TIKVAH-ETHIOPIA
#ደረሰኝ 🔴 " ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " - የውይይት ተሳታፊ 🟠 " የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው) " - የውይይት ተሳታፊ 🔵 " ከቻይኖች (ከፋብሪካዎች) ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷል ፤ ግብረኃይልም ተቋቁሞ…
#ጉምሩክ
" ከስተም (ጉምሩክ) ውስጥ ተደራድሮ ገንዘብ የሚቀበል ሌባ ሰራተኛ (ሰነድ ምርመራ፣ ፍተሻ ...) እንዳለው ሁሉ ሀቀኛ ሰራተኛም አለ " - የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ
🚨" ሀቀኛ አስመጪዎች እንዳሉት ሁሉ ኔትዎርክ ፈጥረው ሃገሪቱን የሚመነትፉ አሉ ! "
👉 " በአክሰሰሩና ዋጋውን በሚተምነው እጅ ላይ ነው ያለነው ፤ እሱ ደስ ካለው ከተመቸነው ዝቅ ያደርጋል ካልተመቸነው ከፍ ያደርጋል ! " - አስመጪ
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ከአስመጪዎች እና አምራቾች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ በተሳታፊዎች በኩል ጉምሩክ ውስጥ ስላሉ ችግሮች ተነስቶ ነበር።
የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ በተገኙበት መድረክ ነው ከስተም (ጉምሩክ) ውስጥ ስላለው ችግር የተነሳው።
አንድ የመድረኩ ተሳታፊ ፤ " ከስተም ያሉ ሰዎች ለአንድ እቃ ብዙ አይነት ዋጋ ነው የሚሰጡት " ብለዋል።
" እኔ ከምን የመነጨ እንደሆነ አይገባኝም። አንዳንዴ የምትናደዱበት ሁኔታ ይፈጠራል። ምናለ ሞጆ ሄጄ ባስቀረጥኩ፣ ምናለ ቃሊቲ ባስቀረጥኩ እያላችሁ የምትናደዱበት ሁኔታ ይፈጠራል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይሄ ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ ልዩነት አለው የቀረጡ ዋጋ ፤ እኔ በቅርብ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያወጣሁት እቃ ስላለ ነው እንደዚህ ጨከን ብዬ የምናገረው " ብለዋል።
" ከቅርንጫፎች ባለፈ ደግሞ ያለው የክፍተት መጠን እንዲህ ነው ብሎ መናገር ይከብዳል ፤ 6 / 7 አይነት ዋጋ አለ በቃ በአክሰሰሩና ዋጋውን በሚተምነው እጅ ላይ ነው ያለነው ፤ እሱ ደስ ካለው ከተመቸነው ዝቅ ያደርግልናል ችግር የለውም ካልተመቸነው ከፍ ያደርግብናል " ሲሉ ያለው ችግር አስረድተዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህ ባለፈው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 10.4 ሚሊዮን ላይን አይተምን ዋጋ ፕሌት መደረጉን ጠቁመዋል።
ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ ዋጋ ይለያያል በሚለው ጉዳይ " በመሰረቱ ዋጋ በማዕከል ነው የሚደራጀው " ሲሉ መልሰዋል።
አቶ ባዘዘው ፥ " እናተ ጋር እንዳለው ሁሉ እኛም ጋር ከፍተኛ የስነምግባር ችግር አለ " ያሉ ሲሆን " ከስተምስ (ጉምሩክ) ውስጥ ሌባ አለ ተደራድሮ ገንዘብ የሚቀበል ፣ ፈታሽ ፣ ሰነድ ምርመራ አለ ስለምንጠይቃቸው፤ የምንጠይቀው አስመጪ አለ የምንጠይቀው ትራንዚተር አለ ፤ ስለ ትራንዚስተር ስላላወራችሁ ነው መሃል የሚደልል መአት አለ " ብለዋል።
በከስተም (ጉምሩክ) ውስጥ ሌባ ሰራተኞች እንዳሉ ሁሉ ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩ ሀቀኛ ሰራተኞችም አሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ሀቀኛ አስመጪዎች እንዳሉት ሁሉ ኔትዎርክ ፈጥረው ሃገሪቱን የሚመነትፉ እንዳሉ በግልጽ አሳውቀዋል።
" እዚህ ቦታ ብፃአን አይደለም ያለው ሁሉም ቦታ ያለ ችግር አለ እሱን ለማስተካከል በጋር መስራት ይጠይቃል ፤ እንዲህ አይነት ጉራማይሌዎችን እያስተካከልን እንሄዳለን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።
#TikvahEthiopiaFamily
#ጉምሩክ
@tikvahethiopia

#ብርሃን_ባንክ
#ይቀበሉ_ይመንዝሩ_ተጨማሪ_ያግኙ
ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ ከብርሃን ጋር ከሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ተጨማሪ ያገኛሉ!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#ይቀበሉ_ይመንዝሩ_ተጨማሪ_ያግኙ
ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ ከብርሃን ጋር ከሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ተጨማሪ ያገኛሉ!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Telegram
➡️ YouTube
🛑 ውድ የምናከብራችሁ የቤተሰባች አባላት በሀሰተኛ ገጾች ተታላችሁ ጊዜያችሁን እንዳታባክኑ ገንዘባችሁንም እንዳትበሉ አደራ እንላለን።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ መድረክ ስም በርካታ ሀሰተኛ ገጾች ተከፍተው በማስታወቂያ ስም ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ከዚህ ቀደም አሳውቀናል።
እኚህ አጭበርባሪዎች አሁን በዚሁ ተግባራቸው ቀጥለዋል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ስለሌላቸው ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።
ከሰዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያንቀሳቅሷቸው ገጾች እና ስልክ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል። ለሚመለከታቸው አካላትም ይድረስ !
የቲክቫህ ኢትዮጵያ መድረኮችን ሁሉ እናተው እስከ ገነባችሁት ድረስ ድምጻችሁን ማሰማት፣ ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።
ከዚህ ባለፈ ከትልልቅ ድርጅቶች በስተቀር ወጣት ስራ ፈጣሪዎች፣ ጀማሪዎች የሆናችሁ የቲክቫህ አባላት ለማስታወቂያ ምንም ክፍያ አይጠበቅባችሁም በነጻ መገልገል ትችላላችሁ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመነሻው አንስቶ በየትኛውም አካል / ድርጅት / ተቋም የማይደገፍ ፣ ድጋፍም የማይጠይቅ ፣ ጠይቆም የማያውቅ መድረክ ነው።
መድረኩ በቀናና ሚዛናዊ አመለካከት ቅድሚያ ሰውነትን ባስቀደሙ ነገሮችን በማመዛዘን የሚመለከቱ ፣ ከጥላቻ እና ጎጂ አመለካከት የነጹ ዜጎችን በማሰባሰብ እርስ በእርስ መረጃ ለመለዋወጥ ፣ ለመተጋገዝ ፣ የአባላቱን ድምጽ ለማሰማት የሚንቀሳቀስ ብቻ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ውድ ቤተሰቦቻችን በትክክለኛው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀስ ፦
❌ ምንም አይነት አክቲቭ የYoutube ገጽ የለም።
❌ ምንም አይነት የTikTok (ቲክቶክ) ገጽ የለም።
❌ ምንም አይነት የFacebook ገጽ የለም።

#Sidama
🔴 " በብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ምክንያት አባላትና አመራሮች እየታሰሩብኝ ነው " -የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ሲህአዲድ)
🔵 " በፓለቲካ አቋሙና አመለካከቱ የታሰረ የፖለቲካ ፓርቲ አባልና አመራር የለም " - የሲዳማ ክልል ፖለቲካ ፖርቲ የጋራ ምክር ቤት
🚨" የታሰርነዉ ለሁለት ፖርቲዎች መዋጮ አናዋጣም ስላልን ነው " - የሲህአዲድ አባላትና አመራሮች
የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል አቶ ሠለሞን ቡሮዳ የፓርቲያቸው አባላትና አመራሮች " ለብልፅግና ፖርቲ መዋጮ አናዋጣም " በማለታቸዉ እየታሰሩና በሐሰት እየተወነጀሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።
በክልሉ ከጥቅምት ወር መገባደጃ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች አባላትና አመራሮቻቸው ሰበብ እየተፈለገ ሲታሰሩና ሲፈቱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
አሁን ላይ ደግሞ በአባላቶቻቸው ላይ ሐሰተኛ ክስ እየተፈበረከባቸዉ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአንዳንድ ወረዳዎች ማሸማቀቅ ተበራክቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ለአብነትም ፦
- ወንሾ፣
- ጠጥቻ፣
- ጎርቼ፣
- ቦና ዙሪያ፣
- ቡርሳ፣
- ጫቤ ጋምቤልቱ፣
- ሸበዲኖ፣
- ጭሬና በንሳ ወረዳዎች አባላትና አመራሮቻቸው " የብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ለምን አታዋጡም " በሚል ለእስር ተዳርገዉ እንደነበር አንስተዋል።
አቶ ሠለሞን ፤ " አሸናፊዉ ፓርቲ ብልፅግና ነዉ፤ ሁሉም ለብልፅግና ፓርቲ የህንፃ ግንባታ መዋጮ የማዋጣት ግዴታ አለበት " የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በአንዳንድ ወረዳዎች በግልፅ እየተስተዋለ ነው ብለዋል።
" በዚህ ሁኔታ የሚደረጉ ኢ-ሕገ መንግስታዊና የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ በሚፃረርር መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የኢሶዴፖ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡባዊ ቀጠና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በለጠ ሲጄቦ አነጋግሯል።
ቅሬታ መቅረቡን አልሸሸጉም።
ቅሬታውን ተከትሎ ምክር ቤቱ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ በማድረግ ኮሚቴ ተሰይሞ የማጣራት ሥራ መስራቱን ገልጸዋል።
በዚህም የታሰሩት ግለሰቦች በደረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ አንጂ በፖለቲካ አቋማቸዉና አመለካከታቸዉ ምክንያት እንዳልሆነ መረጋገጡን አሳውቀዋል።
ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ የፓርቲው የወረዳ አባል መሆናቸውን የሚገልጹት የጠጥቻ ወረዳ ነዋሪ አቶ አስራት ወርሶ ግን " ለሁለት ፓርቲ መዋጮ አላዋጣም በማለቴ ታስሬ ነበር " ሲሉ ስለእስራቸው ምክንያት ይገልጻሉ።
ከአንድ ቀን እስር በኋላም የፓርቲው አመራሮች ባቀረቧቸዉ መረጃዎች ምክንያት ከእስር መለለቃቸዉን አስረድተዋል።
የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የሁላ ወረዳ ስራ አስፈፃሚ መ/ር ሀንሳሶ በበኩላቸው " እኔም አባላቶቻችን ለምን ታሰሩ " በሚል ልንጠይቃቸዉ በሄድንበት ከሁለት አባላት ጋር ታስረን ነበር ሲሉ " ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥተዋል።
አክለውም " ለብልፅግና ፓርቲ የሕንፃ መሰሪያ መዋጮ ካላዋጣችሁ በሚል በአባላትና አመራሮቻቸዉ ላይ በበርካታ ወረዳዎች እየደረሰ ያለዉ ጫና ስጋት ዉስጥ ከቶናል " ሲሉ ገልጸዋል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ እና የገዢዉ ብልፅግና ፓርቲ ሃሳብ ለማካተት ያደረግነዉ ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን ኃሳባቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።
#TikvahEthiopia

ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት። አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው። ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል። …
#Mekelle
በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ።
ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው።
በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ባገኘው መረጃ አዲሱ ከንቲባ ከዛሬ ጀምሮ የከንቲባ ስልጣናቸው የሚፀና ይሆናል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት ፤ " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም ፤ አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያውም መንግስት የመደበው ብቻ ነው። በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም ፤ ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል።
ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ የሾመ ሲሆን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሹመቱ ውድቅ ማድረጉ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
ከቀናት በፊት ዒግራይ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐለም አረጋዊን ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን ከንቲባ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaMekelle

#ፍሬዘርበቀለ👏
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16 ቀን 2024 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50,000 የአሜሪካ ዶላር በታማኝንት ለመንገደኛው ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
አየር መንገዱ " ባልደረባችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምገባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት አስመስክረዋል " ብሏል።
" አየር መንገዳችን ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ምንግዜም ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል " ሲል አክሏል።

#Mekelle በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ። ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም። በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው። በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ…
#Update
በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሾሙት የመቐለ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ስራቸውን በይፋ ጀመሩ።
ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ቢሮ ሲገቡ በከተማው አመራሮች ሰራተኞች አቀባበል እንደተደረገላቸው ተሰምቷል።
ከንቲባው ዛሬ ዝግ ሰብሰባ የሚያደርጉ ሲሆን አብረዋቸው ከሚሰሩ አካላት ጋር ስለ ቀጣይ እቅዳቸው ይወያያሉ።
አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ በቀጣይ ስለ እቅዶቻቸው እና ስራዎቻቸውን ለሚድያ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአቀባበሉ ስነ-ሰርዓት አዘጋጆች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።