TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ብርሃን_ባንክ
መልካም ዜና ለብርሃን ቤተሰቦች

በባንካችን ለሚከፈቱ ዕቁቦች ሁሉ የተሻለ ወለድ እና ለአባላት የሚሆኑ የብድር አማራጮችን የሚያስገኝ ብርሃን ዕቁብ ቀርቦሎታል፡፡
በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ጎራ ብለው ወይም በ8292 የደንበኞች አገልግሎት ቁጥር ደውለው ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፤
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#YeBerhanequb #digitalfinancialservice #berhanbank #bank #Stressfreebanking #bankinethiopia #finance

ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#SafaricomEthiopia

ሌላ የምስራች! 🥳 ⚡️ ፈጣኑን 4G ኔትወርካችንን ወደ ጋምቤላ ፣ መቱ እና በደሌ ይዘን ገብተናል!

በተፈጥሮአዊ መስህብ ፣ በያዮ ደን ፣ በባለ ግርማው የሶር ፉፏቴ እና በአሳ ፣ ቡና ፣ በሻይ እና በማር ምርት የሚታወቁትን እነዚህን ቦታዎች እናንተስ በምን ታስታውሷችኋላችሁ?

አሁንም ፈጣኑን ኔትወርክ ማዳረሳችንን እንቀጥላለን! 🙌🏼 አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#AddisAbaba

የስምና ንብረት ዝውውር ታገደባቸው ክ/ከተሞች የትኞቹ ናቸው ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በ6 ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል ፤ " ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራው ነው " ብሏል።

" ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ ተጀምሯል ፤ አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ተሰርቷል " ብሏል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እንደሚሰራ ፤ የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ 6 ክ/ከተሞች በቀጣይ 5 ወራት ውስጥ እንደሚከናወን
ጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞቹ ፦
- የካ፣
- ለሚ ኩራ፣
- አቃቂ ቃሊቲ፣
- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣
- ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ እንደሆኑ አሳውቋል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክፍለ ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ ድረስ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱን ገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የሹፌሮችድምጽ

" ከታህሳስ 2 እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ 6 ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል " - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር

🚨 " ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው !! "

የከባድ መኪና ሹፌሮች በሃገር አቋራጭ እና ከተማ አቋራጭ ጉዞዎቻቸው ወቅት በታጣቂዎች የሚደርስባቸው እገታ እና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ባለፉት 5 አመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገደሉ ሹፌሮች ቁጥርም 230 መሻገሩን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከታህሳስ 2 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ ስድስት ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል ብለዋል።

አራቱ ሹፌሬች የተገደሉት በመተማ ጎንደር መንገድ ጭልጋ አካባቢ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ከጎንደር ሳንጃ መንገድ ፈረስ መግሪያ አካባቢ ነው።

ፈረስ መግሪያ አካባቢ የተገደሉት ሹፌርና ረዳት ሲሆኑ ከታህሳስ 2 ጀምሮ አግተው ገንዘብ እንዲሰጣቸው ሲደራደሩ ቆይተው ታህሳስ 5/2017 ዓ/ም 120 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ገድለው እንደጧላቸው ሃላፊው አስረድተዋል።

የችግሩን ክብደት ሲያስረዱም " አንዳንድ ቦታዎች ላይ መኪና ሲበላሽ የመጀመሪያ ስራ ወርዶ ዝቅ ብሎ ማየት አልሆነም የመጀመሪያ ስራ ወርዶ መሮጥ ነው ምክንያቱም እንደቆምክ አንድ ታጣቂ መጥቶ ሊያግትህ ወይም ሊገድልህ ይችላል ምን ተበላሸ ብለህ የምታየው አንድ ሚሊሻ ይዘህ ተመልሰህ መጥተህ ነው " ብለዋክ።

ማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ከሶረቃ እስከ ሳንጃ፣ ፈረስ መግሪያ ፣ ' ኢትዮጵያ ካርታ ' የሚባለው አካባቢ ድረስ ለሹፌሮች አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ሳንጃ እና አሽሬ ባለው የመንገድ ክፍል ከህዳር 25 እስከ አሁን ድረስ 5 ሹፌሬች እንደታገቱ ተናግረዋል።

ሃላፊው ፤  " ሰው የሹፌሮችን እገታ እና ግድያ አሁን በክልሉ ከሚታየው የጸጥታ ችግር ጋር ያያይዘዋል ነገር ግን እገታ በጠቀስናቸው አካባቢዎች 7 እና 8 ዓመት አልፎታል ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው " ሲሉ አማረዋል።

" በብዛት የሹፌሮች እገታ ያለበት አካባቢ ግጭት ያለበት አካባቢ አይደለም " ያሉት አመራሩ " ታገትን ተገደልን ብለን ስንናገር : ግጭት ወዳለበት አካባቢ እያሽከረከራቹ በመሆኑ ነው ' እየተባለ ይደበሰበሳል እንባላለንም ነገር ግን ይህ ለወንበዴ ሽፋን መስጠት ነው " ብለዋል።

በመተማ እና ጎንደር መሃል ቦና ፣ መቃ እና ግንታ አካባቢ አንድ ሹፌር እስከ 40 እና 50 ሺ ብር እንዲከፍል እንደሚገደድ አንስተው በ05/04/17 ሳይከፍሉ ያለፉ ሹፌር እና ረዳት በዚሁ አካባቢ መገደላቸውን አስታውሰዋል።

ለምንድነው የምትሰበስቡት ? ስንልም " ከምናግታቹ ብለን ነው " የሚል መልስ ይሰጠናል ብለዋል።

እገታ የሚፈጸምባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ኃይል ካምፕ ያለበት ቢሆንም ለሹፌር ጥበቃ የሚያደርግ ሆነ ወንበዴዎችን የሚያጸዳ ሃይል እንደሌለ ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት በሳንጃ ሶረቃ መንገድ 2 ሺህ ብር በመክፈል በአጃቢ ሚሊሻ ለመንቀሳቀስ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአካባቢውን የጸጥታ አመራሮች ምላሽ እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ #ስናፕቻት በአልባኒያ አንድ የ14 ዓመታ ታዳጊ ልጅ ትምህርት ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ከተገደለ በኃላ የሀገሪቱ መንግሥት ቲክቶክ እና ስናፕቻትን እስከወዲያኛው ለማገድ ሊያቅድ እንደሚችል ተነገረ። ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በዋና ከተማዋ ቲራና በሚገኝ ፋንኖሊ በተባለ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በሌላ ተማሪ በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል። ተማሪዎቹ…
" ቲክቶክ የሰፈር ወሮበላ ነው " - ጠ/ሚ ኤዲ ራማ

ከሳምንታት በፊት አልባንያ ውስጥ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በስለት ተወግቶ መገደሉን ተከትሎ አልባንያ ቲክቶክን ለማገድ ልታስብ እንደምትችል መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ ሀገራቸው ለ1 ዓመት ቲክቶክን እንደምታግድ ተናግረዋል።

ባለፈው ወር የ14 ዓመቱ ታዳጊ ከተገደለ በኋላ ማኅበራዊ ሚዲያ ልጆች ላይ የሚያሳድረው ጫና ስጋት ፈጥሯል።

ይህን ተከትሎ ነው ጠቅላይ ሚኒስት ኤዲ ራማ ቲክቶክ እንደሚታገድ ያሳወቁት።

በአልባንያ መዲና ቲራና መምህራን፣ ወላጆችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ቲክቶክ የሰፈር ወሮበላ ነው " ብለዋል።

" ለአንድ ዓመት ቲክቶክ እናግዳለን። ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ዕድገት የሚከታተሉበት አሠራር እንዘረጋለን " ሲሉ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በቻይና ቲክቶክ የሚያገለግለው ለልጆች ትምህርት፣ ለተፈጥሮ ጥበቃና ባህልን ለመጠበቅ ነው። ከቻይና ውጭ ያለው ቲክቶክ ግን ርካሽና አሳሳች ነው። ይሄን ለምን እንፈልጋለን ታዲያ? " ብለዋል።

መምህራን ፣ ወላጆችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ስለማኅበራዊ ሚዲያው ውይይት እያደረጉ ናቸው።

ባለፈው በደቡባዊ ቲራና ትምህርት ቤት በተነሳ ድብድብ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ ሲገደል ሌላ ታዳጊ ደግሞ ተጎድቷል።

ይህ ፀብ የተጀመረው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነው ተብሏል።

ቲክቶክ ከአልባንያ በአፋጣኝ ማብራሪያ እፈልጋለሁ ብሏል።

ቲክቶክ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " የ14 ዓመቱን ታዳጊ የገደለው ሰውም ይሁን ታዳጊው ቲክቶክ እንዳላቸው ማረጋገጫ አላገኘሁም "  ሲል ገልጿል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
" የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል " - አታላይ አየለ (ፕ/ር)

🚨" የመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው " - አቶ አብዶ አሊ


በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

" በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛውና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል።

በአካባቢው የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው የመጣው።

ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።


በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር ፤ " ዛሬ ከሰዓት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው " ብለዋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱ እና ጭስ መታየቱም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ መፈጠሩን አብራርተዋል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

@tikvahethiopia
" ወላጆች የልጆቻችሁን ውሎና ሁኔታ እንድትከታተሉ አደራ እንላለን " - የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ

ህፃናትን የደፈረው ወንጀለኛ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። 

ወንጀለኛው የደፈራቸው ሁለት ሴት ህፃናት በማጣባቂያ ማስትሺና በጨርቅ በማፈን እንደሆነ ተሰምቷል።

ወንጀሉ መቼ እና እንዴት ተፈፀመ ? 

ወንጀሉ የተፈጸመው መጋቢት 2016 ዓ.ም ሲሆን ቦታው ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 04 ነው። 

የድርጊቱ ፈፃሚ ወንጀለኛ የ28 ዓመቱ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ሲሆን ፤ ነውረኛ ድርጊቱን የተፈፀመው  የ11 እና 12 ዕድሜ ባላቸው እንስት ህፃናት ላይ መሆኑ የጥፋተኛው የክስ የውሳኔ ማስረጃ ያስረዳል።

ወንጀለኛው እድሜያቸው ከላይ የተጠቀሰውን ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ፣ ክፉ ደጉን እንኳን የማይለዩ ሁለት ህፃናትን በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ መደለያዎች በመስጠት #እንዲቀርቡትና #እንዲለምዱት ካደረገ በኋላ ፤ ቀን መርጦ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስትሺ ተጠቅሞ ድምፅ እንዳያሰሙ በማፈን አስገድዶ የመድፈር ተግባር ፈፅሞባቸዋል።

ይህ እጅግ ለመስማት የሚቀፍ አፀያፊ ደርጊት ለወራት ሲያጣራ የቆየው የፓሊስና የፍትህ አካል በመቀበል የግራና ቀኝ ምስክሮች ያዳመጠው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ግለሰቡ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ በ16 ዓመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። 

ጉዳይ በማስመልከት ለሚድያ መገለጫ የላከው የትግራይ ፍትህ ቢሮ ፤ ወላጆች በህፃናት ላይ ይህንን መሰል አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙትን እንዲያጋልጡና የልጆቻቸው ውሎና ሁኔታ እንዲከታተሉ አደራ ብሏል።

በሀገራችን ሴቶች ላይ ለሚፈጸሙ ዘግናኝ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የሚሰጠው ፍርድ ምንም የማያስተምር ፤ ይልቅም ወንጀልን የሚያበረታታ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ ከፍተኛ ቅሬታ ነው።

በተለይ ህጻናትን የሚደፍሩ ወንጀለኞች ላይ የሚተላለፉ ፍርዶች ብዙ ጊዜ ዜጎችን የሚያስቆጡ እንደሆኑ በተደጋጋሚ የተስተዋለ ጉዳይ ነው።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል " - አታላይ አየለ (ፕ/ር) 🚨" የመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው " - አቶ አብዶ አሊ በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ…
#Earthquake

ዛሬ ምሽት 4:42 አካባቢ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደሰሙ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አብዛኞቹ መልዕክታቸውን የላኩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ካለባቸው አካባቢዎች ነው።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " አራብሳ ኮንዶሚኒየም እንደሚኖሩና ከ10 እስከ 15 ሰከንድ ያህል ንዝረቱን እንደሰተማቸው " ገልጸዋል።

ሌላው የቤተሰባችን አባል ገላን ኮንዶሚኒየም አከባቢ 10:44 ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደሰማ አመልክቷል።

በተጨማሪም አንዲት የቤተሰባችን አባል " ከሰሞኑን የዛሬው ጠንክሮ ነው የተሰማኝ ያስፈራ ነበር " ስትል ገልጻለች።

ሌሎች በክልል ከተሞች በተለይ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ስሜት እንደተሰማቸውን ተናግረዋል።

እንደአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ፣ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት መረጃ ፤ በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳ እና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ይገኛል።

ዛሬ ቀን 9 ሰዓት አካባቢ ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛው እና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል።

በተጨማሪ የፍንዳታ ድምጽ እና ጭስም ታይቶ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ ምሽት 4:42 አካባቢ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደሰሙ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። አብዛኞቹ መልዕክታቸውን የላኩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ካለባቸው አካባቢዎች ነው። አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " አራብሳ ኮንዶሚኒየም እንደሚኖሩና ከ10 እስከ 15 ሰከንድ ያህል ንዝረቱን እንደሰተማቸው " ገልጸዋል።…
#Update

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል።

መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን አመልክቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ነው የተሰማው።

@tikvahethiopia
#BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ

እነዚህን መስፈርቶች ካሟሉ ከአፖሎ እሰከ መቶ ሺህ ብር ድረስ መበደር ይችላሉ።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬ 🛑 " ከትላንትና በስቲያም ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ቆስለዋል። የአርሶ አደሩ ስጋት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው " - ኮሬ ዞን 🔵 " እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ በማጽዳት መሬቱን መውሰድ ነው የተፈለገው " - የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ጥቃት እንደቆሰሉ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።…
🔈#ኮሬ

“ ሰሞኑን በጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ንጹሐን ዜጎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - የዞኑ አካል

🔴 “ እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል ፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ ” - በሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት የዞኑ ህዝብ ተወካይ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን የንጹሐን በታጣቂዎች ግድያ ባለመቆሙ ዞኑ እና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዞኑ ተወካይና በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ዛሬም ፍትህ ጠይቀዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አንድ የዞኑ አካል፣ እሁድ ታኀሳስ 13 ቀን 2017 ዓ/ም 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኝሁ አካል በሰጡት ቃል፣ “ ምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ዞኑ ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ገብተው ባደረሱት ጥቃት ሁለት አርሶ አደሮች ተገድለዋል ” ነው ያሉት።

ታጣቂዎቹ ከፈቱት ባሉት ተኩስ ዩኑሱ ኡሱማን ኃይሌ የተባለ ወጣት ወዲያው፣ ወጣት ቡቹቴ ማስረሻ ደግሞ ወደ ኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን ከቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጡ ገልጸዋል። 

በተለይ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ነቅተው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዞኑ በአጽንኦት አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ መንግስት በዞኑ የሚፈጸመውን ጥቃት እንዲያስቆም ከዚህ ቀደም ስለቀረቡት ጥያቄ ምን አዲስ ነገር አለ ? ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ ዞን ህዝብ ተወካይ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)ን ጠይቋል።

በፓርላማ የህዝብ ተወካዩ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ በፓርላማ ባለፈው እኔ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኬዙን አንስቼ ነበር።  ሽማግሌዎችም በተደጋጋሚ እዛ ርዕሰ መስተዳድር ሄደው ነበር።

እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ። የተለዬ ምንም መፍትሄም የለም።

መንግስት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ ያ አካባቢ ይህን ያህል የሚያስቸግር አይደለም፣ ጠባብ ቦታ ነው ገላና ሸለቆና ነጭ ሳር ፓርክ የሚባለው እነዚህ ሽፍቶች የሚንቀሳቀሱበት። 

በቀላሉ ኦፕሬሽን አድርጎ ችግሩን መፍታት ይችላል በሚል በተደጋጋሚ እናቀርባለን፤ ከዛም የመንግስት ሰራዊት ይሄዳል። ትንሽ ቆይቶ በሌሎች አካባቢዎች የጸጥታው ችግር ሲብስ የሚመለስበት ሁኔታ ነው ያለው።

የተለዬ የተሰጠ ትኩረትም የለም። የተለዬ መፍትሄም የለም ”
ብለዋል።

በየጊዜው ጥቃት እንደሚፈጸም ቢገልጹም ጥቃቱ እስካሁን አለመቆሙን እየተገለጸ ነው፤ ችግሩ እንዲቆም ምን መደረግ አለበት ? እንደ ህዝብ ተወካይነትዎ ያለዎት መልዕክት ምንድን ነው? የሚል ጥያቄም አቅርበናል።

አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን መለሱ?

“ የምናስተላልፈው መልዕክት መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ነው። በተጨማሪም ህዝቡን ራሱን መጠበቅ መቻል አለበት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተቻለው ጥረት እያደረገ ነው። በዬአካባቢዎቸለ የሚነሱ ግጭቶችን ኢንፍሎንስ ያደርጋል ኃይል በመላክና ትኩረት እንሰጥ በማድረግ። 

የፓሊስ አባላት፣ ሚሊሻም በደንብ ተመልምሎ ለህዝቡ ጥበቃ እንዲያደርጉ መንግስት ከሌላው አካባቢ በተለዬ ሁኔታ ይህን ያመቻች የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር ለክልሉም፤  አሁንም ይህ ጥበቃ ቢደረግ ነው የተሻለ የሚሆነው።

በዘላቂነት ግን ከአገራዊ ሁኔታው ጋር በተያያዘ ጀነራል ኦፕሬሽን ሰርቶ ብቻ ነው ችግሩን ማቃለል የሚቻለውና ለዛ ትኩረት ይሰጥ።"


በኮሬ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ከጉጂ በሚነሱ ታጣቂዎች ዘርፈ ብዙ ጥቃት እንደሚያርሱባቸው በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጭምር መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም ጥቃቱ ባለመቆሙ የመንግስትን ትኩረት እየተማጸኑ ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ

" በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር ነው " - ኢትዮጵያ

ትላንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዶሎ በተባለ የጁባላንድ ከተማ " በፌዴራሉ የሶማሊያ ጦር ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ፤ በዚህ የሰው ሞት፣ ቁስለት ደርሷል " የሚል ክስ አሰምቷል።

ይህ መግለጫ እና በተፈጠረው ክስተት የኢትዮጵያ ኃይሎችን መክሰሱ ኢትዮጵያ አስቆጥቷል።

ክሱ ሀሰተኛ እንደሆነ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ " ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታለመ ነው " ብሏል።

" ይህ የአፍሪካ ቀንድን ሰላም ለመበጥበጥ የሚፈልጉ እና በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር ነው " ሲል ገልጿል።

" በአንካራው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ሁለቱ ሀገራት ለሰላም የሚያደርጉት ቁርጠኝነት እንዳይደናቀፍ ክፍተት መፍጠር የለባቸውም " ሲል አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚቀጥልም አሳውዋል።

ኢትዮጵያ በአንካራ ስምምነት መሰረት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Somalia #Egypt

የሶማሊያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ኤንድ ሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ ሞሐመድ ዓሊ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

አብዱላሂ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መክረዋል።

ውይይቱ የአንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ሀገራት አቻ ተቋማት የሚጠበቁ የትብብርና የአጋርነት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በውይይቱ የኢትዮጵያና ሶማሊያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት የሚፈጥሩ አካላትን ለመከላከል የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት የጋራ መግባባት እና ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፥ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ኢትዮጽያ ይገኛሉ።

በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋን ወደ ኢትዮጵያ በላከችበት በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ግብፅ ካይሮ ልካለች።

ሚኒስትሯ አሕመድ ፊቂ ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብደላቲ ጋር ከመከሩ በኃላ የጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚሁ መግለጫ ፤ የግብፁ ሚኒስትር " የቀይ ባሕርን ዳርቻ መጠቀም የሚችሉት ከባሕሩ ጋር የሚዋሰኑ አገራት ብቻ መሆን ይገባል ፤ የቀይ ባሕር ዳርቻ አዋሳኝ ላልሆኑ ሀገሮች ክፍት ሊሆን አይችልም " በማለት መናገራቸውን " ኢጂፕት ዴይሊ " ዘግቧል።

ግብፅ ይህን አስተያየት የሰጠችው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ኢትዮጵያ የባህር በርን ልታገኝ የምትችልበትን ስምምነት ፈርመው ፊርማ ሳይደርቅ ነው። በቀጣይ ወር ደግሞ ለዚሁ ጉዳይ ንግግር እንደሚጀመር ይታወቃል።

ከዚህ ባለፈ የግብፁ ሚኒስትር ፤ " የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት መላው የሀገሪቱን ግዛቶች ሙሉ እንዲቆጣጠር " በሚችልበት አግባብ ላይ መምክራቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ግብፅ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ በሚያደረገው ተልዕኮ " ወታደሮቼን አወጣላሁ " ብላለች።

የሶማሊያው ሚኒስትር በሰጡት አስተያየት " ግንኙነታቸን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ተስማምተናል " ሲሉ መናገራቸውን ኢጂይፕት ዴይሊ አስነብቧል።

#Ethiopia #Somalia #Egypt

@tikvahethiopia