና አባላት ላይ አቅዶና ተዘጋጅቶ ድጋሜ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ግጭት አድርጓል " ብሏል።

የዞኑ አስተዳደር " ታቅዶበት የተፈፀመና ዘግናኝ " ብሎ በጠራው በዚህ ጥቃት በመጀመሪያው ቀን የሟቾች ቁጥር 16 ሹፌሮች መሆኑን ሲጠቅስ በሁለተኛው ቀን በተፈፀመው ጥቃት የሟቾችን ቁጥር ከመግለፅ ተቆጥቧል።

በመጀመሪያው ቀን በንፁሃን ላይ ደረሰ ባለው ጥቃት ቁጥራቸውን ያልገለፃቸው ሹፌሮች ታግተው መወሰዳቸውንም አክሏል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡ የአይን እማኝ ግን  ሰኔ 16፤ 2017 ዓ.ም በተፈፀመው ጥቃት የሟቾችን ቁጥር ከመቶ በላይ እንደሚደርስ ተናግረዋል።

ይህዉ የአይን እማኝ እንደሚለው " በእለቱ ከታጣቂ ሀይሉ ጋር መሬት ላይ ሲጨቃጨቁ የነበሩት አድማ ብተና ፖሊስና በFSR መኪና ተጭነው የነበሩ የፀጥታ ሀይሎችን ከጫካ እየወጡ ነው መኪና ላይ እያሉ የጨፈጨፏቸው " ብሏል።

" እነሱን ሲጨርሱ ደግሞ በየመኪናው ባሉ ሹፌሮችና ተሳፋሪዎች ላይ ጥቃቱን ፈፅመዋል" ሲል ገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር " ፅንፈኛ " ሲል የሚጠራውን የቅማንት ታጣቂ ኃይል በአካባቢው ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በንፁሀን ዜጎች ላይ ግድያና እገታ እንደሚፈፅም በመግለጫው አንስቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBD

@tikvahethiopia
585😭322😡32💔27🕊21👏12😢10🙏9🤔7😱3🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ እንዲመለስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ይህ ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የለሌው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል " ብሏል።

" ብርቅዬ የክለባችን ተጫዋቾች በጨዋታ ሜዳ የገጠሙትን ሁሉንም ከጨዋታ ብልጫ ጋር በማሸነፍ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ማሸነፉ የአደባባይ ምስጥር ነዉ " ሲል ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ' የሊግ ካምፓኒ ያወጣውን የፋይናንስ ደንብ አላከበራችሁም ' በሚል በክለቡና በተጫዋቾች ላይ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ቢባልም ክለቡ  ያነሳዉ ዋንጫ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ በ48 ክለቦች መካከል የተደረገው መሆኑ ዕሙን ነው " ብሏል።

" የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን አሰልፎ ከሆነ በጥሎ ማለፉ ያሸነፋቸው ክለቦች በሙሉ ፎርፌ አግኝተው ጉዳያቸው እንደገና መታየት አለበት እንደ ማለትም ይሆናል " ብሏል።

" እርስ በርስ የሚጣረሱ ሀሳቦችን በማገናኘት ውጤቱን ለመቀማት መሞከር  ተገቢና ህግን የተከተለ ውሳኔ ነው ብለን አናምንም " ሲል ቦርዱ አሳውቋል።

" ፌዴሬሽኑ ዉሳኔውን ከህግጋቱ ጋር በማገናዘብ እንደገና እንዲያጠነዉ ቅሬታችንን እናሰማለን " ብሏል።

" ህዝባችን በፌደሬሽኑ ውሳኔ የተከፋ ቢሆንም የአፊኒ ባህል ያለው ታላቅ ህዝብ ስለሆነ ክስተቶችን በመረጋጋት መርምሮ በተገቢው እንዲያጠነውና  ሂደቱን  በትዕግሥት እንዲጠባበቅ በአክብሮት እየጠይቃል " ሲል ገልጿል።

" የተነፈግነው ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ጉዳዩን እስከ ፊፋ ገላጋይ ፍርድ ቤት ድረስ በይግባኝ ወስደን ለጉዳዩ  ተገቢው እልባት እስኪሰጥ ድረስ የክለቡ ቦርድ ቁርጠኛ መሆኑን እናረጋግጣለን " ሲል አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
1.11K🤔144👏77😭48😡47🙏31🕊22😢10😱8💔6🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

19 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

ታዳጊዋ አያንቱ ቱና ላይ የግበረስጋ ድፍረት የፈጸመው ግለሰብ በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሻፋሞ ወረዳ የ13 ዓመቷን ታዲጊ አያንቱ ቱና ላይ የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውና በፖሊስ ተባባሪነት ጭምር አምልጦ ከ1 ዓመት በላይ ተሰዉሮ የነበረዉ ወጣት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ መረጃው ከተሰራጨ በኋላ በተደረገ ክትትልና ፍለጋ ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ዉሎ ክስ ተመስርቶበት እንደነበር የአያንቱ ታላቅ ወንድም ወጣት ጴጥሮስ ቱና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ይኸው ግለሰብ አርብ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ ዉሳኔ እንደተላለፈበት የአያንቱ ወንድም ተናግሯል።

የሻፋሞ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ፉና ስለጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " የወረዳዉ ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ያቀረቡትን ጠንከር ያለ ምርመራ፣ የሰነድ እንዲሁም የሕክምና ማስረጃዎችን የተመለከተዉ የወረዳዉ ፍርድ ቤት ግለሰቡን ጥፋተኛ ነዉ በማለት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል " ብለዋል።

" ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በማቆያ ዉስጥ የምትገኘዉ አያንቱ ደፋሪዋ እንደተያዘ ከተነገራት በኋላ ጥሩ መሻሻል ታይቶባታል " የሚለዉ የታዳጊዋ ወንድም ጴጥሮስ " ከዚህ በኋላ ከማቆያ ወጥታ ወደ ትምህርት ገበታዋ ትመለሳለች " ብሏል

" የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ለታዳጊዋ ድምፅ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.68K😡1.16K👏344🙏161😭65💔60🕊45😢24🤔16🥰14
TIKVAH-ETHIOPIA
የዘውዱ ሃፍቱ ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ከዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ የመጨረሻ ውሳኔ ዛሬ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ሊሰጥ ቀጠሮ ቢያዝለትም ለሰኔ 30/2017 ዓ.ም ተሸጋግሯል። ዛሬ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የችሎት ውሎውን ተከታትሏል። የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ግንቦት 8/2017 ዓ.ም ለመጨረሻ ውሳኔ ተቀጥሮ ነበር ሆኖም የተከሳሽ ቤተሰቦች በቀሰቀሱት ግርግርና ረብሻ…
#Update

" የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል ! " - ሂደቱን የሚከታተሉ ታዛቢዎች

አሁንም የእንስት ዘወዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ ሌላ ቀጠሮ ተይዞለታል።

የግድያ ወንጀሉ ከተፈፀመ የፊታችን ነሀሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ 2017 ዓ.ም በዓል ሁለት ዓመት ይሞላዋል።

አሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የአሸንዳ በዓል በሚከበርበት ወርሃ ነሀሴ 2015 ዓ.ም ነበር የተፈፀመው።  

የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ችሎት የትላንት ውሎ ምን ይመስል ነበር ? 

የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል በመመልከት ላይ የሚገኘው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በተከሳሾች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ላይ ጥፋተኛ የተባሉት ግለሰቦች የሚያቀርቡት የፍርድ የማቅለያ ለመስማት ነው ለሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የተቀጠረው።

የችሎቱ ዳኞች በያዙት ቀጠሮ ተከሳሾች ለፍርድ ማቅለያ የሚሆናቸውን የህክምናና ሌሎች ሰነድ እንዲያቀርቡ ባዘዙት መሰረት በጠበቃቸው በኩል አቅርበዋል።

አንደኛ ተከሳሽ የልብ ህመም ታማሚና የኪንታሮት ህመምተኛ ፣ ሁለተኛው ተከሳሽ ደግሞ የስኳርና የኪንታሮት ህመምተኛ መሆናቸውን በቃል ቢገልጹም በሃኪሞች ማስረጃ እንዲረጋገጥ ለሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በግድያ ወንጀሉ በመፈፀመ የተጠረጠሩ ሁለቱ ወጣቶች ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ/ም በሃኪም የተረጋገጠ የፅሁፍ ማስረጃ ያቀርቡ እንደሆነ ያኔ የሚታይ ሆኖ የችሎት ሂደቱን የተከታታሉ የሚድያ ባለሙያዎች ፣ የሴቶች ጥቃት እንዲቆም የሚሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት " ይህንን ሁሉ በሽታ ተቋቁመው ይህን መሰል ዘግናኝ ግድያ ለመፈፀም እንዴት ጉልበትና አቅም አገኙ ? " የሚል ጥያቄ ጭረዋል።

የችሎቱ የውሎ መረጃ  በማህበራዊ ሚዲያ የተከታተሉ በርካቶች የፍርድ ሂደቱ ለሁለት አመታት መራዘሙ በመቃወም "  የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል " ብለዋል።

የአሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የፍርድ ሂደት ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም መቋጫ ይብጀለት ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
772😭196😡57🕊22🙏19😢10🥰9💔9😱5👏4
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል ! " - ሂደቱን የሚከታተሉ ታዛቢዎች አሁንም የእንስት ዘወዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ ሌላ ቀጠሮ ተይዞለታል። የግድያ ወንጀሉ ከተፈፀመ የፊታችን ነሀሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ 2017 ዓ.ም በዓል ሁለት ዓመት ይሞላዋል። አሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የአሸንዳ በዓል በሚከበርበት ወርሃ ነሀሴ 2015 ዓ.ም ነበር የተፈፀመው።   የእንስት ዘውዱ…
#Update

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ቀጠሮ ሰጠ።

ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በእስር የሚገኙ ተከሳሽ ተጠርጣሪዎች ለውሳኔ ማቅለያ የሚሆን የህክምና ማስረጃ እናቀርባለን ባሉት መሰረት ለዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ዛሬ ችሎት ላይ የቀረቡት የተከሳሽ ጠበቆች " የመቐለ ዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ አርብ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የህክምና ማስረጃ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶናል " ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም ይህን አድምጦና ተቀብሎ የመጨረሻ ቀነ ቀጠሮ ለነገ ሰጥቷል።

በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት የተበዳይና ተከሳሽ ቤተሰቦች ፣ በርካታ ሚድያዎች ፣ በሴት ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ስቪክ ማህበራት አመራሮችና አባላት ተገኝተው ነበር ።

ሁለት አመት ያስቆጠረው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ነገ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ መቋጫ የፍርድ ውሳኔ ያገኝ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የችሎቱን ውሳኔ ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትጵዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
546😭157🙏34😡30🕊19🤔17😢15💔13🥰6👏6