TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በወረዳው የሚገኙ 23 ትምህርት ቤቶች አሁንም በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ናቸው " - የኢሮብ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት

በትግራይ ፤ በምስራቃዊ ዞን የኢሮብ ወረዳ ትምህርት ፅሕፈት ቤት ከሰሞኑን ከተሰጠው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ለትግራይ ቴሌቪዥን ቃሉን ሰጥቶ ነበር።

ፅ/ ቤቱ ፤ በወረዳው በሦስት ቀበሌዎች በሚገኙ ሦስት ትምህርት ቤቶቸ 118 ተማሪዎች ብቻ ፈተናውን እንደተፈተኑ ገልጿል።

በወረዳው ከሚገኙ 47 ትምህርት ቤቶች 23 ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

22 አንደኛ ደረጃ አንድ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ናቸው።

በ23 ትምህርት ሲማሩ የነበሩት 7300 ተማሪዎች ላለፉት አራት ዓመታት በምን አይነት ሁኔታ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም።

ፅ/ቤቱ " በአንዳንድ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በኤርትራ ስርዓተ ትምህርት (curriculum ) እየተማሩ እንደሆነ መረጃው ደርሶናል " ብሏል።

" የኢሮብ ብሄረሰብ እንደ ብሄረሰብ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦቦታል ስለሆነም የክልሉ ጊዚያዊ አስተደደርና የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ሊታደጉት ይገባል " በማለት ጠንካራ ጥሪም አቅርቧል

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹" ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን አክሰስ የማድረግ ፍላጎቷን በዝርዝር ተወያይተናል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

🇫🇷" የባህር በር መኖር አስፈላጊነት ፤ ለወደፊት ያሉትን ነገሮች ማመቻቸት መቻል ትክክለኛ ጥያቄ ነው " - ፕሬዜዳንት ማክሮን

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ሄደዋል።

ትላንት አዲስ አበባ ከገቡ በኃላ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የቀይ ባህር ጉዳይ ተነስቷል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ የመሆን ፍላጎቷ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን ተከትሎ መሪዎቹ የጋራ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመው (ዶ/ር) ፤ " ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን አክሰስ የማድረግ ፍላጎቷን በዝርዝር ተወያይተናል " ብለዋል።

" ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው 130 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሀገር ፣ ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እያደገ ያለ ሀገር ፣ ተጨማሪ የባህር በር አክስሰ የሚያስፈልጋት ሀገር በዓለም ህግ በሰላማዊ መንገድ ፣ በዴፕሎማሲያዊ መንገድ እንደ ፈረንሳይ ያሉ ወዳጅ ሀገራትን ተጠቅመን የምናገኝበት (የባህር ባር አክሰስ) መንገድ ላይ የእሳቸው ጠንካራ ድጋፍ እንዳይለየን የቀረበላቸውን ጥያቄ እሳቸውም በአክብሮት ተቀብለዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ፕሬዜዳንቱ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቀበላቸው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ከፈረንሳይ እና ከፕሬዜዳንት ማክሮን የሚጨበጥ ውጤት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦

➡️ በቅርቡ ኢትዮጵያ ያካሄደችውን ኢኮኖሚክ ሪፎርም ፈረንሳይ እና ቻይና ኮቼኤር የሚያደርጉት እንደሆነ ፕሮግራሙ እንዲሳካ ማክሮን ከፍተኛ ድጋፍ ለኢትዮጵያና ለሪፎርሙ እንዳዳረጉ ፤ የፈረንሳይ መንግሥት በቀጥታ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በEU እና IMF አይተኬ ድጋፍ እንዳደረገ ገልጸዋል።

➡️ ፈረንሳይ በኢትዮጵያ አንከር ኢንቬስተር ሆና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትን በማስተባበር በወሳኝ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን አሳውቀዋል።

➡️ " ማክሮን የሚገቡትን ቃል በመፈጸም የሚታወቁ ናቸው ፤ በኢንቨስትመንት ረገድም አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።


ፕሬዜዳንት ማክሮን ምን አሉ ?

ለኢትዮጵያ የባህር በር አክሰስ መኖር ላይ የተነሳው ጥያቄ ትክክለኛ እንደሆነ ማክሮን ገልጸዋል።

" ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የገለጹት የባህር በር መኖር አስፈላጊነት ፤ ለወደፊት ያሉትን ነገሮች ማመቻቸት መቻል ትክክለኛ ጥያቄ ነው " ያሉት ማክሮን " በዚህ ላይ ፈረንሳይ ባላት አቅም ልትጫወት የምትችለውን ሚና መወጣት ትፈልጋለች። ይሄ በምን አይነት መንገድ መሆን አለበት የሚለው በንግግር፣ በውይይት፣ ዓለም አቀፍ ህጎችን ባከበረ መልኩና ጎረቤት ሀገሮችን ባከበረ መልኩ መሰራት የሚችልበትን መንገድ ለኢትዮጵያና ለቀጠናው መሳካት እንዲችል ሚናችንን እንወጣለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዜዳንት ማክሮን ፦

👉 " ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ ተነጋግረናል ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ማስፈን ይቻል ዘንድ ትልቅ እርምጃ መሆኑንና ለማሳካትም እየተሞከረ መሆኑን እንገነዘባለን ፈረንሳይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያሉ ነገሮችን ለመደገፍ ትፈልጋለች ፤ እርሻን ማበረታታ፣ የተጎዱ ሆስፒታሎችን መልሶ ማቋቋም ፤ ከሽግግር ፍትህ ጋር በተያያዘ ደግሞ የሚሰራውን ስራ የህግ የበላይነት የሚከበርበትን መንገድ ማየት እንፈልጋለን ለዚህ እናተ በምትጠይቁን መሰረት ከጎናችሁ ሆነን ሁል ጊዜ እንቀጥላለን  " ብለዋል።

👉 " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያመሰገንጉበት ጉዳይ በቱርክ ከሶማሊያው ፕሬዜዳንት ጋር የሰላም ንግግር መደረግ መቻሉን ነው ይሄ የሚደገፍ ነገር ነው። የሁሉንም ሉዓላዊነት ማክበር ጋር የሚያያዝ ነው። ከዛ በኃላ ግን ስለ ባህር በር መኖር አስፈላጊነት ጠቅላይ ሚኒስትር የገለጹ ትክክለኛ ጥያቄ ነው ፤ ፈረንሳይ ባላት አቅም ልትጫወት የምትችለውን ሚና ታመቻቻለች። በንግግር ፣ በውይይት ፣ ዓለም አቀፍ ህግ ባከበረና ጎረቤት ሀገሮች ባከበረ መልኩ " ሲሉ ገልጸዋል።

👉 " ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ተነጋግረናል። በ2019 በመጣሁበት ጊዜ ያንን ታላቅ የኢኮኖሚ ሪፎርም ከመንግሥቶት ጋር በተያያዘ 100 ሚሊዮን ዩሮ በAFD አማካኝነት እንዲሁም የተለያዩ ቴክኒካል ድጋፎችንም መጨመር ችለናል።  በአሁን ጊዜ ደግሞ ያለንን ሁሉ ነገር እንደምናደስ ለዚህም በ25 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ድጋፍ ለማድረግ ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

👉 " ከኤሌክትሪክ ኔትዎርክ ጋር በተያያዘ የፈረንሳይ ድርጅቶች መግባት የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራል በዚህ ከአውሮፓ ህብረት ፈንድ ጋር እንዲሁም አውሮፓ ካሉ ባንኮች ጋር በመሆን 80 ሚሊዮን ዩሮ ይቀርባል " ብለዋል።

👉 " ከዕዳ ጋር በተያያዘ ከG20 ጋር የሚያያዘውን ከቻይና ጋር የሚሰራ ስራ ይኖራል። ይህ ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚቀርብ ነው። ባለፈው ፓሪስ ባዘጋጀነው ዝግጅት ተጨባጭ ነገር ተገኝቷል። ይህም እርሶ እያደረጉት ባሉት የሪፎርም ስራ ሲሆን 3 ቢሊዮን ዩሮ የምናመቻች ይሆናል እናተንም በሙሉ መደገፍ እንፈልጋለን ፤ መመቻቸት ስላሉባቸው ጉዳዮች ከIMF ጋር እንነጋገራለን  " ብለዋል።

👉 " የፈረንሳይ ድርጅቶች ይበልጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ (በኢንቨስትመንት) ፍላጎት አለን " ሲሉ ገልጸዋል።

ማክሮን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ሀገራቸው ትልቁን ድጋፍ አድርጋበታለች የተባለውን የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ስራን ተመልክተዋል።

ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ስራዎችን በግንባር ቀደምትነት በፋይናንስና ቴክኒክ ረገድ እየደገፈች ሲሆን ስራው 50% መሰራት እንደተቻለ ተነገሯል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለፈረንሳይ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ትላንት እና ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።

በዚህም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ ታካሂዷል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአብላጫ ድምፅ ማሸነፉ ተነግሯል።

በምርጫው ከተሰጠ 26 ድምጽ 11 ድምፆችን አግኝቷል የተባለው ስለሺ ስህን ፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት በሚቀጥሉት 4 አመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።

የምርጫው ውጤት ምን ይመስላል ?

🇪🇹 አትሌት ስለሺ ስህን 👉 11 ድምጽ (ከኦሮሚያ ክልል)
🇪🇹 አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም 👉 9 ድምጽ (ከትግራይ ክልል)
🇪🇹 ያየህ አዲስ 👉 4 ድምጽ (ከአማራ ክልል)
🇪🇹 ሪሳል ኦፒዮ 👉 1 ድምጽ (ከጋምቤላ ክልል)
🇪🇹 ኮማንደር ግርማ ዳባ 👉 1 ድምጽ (ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል)
🇪🇹 አቶ ዱቤ ጂሎ 👉 0 ድምጽ (ከአዲስ አበባ)


Via @Tikvahethsport   
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ትላንት እና ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል። በዚህም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ ታካሂዷል። ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአብላጫ ድምፅ ማሸነፉ ተነግሯል። በምርጫው ከተሰጠ 26 ድምጽ 11 ድምፆችን አግኝቷል የተባለው ስለሺ ስህን ፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት በሚቀጥሉት 4 አመታት…
" የወከለኝ አዲስ አበባ ከተማ እንኳን እንዴት አንድ ድምፅ ይነፍገኛል ? ድምጽ ካልሰጠኝ ታዲያ ለምን ወከለኝ ? " -  አቶ ዱቤ ጁሎ

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወክለው በእጩነት የተወዳደሩት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ " ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም " አሉ።

" ' ምርጫው አልቋል አትሂድ ' ተብዬ ተነግሮኝ ነበር " ያሉት አቶ ዱቤ " በጉባኤው ያጋጠመኝም ይሄው ነው " ብለዋል።

አቶ ዱቤ " የወከለኝ አዲስ አበባ ከተማ እንኳን እንዴት አንድ ድምፅ ይነፍገኛል ? " ያሉ ሲሆን " ድምፅ ካልሰጠኝ ታዲያ ለምን ወከለኝ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" በሀገር ላይ ደባ እየተሠራ ነው ፤ ምርጫው ፍትሃዊ ነው ብዬ ለመቀበል ይቸግረኛል የቡድንተኝነት ስራ ነው የተሰራው " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

ለተመረጡት ሀላፊዎች መልካም እድል እንደሚመኙ የገለፁት አቶ ዱቤ ጁሎ እንደዚህ አይነት ነገሮች መኖራቸው ለወደፊት ለስፖርቱ " አደገኛ ነው " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወክሏቸው ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ በምርጫው ምንም ድምፅ አላገኙም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ነው።

Via @Tikvahethsport   
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

አትሌት መሠረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል ሆና ተመርጣለች።

አዳዲሶቹ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች እነማን ናቸው ?

1. አትሌት ስለሺ ስህን -ፕሬዚዳንት
2. አትሌት መሠረት ደፋር -ስራ አስፈጻሚ አባል
3. ወይዘሮ ሳራ ሐሰን- ስራ አስፈጻሚ አባል
4. ወይዘሮ አበባ የሱፍ -ስራ አስፈጻሚ አባል
5. ዶክተር ኤፍረህ መሀመድ -ስራ አስፈጻሚ አባል
6. አቶ ጌቱ ገረመው -ስራ አስፈጻሚ አባል
7. አቶ አድማሱ ሳጂ -ስራ አስፈጻሚ አባል
8. አቶ ቢኒያም ምሩጽ -ስራ አስፈጻሚ አባል እንዲሁም
9. ትዕዛዙ ሞሴ (ዶ/ር) ለመጪዎቹ 4 ዓመታት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ስራ አስፈጻሚ አባላቱ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትና አቃቤ ንዋይ ይመርጣሉ።

#AMN

@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ልዩ ቅናሽ የተደረገባቸውን ውብ እና ምቹ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን አሰናድተን ሞቅ ካለ መስተንግዶ ጋር እይጠበቅንዎ እንገኛለን! 🎁

🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Telegram👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Insagram👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 TikTok/yonatanbtfurniture

የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !

📍አድራሻችን
1.ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2.ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3.ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)

ስልክ ፦ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282
" የሂጅራ ባንክ አጠቅላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል " - የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል

ሂጅራ ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ታህሳስ 13 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል የ2023/2024 የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች ያቀረቡ ሲሆን ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 100 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ማጠናቀቁን ያበሰሩ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ334.78%  ብልጫ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ከምን ጊዜውም በላይ የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፍ ብዛቱን ወደ 100+ ከፍ ማድረጉን ገልጸው ይህም 40% እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል።

ባንኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የደንበኞች ብዛቱን በማሳደግ ከ700,000 በላይ ደንበኞችን ማፍራቱንም ገልጸዋል።

በዚሁ ረገድ ባንኩ ስኬታማ አፈፃፀም በማስመዝገብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ለባንኩ ባለአክሲዮኖች አብስረዋል።

ባንኩ ከፋይናንሺያል አፈፃፀም በተጨማሪ  የማህበረሳችንን እሴቶች ማእከል ያደረጉ ምርትና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ባንክ የመሆን ራዕዩን አጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል::

#ሂጅራባንክ
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

🚨“ የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝና፣ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈለን የዱቲ ሥራ ለማቆም ተገደናል” - የሀላለ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች

🔴 “ የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈላቸውም ” - ሆስፒታሉ

🔵 “ የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም ” - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ

በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሀላለ ሆስፒታል የሚገኙ 78 ጤና ባለሞያዎችና ሌሎች ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዝና የ3 ዓመት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው የትርፍ ሰዓቱን ሥራ ለማቆም መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ጤና ባለሞያዎቹ በሰጡን ቃል ምን አሉ?

“መንግስት ከሚመድበው በጀት ክፈሉ ብለን በደብዳቤ ብንጠይቅም ‘እንከፍላለን አሁን ግን የካሽ እጥረት አለብን’ አሉን። ከዚህ ባለፈ ማስፈራሪያ፣ እስራት፣ ድብደባ ይደርስብናል።

የመጀመሪያ የስምነት ወራት የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ተካስሰን ፍርድ ቤት እንዲከፈለን ውሳኔ ቢሰጠንም በፖለቲካ ሰዎች ጣልቃ ገብነት ውሳኔ ባለመከበሩ አልተከፈለንም።
 
ከዚያ ወዲህ የሰራነውን የ15 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያንም ቢሆን ባለመክፈላቸው፣ ለመክፈልም ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑ ከሆስፒታሉ ሠራተኞች ኃላፊ ውጪ በአጠቃላይ ተፈራሪመን የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማቆም ተገደናል።

በደላችንን፣ ድምፃችንን ለህዝብ እና ለመንግስት አሰሙልን። ጤና ሚንስቴር በህይወት ካለ መብታችንን ያስከብርልን” ሲሉ አሳስበዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የአንድ ወር ደመወዝና የ23 ወራት ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተፈጸመበት ምክንያት ምንድን ነው? ሲል ለሆስፒታሉ ጥያቄ አቅርቧል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ በረከት ሌራ ምን ምላሽ ሰጡ?

“የኛ ተቋም የሚያስተዳድረው ገንዘብ የለም ስራዎች ከተሰሩ በኋላ ለወረዳ ፋይናንስ ሪፓርት ቀርቦ ያንን መሠረት በማድረግ ነው ክፍያ የሚፈጸመው። 

የ2016 ዓ/ም የሐምሌ ደመወዝ 13% ብቻ ነው የሚቀረው 87% ተከፍሏል። የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ሰፊ ነው ችግሩ። የካሽ እጥረት በሚል ብዙ ነገር እየተባለ ነበር።

የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ፍርድ ቤት ክፍያ እንዲፈጸም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል። የወረዳው መንግስት ከክስ ሂደቱ በኋላ መክፈል ከጀመረ በኋላ ነው የቆመው።

‘በንግግር ችግሮችን እየፈታን እንመጣለን’ በሚል ቃል ከተገባልን በኋላ ነው በመካከል ክፍያው የቆመው።  የሚያዚያ ወር በከፊል መከፈል ከተጀመረ በኋላ ነው ቆመ”
ብለዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ በማታ የሚመጡ ወላድ እናቶችን ብቻቸውን እያከሙ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ባለሙያዎቹ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ቅሬታ አቅርበዋል፣ ሆስፒታሉም የ20 ወራት የዱቲ፣ የሐምሌ ደመወዝ 13 በመቶ ክፍያ አለመፈጸሙን ገልጿል፣ ይህ ለምን ሆነ? ጉዳዩን ተመልክታችሁት ነበር? ስንል ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ጥያቄ አቅርበናል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ምን አለ?

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ፣ “የ23 ወራት እንዳልተከፈለ መረጃው የለኝም። ተከፍሎ ነው እየተሰራ ያለው። ትክክል ነው ለማለት እቸገራለሁ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል።

የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ሆስፒታሉም እንዳረጋገጠ ስንገልጽላቸውም፣ “20 ወራት አይደርስም እኔ እንደማውቀው። ማጣራት ይጠይቃል” ነው ያሉት።

“የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም” ያሉት ኃላፊው፣ ጉዳዩን አጣርተው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ሆስፒታሉ ያልተከፈላችሁ የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ መሆኑን ገልጿል፣ እናንተ ደግሞ ያልተከፈላችሁ የ23 ወራት እንደሆነ ገልጻችኋል ፣ የትኛው ነው ትክክል ? ስንል የጠየቅናቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ከ23 ወራት የዱቲ የ3 ወሯን ለተወሰኑ ሰዎች ነበር የከፈሉት። በትምህርት፣ በዝውዝውር፣ ሥራ በመልቀቅ ሄዱት ሳይከፊሉ ነው ‘ከፍለናል’ የሚሉት ነገር ግን እነዚህ ባለሙያዎች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ህብረተሰቡን እንዳገለገሉ መረሳት አልነበረበትም ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM