TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ድሬዳዋ

" አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር። ነግሬያችኃለሁ
!! " - ኮሚሽነር ዓለሙ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዓለሙ መግራ ድሬ ውስጥ ሰዎች ቤት ሲቀይሩ " ጫኝ አውራጅ ነን እያሉ የሚከተሉ ጎረምሶች እንዳይኖሩ " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

ይህን እጅግ ጠንካራ ትዕዛዝ የሰጡት ከከተማውን የፀጥታ አመራሮች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።

በህዝብ ላይ እንግልትና ዘረፋ በሚፈፅሙ ጫኝና አውራጆች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

ኮሚሽነር ምን አሉ ?

" ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

በየቀጠናችን ያለው የጫኝ አውራጅ ስቃይ ህዝቡን ብታዩ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም።

ይሄን ያደራጀ ሰው ካለ ኃላፊነቱን አናውቀውም።

አንድም ጫኝ እና አውራጅ በየትኛውም ቀጠና የውሃ ፋብሪካ ምናም ካልሆነ በስተቀር ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

ይሄ ከተገኘ እወቁ ! አንድም ቦታ ሰውዬው ሲፈልግ ተሸክሞ ያውርድ ሲፈልግ ይስበረው።

በቀደም አንዱ መጥቶ ነገረኝ ትንሽ እቃ ነው በዳማስ ሄዶ ቀስ ቀስ እያለ አወረደ ... ከዛ ሮጠው መጡና አንኳኩ ' ክፈቱ ' አሉ ግር ብለው ገቡ ፤ እቃው ወርዷል ከዛ ' ስጡን (ብር) ' አሉ ለምን ? ' የደንቡን ' የምን ደንብ ? እኛ አውርደናል እቃችንን አላቸው ' ሊሰጠን ይገባል አታውቅም እንዴ ይሄ የሰፈሩ ደንብ ነው ' አሉ።  ሰውዬው ወደ ፖሊስ ሲደውል ከግቢ ወጥተው በር ላይ ቁጭ አሉ። ትንሽ ሲቆይ አንድም ሁለትም እየሆኑ ሄዱ።

እኚህ ወጣቶች ሌላ ቀን ወንጀል ከመስራት ወደኃላ አይሉም። ለዚህ ነው ሰግቶ የነገረኝ።

ሰው በፍርሃት ነው ያለው።

አይቻልም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል !! ነግሬያችኃለሁ።

ቤት ሲቀየር ገና ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ነው ሰው የሚደራጀው ስራ ?

አይቻልም !

ብሎኬት ማውረድ ከፈለገ ሰውየው ቤት ሲሰራ እዛው ጋር የሚሰሩትን ሰዎች ማስወረድ ይችላል ፤ ሌላ ሰው ጠርቶ ዋጋ ተደራድሮ እሱ ባለው ዋጋ ማስወረድ ይችላል አለቀ።

' እኔ ማህበር ነኝ ፤ እኔ እንደዚህ ነኝ ' ማን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ።

አንድም እንዳይኖር ይሄን ሰፈራችሁ ላይ አወያዩ ፤ ማህበረሰቡ ይሄን ይወቅ ለናተ መረጃ ይስጣችሁ። ሰፈር መድረስ ማለት ይሄ ነው።

ጫኝ እና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።

ይሄ የጫኝ እና አውራጅ ስቃይ የድሬዳዋ ብቻ አይደለም። በአዲስ አበባ በየሰፈሩና በክልል ከተሞች ተመሳሳይ ነው።

ገና ሰው እቃ ይዞ ሲመጣ " እኛ ካላወረድን ማንም ማውረድ አይችልም " በሚል አምባጓሮ የሚፈጡ አሉ።

አውርዱ ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው የሚጠሩት ብር ደግሞ አስደንጋጭ ነው።  ሰው በስንት ድካም ገንዘቡን እንደሚያገኝም አይረዱም።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ በስንት መከራና ጭቅጭቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ እቃውን ያስወርዳል። " ነገ የት እኖራለሁ " ብሎ በመፍራት።

እራሱና ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ በጋራ የገዛ እቃቸውን እንዳያወርዱ ዛቻ ሁሉ ሊፈጸምባቸው ይችላል።

ይህንን ስርዓት አልበኝነትና ድንፋታ እንዲያስቆሙ የሚጠሩ አንዳንድ የፀጥታ አባላት ነገሩን ለማስተካከል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የሚሉት ' ከነሱ ጋር ተስማሙ ' ነው።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃውን ይዞ ይገባል። በገዛ ሀገሩ በገዛ ከተማው በገዛ እቃው ተሳቆ ነው የሚኖረው። ስቃዩ ብዙ ነው !

#TikvahEthiopiaFamily

#DirePolice #ድሬ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የኮሚሽነር ትዕዛዝ ለሌሎችም ከተሞች ምሳሌ ነው ! " - ነዋሪዎች

ከጫኝ እና አውራጆች ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ለከተማው ፀጥታ አመራሮች የሰጡት ትዕዛዝ እጅግ እንዳስደሰታቸው ፤ ይህ ትልቅ ተሞክሮ በሌሎች ከተሞችም ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው እንደሆነ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የኮሚሽነሩን መረጃ ተመልክተው ቃላቸውን ከሰጡን ነዋሪዎችና የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መካከል የአዲስ አበባ፣ ሸገር ሲቲ ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ ፣ ጅማ ... የሌሎችም ይገኙበታል።

ነዋሪዎቹ " የገዛ እቃችንን ለማውጣት እና ለማስገባት የሰፈር ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ማግኘት አለብን ይህ ምን አይነት ነገር ነው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ ተሞክሮ ወደ ሌላም ቦታ መሄድ እንዳለበት ገልጸዋል።

" የገዛ እቃችንን ማስገባት እና ማስወጣት ፈተና ነው ፤ ለትንሽ እቃ እንኳን የሚጠይቁት ክፍያ ደግሞ የሚያስደነግጥ ነው ፤ አንዳንዴ እኮ ከእቃውም በላይ ይጠራሉ " ብለዋል።

" ሲፈልጉ ' ያለኛ እቃው አይገባም ' ብለው ያስፈራራሉ ሲያሻቸው ለፀብ ይጋበዛሉ ያለነሱ ሰው ያለ አይመስልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ሰው በገዛ እቃው ስንት ሰዓት ሙሉ ተከራክሮ ትንሽ ይቀነስለትና ብሩን ይሰጣል። ይህ " ክፍያ ሳይሆን ዝርፊያ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አንዳንዴ ህግ እንኳን እነሱ ላይ የሚሰራ አይመስልም እንደልባቸው ገንዘብ ይጠይቃሉ ኧረ የህግ ያለህ ብለን የሚመለከታቸውን ስንጠይቅ " ተስማሙ " ይሉናል ብለዋል።

" ሰዎች ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃ ለማስገባት ይገደዳሉ ሰዎቹ አንዳንዴ ለሊት ሁሉ ተጠራርተው ይመጣሉ ፤ አንደንዴ ደግሞ ለሊት እቃ ማስገባት አይቻልም ይባላል " ሲሉ ችግሩን አስረድተዋል።

" ዛሬ ሰዎቹን እንቢ ብንላቸው ነገር መውጫና መግቢያ ስለሚያሳጡን ትንሽ ብርም ቢሆን አስቀንሰን እቃውን እናስገባለን " ሲሉ አክለዋል።

ይህ ቀላል ነገር አይደለም ስቃዩን እና እንግልቱን ያየ ብቻ ነው የሚያውቀው ብለዋል።

" ማንኛውም ሰው የገዛ እቃውን ቢፈልግ በራሱ ሰው ካስፈለገ እና ከፈቀደ አቅሙ በሚፈቅደው ተደራድሮ በጫኝ እና አውራጅ ማስወረድ መቻል አለበት " ሲሉ አክለዋል።

" የገዛ እቃችንን ለማስገባት የሰፈር ጎረምሳ ፍቃድ አያስፍልገንም ይህንን ማስከበር ያለበት የፀጥታው አካል ነው " ብለዋል።

ድሬዳዋ ለዚህ የዜጎች የሁል ጊዜ ስቃይ እና ሮሮ የሰጠችው መፍትሄ እጅግ ትልቅ ነው ሲሉ አወድሰዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ከፀጥታ ኃይል አመራሮች ጋር በነበራቸው ምክክር ፤ ህዝቡ በጫኝ እና አውራጅ የሚያየው ስቃይ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

" ሰፈር ላይ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም ፤ ከአሁን በኃላ ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

" እኔ ማህበር ነኝ እኔ እንደዚህ ነኝ " የሚሉ ማን እንካን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ ናቸው ብለዋል።

ሰው በፍርሃት እየኖረ እንዳለ በመሆኑም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር ሰው ከፈለገ በራሱ ካልፈለገ ሰው ጠርቶ ተደራድሮ በሚችለው ማስወረድ እንደሚችል ገልጸዋል።

ገና ለገና ቤት ሲቀየር ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ሰው የሚደራጅበት ስራ ትክክል እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

ጫኝና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ እንደሆነም ተናግረዋል።


#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል። " ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር…
የምግብ ዋጋ ጣሪያ መንካት 💥

ዛሬ ላይ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቀን የምግብ ወጪ የሚመደበው ገንዘብ እንዲጨምር ተደርጓል።

ይህ የሆነው ደግሞ የምግብ ዋጋ በመጨመሩ ነው።

በፊት ለአንድ ተማሪ ይመደብ የነበረው 22 ብር  ዛሬ ላይ ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

የተቋማት የምግብ ሜኑም ተመሳሳይ እንዲሆን ተወስኗል።

በፊት በፊት ምንም እንኳን ከግቢ ግቢ ጥራቱ ቢለያይም የዩኒቨርሲቲ ካፌዎች ከዓመት ዓመት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ያለ ሰቀቀን መግበው ያስመርቁ ነበር።

የጥራቱ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ካለው የተማሪዎች ቁጥር ብዛት አንጻር ተቋማት በየዕለቱ ያለ ችግር ተማሪዎችን የተለያየ አይነት ምግብ ነበር የሚመግቡት።

ዛሬ ላይ ያለው የምግብ ዋጋ መናር ግን ፈተና ሆኗል። ለዚህም የመስላል የቀን የተማሪዎች የምግብ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የተደረገው።

ሌላው ግን በአጭር አመታት በሀገሪቱ የታየው የምግብ ዋጋ መጨመር ግርምትን የሚያጭር ፤ ልብን ቀጥ የሚያደርግ ነው።

ከዛሬ 4 እና 5 ዓመት በፊት በዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች በተለይም ደግሞ ግቢ መመገብ የማይፈልጉ ምግብ በርካሽ ዋጋ ያገኙ ነበር።

500 ብር የማትሞላውን ወርሃዊ ኮስት ተቀብለው እዛ ላይ ከቤተሰብ የሚላከውን ጨምረው ወጣ ብለው የምግብ ኮንትራት ይዘው የሚበሉ በርካቶች ነበሩ።

ከኮቪድ በፊት እጅግ ጥሩና ፅድት ብሎ የተዘጋጀ በየአይነቱ በየዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ባሉ መንደሮች በኮንትራት ከ12 ብር እስከ 17 ብር ድረስ ይገኝ ነበር።

የስጋ ነክ ምግቦችንም ከ23 ብር 35 ብር ድረስ ማግኘት ይቻል ነበር።

እንጅራው ወጡም ፍጹም ጤነኛ።

በግቢ ባሉ የተለያዩ የኢንተርፕራይዝ ካፌዎችም ምግብ በቅናሽ ማግኘት ቀላል ነበር።

ዛሬ ላይ የበፊቱ የበየአይነቱ ዋጋ ደረቅ እንጀራ ለመግዛት አይበቃም።

በበፊቱ የስጋ ነክ ምግቦች ዋጋ ዛሬ ላይ ወጥቼ ልብላ ማለት ቅንጦት ነው፤ አይታሰብም።

ይህ እንግዴ የዛሬ 4 ፣ 5 ፣ 6 ዓመት ታሪክ ነው የረጅም ጊዜ መስሎ የሚወራው።

በአጭር አመታት የታየው የምግብ ዋጋ መተኮስ የሚያስደንግጥ ነው።

ምንም እንኳን በኮስት ከተቋማት የሚገኘው ብር ትንሽ ቢሆንም እሱ ላይ የቤተሰብ ትንሽ ብር ከተጨመረበት ዘና ብሎ ያለሰቀቀን ወር ሙሉ ውጭ መመገብ ይቻል ነበር።

ዛሬ ላይ በሀገራችን ያልጨመረ ነገር ባይኖርም ለመኖር መሰረታዊ ያሆነው የምግብ ዋጋ ተተኩሶ የደረሰበት ደረጃ ብዙዎችን የሚያስጨንቅ ነው።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬም ቀጥሏል። ዛሬ ረቡዕ ከጥዋት አንስቶ እስከ ምሽት በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ከ4.5 እስከ 4.9 ድረስ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌና አካባቢው ተከስቷል። ሰሞኑን ጠንከር ያለውና ተደጋግሞም እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል። ወገኖቻችን የመሬት መንቀጥቀጡ ካየለባቸው ቦታዎች…
#Earthquake

ዛሬ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን 36 ኪ/ሜ በኩል ነው የተመዝገበው።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት አዲስ አበባ እና ቦታዎችም የተሰማ ሲሆን በተለይ በአዲስ አበባ ንዝረቱ በደንብ ይሰማ ነበር።

አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፥ " የመሬት ንዝረት እየተሰማ ነው ፤ ያለሁት ቦሌ አካባቢ መኪና ውስጥ ነው ፤ በደቂቃዎች ልዩነት ሁለቴ አጋጥሟል " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል  " መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ትንሽ ንቅንቅ ስል ተሰምቶኛል ወደ አያት አካባቢ ቆሜ ባለሁበት " ሲል ገልጿል።

ከሰሞኑን የተለያየ መጠን ያላቸው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተመዘገቡ ሲሆን የዛሬው 5.1 ከፍ ካሉት አንዱ ነው።

በሬክተር ስኬል 5.1 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥም ነበር።

አፋር ላይ በተለይ የመሬት መንቀጥቀጡ አይሎ በሚሰማባቸው ቦታዎች ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካቶችም ከቤታቸው ሸሽተው ሄደዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዱአ ያስፈልጋል !! " " አፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን ሀን ሩካ ወረዳ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ህዝቡን ከመኖሪያ ቤቱ አውጥቶ ሜዳ ላይ እያሰደረው ነው። በተለያየ ግዜ በጎርፍ አደጋ ሲጠቃ የኖረው የአፋር ህዝብ ዛሬም አላህ ይድረስለት። ሁሉም ሰው ቤት ውስጥ መተኛት አቁሞ ውጭ በረንዳ ላይ ወጥቶ እየተኛ ነው። ዱአ ያስፍልጋል !! " - መሀመድ ኢሴ @tikvahethiopia
" የአሁኑ ከእስከዛሬው ሁሉ ይለያል ፤ በጣም ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

በርካቶችን ለሊት ከእንቅልፍ የቀሰቀሰ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ተከስቷል።

ከለሊቱ 9:52 ላይ ከአቦምሳ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት በሬክተር ስኬል 5.8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰምቷል።

የቤተሰብ አባላቶቻችን ምን አሉ ?

➡️ " ሩፋኤል አካባቢ ነው ያለሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የሰማሁት ያስፈራል እስካሁን አዲስ አበባ ላይ ሲባል ነው ስስማ የነበረው። "

➡️ " በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ ከእንቅልፍ ነው የቀሰቀሰኝ። እንዲህ ከፍ ብሎ ተሰምቶኝ አያውቅም። "

➡️ " ሰሚት ነው የምኖረው ፤ እግዚኦ የአሁኑ 9:52 የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እና የቆየበት ሰከንድ ያስፈራ ነበር። "

➡️  " የአሁኑ በጣም ከበድ ያለ እና ረዘም ያለ ነው ከአያት ኮንዶሚኒየም። "

➡️ " ከአራብሳ ኮንዶሚኒየም ነበር። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በጣም ከፍ ያለ ነው። "

➡️ " ከእስካሁኑ ጠንካራውን ንዝረት ነው የሰማነው። ከቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም። እቃዎች ሲወድቁም አስተውያለሁ። "

➡️ " በከባዱ ነበር የዛሬው ደግሞ ከሌሎቹ የተለየ ነበር። "

➡️ " እኔ ባለሁበት ቀጨኔ ከወትሮው ርዝማኔው የጨመረ የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከር ያለ ንዝረት ተከስቷል። "

➡️ " ዱከም ነው ያለነው ንዝረቱም ጠንክሮ እዚህም ተሰምቷል። "

➡️ " ኧረ ያአሏህ ጎሮ ሰፈራ ላይ ነኝ ያለሁት እና የመሬቱ መንቀጥቀጥ ንዝረት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ወይስ በህልሜ ይሁን ያረቢ ብቻ ከባድ ነው በጣም ነው የሚያስጠነግጠው። "

➡️ " በከሚሴ  የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቶናል። በጣም ያስፈራ ነበር  አሏህ መጨረሻችንን ያሳምርልን ! '

➡️ " ከለሊቱ 9:53 ላይ ለ5 ሰከንድ የቆየ ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር። የካ ክፍለ ከተማ ነው። ድምጹም ከመኝተየ የቀሰቀሰኝ የቤታችን ቁም ሰጥን ሲንቀጠቀጥ ሰምቸ ነው። መሬቱም በጣም ነበር ከተኜውበት የቀሰቀሰኝ። ያስፈራ ነበር። "


በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ ዳግም በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥም ተከስቶ ነበር።

ውድ ቤተሰቦቻችን " ነገሩ ተለምዷል ፤ ምንም ሊፈጠር አይችልም " ብላችሁ እንዳትዘናጉ በድጋሚ አደራ እንላለን።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመሬት መንቀጥቀጡ እየተከሰተ ባለበት አፋር ክልል አዋሽና አካባቢው ህዝቡ ለበርካታ ሳምንታት ቀን እና ለሊት ከአሁን አሁን ምን ሊፈጠር ነው እያለ በሰቀቀን እያሳለፈ ነው የሚገኘው። ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው ሄደዋል። በርካቶች ቤት ውስጥ ማደር አቁመው ውጭ በረንዳ ላይ ለማደር ተገደዋል። ከየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በላይ ፤ የአፋር ነዋሪዎች ተደጋጋሚና ሊቆም ያልቻለው የመሬት…
🚨#ጥንቃቄ

ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ ድንገተኛ ፣ ቅፅበታዊ መቼ እንደሚፈጠር መቼስ እንደሚቆም የማይታወቅ ክስተት ነው።

መሬት መንቀጥቀጥ ክስተትን መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን ተመራማሪዎች መተንበይ አይችሉም።

ስለዚህ በየትኛውም ሰዓት፣ ጊዜ ሊከሰት ይችላል ፤ ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ የግድ ይላል።

" አሁንማ እኮ ተለመደ " ተብሎ መዘናጋት አይገባም።

" ፈጣሪ ክፉን ሁሉ ያርቅልን " እያልን መማፀኑ እንዳለ ሆኖ በዚህ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በአግባቡ ማወቅ ያስፈልጋል።

የሰሞነኛው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንዳለ ሆኖ የትላንት ለሊቱ ከፍተኛ የሆነ የማንቂያ ደውል ነው።

ብዙዎች ተኝተው ከነበሩበት ቀስቅሷል ፣ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ብለዋል፣ እቃዎች ከላይ ወደ ታች ወድቀዋል።

ሰዓቱ ለሊት የመኝታ ሰዓት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ያልሰሙት ይሆናል እንጂ ጥንካሬው ከእስከዛሬው ሁሉ የተለየ ፤ " ሰምተን እናውቅም " ያሉ ሰዎች ሁሉ የሰሙት ሆኗል።

አዲስ አበባ ብዙ ህንጻዎች ያሉባት በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።

በመሆኑም ውድ ቤተሰቦቻችን ፍጹም አትዘናጉ ! ፈጣሪያችንን ከክፉ ሁሉ ነገር እንዲጠብቀን እየተማፀንና ሳንደናገጥ ንቁ ሁነን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበር በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆን ይገባናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። " (ሉቃ. 2÷11)

መልካም የልደት በዓል !
Ayyaana Qillee Gaarii!
ርሑስ በዓል ልደት!

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል። እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል። ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ…
" የቁስ አካላቱ ሞያሌ ላይ አልወደቁም " - ነዋሪዎች

በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ  ነገር ሞያሌ ላይ አለመዉደቁን ነዋሪዎች ገለጹ።

ትላንት ምሽት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍሎች ሰማይ ላይ ከተለመዱት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለየ መልኩ በመጠን የገዘፈና በዘገምተኛ አኳሃን ሲጓዝ እንደነበር የተገለጸው ብርሃናማ የተቀጣጠሉ ቁስ አካላት " ሞያሌ አከባቢ ወድቋል " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሞያሌ ኢትዮጵያ እና ጋምቦ አካባቢዎች ባደረገው ማጣራት ብርሃናማዉ አካል በተመሳሳይ መልኩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ወደ ሶማሊያና ምስራቃዊ ኬንያ አቅጣጫ ማለፉንና በአከባቢው አለመዉደቁን ለማወቅ ችሏል።

በሞያሌ ጋምቦ የሚገኘው የመረጃ ምንጫችን ስለጉዳዩ በሰጠው ቃል " በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር አከባቢ መደጋገሙን ስንሰማ ስለነበር በዚህም ክስተት ሰዉ ሁሉ ደንግጦ ነበር፤ ነገሩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ሲያልፍ አይቻለሁ " ብሏል።

አክሎ " ሪችት ይመስላል-ሞያሌ ወደቀ የሚል ነገር ሰምቼ እስከ ማርሳቤትና ናይሮቢ ድረስ ደዋዉዬ አጣራሁ ያሉኝ ነገሩ ናይሮቢ አልደረሰም፤ ነገር ግን የማርሳቤት ሰዎች ሰማይ ላይ አይተነዉ ኡጂሩ በተባለች የኬንያ ድንበር አድርጎ ወደ ሶማሊያ መሄዱን ነግረዉኛል " ሲል ገልጿል።

አንዳንድ ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስነ ከዋክብትና ስፔስ ሳይንስ አጥኝዎች ይኸው ተቀጣጣይ ነገር " የጠፈር ፍስራሾሽ " ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

በኢትዮጵያም ይሁን በኬንያ ተቋማት በኩል ቁርጥ ያለ ነገር ባይነገርም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኩል ጉዳይን በዝርዝር ለማሳወቅና ለማብራራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ማገባደጃ በኬኒያ ሙኩኩ በተባለ ገጠራማ መንደር 500 ኪ.ግ የሚመዝን ቀለበታማ የጋለ ብረት  መውደቁ የተነገረ  ሲሆን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል ማስታወቁ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamily #Moyalle #Gambo

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የጥምቀት በዓል !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia