TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ዛሬ ሰኞ ምሽት 5:24 ሲል በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ተሰምቷል። " አሁን ላይ ቀንሷል ቆሟል ፣ ከአሁን በኃላ ምንም ነገር አይፈጠርም " በሚል መዘናጋት ጥንቃቄ እና ትኩረት ማጣት እንዳይመጣ መጠንቀቅ ይገባል። የመሬት…
“ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ነው እየመነጨ ያለው። ደብረ ብርሃን የተሰማ ነገር የለም” - አታላይ አየለ (ፕ/ር)

ትላንት ከሌሊቱ 10፡46 በደብረ ብርሃን አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የጀርመን የጂኦ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ማዕከል ድረጽ መረጃ አውጥቷል ፤ ይኸው መረጃም ሲዘገብ ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵዮጵያ በበኩሉ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከዘርፉ ተመራማሪ ማብራሪያ ጠይቋል።

ደብረ ብርሃን አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል መባሉን እውነት ነው ? ብለን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ሮ)፣ " ኧረ ውሸት ነው " ሲሉ መልሰዋል።

" ደብረ ብርሃን አካባቢ የለም። እዛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ነው እየመነጨ ያለው። ደብረ ብርሃን የተሰማ ነገር የለም " ነው ያሉት።

" የዘርፉ ተቋማት በሚያወጡት መረጃ፣ ' ከደብረ ብርሃን ይህን ያህል ኪሎ ሜትር፣ ወይ ከመተሃራ ይህንን ያህል ኪሎ ሜትር ' ይላሉ ስም እየጠሩ። ከዛ በመለስ ግን እንደዚህ የሚባል ነገር የለም። ደብረ ብርሃን አሁን ከየት የመጣ መንቀጥቀጥ ነው? " ሲሉ ነው ምላሽ የሰጡት።

ከዚህ ቀደም ከደብረ ሲና በ52 ኪሎ ሜትር ተከሰተ ለተባ የመሬት መንቀጥቀጥ በተለመለተ፣ ከሚከሰትበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አደረገ ማለት እንዳልሆነ ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

" በአንዳንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " ነበር ያሉት።

አዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ንዝረቱ እየተሰማ እንደሆነ ይታወቃል።

ሌላው በተያያዘ፣ የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንስ በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው ? በሚል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ለቀረበላቸው ተጨማሪ ምላሽ ሰጥተዋል።

አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ምንም የተለዬ ነገር የለም እንደቀጠለ ነው። ከቀን ቀን ትንሽ ለውጥ ያለው ይመስላል። ግን ነገ ይቆማል የሚባል ነገር አይደለም።

ስቲል ይታያል እንቅስቃሴ። የሚረግብ አይመስልም በአጭሩ። 

ዌብ ሳይት ተለጠፈ የሚለው ሳይሆን ለሊት 10 ገደማ ተፈጠረ የተባለው አካባቢ አንድ ነው ሪፓርት የተደረገው ግን ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስካሁን ስንት ተፈጠረ ብትለኝ ከ100ዎች በላይ ሊሆኑ ይችላሉ።

ያ ማለት የሚረግብ አይነት አይደለም
" ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ...ሙሉ ተሳፋሪውን ነው የወሰዷቸው። መጀመሪያ የተመታው ግን አንድ ሹፌር ነው - " ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

አዋሽ ፓርክ አካባቢ ሰሞኑን አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሙሉ ተሳፋሪዎች ከነአሽከርካሪው መታገታቸውን ጣና የከባድ ተሽከርከሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማኀበሩ በሰጠን ቃል " አዋሽ አካባቢ ፓርክ አለ። እዚያ አካባቢ ታጣቂዎች ተሽከርካሪውን በጥይት መትተውት ሰው ቆስሏል " ብሏል።

" ተሽከርካሪው ተቃጥሏል። ኤክስፓርት ይሁን ሌላ የጫነ ተሽከርካሪ አልታወቀም። ተሳፋሪ ሰዎችንም ይዞ ነበር " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

ተሳፋሪዎቹና ሹፌሩ ከምን ደረሱ ? ለሚለው ጥያቄ ማኀበሩ በምላሹ፣ " ሹፌሩም ታግቷል። ተሳፋሪውንም እንደዚሁ ሙሉ ተሳፋሪ ወስደዋል " ነው ያለው።

ተሳፋሪ ከያዘ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ነበር እንዴ ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ ማኀበሩ፣ " በተለምዶ ' አባዱላ ' የሚባለድ ሚኒባስ ነው፣ አዎ የሕዝብ ተሽከርካሪ ነበር " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ምን ያክል ሰዎች እንደታገቱ ሲጠየቅም፣ " ቁጥሩ አልታወቀም። ሙሉ ተሳፋሪውን ነው የወሰዷቸው። መጀመሪያ የተመታው ግን አንድ ሹፌር ነው " ሲል መልሷል።

ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት እንነማን እንደሆነ ሲያስረዳ፣ በዛ አካባቢ ላይ ከሸኔ ታጣቂዎች ውጪ ከማኀበረሱ የወጣ እንዲህ አይነት ድርጊት ከዚህ ቀደም አጋጥሞ እንደማያውቅ ነው የገለጸው።

ለአመታት ይኸው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ያልተገኘለት የታጠቁ አካላት ሹፌሮች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ልጅን ያለ አባት፣ ወላጅን ያለ ልጅ እያስቀረ በመቀጠሉ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ አሁንም ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል።

ደረሰ ለተባለው ጥቃትና እገታ የባለስልጣናትን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ሙከራ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው " -  የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምን ደረሰ ? የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ፦ " በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል። ጉዳዩ…
#Update

🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ?

“ አጋቾች  ያገቷቸውን ልጆቻችንን ‘መንግስት አስለቀቀ’ መባሉ ትክክል አይደለም።

አጋቾቹ ሲቀጧቸው የተጎዱ፣ በህመም ሳቢያ መስራት የማይችሉ ልጆችን ከካምፕ አውጥተው ታይላንድ ድንበር ሲጥሏቸው ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤን.ጂ.ኦ አንስተው ታይላንድ በመውሰድ አሳክመው ህንድ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ነው ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጓቸው።

አንዳንድ ሚዲያዎች የዘገቡትና መንግስትም ድፍን ባለ መልኩ የሰጠውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ማይናማር ያሉ ልጆች የተለቀቁ የመሰላቸው
አድማጮች እንኳን ደስ አላችሁ ’ የሚለን በዝቷል። እውነታው ይሄ አይደለም።

ይህን ጉዳይ ህዝብ ይረዳው። ማይናማር ከታገቱት ልጆች መካከል እንዲለቀቁ በተደረገ ጥረት ማንም አልተለቀቀም።

ታይላንድ ያሉት ናቸው እንጂ ማይናማር ያሉት አይደሉም የወጡት። ዋሽተው ነው። ዜናውን አካብደውታል። እኛን ምንም ተስፋ አልሰጡንም። ‘አትምጡ’ ነው ያሉን ” ሲሉ አስረድተዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

በዚህ መልኩ (ታጋቾች ተለቀዋል በሚል) የዘገቡት ሚዲያዎች ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ድምፅ እንዲሆኑን ጠይቀናቸው ሳለ ‘ እንከሰሳለን ’ ብለው ነው የፈሩት። አሁን ግን ያልተወራውን ማስተላለፍ ከኢቲክስ ውጪ ነው። በጣም ቅር ብሎናል። እውነታውን አሳውቁልን።

በታይላንድና በማይናማር ድንበር ያሉት ልጆች እንጂ ወጡ የተባሉት ከማይናማር ግዛት ካሉት ጋር እንደማይገናኝ በህንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል።

የኤምባሲው ሰዎች ‘እኛ የሚመለከተን ታይላንድ አካባቢ ያለውን ብቻ እንጂ የማይናማሩ የሚመለከተው ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነውና ማይናማር ያሉትን አንድም ነገር አልሰራንም’ ብለው ቃል በቃል ነው የነገሩን።

ከኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በመግቢያ ንግግራቸው ያስተላለፉት ትክክለኛውን ‘ታይላንድ አካባቢ ያሉትን’ ብለው ነው።

ነገር ግን አንዳንድ ሚዲያዎች በስቃይ ላይ ያሉ ልጆችን መንግስት እያስወጣ እንዳለ አድርገው ነው መግለጫውን የዘገቡት። ይህ ቅር አሰኝቶናል።


ሌሎች አገራት እኮ ዜጎቻቸውን ያስወጡት ከትራደሽናል ሊደሮች፣ ከኤምባሲዎች ጋር ሆነው በመስራት ነው። የኛዎቹ ግን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም።

አንዱን ኢትዮጵያዊ የመራቢያ አካሉን የዘር ፍሬ ነቅለውታል። በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ።

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ በችግር ላይ ያሉ ልጆችንን  ካሉበት ስቃይ እንዲታደጋቸው በአጽንኦት እንጠይቃለን ” ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“ የትራንስፓርትም ዋጋ ጨምሮባቸዋል። መድኃኒትም ከውጭ ነው የሚመጣውና በሁሉም ዋጋ ጨምሮባቸው በጣም በከፍተኛ ሲቃይ ናቸው ህሙማኑ ” - ማህበሩ

“ 400 ሺሕ ሰዎች ዲያሌሲስ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛዎቹ ዲያሊስ ማድረግ ስለማይችሉ ትተው ነው ያሉት ” በማለት የኩላሊት ህክምና እጥበት በጎ አድራጎት ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የማኀበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ?

“ ብዙ ወጣቶች ናቸው ዲያሌሲስ እያደረጉ ያሉት። ኩላሊት ደግሞ ከዘመድ ካልሆነ ከእኛ ሀገር ከሌላ ቦታ ማገኘት አይቻልም። 

ትልቁ ችግር የኩላሊት ማግኘት ነው። ህሙማኑ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ፍላጎት ቢኖራቸውም የሚሰጣቸው ሰው የለም። ቢኖርም እንኳ ቢኖር አንዳንዱ ማች አያደርግም።

አብዛኞቹ ዲያሌሲስ ማድረግ ላይ ነው ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ንቅለ ተከላውን እስከሚያደርጉ ድረስ። 

የትራንስፓርትም ዋጋ ጨምሮባቸዋል። መድኃኒትም ከውጭ ነው የሚመጣው በሁሉም ዋጋ ጨምሮባቸው በጣም ከፍተኛ ሲቃይ ላይ ናቸው ህሙማኑ።

ድጋፍ የሚያደርገው ሰውም በጣም እየቀነሰ ስለመጣ ህሙማኑ በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው። ዲያሌሲስ ሁለት ጊዜ፣ አንዴ የሚያደርጉ አሉ። አንዳንዶች የሚበሉትን፣ የሚጠጡትን እየቀነሱ ይገኛሉ”
ብለዋል።

በኢትዮጵያ ስንት የኩላሊት ህሙማን አሉ ? ከእነዚህ መካከል ስንቶቹ ህክምና የመከታተል እድል አግኝተዋል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ፦

“ 400 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ዲያሌሲስ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛዎቹ ዲያሌሲስ ማድረግ ስለማይችሉ ትተው ነው።

ግማሹ ጸበል ይሄዳል። ስለማንሰማ እንጂ ህይወታቸው የሚያልፈው ይበዛሉ። ዲያሌሲስ በማድረግ የሚታገለውን ነው የምናውቀው። ያም ቢሆን ሲቸግረው አንድም ሁለትም ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርግ አለ በወር ውስጥ።

ይተዛዘናሉ። ሦስት ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርገው ሰውዬ ‘ሁለት ይበቃኛል’ ብሎ አንዱን ለሌላ ይሰጣል። በእንደዚህ እየታገሉ ነው ያሉት።

የምንችለውን እያደረግን ለተወሰኑ ሰዎች ነው ለመድረስ የቻልነው ለብዙ ሰዎች መድረስ አልቻልንም። ምንክንያቱም ድጋፉ በደንብ ተጠናክሮ እየቀጠለ አይደለም።

ህብረተሰቡም ደግሞ ስለ ጉዳዩ ያገባኛል ብሎ ትኩረት ሰጥቶ ሲረዳ አንመለከትም። የሚያጭበረብረው ሰውም በዝቷል ”
ሲሉ አስረድተዋል።

ማህበሩ ፤ “ ሰው ለመርዳት ችግር የለበትም ይረዳል። ትልቁ ችግር ማስታወስ ላይ ነው ያለው። እናንተም ለህብረተሰቡ በማስታወስ እርዱን ” ሲል አሳስቧል።

“ ትልቅ መፍትሄ ይሆናል ብለን የምናስበው ከሞተ ሰው ኩላሊት እንዲወሰድ የህግ ማዕቀፍ ሲወጣ ነው ” ያለው ማኀበሩ፣ “ ሲጸድቅ ሰዎች ሰላም ያገኛሉ። እስከዚያ ድረስ ዲያሌሲስ እያደረጉ መቆየት ግድ ይላቸዋል ” ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መታወቂያ መስጠት መቼ ይጀመራል ? " አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል " - CRRSA የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክልል ከተሞች መሸኛ ለሚያመጡ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት መቼ እንደሚጀምር ጠይቀነው የሰጠንን ምላሽ በተደጋጋሚ አድርሰናችሁ ነበር። ኤጀንሲውን ከዚህ ቀደም…
#አዲስአበባ #መታወቂያ

“ ወደ 33 ሺሕ የሚሆን መረጃ ለሰላምና ጸጥታ ልከናል በየክልሉ ተጠርቶ እንዲመጣ በአንድ ወር ውስጥ ” - CRSSA

ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ለሚመጡ ተቋርጦ የቆየው የአዲስ አበባ መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት መቼ እንደሚጀመር ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ መቼ ይጀመራል? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው ኤጀንሲው፣ “ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” የሚል መስጠቱ አይዘነጋም።

አገልግሎቱ ባለመጀመሩ በድጋሚ መቼ እንደሚጀመር ስንጠይቀውም፣ “ ነሐሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም የትምህርት ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ እንሰጣለን ” ነበር ያለው።

ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላም አገልግሎቱን የመስጠት ተግባሩ ሲጓተት ቆይቷል።  

አሁንስ አገልግሎቱ ተጀመረ ?

አሁንስ ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ለሚመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት የመስጠት ስራው ተጀመረ ? ተብሎ የተጠየቀው ኤጀንሲው አገልግሎቱ እንደተጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኤጀንሲው ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ ምን አሉ ?

“ አገልግሎቱ ከተጀመረ ወር ሆኖታል። በሁለት መልኩ ነው ሥራውን እየሰራን ያለነው።

አንደኛው ቀርበው ሪፓርት እንዲያደርጉ፣ የፋይዳ ቅድመ ሁኔታ አደረግን። ከተጠሩት ውስጥ ቀድመው ሪፓርት ያደረጉት በጣም ጥቂት ናቸው።

ከዚያ ባሻገር ደግሞ ለሚዲያ በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ክልል የመጡ መሸኛዎችን መልሰን ለክልል እንልካለን ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ብለን ነበር። 

በዚህም በዛም መልኩ እንግዲህ እኛ ጋ ሪፓርት ያደረጉ ሰዎች ቁጥር ካመለከቱት ቁጥር ጋር ሲያያዝ በጣም አንሷል መጥተው ሪፓርት ያደረጉ ማለት ነው።

እናጣራለን ስንልም ሀሰተኛ ሰነድ ላይ ያለው ሁኔታ ትንሽ ፍርሃት ፈጥሯል መሰለኝ። ወደ 33 ሺሕ የሚሆን መረጃ ለሰላምና ጸጥታ ልከናል በየክልሉ ተጠርቶ እንዲመጣ በአንድ ወር ውስጥ።

ያ ማለት ሀሰተኛ መሸኛ ይዞ መጥቶ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያደረገውን፣ ሀሰተኛ መሸኛ ያስገባውንም ሰው ወደ ወንጀል ተጠያቂነት እናመጣለን የማይቀር ነው።

ዞሮ ዞሮ አገልግሎቱ ክፍት ነው ”
ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ኤጀንሲው ከ42 ሺሕ በላይ ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ወረፋ እየጠበቁ ያሉ አገልግሎት ፈላጊዎችን መረጃ አጣርቶ አገልግሎት እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።

(በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ዌብሳይቱ ላይ የሚያሳየን ንግድ ፈቃዱ እንደታደሰ ነው ግን ፕሪንት አያደርግም። ... ክፍያውንም እንደ ከፈልን ያሳያል ግን ክፍያ አልከፍልንም ፤ ይሄ ደግሞ የሲስተም ችግር ነው " - ቅሬታ አቅራቢ

የንግድ ፈቃድ ያለ ቅጣት ማደሻ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ይጠናቀቃል።

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሃምሌ 1 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ያለ ቅጣት እንዲካሄድ ፕሮግራም ወጥቶ ሲካሄድ ነበር።

በኃላም ተጨማሪ ቀን ተጨምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ተራዝሟል።

ይህ የተጨመረው ቀን ማለትም ያለ ቅጣት ማደሻ ሊጠናቀቅ 3 ቀን ብቻ ቀርቶታል።

ተገልጋዮች በኦንላይን ፈቃድ ለማሳደስ በስራ ቀናት እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

የንግድ ፈቃድ በኦንላይን የሚታደሰው በ
www.etrade.gov.et ላይ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ፈጽመው ምስክር ወረቀት በመጠባበቅ ላይ ያሉ ' የምስክር ወረቀት ያትሙ ' (Print Certificate) የሚለውን ቁልፍ በመጫን የምስክር ወረቀታቸውን ማግኘት ይችላሉ።

ከዚሁ ከንግድ ፈቃድ እድሳት ጋር በተያያዘ ግን አንዳንድ ተገልጋዮች እክል ገጠመን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ልከዋል።

ከነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች አንደኛው  ፦

"  ክሊራንስ በታህሳስ 30 ላይ ነበር የጨረስኩት ፤ ከጨረስኩበት ሰዓት ጀምሮ ንግድ ፈቃዱን ለማደስ ክፍያ በምከፍልበት ሰዓት አንደኛ ክፍያው እንደ ተከፈለ ነው የሚያሳየኝ ፤ ሁለተኛ የመክፈያ ቁጥር ተብሎ የተሰጠኝ ቁጥርን ቴሌብር ላይ ስሞክረ ' ይሄ ክፍያ ተከፍላል ' ነው የሚለው።

በሲስተሙ ምክንያት ምንም ነገር መስራት እና ፈቃዱን ማደስ አልቻልኩም። ዌብሳይቱ ላይ የሚያሳየን ንግድ ፈቃዱን ፕሪንት አያደርግም ግን እንደ ታደሰ ያሳያል። ክፍያውንም እንደ ከፈልን ነው የሚያሳየው። ግን ክፍያ አልከፍልንም ይሄ ደግሞ የሲስተም ችግር ስለሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ያስጠይቀናል።

ሲስተም እስከሆነ ድረስ ቅጣቱን እና ወለዱን ይዞ ነው። አሁን ባለው እንኳን ቅጣት 2,500 ነው ከዛ የጊዜ ገደብ ተሰጥቶ ካለፈ ወደ 10 ሺህ ከፍ ይላል።

እኛ ባላጠፋነው ፤ በጊዜው ክሊራንስ ጨርሰን ብንገኝም በሲስተም ምክንያት ማደስ አልቻልንም። ለዚህ መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" ኦንላይን ባሉበት ማራዘም ይችላሉ የሲስተም ችግርም የለም እስከ አሁን ያላደሱ ነጋዴዎች ቅጣት ውስጥ መግባት ይገባቸው ነበር ነገር ግን እስከ ጥር 15 ያለቅጣት እንዲያራዝሙ ተፈቅዶላቸዋል።

ችግርም ካለ የተጠቃሚዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ነው የሚሆነው አሁንም ሲስተሙ እየሰራ ነው ከሦስት ቀን በኃላ ግን ሊያበቃ ይችላል።

አዋጁ የሚለውን ትተን ለንግዱ ማኅበረሰብ በማሰብ ያለቅጣት ከታህሳስ 30 በኋላ ለ15 ቀን እንዲያድሱ ፈቅደናል ሲስተሙ 24 ሰዓት ይሰራል ኤረር (Error) የሚላቸው የአጠቃቀም ችግር ነው በጣም የለማ ሲስተም ነው ያለን።

ለውጤታማነቱም በዚህ አመት በ6 ወር ውስጥ ሁለት ሚሊየን ሃምሳ ሺህ (2,050,000) ሰዎች ንግድ ፈቃድ የማውጣት እና የማደስ አገልግሎት አግኝተዋል።

የሚቀር ነገር አይጠፋም አልፎ አልፎ የሲስተም መቆራረጥ ሊኖር ይችላል ነገር ግን በአብዛኛው አፈጻጸማችን ውጤታማ ነው።

ይህ ሁሉ ሰው ካሳደሰ የሚቀረው ጥቂት ነው በርካታ ሰው ተገልግሏል በነጋዴዎች ችግር ካልሆነ በቀር ከሃምሌ ጀምሮ ማሳደስ ይችሉ ነበር ለምን እስካሁን አረፈዱ በመጨረሻ ሰዓት እንደዚህ አይነት ቅሬታ ማቅረብ ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

🔴 እዛው አካባቢ በዘመናዊ መኖሪያ ቤት የማስፈር ሀሳብ ታጥፎብናል ” - ቅሬታ አቅራቢ ነዋሪዎች

🔵 “ በመመሪያው መሠረት እንደማንኛውም የቀበሌ ተነሽ እንዲስተናገዱ ነው አቅጣጫ የተሰጠው ” - የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀድሞ መሬት ልማት አስተዳደር አካል

ከዓመታት በፊት ኤግል ሔልስ የተሰኘው ድርጅት ለገሀር አካባቢ በያዘው የግንባታ ፕሮጀክት ላይ የቦታው ነዋሪዎች መንግስት የገባላቸው ቃል ታጥፎ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ መገደዳቸው እጅጉን ቅር እንዳሰኛቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ስሞታቸውን ልከዋል።

“ ከስድስት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቃል የተገባውን እዛው አካባቢ በዘመናዊ ቤት የማስፈር ሀሳብ በማጠፍ ቦሌ አራብሳ በቆርቆሮ በተሰሩ ቤቶች ” እንዲሄዱ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ቅር ያሰኛቸውን ቆርቆሮ ቤት የሚያሳይ ቪዲዮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ነዋሪዎቹ፣ ለጉዳዩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደርን፣ የወረዳ 10 መሬት ልማት ጽሕፈት ቤትን ተጠያቂ አድርገዋል።

ለቅሬታው ማብራሪያ የጠየቅናቸው አዲሱ የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደርና ወረዳ 10 መሬት ልማት አስተዳደር አካላት የቅሬታውን ዝርዝር በጽሞና ከሰሙ በኋላ ለጊዜው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ ከ15 ቀናት በፊት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር የነበሩትን (አሁን ከስፍራ የለቀቁ) አካል ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቋል።

በቦታው ቤት ‘ይሰራላችኋል’ ተብለው የነበረ ቢሆንም ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ ስለመገደዳቸው ነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ የገለጽንላቸው እኚሁ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ 27 ናቸው እዛ አካባቢ ያሉት ነዋሪዎቹ። የዛኔ ተብሎ ነበር። አሁን ደግሞ ሰዎቹ እንዲነሱ ሆኗል ” ብለዋል።

“ ሙሉ ለሙሉ ይዞታቸውን ‘አስረክቡን’ እያሉ ነው። ስለዚህ መንግስት ምን አደረገ፦ ቤቶቹን ድሮ በምድር ባቡር ነበር ያከራየው ለሰዎቹ፣ ወደ መንግስትም አልተመለሰም ዝም ብሎ ለነዋሪዎቹ በምድር ባቡር ሰጣቸው ” ነው ያሉት።

“ ምድር ባቡር አሁን ጥሎ ሲወጣ መንግስት ወደ መንግስት አዞረና በመመሪያው መሠረት እንደማንኛውም የቀበሌ ተነሽ እንዲስተናገዱ ነው አቅጣጫ የተሰጠው ” ሲሉ አክለዋል።

በመርሀ ግብር ማስጀመሪያው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጭምር ነዋሪዎቹ ሳይፈናቀሉ በአካባቢው መኖሪያ ቤት እንደሚገነባ ገልጸው ነበር፤ አሁን ያ ቃል ታጥፎ ነው ? ስንል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

የቀድሞው የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፣ “ 27 ብቻ አይደለም የነበሩት የዛኔ። እነዚህ 27ቱ የቀሩበት ምክንያት የምድር ባቡር ቤቶች ስለነበሩ ነው ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ሌሎቹ የቀበሌ ቤቶችኮ ሙሉ ለሙሉ ተነሱ” ያሉት እኚህ አካል “ ይሄንን መንግስት ያደረገው እነዚህ ሰዎች ነዋሪ ናቸው። ነዋሪ መበተን የለበትም ቀበሌ ቤትም ባይሆን የመንግስት ቤት ስለሆነ በመንግስት ቤት መመሪያ መሠረት አገልግሎት ይሰጣቸው ነው ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ወቅት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ምን ብለው ነበር ?

" የኛ ፍልስፍና ሀብታሞች ገንዘብና እውቀት ይዘው መጥተው እነርሱም ሞር ሀብታም የሚሆኑበት፣ በአካባቢው ያለውን ነዋሪ ሞር ስደተኛና ድሃ የሚደረግበት ሁኔታ መቆም አለበት የሚል ጽኑ አቋም አለን።

በዚሁ ምክንያት እዚህ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ከ1,600 የሚበልጡ ቤተሰቦች፣ አባወራዎች አንደኛ ለዘመናት የኖሩበት፣ ከአዲስ አበባ ምናልባት ከአካባቢ አገራትም ከተማ በእነርሱ ይገነባል።

ሁለተኛ ለእነርሱ የመኖሪያ ቤት መስሪያ 1.8 ቢሊዮን ብር ኤግል ሔልስ ለመንግስት ስለሰጠ እዚሁ ቦታ ላይ ቤት ይገነባላቸውና አሁን ካላቸው የኑሮ ደረጃ የተሻለ የቤት ባለቤት ያደርጋቸዋል።

ሰፈሩ እዛም ውስጥ ያሉ እስከዛሬ ሲገፉ የነበሩ ሰዎችን ስናስታውስ ያንን ችግር የሚቀርፍ ይሆናል። ይህንን የመንግስት የተጀመረ አሰራር ወደ ፊት ወደ አርሶ አደሮች፣ ወደ ግለሰቦች ለማስፋፋት እንፈልጋለን።

አንድ ሰው ቦታ ኖሮት ሌላ ሰው በዚያ ቦታ ማልማት ሲፈልግ ሰውየውን ሳያፈናቅል፣ ከአጠቃላይ ፖሮጀክቱ 5ም፣ 10ም ፐርሰንት ሰጥቶ ሰውየውም አድጎ አዲስ የመጣውም ባለሃብት አብሮ የሚያድግበት ነገር ስለሚፈጥር እዚህ ቦታ ላይ ለኤግል ሔልስ አልሰጠንም። 

ቦታውን መንግስት 27 ፐርሰንት ሼር ውስዷል። ይሄ የሆነበት ምክንያት ጆይንት ቤንቸር ለመፍጠር ነው።

የነበረውን እያጠፋን፣ በአካባቢው ያለውን ሰው እየገፋን ሳይሆን ሰው ባለበት፣ ታሪካችንም ባለበት ግን የተሻለና ያማረ ነገር መፍጠር በውስጡ የያዘ በመሆኑ ይህንን ለሚያደርገው ኩባንያውንም፣ ቸር ማኑንም በሙሉ ልብ ስለማምን ዝርዝር ዲዛይን ዝርዝር ውይይት አድርገናል። 

ካሁን በኋላ ከዚህ ያነሰ፣ ሰው የሚያፈናቅል፣ ለአካባቢው ሰው ቤት የማይሰራ ባለሃበት ከሆነ ሂዳችሁ ከኤግል ልምድ ውሰዱ ይባላል ” ብለው ነበር። 


ይሁን እንጂ ይህ ቃል ታጥፎ ነዋሪዎቹ ወደ ቦሌ አራብሳ እንዲሄዱ መገደዳቸውን ገልጸዋል። 

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#iSonXperiences ከትላንት ጀምሮ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያሳያል። ሰራተኞቹ የሥራ አድማውን ያደረጉት መስሪያ ቤታችን ቅሬታችንን ሊመልስልን አልቻለም በሚል መሆኑን ገልጸዋል። ሰራተኞቹ ካቀረቡት ጥያቄዎች ዋነኛው " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞቹን በራሱ ሥር ያካተን ፤ በኤጀንት…
የስራ ማቆም አድማ የመቱት ሰራተኞች ምን አሉ ?

🚨“ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም” - የሥራ ማቆም አድማ የመቱ ከ350 በላይ ሠራተኞች

➡️ “ በዚሁ ዙሪያ ስብሰባ ላይ ነኝ ” - ድርጅቱ

በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ የሰራተኞች ማኀበር ሥር እንደሚተዳደሩ የገለጹ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ከ350 በላይ ሠራተኞች ዘርፈ ብዙ ቅሬታዎች ስላልተፈቱላቸው ከትላንት ከሰኞ ጅምሮ ሥራ ማቆም አድማ ለመምታት መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሚከፈላቸው ደመወዝ በቂ እንዳልሆነ፣ ድርጅቱ 80 ሰራተኞችን ያለ አግባብ እንዳሰናበተ፣ የትራንስፓርት አገልግሎት ባለመኖሩ በድርጅቱ ለማደር የሚገደዱ ሰራተኞች እንዳሉ አስረድተዋል።

ሰራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ?

“ አይሰን ኤክስፕሪያንስ የሚባለው ድርጅት የሳፋሪኮምን የኮል ሴንተሩንና የሲምካርድ አፕሩቫሉን ፕሮሰስ ወስዶ የሚሰራ ድርጅት ነው።

በዚህ ድርጅት ላይ ያለን ቅሬታ፣ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም።

ማታ አራት ሰዓት ከሥራ ለሚወጡ ሰዎች ትራንስፓርት የለም። ግማሽ መንገድ ወስዶ ከዚያ ‘በራሳችሁ ሂዱ’ ነው የሚለው። ይህ አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ጭራሽም ትራንስፓርት የሌላቸው ሠራተኞች ከመስሪያ ቤቱ አድረው የሚወጡ አሉ። 

አመታዊ እረፍት ሠራተኞች በፈለጉት ጊዜ አይሰጣቸውም። ከሁለት ዓመት በላይ የተጠራቀመ የአመት እረፍት ያላቸው ልጆች አሉ። ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ሠራተኞች ቅነሳ አለ። በርካታ ችግሮች ናቸው ያሉት።

በእነዚህ ጉዳዮች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በተገኙበት ስብብሰባ አድርገን ነበር። የመጣው ለውጥ ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። 

የመጨረሻውን ስብሰባ ያደረግነው ያለፈው አርብ ነበር። እንደማንስማማና ኃላፊነታችንን እንዳነሳን ተናግረናል። ከሰኞ ጀምሮም ሠራተኛው መብቴን በሕግ አስከብራለሁ ብሎ የሥራ ማቆም አድማ እያደረገ ይገኛል።

አሁን የሰፋሪኮም የጥሪ ማዕከል አይሰራም። ሲም ሽያጭ ላይ አፕሩቭ ከሚሰሩ ልጆችም ጭምር ነው አድማ ያደረግነው ስለዚህ ሁለቱም ሰርቪሶች አይሰሩም።

ይህን ከማድረጋችን በፊት ከሁለት ዓመታት በፊትም ተወያይተን ስላልተስማማን አድማ አድርገን ነበር፡፡ አሁንም በ10 ቀናት ጥያቄያችንን መልሱልን ብለን ከወር በፊት ደንዳቤ አስገብተን ነበር፡፡ ምላሽ አልተሰጠንም፡፡

ደብዳቤውን ካስገባን በኋላ አንድ ወር በፈጀ መደራደር በአራት ጊዜ ቀጠሮ ለመደራደር ሞክረን ነበር፡፡

ኢሰማኮ፣ የሰራተኛ አሰሪዎች ፌደሬሽንና ሌሎች ተቋማት በመካከል ገብተው ለማደራደር ሞክረው ካቅም በላይ ስለሆነ ሥራ የማቆም አድማ ለማድረግ ተገደናል፡፡ ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው፡፡

አይሰን ኤክስፕሪያንስን ስንጠይቅ አሁን 'ግቡልንና እናስተካክላለን' የሚል ሀሳብ እያመጡ ነው። ግን የሚጨምሩት ደመወዝም የሚያስማማን አይደለም፡፡ እስከ 15 ፐርሰንት እንጨምራለን' ነው እያሉ ያሉት፡፡

ሥራ ለማቆም የተገደደው መሰረታዊ ፍላጎታችን ማሟላት ስላልቻለ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየጨመረ ነው ያለውና ድርጅቱ መፍትሄ ይስጠን፡፡

የምንሰራበት ሰዓት ከቀኑ 2 እስከ 11 ሰዓት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሽፍት ሌሊትም ሥራ  እንገባለን፡፡ በሌሊት ሽፍት የትራንስፖርት አገልግሎት አናገኝም። ህይወታችንን ለአደጋ የሚጥል ሥራ ነው እየሰራን ያለነው
ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ የሚመለከታቸው አካላትና ድርጅቱ ለቅሬታው የተሻለ ምላሽ ቢሰጡ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ጉዳዩ በቀጥታ አይሰን ኤክስፕሪያንስን እንጂ እሱን እንደማይመለከት ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪም፣ ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ከአይሰን ኤክስፕሪያንስ አቶ በፍቃዱ አበራን ጠይቋል።

አቶ በፍቃዱ፣ በጉዳቹ ዙሪያ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ተጠይቀው በሰጡት ቀጠሮ ወቅት ሲደወልም ስልክ ለማንሳት ለጊዜው ፍቃደኛ አልሆኑም።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ አስተያዬት እንዲሰጡ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኀበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ለጊዜው የማይመች ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸው ቀጠሮ ሰጥተዋል።

የሚመለከታቸው አካላት በቅሬታው ላይ አሁንም አጥጋቢ ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። (የቅሬታ አቅራቢዎቹ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የስራ ማቆም አድማ የመቱት ሰራተኞች ምን አሉ ? 🚨“ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም” - የሥራ ማቆም አድማ የመቱ ከ350 በላይ ሠራተኞች ➡️ “ በዚሁ ዙሪያ ስብሰባ ላይ ነኝ ” - ድርጅቱ በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ የሰራተኞች ማኀበር ሥር እንደሚተዳደሩ የገለጹ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ከ350 በላይ…
#Update

🔴 “ በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል ” - ማኀበሩ

🔵 “ 20% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል ” - ሠራተኞቹ

“ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰናል ” - ፌደሬሽኑ

በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ መሠራተኞች ማኀበር ሥር የሚተዳደሩት የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ሠራተኞች በማኀበሩ ላይ ቅሬታ ማቅረባቸውን ከሰዓታት በፊት መረጃ አድርሰናችሁ ነበር። 

ቅሬታ የቀረበበት ማኀበሩ በወቅቱ ማብራሪያ ሳይሰጥ የቆዬ ሲሆን፣ በኋላ ለቀረበበት ቅሬታ በሰጠን ምላሽ፣ “ስምምነት ላይ ደርሰናል” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማኀበሩ የሰው ኃብት አቶ በፍቃዱ አበራ፣ “ስብሰባ ላይ ነበርኩ። ውይይት ላይ የነበረ ጉዳይ ነው። ውይይቱም በሰላም ተጠናቋል” ብለዋል።

ሠራተኞቹ ብዙ ቅሬታ አላቸውና በምን ተስማማችሁ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “አጠቃላይ እንደቀረፍን ነው ልነግርህ የምችለው። በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል” ነው ያሉት።

ስምምነት ላይ ደርሳችኋል ስንል የጠየቅናቸው ሠራተኞቹ በበኩላቸው አሁንስ ምን አሉ ?

“ ተነጋግረናል ሥር ጀምረን ከዛ ለማስተካከል፡፡ 20% የደመወዝ ጭማሪ አደርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል፡፡

'የትራንስፖርት ጉዳይም ይስተካከላል፣ አሁን ባለው የሥራ ማቆም ምክንያት ማንም ሰው እንዳይባረር፣ ሌሎችንም ጥያቄዎች ደግሞ በኅብረት ስምምነት ገብተን እንፈታልን’ ብለው ሁሉም ሠራተኞች እንዲመለሱ ነው የስማማነው፡፡

ችግሩ ተፈትቷል፡፡ የሚዲያ ትኩረት አጣንና በመጨረሻ በማይሆን ነገርም መስማማት ግዴታ ሆነብን፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በላይ ሥራ ካቆምንም የሥራ ዋስትና አይኖርም ብለን እጅ ሰጥተናል፡፡ 

አንገብጋቢው ጉዳይ የደመወዝ ጉዳይ ስለነበረ እሱ ላይ 20% ጭማሪ በቀጣይ ወር ኢፌክቲቭ እንደሚሆን፣ ከዚያ ውጪ ሌሎች የሚሻሻሉ ነገሮችን በውይይት ተቀራርበን መስራት አለብን በሚለው ተነጋግረናል ” ብለዋል።


የ20% ደመወዝ ጭማሪ እዳደረገላቸው ነው የገጹት ሠራተኞቹ፣ ይሄ እውነት ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ የማኀበሩ የሰው ኃብት፣ “ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ከመስጠት እቆጠባለሁ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ ተደርጓል የተባለው የደመወዝ ጭማሪ ትክክል ነው? ሲል በውይይቱ ሲሳተፍ ለነበረው ለትራንስፓርትና መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ጥያቄ አቅርቧል።

የፌደሬሽኑ ፕሬዜዳንት አቶ አባትሁን ታከለ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ ደመወዝ ጭማሪ በኀብረት ስምምነቱ የሚቀመጥ ነው። ኀብረት ሰምምነት አልነበረም። ወደፊት በኅብረት ስምምነት እንደምናስቀምጥ፣ ዘላቂ መፍትሄ እንደምናመጣ ተግባብተናል ከአሰሪው ጋ።

ነገር ግን ለጊዜው አሁን ያለውን ሁኔታ አገናዝበን አሰሪው ከታች ከ5% ተነስቶ ወደላይ ከፍ ብሎ፣ ሠራተኞም ከላይ ወደታች መጥተው፣ በኛም መሠረት ከየተካቲት 1/2017 ዓ/ም 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምነት ላይ ደርሰናል።

አሁን ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከነገ ጀምሮ ሥራ ይገባሉ ”
ብለዋል።

ሠራተኞቹ ቅር የተሰኙባቸው ከደመወዝ ውጪ ያሉ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በምን ተስማማችሁ! ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፕሬዜዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ሌሎች የተነሱ ወደ ዘጠኝ ጥያቄዎች ነበሩ፣ ለጊዜው በኅብረት ስምምነት ወደፊት የሚፈተለ አሉ። የትራንስፓርት ጉዳይም በኀብረት ስምምነት የሚፈታ ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

⛽️“ ነዳጅን በኮፓን የማድረግ እሳቤው በነዳጅ እጦት ተማረን ግዴታ የኤሌክትራክ ተሽከርካሪ እንድንጠቀም ለማድረግ ነው ” - አሽከርካሪዎች

➡️ “ ማደያ የነበረው ነዳጅ ሲጎድል የወሰዱትን በሁለት፣ በሦስት እጥፍ ጨምረው የመሸጥ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት አረጋግጠናል” - ቢሮው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከጥር 30 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ነዳጅ የሚቀዳው ኩፓን እንደሆነ የሚገልጽ ሰርኩላር ከቀናት በፊት አውርዷል።

እንደ ቢሮው ገለጻ ከሆነ መመሪያውን ለማውረድ የተገደደው በተለይ ባለሁለትና ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ነዳጅ በተደጋጋሚ በመቅዳት በውድ ዋጋ እየሸጡ ሌሎቹን ለነዳጅ እጥረት እያጋለጡ በመሆኑ ነው።

መመሪያውን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች ደግሞ፣ “ ነዳጅ በኩፖን እንዲሆን የተደረገው በአሽከርካሪዎች ሳቢያ ነው መባሉ የተጨፈለቀ እሳቤና እንደማንፈለግ ማሳያ ነው ” ሲሉ ትችታቸውን አቅርበዋል።

ጉዳዩን በጥናት ደርሰውበት ከሆነም ድርጊቱን የፈጸሙት ላይ እርምጃ መውሰድ እንጅ ሁሉን በአንድ ላይ ጨፍልቆ መውቀስ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸው፣ “ ነዳጅን በኮፖን የማድረግ እሳቤው በነዳጅ ተማረን ግዴታ የኤሌክትራክ ተሽከርካሪ እንድንጠቀም ለማድረግ ነው ” ብለዋል።

“ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪውንም መጠቀም አይገደንም ” ያሉት አሽከርካሪዎቹ፣ “ ግን በየትኛው የተሟላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው የምንጠቀመው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ነዳጅ በኮፖን እንዲቀዳ የተላለፈውን መመሪያ ተከትሎ ላቀረቡት ቅሬታና ስጋት ምላሽ እንዲሰጡ የቢሮውን ምክትል ኃላፊና የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ታዲሁንን ጠይቋል።

ምን መለሱ?

“ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ጋር የሚገናኝ ነገር የለም፡፡ 

የአገሪቱ የቀጣይ አቅጣጫ በእርግጥ እየተከተልን ካለነው ዓለማዊ አጠቃላይ ሁኔታ አኳያ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን መጠቀም ጠቀሜታው የጎላ ነው ወደዛም ነው የምንሄደው በሂደት፡፡ 

ግን ዛሬ በአስገዳጅ ሁኔታ ይህን ፈጽሙ የሚል የተቀመጠ አቅጣጫ የለም፡፡ የኛም ፍላጎት ይሄ አይደለም፡፡ ችግሩን መፍታት ስላለብን ነው፡፡ 

ደብዳቤውም ሲጻፍ አጠቃላይ በክልሉ ያሉ ባለሁለትም ሆነ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ይህንን ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ኢንቴንሽን የለውም፡፡ ይሄን አይነት እይታ የለንም፡፡

ግን ችግሩን የሚፈጥሩ አካላት በስፋት አሉ። ችግሩ በገሃድ የሚታይ ነው፡፡ የህዝቡም ቅሬታ ነው፡፡ ስለዚህ ካለው ነገር አኳያ ችግሩን ለመቅረፍ ከተቀመጡ አሰራሮች ውስጥ አንዱን ተግባራዊ ወደ ማድረግ ነው የገባነው፡፡ 

ይሄ ሲባል ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ደረጃ ወንጀል እየሰራ ነው የሚል እይታ የለንም፡፡ ግን ችግር የሚፈጥሩ አካላትን ለይቶ እርምጃ ለመውሰድ ያገለግለናል ” ብለዋል።

አጠቃላይ መመሪያውን መተግበር ያስፈለገበትን ምክንያት በተመለከተ ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽስ ምን አሉ ?

“ ምርት በስፋት ይገባ ነበር ከዚህ በፊት። የሚመጣው ምርት ግን በተቃራኒው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚወጣበት፣ የሚባክንበት ሁኔታ አለ። ምርትን ከካምፓኒዎች ተቀብለው የሚያሰራጩ የማደያ ባለቤቶችም አሉ። 

ሁሉም ማለት አይቻልም የተወሰኑት ግን ለሚፈለገው አገልገግሎት እንዳይውል ጨለማን ተገን በማድረግ የድለላ ሥራ ለሚሰሩ አካላት በመስጠት የመጣን የነዳጅ ምርት ግማሽ ወይም ሙሉውን ዋጋ ጨምረው በአይሱዚ ጭነው የማውጣት ሁኔታዎች አሉ። 

ከዚያ ባሸገር ግን እንደ ክልል በጣም የተቸገርነው የባጃጅና ሞተር ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ከቀዱ በኋላ ውስጥ ለውስጥ ባሉ ቤቶች ውስጥ ወስደው ወደ ልላ እቃ በመገልበጥ በቀን ብዙ ዙር በመመላስ ነዳጅ ይቀዳሉ። 

ያ ሲሆን ማደያ የነበረው ነዳጅ ሲጎድል የወሰዱትን በሁለት፣ በሦስት እጥፍ ጨምረው የመሸጥ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት አረጋግጠናል። አብዛኛዎቹ ላይ እርምጃ ወስደናል።

ስለዚህ ይሄን ችግር ለመፍታት ሲባል ከዚህ በፊት በሪፎርም የተቀመጠ አሰራር ስለነበረ ይሄን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ተብሎ ነው በአዲስ መልክ ሰርኩላር የተጻፈው።

ስለዚህ በአካባቢው ያሉ የንግድ ተቋማት ኮፖን ያዘጋጃሉ። ኮፓን ሲያዘጋጁ የአሽከርካሪው ስም፣ ፎቶ፣ የተሽከርካሪው ታርጋና ውስጥ ክፍል ያለ የሞተር ሚስጢር ቁጥር በማካተት ነው የሚዘጋጀው።

ያ ሲሆን ለአሽከርካሪው ትክክለኛ ምድባ ይደረለታል። በዚህ መልክ ስምሪት ይሰጥና በተፈቀደለት ቦታ ተኪዶ ነዳጅ ይቀዳል። ለአገልግሎት ሲያውል ተመልሶ ይቀዳል። ” ብለዋል።

ይህ በጥናት ጭምር የተረጋገጠ ከሆነ ነዳጅን አውጥቶ በመሸጥ አኳያ በተጨባጭ ምን ያህል አሽከርካሪዎችና ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል? ስንል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

ቢሮው ምን ምላሽ ሰጠ ?

“ ዋናው መሠረቱ፣ ምንጩ ማደያው ስለሆነ እሱ ላይም ቁጥጥር ተደርጓል። በተደጋጋሚ ከተለያዩ አካባቢዎች እርምጃ የተወሰደባቸው ወደ ሰባት ማደያዎች አሉ።

ወላይታ ዞን ወደ 4 ቦታዎች፣ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ላይ፣ ጌዲዮ ዞን ላይ ይርጋጨፌ ከተማ፣ ሌሎቹም ጋ የነበሩትን አሽጎ በህግ ሂደት የተከሰሱበት ሁኔታ አለ። 

የነዳጅ ምርቶችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙት ቁጥር ስፍር የለውም።

የተሽከርካሪዎቹ  ቅርብ ጊዜ ነው በጥናት የተረጋገጠው። ከዚያ አኳያ ይህን ሰርኩላር መበተን ነበረብን። ግን በተጨባጭ ችግሩን እያወሳሰቡ ያሉት እነርሱ ናቸው። ” ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል ” - ማኀበሩ 🔵 “ 20% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል ” - ሠራተኞቹ “ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰናል ” - ፌደሬሽኑ በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ መሠራተኞች ማኀበር ሥር የሚተዳደሩት የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና…
#Update

“ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” - ሠራተኞቹ

በርካታ ቅሬታዎች ያደሩባቸው ከ350 በላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሱቫል ሠራተኞች ለቅሬታቸው አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።

“ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሩቫል ሰርቪሶች ተቋርጠዋል ” ብለው የነበረ ሲሆን፣ ሠራተኞቹን የሚያስተዳድረው አይሰን የተሰኘው ድርጅት ቅሬታውን በውይይት እንደፈታ ትላንት ምላሽ ሰጥቶን ነበር።

የትራንስፖርት መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን፣ ሠራተኞቹ ደመወዝ ሊጨመርላቸው ስምምነት ላይ እንደተደረሰ፣ ሌሎች ጥያቄዎቻቸው በሂደት እንዲፈቱ፣ ለዛሬ ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ነግሮን ነበር።

ሠራተኞቹ አቋርጠውት ወደነበረው ሥራ ተመለሱ ?

ለቅሬታዎቻችሁ " መፍትሄ አላገኘንም " በማለት መብታችሁን ለማስከበር ካደረጋችሁት የሥራ ማቆም አድማ በኋላ ዛሬስ ወደ ሥራ ተመለሳችሁ ? ስንል ጠይቀናቸዋል። 

ሠራተኞቹም፣ “ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” የሚል ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ሠራተኞቹ ፦

“ ሥራ ጀምረናል። ግን ገና ብዙ የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ። ሁሉም ቀስ እያሉ ይስተካከላሉ። የደመወዙ ጭማሪ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።

ሌሎቹን ጉዳዮች በተመለከተም ከቀጣይ ሳምንት ጀምረን ወደ ድርድር እንገባለን። 

ሁሉም ሠራተኞች ወደ ስራ ተመልሰዋል። ምክንያቱም ማንም ሰው ባደረገው የሥራ አድማ ምክንያት አሉታዊ ነገር እንዳይደርስበት ተፈራርመን ነው የተመለስነው ” ብለዋል።


በጉዳዩ ዙሪያ የሚፈጠር አዲስ ነገር ካለም የምንከታተልና መረጃም የምናደርሳችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች

🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ 

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው እየተስተጓጎሉ በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠንከር ያለ ስሞታ አቅርበዋል።

የተማሪዎቹ ዝርዝር ስሞታ ምንድን ነው ?

“ ኒቃብና ጥቁር ማስክ እንዳንለብስ ነው የተከለከልነው። ክልከላው የጀመረው ከአንድ ወር በፊት ነበር። በዚህም ማመልከቻ አስገብተን ነበር መልበስ እንዲፈቀድልን። ሆኖም ግን ምላሽ ሳይሰጠን ቆዬ።

ትምህርታችን በስርዓት እንዳንከታተል አስተጓጎሉን። ቅዳሜ፣ አንዲት እህት ማስክ አድርጋ፣ ሂጃብ ለብሳ በምትገባበት ወቅት ኦዲያ ካምፓስ በሁለቱም በሮች እንዳትገባ ከልክለዋታል።

እንዲያውም ወንዶቹ የግቢው ጥበቆች አስፈራርተው ፊቷን አስከፍተዋታል። እንደዛም ሆኖ ማስክ ለብሳ ወደ ግቢ መግባት እንደማትችል ነግረው መልሰዋታል። 

ቅዳሜ ከሰዓት ሁለት ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎች ግቢ ሊገቡ ሲሉ ተከልክለዋል። ለምን እንደተከለከሉ ሲጠይቁ ‘ ለደህንነት ሲባል ፊታችሁ መሸፈን የለበትም ’ አሏቸው።

ለደኅንነት ሲባል ከሆነ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሴት ጥበቃ ተፈትሸው፣ አይዲያቸውን አሳይተው እንዲገቡ ሲጠይቋቸው ‘ ያንችን ፊት ማየት ምንም አይሰራልኝም። ፊትሽን ለምታሳይው አሳይ ’ የሚል መልስ ተሰጠን።

ከዚያ በኋላም ሰኞ እለት ደግሞ ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ መልበስ እንደማይቻል በፕሬዜዳንቱ ጭምር ተወሰነ። የተማሪ ተወካዮች ጠርተው ይህን አሳወቋቸው።

ጥበቃዎቹም ውሳኔውን በመጥቀስ ‘አናስገባም’ አሉን። ማክሰኞ እለት ማታ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን።

ረቡዕ ጠዋትም ከለር ማስክ አድርገው የገቡትን በፌደራል ጭምር አስፈራርተው ፊታቸውን እንዲገልጡ አድርገው፣ ሂጃብም ማውለቅ እንዳለባቸው አሳሰቧቸው።

ከሰኞ ጀምሮ ክላስም እየተከታተልን አይደለም፣ ኤግዛም አልፎናል፣ አሳይመንትም እያለፈን ነው። ማውለቅ ስለማንችል ከግቢ ውጪ ነን። በቃ ከተማሪነት ውጪ ባለ ህይወት ነን። እንደ ሴትነታችን ትልቅ የመብት ጥሰት ነው የተፈጸመብን። 

ከምሽቱ 3 ሰዓት እንዳንገባ ሲከለክሉን የት እንድናድር፣ ምን እንድንለብስ፣ ምን እንደምንምገብ ያሰቡትን አናውቅም። ስለዚህ እንደንገባ ቢፈቅዱም እንዲህ ያደርጉበት ምክንያትን ሊጠየቁ ይገባል ”
ሲሉ ተናግረዋል።

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅናቸው ስማቸው እንዲነገር ያልፈቀዱ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ ስለጉዳዩ በዩኒቨርሲቲው ፌስ ቡክ ገጽ የወጣውን መረጃ እንድንጠቀም ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎቹ ነቃብ፣ ማስክና ሂጃብ ለብሰው እንዳይገቡ ተከልክለው ከግቢ ውጪ በመሆናቸው ትምህርት እያለፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፤ መከልከሉ ልክ ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

በምላሻቸው፣ “ እንዲህ አይነት ነገር የለም። የተሳሳተ መረጃ ነው። ማንም ተማሪ እዚህ ግቢ በተፈቀደለት ሰዓት ይገባል፤ ይወጣል ” ሲሉ መልሰዋል።

“ የተቋሙንም ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት አስተዳደር መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” ብለዋል።

ተማሪዎቹ በተጨባጭ ከግቢ ውጪ እንደሆኑ፣ ክላስ እያለፋቸው እንደሆነ በድጋሚ የገለጽንላቸው እኝሁ አካል፣ በድጋሚም “ የለም ” የሚል ማስተባበያ ነው የሰጡት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የጌዴኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን ተማሪዎች ደረሰብን የሚሉት ክልከላ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲው “ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” ብሏልና እናንተ ጉዳዩን አይታችሁት ነበር ? ሲል ማረጋገጫ ጠይቋል።

ምክር ቤቱ ምን መለሰ ?

“ ጉዳዩ ከወር በፊት ደርሶን ነበር። እየቆየ ከፍ እያለ መጥቶ ተማሪዎች ግቢ ለመግባት ሲከለከሉ እኛም ደብዳቤ ፅፈን ነበር ችግሩ እንዲፈታ።

ዩኒቨርሲቲው እርከን ያልጠበቀ ጉዳይ ተደርጎ ታይቶ ነው፤ ተማሪዎቹን እናገኛቸዋለን የሚል ጥሩ ስሜት ነበረው። 

የእስልምና አለባበስ ከጥንት ጀምሮ ራሱን የቻለ ሊቃውንቶች ያስቀመጡት ነው። ይሄ የተሻለውና ተመራጭ የሆነው አለባበስ ነው ” ብሏል።


(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ ቪዲዮው ደርሶናል። ምርመራ እያደረግን ነው ” - ኢሰመኮ

የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሰና መሳሪያ የታጠቀ አካል እጁን ወደ ኋላ የፊጢኝ የታሰረን ወጣት ከወደጀርባው በመሆን ጭንቅላቱ ላይ ሲተኩስበት የሚያሳይ ቪዲዮ ከሰሞኑን በማኀበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ድርጊቱ ብዙዎችን ያስለቀሰና ያስቆጣ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ “ እንዲያው እንደዚህ ያጨካከነን ምን ይሆን? ” ሲሉ በሀዘን ስሜት ተውጠው ሲጠይቁ ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበከሉ፣ ድርጊቱ ደርሶት በሰብዓዊ መብት ጥሰት አኳያ ጉዳዩን ዳሶት እንደሆን በሚል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ይህንን ግፍ የተሞላት ድርጊት ተመልክቶት ይሆን ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ ጉዳዩ ደርሶናል። እኛ የራሳችንን ኢንቨስቲጌሽን ስለምንሰራ በቪዲዮው ላይ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

ድርጊቱ የት ? መቼ ? በማን ተፈጸመ ? ለሚለው እካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የሌለ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ “ መቼ ነው የተፈጸመው ? ማነው የሞተውስ ? የሚለውን ዝርዝሩን በሙሉ እያጣራን ነው የምንገኘው ” ሲል ጠቁሟል።

“ ዲጂታሊ ሰርተን ስናበቃም እዚያው የነበሩ የአካባቢው ሰዎችን ደግሞ ማነጋገር ይኖርብናል” ነው ያለው።

ድርጊቱ የተፈጸመበት አካባቢ ታውቋል ? ለሚለው ጥያቄ ኮሚሽኑ በምላሹ፣ “ ፍንጭ አለን ግን አሁን ለሚዲያ መግለጽ አንችልም። ምክንያቱም እርግጠኛ አይደለንም። እሱን እርግጠኛ ስንሆን እንነግራችኋለን ” ብላል።

ስለዚህ አሁን ምርመራው ተጀምሯል ማለት ይቻላል? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ፣ “ ቪዲዮው ደርሶናል። ኢንቨስቲጌት እያደረግን ነው ” ሲል መልሷል ኮሚሽኑ።

እንዲህ አይነት ግልጽ የወጡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶትን በተመለከተ አስተያዬት እንዲሰጥ ጠይቀነው ባስረዳበት አውድ ደግሞ፣ “ አሁን ባለው ሁኔታ እንዲህ አይነት ቪዲዮዎች በብዛት እየወጡ ናቸው ሚዲያ ላይ። እኛ ጋም የሚደርሱ አሉ ” ሲል የድርጊቱን ሁኔታ አስረድቷል።

“ አስቸጋሪ ነው። በጣም ብዙ ናቸው እናንተ አንድ ብቻ ስላያችሁ ነው እንጂ። ስለዚህ ይሄ ቪዲዮ ላይ ብቻ አሁን ላይ ኮመንት ማድረግ አልችልም ” ነው ያለው።

“ በአጠቃላይ አገሪቱ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ለሚለው በየጊዜው የምናወጣቸው ሪፓርቶች አጠቃላይ የሚያሳዩት ገጽታ አለ እሱን መያዝ ነው ” ብሏል።

የሰሞንኛውን ቪዲዮ ምርመራ ሲያልቅ ሙሉ አስተያዬትና ማብራሪያ እንደሚሰጥ ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል የገባ ሲሆን፣ ሁነቱን ተከታትለን በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ የምናደረሳችሁ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ' ብር (ጉቦ) ክፈሉና እንቀጥልላቹ ' ያለን የቴክኒክ ክፍል ሰራተኛ አለ " - ቅሬታ አቅራቢዎች

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ሳይት 3 የብሎክ 734 እና 735 ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በገቡት የቆጣሪ እዳ ውዝግብ ምክንያት ሃይል ከተቋረጠባቸው 1 ወር ከ 5 ቀን መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠቀሱት ብሎኮች ሃይል ያቋረጠው " በሦስት ቆጣሪዎች ያልተከፈለኝ ከ160 ሺ ብር በላይ እዳ አለ " በማለቱ ምክንያት ነው።

ቆጣሪዎቹ የተተከሉት ሳይቶቹ በግንባታ ላይ በነበሩበት ወቅት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በገባው ውል ሲሆን ቆጣሪዎቹ የተመዘገቡት ደግሞ ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ውል በገባው እና ግንባታዎቹን ባከናወነው የስራ ተቋራጭ (ኮንትራክተር) ስም ነው።

" ይህ በሆነበት ሁኔታ ቆጣሪዎቹን ባልተረከብንበት እና ከእነዚህም ቆጣሪዎች ሃይል ቀጥለን ባልተጠቀምንበት ሁኔታ እዳውን ክፈሉ ተብለናል " ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" የመኖሪያ መንደሩ በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት የስራ ተቋራጩ (ኮንትራክተሩ) የተጠቀማቸው እና ግንባታቸው ተጠናቆ ከገባን በኋላም እንዲነሱ ባልተደረጉ ቆጣሪዎች ምክንያት የቆጣሪዎቹን የተጠራቀመ የክፍያ እዳ ክፈሉ ተብለናል ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናችንም ምክንያት ላለፈው አንድ ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ ሃይል ታቋርጦብናል" ነው ያሉት።

በሁለቱ ብሎኮች ከ60 በላይ ነዋሪዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኙ የልማት ሥራዎች ምክንያት የተነሱ እና ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት ወር ለሚሆን ጊዜ ገብተው መኖር የጀመሩ ናቸው።

ነዋሪዎቹ ቅሬታቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ያሳወቁ ሲሆን ጽ/ቤቶቹም ሃይል እንዲመለስላቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ በተናጠል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽፈዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢ/ር በላይ ሞቱማ ተፈርሞ በ07/05/17 ዓም የወጣው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ብሎኮቹን የገነባው ኮንትራክተር ቆጣሪዎቹን ከኮርፖሬሽኑ መረከቡን ከግንባታው በኋላም እነዚህን ቆጣሪዎች ከኮንትራክተሩ በመረከብ ለነዋሪዎች አለመተላለፉን እና አሁንም በኮንትራክተሩ የተመዘገበ መሆኑን ይገልጻል።

በዚህም ምክንያት ከቆጣሪው ጋር ተያይዞ የሚመጣ እዳ ሁሉ ኮንትራክተሩን እንጂ ነዋሪዎችን እንደማይመለከት በማስረዳት አስፈላጊውን ህጋዊ ድጋፍ ይደረግላቸው ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ጠይቋል።

የለሚኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በበኩሉ በ 09/05/17 ዓም በጻፈው ደብዳቤ  የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጻፈውን ደብዳቤ በመጥቀስ ለነዋሪዎች የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲደርግ እንገልጻለን ብሏል።

ሁለቱም ጽ/ቤቶች በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ሃይል የተቋረጠባቸው ነዋሪዎች  የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ቢጠይቁም አገልግሎቱ ሃይሉን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ላለፉት አንድ ወር በላይ በጨለማ ለመቀመጥ መገደዳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች በዝርዝር ባቀረቡት ቅሬታ ምን አሉ ?

" የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጠራቀመውን እዳ ኮንትራክተሩን ፈልጋቹ አስከፍሉ ወይም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እዳውን እንዲከፍል አድርጉ እያለን ነው እነሱ በተዋዋሉት እኛ የምንጠየቀው ለምንድነው ?

መንገድ ላይ ያሉ ቆጣሪዎች እንዲነሱ ማህበረሰቡ ከአመት በፊት ጀምሮ አቤቱታ እያቀረበ ነው ያለው አልተሰማንም ቆጣሪዎቹ ሃይል አልተቋረጠባቸውም፣ አላነሳቸውም እኛ ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል አልቀጠልንም።

በዚህም ምክንያት ተዋውለን ለብሎካችን ያስገባነውን ስሪ ፌዝ ቆጣሪ ሃይል አቋረጡብን ለምን ? ስንል የዛኛውን ቆጣሪ እዳ ካልከፈላቹ ተባልን ባልገባነው ውል ባልተጠቀምንበት ሃይል ክፈሉ ተብለን ለምን እንገደዳለን ? እዳው የተመዘገበው በኮንትራክተሩ ነው እኛ ለምንድነው የምንከፍለው።

ምግብ ለማብሰል እንጨት እና ከሰል ነው እየተጠቀምን ያለነው ተማሪዎች አሉ የሚመገቡትን ትተን ፈተና የሚፈተኑበት ጊዜ እንደመሆኑ ያጥኑ እንኳን ቢባል በምን ? ለተጨማሪ እና አላስፈላጊ ለሆነ ወጪ ነው የተዳረግነው።

ፊዩዝ በተደጋጋሚ እያመጡ እየነቀሉ እያዋጣን መክፈል ሥራ ሆነብን ሲበዛብን ከወር በፊት ሊነቅል የመጣውን ሰራተኛ ለማስቆም ሞከርን ለምን ታስቆሙታላቹ በሚል አጠፉብን በዚህ ምክንያት እየተበቀሉን ነው እስካሁን መብራት የለንም።

እያዋጣን ጉቦ መክፈል ሰልችቶናል ' ብር ክፈሉና እንቀጥልላቹ ' ያለን የቴክኒክ ክፍል ሰራተኛ አለ ይሄንን እና ሌሎች ነገሮች ስላሳወቅንባቸው ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ ቆጣሪ ያለባቸው ሳይቶች ላይ እንደዚህ አይነት እርምጃ ሳይወሰድ እኛ ላይ የተደረገው ለብቀላ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“ 763 ሠራተኞች ከ2013 ዓ/ም እስካሁን ደመወዝ አልተከፈላቸውም። ሌላ ቦታ እንዳይቀጠሩም የስንብት ደብዳቤ የለም ” - ጽሕፈቱ ቤቱ ስለቀድሞ ሰሜን ዕዝ ሲቪል ሰርቫንቶች

ከ760 በላይ የቀድሞ ሰሜን ዕዝ ሠራተኞች ከ4 ዓመት በላይ ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ከነቤተሰቦቻቸው በከፋ ችግር መሆናቸውን በኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የምን ያህል ጊዜ ደመወዝ ነው ያልተፈጸመላቸው? ስንል የጠየቅናቸው የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፀሐዬ እምባዬ፣ “763 ሠራተኞች ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ደመወዝ አልተከፈላቸውም። ሌላ ቦታ እንዳይቀጠሩም የስንብት ደብዳቤ የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“በሌላ መስሪያ ለመቀጠርምኮ የአገልግሎት ድጋፍ ያስጋል። ይህን የፃፈላቸው አካልም የለም። ዝም ብለው በባዶ እናንተ ‘ስላላመለከታችሁ ተሰናብታችኋል’ የሚል ነው” ነው ያሉት።

“ ይህ እንደ ዜጋ አግባብነት የለውም። ከ20 ዓመት በላይ የሰሩ ናቸው የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ሲቪል ሰርቫንት ሆነው ” በማለት ሁነቱን አስረድተዋል።

“ ከሠራተኞቹ ወጣት የሚበል የለም ማለት ይቻላል” ብለው፣ “ ከነቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ ናቸው የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጥ ” ሲሉም አሳስበዋል።

ኃላፊው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ከጦርነቱ በኋላ ሰሜን ዕዝ ከፈረሰ በኋላ ሰሜን ዕዝ ሲቪል ሰርቫንት በሥራ ላይ አልነበሩም እንደማንኛውም ሲቪል ሰርቫንት ሰራተኛ። ከፕሪቶራያው በኋላም ስምምነት ማንም ሰው ሊመለከታቸው አልቻለም።

ወደ ዋና መስሪያም ቤት ደብዳቤ ልከናል። መከላከያ ሚኒስቴርም ተጠይቋል። እነርሱ ግን ‘ነገሩ ከተስተካከለ በኋላ ተመለሱና ረፖርት አድርጉ ብለን አሳውቀናል’ይላሉ።

ግን በዚህ ጉዳይ የተፃፈ ደብዳቤም፣ የደረሳቸው ነገርም የለም። 2016 ዓ/ም እንደደረሳቸው ወዲያውኑ መጥተው ወደኛ አመለከቱ። ግን ሪፓርት ያደረጉትን ተቀብለናቸዋል፤ ያላደረጉ እንደሰናበቱ ይቆጠራል’ ብለው ነው የፃፉላቸው። 

የሚከታተል ሰው ካለ መጥቶ ያለና የሌለ፣ የሚገባውና የማይገባውን መለየት እንጂ የዓመታት ደመወዝ የሌላቸውን ሠራተኞች ‘ወደ አዲስ አበባ ተጉዛችሁ ሪፓርት አድርጉ’ ማለት አግባብ አይደለም። 

ሊሄዱ የፈጉም ነበሩ ግን የሦስትና አራት ዓመታት የቤት ኪራይ እዳ አለባቸው። እዳቸውን ሳይከፍሉ የሚለቃቸው የለም። ይህን ለማድረግ ንብረታቸውን ለአከራይ ማስረከብ አለባቸው።

እንዳይሄዱ መሳፈሪያ ገንዘብ የላቸውም። መካላከያም ‘ካልመጣችሁ አይሆንም ነው ያለውያና መንግስት እያሰራቸው በነበረው ቦታ ሰው ልኮ ቁጥጥር አድርጎ የሚገባውና የማይገባው ማጣራት አለበት ” ብለዋል።


“ ሲቪል ሰርቫንቱ መፍትሄ እየጠበቀ ነው ያለው። መፍትሄ ሊልጣቸው ይገባል። በወረቀት መወራወር ከሆነ ግን ጥሩ አይደለም ለቀጣይም ዜጋ ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

(የሚመለከታቸው አካላት ለዚህ ቅሬታ ምላሽ እንደሰጡ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 " ዩኒቨርሲቲያችን እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ➡️ " ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " - ሙስሊም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ / ሙስሊም…
#Update

“ በቋሚነት ይሁን ለጊዜው የተብራራ ነገር የለም፡፡ አሁን ግን ተማሪዎቹ ገብተው ትምህርታቸውን መማር ጀምረዋል ” - የዞኑ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በአለባሳቸው ሳቢያ ግቢ እንዳይገቡ በመከልከላቸው፣ ከትምህርት፣ ከካፌና ከማደሪያ ውጪ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡

ተማሪዎቹ በሰጡት ቃል፣ " 44 ሴት ተማሪዎችን ጥቁር ማስክ አድርጋችሁ 'አናስገባም' ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን " ነበር ያሉት።

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው ዩኒቨርሲቲው፣ እንደ ሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም እንደሆነና ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ እንዳልተከለከለ ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ እንደማይደረግ ገልጾ ነበር።

ተማሪዎቹ ግቢ እንዲገቡ ተፈቀዳላቸው ?

ወደ ግቢ ገባችሁ ወይስ አሁንም ከግቢ ውጪ ናችሁ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ተማሪዎቹ፣ " ለጊዜው ከስምምንት ተደርሷል " ሲሉ መልሰዋል።

" በተወካዮቻችን በኩል ኒቃብ፣ ማስክና ሂጃብ ለብሰን መግባት እንደምንችል ተነገረንና ትላንት ገብተናል " ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረት ለብሰው እንዲገቡ ከመነገራቸው ውጪ ሌላ የተባሉት ነገር እንደሌለ አስረድተው፣ " ለጊዜው ግን ግቢ ገብተናል " ነው ያሉት፡፡

በደብዳቤ ጭምር በመጠየቅ ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየውን የጌድኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትንም ግቢ እንደይገቡ ተከልክለው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ግቢ ገብተዋል ? ስንል ጠይቀናል፡፡

የዞኑ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ?

" በቋሚነት ይሁን ለጊዜው የተብራራ ነገር የለም፡፡ ግን ተማሪዎቹ ገብተው ትምህርታቸውን መማር ጀምረዋል፡፡

በዘላቂነቱ ላይ እንደ አገር የሚያዝ አቅጣጫ ይኖራል፡፡ ከዚያ ውጪ ግን ይሄ ነው ተብሎ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ ሲጀመር ክልከለውን በተመለከተም በፅሑፍ የተገለጸ የለም፡፡ አሁን ሲፈቀድም በተመሳሳይ ነው፡፡

አገራችን የብዙ ሃይማኖቶችና ብሔሮች መገኛ ስለሆነች ስርዓቶችም ሃይማኖቶችን፣ ብሔር ብሔረሰቦችን ያማካሉ ቢሆኑ፤ ለአንዱ እድል ሰጥቶ ሌላኛውን ያላገለሉ፣ ሃይማኖት ባሉ ነገሮች ምክንያት በሌሎች ቦታዎችም ሁሉን ያማከለ ሆነው ቢወጡ የተሻለ ነው፡፡

የጥብቅ ደን/ብዙ እፅዋቶችን አንድ ላይ ነው በማልማት የሚታወቀውና እንደ አገርም ቅርስ የተያዘለት ማህበረሰብ ያለበት ዩኒቨርሲቲም ስለሆነ ነገሮች ሲከናወኑ በዚያ ቢታሰቡ እጅግ መልካም ይሆናል
" ብሏል፡፡

የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ የዩኒቨርሲቲው አካላት ስልክ ለማንሳት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ለጊዜው ሃሳባቸውን ማካተት አልተሳካም፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ አቶ ዮሐንስን ቧያለውን ለይተው ‘ዞን አምስት’ የሚባል ቦታ አስገብተውታል። ያ ቦታ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሰው ከባድ ጥፋት ሲያጠፋ መቅጫ ነው ” - ጉዳዩን የሚከታተሉ አካል ለ1 ዓመት ከ5 ወር በእስራት ላይ የሚገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው አብረዋቸው ከነበሩት 41 እስረኞች ተለይተው “ ለሕይወታቸው አስጊ ወደሆነ ቦታ ” ለማዘወር ተገደዋል ይህ ደግሞ ጭንቀት ፈጥሮብናል…
“ ‘እስካሁን የተፋጠነ ምላሽ አላገኘንም' እያሉ ያሉ በችሎት ሁሌ ነው የሚያነሱት፤ በኛ እምነትም የተፋጠነ ፍትህ እያገኙ አይደለም ” - የእነ አቶ ክርስቲያን ጠበቃ

እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለድ ትላንት የችሎት ቀጠሮ ነበራቸው።

ጉዳዩን የሚከታተሉ የቅርብ ሰዎች፣ “የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ነበር ትላንት ተዘጋጅተው የሄዱት ግን ያ ሳይሆን ቀርቷል” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ትላንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ክሱን አሻሽሎ ይቀርባል ተብሎ ስለተጠበቀ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ሐምሌ 29/2016 ዓ/ም ላይ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ከዛ ‘አሻሽዬ አላቀርብም ብሎ ይግባኝ’ ብሎ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀረበ። 

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የስር ፍርድ ቤቱ የወሰነው ትክክል ነው ብሎ ባለፈው ሐሙስ በድጋሚ ክሱን እንዲያሻሸል ትዕዛዝ ሰጥቶት ነበር። በዚያ መሠረት ትላንት አሻሽሎ መጥቶ የእምነት ክህደት ቃላተቸውን ይሰጣሉ፤ ክሱም ይሻሻላል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ግን ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አሻሽሎ አልመጣምና አሻሽሎ እንዲመጣ ብሎ ረዘም ያለ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር ፍርድ ቤቱ። ነገር ግን አቶ ዮሐንስና አቶ ክርስቲያን ባቀረቡት ጠንካራ ክርክር ምክንያት ክሱ ተሻሽሎ መጥቶ ለጥር 29 የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
" ብለዋል።

ስለትላንቱን የችሎት ውሎ ማብራሪያ የጠየቃቸው የእነ አቶ ክርስቲያን ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ “ ከአራት ወራት በኋላ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናት ነው ትላንት የቀረቡት ” ብለዋል።

“ ትላንትም ታግዶ የነበረው የከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ተንቀሳቅሷል። ከዚህ በኋላ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ነው የሚሰጡት እርሱም ለጥር 29 ተቀጥሯል ” ነው ያሉት። 

እየ ክርስቲያን ትላንት የእምነት ክህደት ቃል አልሰጡም መባሉንና የጤንነታቸውን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ጠበቃቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

“ በስነ ስርዓት ህጉ መሠረት አንድ ለጊዜው የተዘጋ ፋይል መንቀሰቀስ አለበት፡፡ ከተንቀሳቀሰ በኋላ ነው ሌላው ሂደት የሚቀጥለው። በእለቱ መሆን ያለበት ፋይል ተንቀሳቅሶ ቀጠሮ መስጠት ነው እንጅ ሁለቱም አንድ ጊዜ አይታይም።

ስለዚህ እኛም ግልባጭ አምጥተን ከእግድም የተነሳ ነው በማለት ተዘግቶ የነበረው መዝገበ ተንቃሳቅሷል፡፡ ለእምነት ክህደት ቀጠሮ በማለት እንጅ በሌላ ምክንያት አይደለም።

ስለጤንነታቸውን በ6 እና በ3 ወራት የሚታወቅ ውጤት ስላለ ሙሉ ለሙሉ ተሸሏቸዋል ማለት አይቻለም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ወደነበሩበት ሙሉ ጤና ተመልሰዋል ማለት አይቻልም ግን የህመም ስሜታቸው ቀንሷል”
  ብለዋል።

የፍርድ ሂደቱ በየወቅቱ እየተራዘመ ነው ያለው ፤ ታራሚዎቹም በህመም እየተሰቃዩ እንደሆነ በቤተሰቦቻቸው በተደጋጋሚ ተነግሯል ፤ የፍርድ ሂደቱ ምን መሆን ነበረበት ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

“ ተከሳሾቹም በችሎቱ የሚያነሱት ጉዳይ ነው፡፡ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ህገ መንግስታዊ መብት ነው ይሄ፡፡ ሕገ መንግስታዊ ብቻም ሳይሆን ዓለም ዓቀፋዊም መብት ነው፡።

‘እስካሁን የተፋጠነ ምላሽ አላገኘንም' እያሉ ያሉ በችሎት ሁሌ ነው የሚያነሱት፤ በኛ እምነትም የተፋጠነ ፍትህ እያገኙ አይደለም፡፡ 

ምንያቱም የሽብር ችሎት አንድ ችሎት ነው፡፡ ይሄ ችሎት ነው ከ10 ዓመታት በላይ መዝገብ ይዞ እያየ ያለው፡፡ በዳኞችም ሆነ በችሎቱ መፍረድ አይቻልም፡፡ የፍርድ ቤቱ የተለያዩ ችሎቶችን አለመመደብ ችግር ነው እንጂ የዳኞች ስራ አለመስራት ችግር አይደለም፡፡

ስለዚህ ትልቁ ችግር የችሎት ማነስ ነው፡፡ አንድ ችሎት ብቻ ነው ያለው፡፡ የችሎት መታጠፍ አለ፡፡ ሦስት ችሎት ነበር ከዚህ በፊት። አሁን አንድ ችሎት ብቻ ነው ያለው፡፡ በአንድ ችሎት ደግሞ ሊታይ አይችልም፡፡

ከዚያ ውጪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላይም ደግሞ 4፣ 5 ወራት ቆይቷል፡፡ የተጓደለ ፍትህ ፍትህ እንዳለማግኘት የሚቆጠር ነውና የፍትህ መዘግየት የፍትህን መጓደል የሚያሳይ ነው፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 4፣ 5 ወራት ማቆየት አልነበረበትም፡፡ በተመሳሳይ ደግሞ በተመሳሳይ ጉዳይ፣ በተመሳሳይ መዝገብ የተወሰነ ውሳኔ አለ፡፡ ያ ውሳኔ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የተወሰነው ይኼኛው ግን 4፣ 5 ወራት ነው የቆየው፡፡ አሁንም የፍትህ መዘግየት አለ።”

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

“ ማንም መልስ የሰጠን የለም። ችግሮቹም ከቀን ወደ ቀን እየተባበሱ ነው ” - የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር፣ “ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሀኪሞቻችን ተገቢውን ህክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ” ሲል ወቅሷል።

ማኀበሩ ይህን ያለው፣ ከየካቲት 14 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ስለሚያካሂደው 61ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባዔ በተመለከተ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

ጉባኤው፣ “ በኢትዮጵያ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች ደህንነት አሁናዊ ሁኔታና አማራጭ መፍትሄዎች ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለሀኪሞች ህክምና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስል፣ ለኢትዮጵያ ሀኪሞች ምን መደረግ እንዳለበት ማኀበሩን ማብራሪያ ጠይቋል።

የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት፣ በሰጡት ምላሽ “ በብዛት በኢንሹራስ ከቨር የሚደረግበት ሁኔታ አለ በጥናት የተደገፈ መረጃ ባይኖርም የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በተመለከተ ” ብለዋል።

አክለው፣ “ የኛ አገርን በተመለከተ የኢንሹራንስ ከቨርም ስለማይደረግ ጤና ባለሙያዎች እንደማናቸውም ማኀበረሰብ በትንሽ በሀገር ታክመው የማይዳኑ በጣም የተወሳሰቡ ህመሞች ሲታመሙ እናያለን ” ነው ያሉት።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የማኀበሩ የቦርድ አባል ዶ/ር በሀሩ በዛብህ ፣ “ ችግሩ የቆዬ ነው። ማንም መልስ የሰጠን የለም። ችግሮቹም ከቀን ወደ ቀን እየተባበሱ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ዶ/ር በሀሩ በዛብህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ለሀኪሞች የኢንሹራንስ ከለላ መኖር አለበት። ራሳችን ያመጣነው በሽታ እንኳ ሳይሆን ስናክም ብዙ በሽታዎችን ነው የምናገኘው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች በህክምና ሂደት ላይ ግራጁዋሊ በሚያገኙት በሽታ ሞተዋል።

ክብደት ያለውን ታካሚ እያነሳ የአካል ጉዳተኛ የሚሆንም አለ። ከተላላፊ በሽታዎች ጋር እንሰራለን። ስለዚህ ጤና ባለሙያዎች በእነዚህ በሽታዎች ይጎዳሉ።

ብዙዎች እንደዚህ አይነት ችግሮች መኖራቸውን ሲያውቁ ሙያቸውን ሁሉ የቀየሩ አሉ። ወጣቶች ትምርታቸውን አቋርጠው ወደ ሌላ ሙያ የሚሄዱበት ሁኔም አለ።

ለሀኪሞች ተላላፊ የሆነ በሽታ መከላከያ ሂደቶች የሉም። መካላከያ ኖሮም በሽታ የሚተላለፍበት ሁኔታ አለ። ግን ለማገገም የሚሰጥ ህክሞና የለም። 

አንዳንድ መከላከያዎች ውድ ናቸው። ያን ለማቅረብም የኢኮኖሚው ሁኔታ ያን ያክል አይፈቅድም”
ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ሀኪሞች ብዙ ጭናዎችን ተቋቁመው እየሰሩ የሰሩትን የዲዩቲ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ሲጠይቁ ለእስር ሲዳረጉ መስተዋሉን የገለጸው ማኀበሩ፣ በጉባዔው ወቅት ውይይት እንደሚደረግበት ጠቁሟል።

(የማኀበሩ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የአርሶአደሮችድምጽ

🔴 “ አምና 3,600 ብር ስንገዛው የነበረውን ማዳበሪያ ዘንድሮ በ8,400 ብር ለመዛት ተገደናል ” - አርሶ አደሮች

➡️ “ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል ” - የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ

የሲዳማ ክልል አርሶ አደሮች ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በቆሎ የቀረበላቸው በውድ ዋጋ በመሆኑ ለመግዛት መቸገራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ አምና የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ (ዳፕ) ዋጋ 3,600 ብር ነበር። ዘንድሮ ግን 8,400 ገብቷል። አምና 1,800 ብር የነበረው ምርጥ ዘር በቆሎ የአንድ ፕሎት ዋጋ ዘንድሮ 4,600 ብር ገብቷል። ይህ ለበቆሎ ብቻ የሚከፈል ነው።

በቆሎ ስንወስድ ለብልጽግና ቤት ግንባታ 1,500 ብር፣ ለማኀተም 1,000 ብር፣ ለግብር እስከ 3,000 ብር፣ ለብልጽግና ፓርቲ መዋጮ 300፣ ለቀይ መስቀል 200 ብር ወረዳው በግዴታ የሚያስከፍለን ወጪዎችም አሉ።

በአጠቃላይ ለአንድ ፕሎት ምርጥ ዘር በቆሎ አንድ አርሶ አደር ከ10,000 ሺሕ ብር በላይ እንዲያወጣ ተገዷል።

ስለዚህ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በተለይ በቆሎን በስፋት በማምረት የሚትታወቀው የሻመና አርሶ አደሮች ዘንድሮ በቆሎ ማምረት ይቸገራሉ"
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አርሶ አደሮች ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ እንዲድሰጥ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮን ጠይቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ምን መለሱ ?

“ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። እኛ የጨመርነው ነገር የለም የትራንስፓርት ብቻ ነው። ስለዚህ ያለ ዋጋ ነው፤ ያሳወቅነው ዋጋ።

ሌሎች ጋ አሁን ላይ ስርጭት ስላልጀመረ እንጅ ተመሳሳይ ነው። እነርሱ ቀድመው ስለሚገቡ በሚል እንጅ ፎርማሊ አሳውቀናል እኛ በደብዳቤ። አገራዊ ነው።

አምና ላይ ወደ 4,000 ገደማ ነበር። አሁን ላይ ከ7,500 - 8,000 ብር ይሄዳል እስከ ትራንስፓርት ታሳቢ ተድርጎ
ማለት ነው።

የበቆሎም አዎ በመሳሳይ ነው ይጨምራል። ፕሮዳክሽን ኮስት በየጊዜው ይጨምራል። ባለበት አይሆንም

ስለዚህ ለምሳሌ የአንድ ትራክተር ዋጋ፣ የነዳጅ ዋጋ ታሳቢ አድርጎ በየአመቱ ይጨምራል። መጨመር ያለ ነው። ከሌላ ጋ ካልሆነ በስተቀር ከኛ ጋ ኦፊሻሊ ታይቶ ዋጋ እንደ ሀገር ወጥቶለት በዚያ የምናቀርበው ስለሆነ ችግር ያለው አይደለም።

ለምሳሌ በትራክተር ለሚያርስ ነዳጅ፣ የጉልበት.. ካችአምናና አምና የነበረ ተመሳሳይ አይደለም። ያምና እና የዚህ ዓመት ተመሳሳይ አይሆንም። በዚያ ምክንያት የተወሰኑ መጨመሮች አሉ።

ማዳበሪያ ከአገር ውጪ የሚመጣ ስለሆነ እኛ መተመን አልችልም። መንግስት ሳብሲድ አድርጓል። እንደመንግስት እንዲያውም ከድጎማ በፊት 12 ሺህ ብር ነው የሚሆነው የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ። 

በድጎማው ቀንሶ ነው ወደዛም የወረደው። 4,000 ከአንድ ኩንታል ድጎማ ነው ”
ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Afar

🚨“ የሟቾች ቁጥር 8 ነው። ቁስለኞች ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - ነዋሪዎች

➡️ “ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ”ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ  ስምንት ነው" - ኤሊዳዓር ወረዳ

በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በአርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ህፃናት  ሞትና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎችና ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ በሰጡን ቃል፣“ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 በላይ ደግሞ ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል ገብተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከወደ ጅቡቲ አቅጣጫ በመጣ ድሮን ነው ” ብለዋል።

መረጃ አቀባይ ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ትላንት ሌሊት አካባቢ መጀመሪያ ሦስት ሰዎች ተገደሉ። ሦስቱንም ዱሮን ነው ያጠቃቸው። ከዚያ ዛሬ ጠዋት ሟቾቹን ሊቀብሩ የነበሩ ሰዎችን ዱሮን እንደገና መጥቶ ነው ያጠቃቸው።

መጀመሪያ ሦስት ወንዶች የሞቱ ሲሆን፣ እንደገና መጥቶ ሦስት ጊዜ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ሦስቱ ከተገደሉ በኋላ ድሮን መጥቶ ሴቶችና ህጻናትን አታክ ተደረጉ።

አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ስምንት ነው። ቁስለኞች ደግሞ ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዱብቲ ሆስፒታል ገብተው ነው የሚገኙት።

ጥቃት የተፈጸመበት አካባቢ ድንበር ነው ለጅቡቲ። ድሮኑ በየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ይታውቃል። ይታያል ማለት ነው ከጅቡቲ እንደመጣ ይታወቃል።

‘ ጅቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች አሉ ’ ብለው ነው ጥቃቱን የሚፈጽሙት። ከቁስለኞቹ ውስጥ የአስር አመት ህጻናት አሉ። ሴቶች አሉ። ዱብቲ ሆስፒታል እግሯና እጇ የተቆረጠች ልጅ አለች ”
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ “ የድሮን ጥቃት ደርሷል ” መባሉን እንዲያረጋግጡልን የጠየቃቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኤሊዳዓር ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን አካል፣ “ አዎ። ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ ስምንት ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ጥቃት የደረሰበት ሲያሩ ቀበሌ የጅቡቲ ድምበር ” መሆኑን ጠቅሰው ለተጨማሪ መረጃ በቦታው ያሉ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።

“ በዚያኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ፣ በዚህኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ ነው ” ሲሉ ጠቁመዋል።

ከሟቾች በተጨማሪ በሴቶችና ሕጻናት ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል ስለዚህስ ጉዳይ ምን ይላሉ ? ምን ያክል ሰዎች ናቸው የተጎዱት? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም የወረዳው አካል ምላሽ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም፣ “ አዎ፡፡ እኛ በቦታው ስላልቆምን የጸጥታ አካላት ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ፤ ቁስለኛው ፣ምን ያህል እንደሆነ አጣርተው እስከሚያመጡ እየተጠበቀ” ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ የክልሉ ፓሊስ አባል፣ “ ከመረጃ ውጪ ነኝ ” ሲሉ የስልክ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ኔትዎርክ የሌለበት ቦታ ነው ያለሁት። በእርግጥ መረጃ የለኝም። እያሉ ግን ሰምቻለሁ ” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

(በጉዳዩን ተጨማሪ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)

 #TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia