#Oromia
🕊 " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም ! " - ነዋሪዎች
🟢 " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
⚪ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው፤... ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ ይሰጣል " - ጃል ሰኚ
⚫ " ስምምነቱን ቀድሞውኑ ከተባረሩ ግለሰቦች ጋር ነው የተፈጸመው " - ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር ለድርድር ቁጭ ብሎ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት
ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የቀድሞው የማዕከላዊ ዞን አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።
የስምምነት ሰነዱ ምን እንደያዘ ፣ ምን ምን ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሶ ስምምነት እንደተፈረመ ፣ በጃል ሰኚ ስር ምን ያህል ታጣቂ ወደ ሰላም እንደሚመለስ (በቁጥር) ፣ የነዚህ ታጣቂዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ በይፋና በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።
ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይህ የሰላም ስምምነት ለዜጎች እረፍትን የሚሰጥ ሰላም የሚያሰርጽ መሆኑን ገልጿል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " ብለዋል።
" የኦሮሞ ህዝብ በባህልና በወጉ መሰረት በሮቹን ጠምዶና ፈረሶችን ጭኖ በመውጣት ሰላም ይውረድ ባለው መሰረት ጥሪውን ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ በራሴና በክልሉ መንግስት ስም አመሠግናለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ሂደት ትልቁን ስራ ለሰራው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምስጋና አቅርበዋል።
ጃል ሰኚ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የኦሮሞ ህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" በዓለም ላይ የሰው ልጅ የፖለቲካ ልዩነት አለው ፤ እኛም ያለንን የፖለቲካ ልዩነት በጠመንጃ ከመፍታት ይልቅ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ወስነን ነው ስምምነቱን የመረጥነው " ብለዋል።
ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር ውጭ ሀገር ለሰላም ድርድር ቁጭ ብሎ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ባወጣው መግለጫ " ስምምነቱ ህዝቡን ለማምታታ የተፈጸመ ነው " ሲል ተችቷል።
ስምምነቱን ቀድሞውኑ ከተባረሩ ግለሰቦች ጋር ነው የተፈጸመው ብሏል።
ያም ሆነ ይህ ስምምነቱን ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ማዕከል እየገቡ እንደሆነ ተነግሯል።
ለመሆኑ ነዋሪዎች ምን ይላሉ ?
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች በርካታ ታጣቂዎች ወደተዘጋጀላቸው ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በርካታ የታጣቂ አባላት የሰላም መንገድ መርጠው በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እየተመለሱ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ምዕራብ ሸዋ ጮቢ፣ ኢልፈታ፣ ዳኖ እና ጅባት ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ እና ዳው በሚባሉ ወረዳዎች የቡድኑ አባላት ቅብላ እየተደተገላቸው ነው።
ጃለታ አበበ ፤ " ትላንት እና ዛሬ ብቻ 7 መኪና ነው የተሃድሶ ትምህርት ለመውሰድ ወደ ዞን ከተማ የገቡት። የሰላም ጥሪውን ከተቀበሉት ምንም የቀሩ አይመስለኝም ፤ ክላሽ መትረየስ እና ስናይፐር ይዘው ነው ያሉት " ብለዋል።
" ኢልፈታ፣ ግንደበረት ፣ ወዴሳና አምቦ አጠቃላይ ምእራብ ሸዋ ላይ ብዙ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባል የሰላም ጥሪ ተቀብሎ እየገባ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በዚህ ልክ የሰላም ጥሪ ተቀብሎ የተመለሰ የታጣቂ ቡድን አባላትን አይተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ጀልዱ ወረዳ በተመሳሳይ ቅበላ እየተደረገላቸው እንደነበር ተሰምቷል።
አቶ ግርማ ሌሎ የጀልዱ ወረዳ ኪልቤ ቀበሌ አስታዳዳሪ ፥ " በትክክልም በሁሉም አቅጣጫ እየተመለሱ ናቸው። ዛሬ እና ትላንት ጀልዱ ወረዳ ጉጁ ከተማ ሲደረሱ ሰው ሁሉ ወጥቶ ሲመለከታቸው ነበር " ብለዋል።
" መጀመሪያ ሲመጡ በየቀበሌያቸው በየቦታው ይሰበሰባሉ ከዛ ወደ መንግሥት ኃይሎች ስልክ ደውለው ነው የቅበላ ሰርዓት የሚደረገው። በጀልዱ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ነው እየተበልን ያለነው " ሲሉ አክለዋል።
ዊቱሺኩቴ፣ ኢልኬ ፣ጎሮ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የመጡባቸው እንደሆኑ ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በጃል ሰኚ የሚመሩት የሰላም አማራጭ ተከትለው እየተመለሱ ቢሆንም የሌሎች የቀሩትን እንደማያውቁ አቶ ግርማ ገልጸዋል።
" የህዝቡን ፍላጎት ተመልክተው ይመለሳሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር በኪልቤ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በመንግሥት የፀጥታ አካላት መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ የብዙ ሰው ህይወት አልፏል።
" አሁን ሰላም መውረዱ መሰል የሰው ህይወት ቀጥፈትን ይታደጋል " ሲሉ አቶ ግርማ ተናግረዋል።
እርስ በእርስ መተኳኮሱ ከቆመ በአካባቢው የተደናቀፈው ልማት ይቀጥላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ፤ የህዝቡ ፍላጎትን ስለሚያስጠብቅ ሰላም መውረዱ አስደሳች እንደሚሆን አክለዋል።
የጮቢ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ጃለታ በቀለ ፤ " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም። አሁን ህዝቡ ለ5 ዓመታት በቀጠለው ጦርነት ተጎድቷል መንግሥት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች የህዝቡ ህይወት የሚንሰራራበትን መላ ይዘው ቢመጡ መልካም ነው " ብለዋል።
[ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎች ቃል ምንጭ ቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ሬድዮ እንደሆነ ይገልጻል ]
ኦሮሚያ ባለፉት አመታት ?
ከ6 ዓመታት በፊት " ለውጥ መጥቷል " ከተባለና መንግሥት ኤርትራ አስመራ ላይ ከኦነግ ጋር ስምምነት ደርሷል ከተባለ በኃላ (ምንም እንኳን የስምምነት ሰነዱ ለህዝብ ይፋ ባይደረግም) ወደ ክልሉ በርካታ ታጣቂዎች ገብተዋል።
ከነዚህም ውስጥ ትጥቅ ሳይፈቱ የገቡ በርካቶች ነበሩ።
ወደ ሃገር ከገቡት ውስጥ " ከኦነግ ፓርቲ ጋር ተለያይተናል " ያሉ አባላት " መንግሥትን በትጥቅ ነው የምንታገለው " ብለው ወደ ጫካ ገብተዋል።
ይህን ተከትሎ በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ በርካቶች አልቀዋል።
እገታ፣ ዘረፋ ተስፋፍቷል።
ተማሪዎች ትምህርት መማር አልቻሉም ፡ ገበሬዎች ማረስ አልቻሉም። ንፁሃን ዛሬም ድረስ ፍዳቸውን እያዩ ነው።
ሰላም ወጥቶ መግባትም የማይታሰብ የሆነባቸው በርካታ ቦታዎች ተፈጥረዋል።
በተለያዩ ቦታዎች ትጥቅ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ትንንሽ ቡድኖችንም እንዲበዙ ሆኗል።
በክልሉ ያለውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ሆነ ሰላም የራቃቸውን ቦታዎች ወደ ሰላም ለመመለስ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና መንግሥት መካከል የጠረጴዛ ድርድር ሁለት ጊዜ ከሀገር ውጭ ቢደረግም ጠብ ያለ ተስፋ ያለው ውጤት ሳይመጣ ቀርቶ የትጥቅ እንቅስቃሴ በክልሉ ቀጥሏል።
አሁን ተደርጓል የተባለው የሰላም ስምምነት በጃል ሰኚ ከሚመራው ቡድን ጋር ቢሆንም ሌሎችም የሚመሯቸው ታጣቂዎች በክልሉ ይንቀሳቀሳሉ።
#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ኦሮሚያ
@tikvahethiopia