TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ " ዜጎች በሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ወደ ማይናማር እና ታይላንድ ከመጓዝ ሊታቀቡ ይገባል " ሲል አሳስቧል።

ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በይነ መረብን በመጠቀም በርካታ ዜጎች ችግር ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል።

" ዜጎች ባልተረጋገጡ አማላይ ማስታወቂያዎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው " ብለዋል።

" በጃፓን የሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮን የዜጎችን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደርገ ነው " ብለው ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ተናግረዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት የጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት ኖቫርቲስ ፋርማ ሽዌይዝ AG/ Novartis Pharma Schweiz AG በተባለ የገበያ ፍቃድ ባለው የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ የሚመረት ነው።

ቴግሬቶል (ካርባማዜፔይን) 100 mg/5ml Oral Suspension (OS) የተሰኘው መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ አጠቃላይ ለሚጥልና ከፊል መንቀጥቀጥ/ management of generalized tonic clonic and partial seizures ለማከም የሚያገለግል ነው።

ይሁን እንጂ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ፕሮፓይሊን ግላይኮል (propylene glycol) የሚባል ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት ወይም በሶስት ወራት የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት ሊወስዱት እንደማይመከር ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ተቋሙ ፥ በዚህ ምርት ውስጥ ከሚገኙት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ፕሮፓይሊን ግላይኮል ለምግብ እና ትንባሆ ምርቶች እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል እና መዋቢያዎች በአጠቃላይ በአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ይታወቃል ብሏል።

ይሁንና በዚህ ምርት ውስጥ ያለው መጠን በዚህ የማሳወቂያ መልዕከት ላይ ከተጠቀሱት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነው ያለው።

ስለሆነም ይህንን መድኃኒት በጨቅላ ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም መድኃኒቱን እንዳይጠቀም መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" ተግባራችሁ በህግ የሚያስጠይቅ ነው። ይህን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ተግባራችሁ ታቀቡ " - ጤና ሚኒስቴር

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የስኳር ህመምን ጨምሮ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ሃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተለቀቁ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

" ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል " በሚል ሰሞኑን እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

አሁን አሁን የህክምና ሞያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎትም ህጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በየማህበራዊ ሚዲያው ላይ እየወጡ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ተበራክተዋል ብሏል።

ይህ ተግባር ደግሞ ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ ፈውስ ፈላጊ ዜጎችን ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ አስገብዟል።

በዚህ መሰል ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላት ይህ ተግባር በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝበው ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ማህበረሰቡ ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልእክቶችን እንዲመረምር ፤ አገልግሎቶችንም ከመጠቀሙ በፊት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተብሏል።

አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ "[email protected]" ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

ሀሰተኛ የጤና መረጃ ከፍተኛ ቀውስ የሚፈጥር በመሆኑ ዜጎች ሀሰተኛ የጤና መረጃ የሚያሰራጩትን በመጠቆም ስለ ጤናው የጤና ባለሙያን ብቻ በማማከር ጤንነቱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።

#Ethiopia #MinistryofHealth

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በተለይም ኮድ 3 እና ኮድ 2 መኪና ይዘው እየተነቀሳቀሱ ሰዎችን የሚዘርፉ የዘነጡ ሌባዎች በከተማይቱ እንዳሉ በተለያዩ ቦታዎችም ዜጎች እየተዘረፉ መሆኑን ጥቆማ ሰጥተናችሁ ነበር።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድ መረጃ አጋርቷል።

መረጃው ምን ይላል ?

በተሽከርካሪዎች ላይ ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር በመለጠፍ ቅሚያ ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ይገልጻል።

ተጠርጣሪዎቹ ተሽከርካሪ
#በመከራየት በቂርቆስ፣ በቦሌ እና በጉለሌ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ  ሞባይል ስልክ  እየቀሙ እንደሚሰወሩ ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል፡፡

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው በተለምዶ " ወሎ ሰፈር " እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ተጠርጣሪዎቹ በኮድ 2 A-28629 አአ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3 B-35824 አአ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር ለጥፈው ግምቱ 12 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ ሳምሰግ ሞባይል ቀምተው ይሰወራሉ።

ወንጀሉን በፈፀሙ በአንድ ሰዓት ልዩነት  በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ጉለሌ ሸገር አካባቢ  ከአንድ ግለሰብ ላይ 8 ሺህ ብር የሚገመት ቴክኖ ሞባይል ይቀማሉ፡፡

የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመያዝ በክትትል ላይ እያለ ወንጀሉን በፈጸሙበት እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።

በተመሳሳይ  ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በኮድ 2C -28629 አዲስ አበባ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3A-21634 አዲስ አበባ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር  በመለጠፍ  በተመሳሳይ የቅሚያ ወንጀል ለመፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 " ሸዋ ዳቦ " አካባቢ ተይዘዋል።

በተሽከርካሪ ውስጥ ከተለያዩ ግለሰቦች የተቀሙ ሶስት ሞባይሎች የተገኙ ሲሆን ከሶስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ሲሆን ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በቀን ገቢ ተሽከርካሪዎችን በመከራየት እና ሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር አዘጋጅተው በመለጠፍ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ  ወንጀል ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል።

የሞባይል ቅሚያ የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ንብረታቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ተሽከርካሪን ማከራየት የሚቻለው የህግ አግባብን ተከትሎ መሆን ስላለበት መኪና የሚያከራዩ ባለንብረቶች ተገቢውን
ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገበ ፖሊስ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት እንዳይፈፀም ተገቢውን
ጥንቃቄ ከማድረግ ባሻገር አጠራጣሪ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ቁጥር ካጋጠመው ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

መኪኖቻችሁን ለማን እንደምታከራዩ ለማንስ እንደምታውሱ እወቁ ፤ ተጠንቀቁ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመሬት መንቀጥቀጡ እየተከሰተ ባለበት አፋር ክልል አዋሽና አካባቢው ህዝቡ ለበርካታ ሳምንታት ቀን እና ለሊት ከአሁን አሁን ምን ሊፈጠር ነው እያለ በሰቀቀን እያሳለፈ ነው የሚገኘው። ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው ሄደዋል። በርካቶች ቤት ውስጥ ማደር አቁመው ውጭ በረንዳ ላይ ለማደር ተገደዋል። ከየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በላይ ፤ የአፋር ነዋሪዎች ተደጋጋሚና ሊቆም ያልቻለው የመሬት…
🚨#ጥንቃቄ

ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ ድንገተኛ ፣ ቅፅበታዊ መቼ እንደሚፈጠር መቼስ እንደሚቆም የማይታወቅ ክስተት ነው።

መሬት መንቀጥቀጥ ክስተትን መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን ተመራማሪዎች መተንበይ አይችሉም።

ስለዚህ በየትኛውም ሰዓት፣ ጊዜ ሊከሰት ይችላል ፤ ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ የግድ ይላል።

" አሁንማ እኮ ተለመደ " ተብሎ መዘናጋት አይገባም።

" ፈጣሪ ክፉን ሁሉ ያርቅልን " እያልን መማፀኑ እንዳለ ሆኖ በዚህ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በአግባቡ ማወቅ ያስፈልጋል።

የሰሞነኛው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንዳለ ሆኖ የትላንት ለሊቱ ከፍተኛ የሆነ የማንቂያ ደውል ነው።

ብዙዎች ተኝተው ከነበሩበት ቀስቅሷል ፣ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ብለዋል፣ እቃዎች ከላይ ወደ ታች ወድቀዋል።

ሰዓቱ ለሊት የመኝታ ሰዓት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ያልሰሙት ይሆናል እንጂ ጥንካሬው ከእስከዛሬው ሁሉ የተለየ ፤ " ሰምተን እናውቅም " ያሉ ሰዎች ሁሉ የሰሙት ሆኗል።

አዲስ አበባ ብዙ ህንጻዎች ያሉባት በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።

በመሆኑም ውድ ቤተሰቦቻችን ፍጹም አትዘናጉ ! ፈጣሪያችንን ከክፉ ሁሉ ነገር እንዲጠብቀን እየተማፀንና ሳንደናገጥ ንቁ ሁነን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበር በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆን ይገባናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia