TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.4K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በቤት እቃዎቻችን ላይ ከ10 እስከ 25% ቅናሽ ማድረጋችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው! 🌼🌼 ይምጡ እና ይጎብኙን በዕቃዎቻችን ጥራትና ጥንካሬ ይደመማሉ!

የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር!

አድራሻችን፦
1.ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251995272727
2.ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251957868686
3.ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251993828282

👉 Telegram
👉 Facebook
👉 Instagram
👉 TikTok

#yonatanbtfurniture #furniture #modernfurniture #sofa #diningtable
6 ቀን ብቻ ቀረ!!!!

ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች ለሁላችንም በታላቅ ቅናሽ ከዲኤስቲቪ !

ዛሬውኑ የዲኤስቲቪ ዲኮደርዎን ከ800 ብር ቅናሽ ጋር በመግዛት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ ላሊጋ ፣ ሴሪ አን ጨምሮ የሚወዱትን ክለብ በሚመርጡት ፓኬጅ ላይ እንደየምርጫዎ በዲኤስቲቪ ይዝናኑ!

ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች፣ ሁሉንም የቡድን ወኔ፣ ሁሉንም ትንታኔዎች ... ሁሉም በዲኤስቲቪ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#Telegram

የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቨል ዱሮቭ ፈረንሳይ ውስጥ ታሰረ።

በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ የዱሮቭን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ነው።

ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች የተቃውሞ ሰልፍ እየጠሩ ናቸው።


የቴሌግራም መተግበሪያ መስራቹና ዋና ስራ አስኪያጁ ፓቨል ዱሮቭ ትላንት ቅዳሜ ምሽት ፈረንሳይ ፣ በፈረንሳይ ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቡርጌት ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ዱሮቭ በግል ጄቱ ተሳፍሮ ሊጓዝ ሲል ነው የታሰረው።

ለእረፍት ካቀናበት አዘርባጃን ተነስቶ በፈረንሳይ አድርጎ ሊጓዝ በኤርፖርቱ ባረፈበት ወቅት ነው መያዙ የታወቀው።

በፈረንሳይ የመጀመሪያ ደረጃ የፖሊስ ምርመራ አካል በሆነ የእስር ማዘዣ እንደተያዘም ነው የተነገረው።

ምርመራው ያተኮረው በቴሌግራም ሞደሬት / ቁጥጥር የማድረግ ክፍተት ላይ ነው። የፈረንሳይ ፖሊስ " ቴሌግራም የወንጀል ድርጊቶች፣ የአደገኛ እፅ ዝውውር፣ ሽብር፣ መኒ ላውንደሪንግ፣ ማጭበርበር ያለገደብ የሚተለለፉበት ሆኗል " በሚል ምርመራ ያደርጋል ነው የተባለው።

ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሏል።

ቴሌግራም በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። የፈረንሳይ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፖሊስም በጉዳዩ ላይ ምንም አላሉም።

የሩስያ ምክትል የዱማ አፈ-ጉባዔ ቭላዲላቭ ዳቫንኮቭ ዱሮቭ እንዲፈታ የሚጠይቅ መልዕክት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ፅፈዋል።

እስራቱ በፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያለውና የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለማግኘት መሳሪያ ሊሆን ይችላል ነው ያሉት።

በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ ነው።

ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች ተቃውሞ እየጠሩ ናቸው።

በርካቶች ቴሌግራም ላይ ያነጣጠረው የሃሳብ ነጻነትን መንፈግ ነው ብለዋል።

ቴሌግራም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠቃሚዎች እጅ በጣም መጨመራቸው ይታወቃል።

በተለይ በሩስያ፣ ዩክሬን አካባቢ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በመላው ዓለም ተጠቃሚዎቹ 1 ቢሊዮን ደርሰዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት ዋነኛ ተመራጭ የመልዕክት ማስተላለፊያ መድረክ ሆኗል።

ዱሮቭ የሩስያ-ፈረንሳይ ዜግነት አለው።

#TF1TV #BFM

@tikvahethiopia
#GRED🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 3ኛው እና 4ኛውን ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሳውቀዋል።

" ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል " ብለው " የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠር፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ፣ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል " ነው ያሉት።

" ይህ የተመዘነና የተመጣጠነ የውሃ ልቀት ግብርናን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን፣ በቀጠናው ያለ የሀብት አጠቃቀም ምጣኔን ለማጎልበት በእጅጉ ይጠቅማል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ። ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ…
#TPLF #Tigray

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ።

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ መሾማቸው ዘግበናል።

ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።

ትግራይ ካሉዋት ሰባት የዞን አስተዳደሮች በአሁኑ ጊዜ ስድስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ የመቐለ ከተማ ብቻ በቅርቡ  በተካሄደ ጉባኤ  የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይመራል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Telegram የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቨል ዱሮቭ ፈረንሳይ ውስጥ ታሰረ። በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ የዱሮቭን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ነው። ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል። ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች የተቃውሞ ሰልፍ እየጠሩ ናቸው። የቴሌግራም መተግበሪያ መስራቹና ዋና ስራ አስኪያጁ ፓቨል ዱሮቭ ትላንት ቅዳሜ ምሽት ፈረንሳይ ፣ በፈረንሳይ ከፓሪስ ወጣ ብሎ…
" እንዲለቀቅ ይጠይቃሉ ወይስ ምላሳቸውን ውጠው ጸጥ ይላሉ ? " - ዛራኮቫ

የምዕራባውያኑ ለሰብዓዊነትና ነጻነት ቆመናል የሚሉ ድርጅቶች የቴሌግራም መስራች ፓቨል ዱሮቭ እንዲለቀቅ ይጠይቃሉ ?

የዱሮቭን ፈረንሳይ ውስጥ መታሰረን በመለተከተ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች " ምላሳቸውን ውጠው ዝም ይላሉ ? ወይስ እንዲፈታ ይጠይቃሉ ? " ብለዋል።

እ.ኤ.አ. በ2018 ፦
- ሂዩማን ራይትስ ዎች ፣
- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፣
- ፍሪደም ሃውስ ፣
- ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች እና ሌሎችን ጨምሮ 26 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቡድን የሩስያ ፍርድ ቤት ቴሌግራምን ለማገድ የሰጠውን ውሳኔ አውግዘው ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።

ዲፕሎማቷ ፤ " አሁን ፓሪስ ደውለው የዱሮቭን መፈታት የሚጠይቁ ይመስላችኋል ? ወይስ ምላሳቸውን ውጠው ዝም ይላሉ ? " ሲሉ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ፅፈዋል።

ዛራኮቫ ፤ በ2018 ቴሌግራም ላይ የሕግ አውጭ ቅሬታዎች ነበሩ፣ ይህም በብዙ የኢንክሪፕሽን ሥርዓቱ ቴክኒካል መለኪያዎች ምክንያት ነው ሲሉ አስታውሰው ፤ ዱሮቭ ግን ነፃ ሆኖ መቆየቱን መተግበሪያውን ማሳገዱን ገልጸዋል።

የዱሮቭ በተያዘበት ቅፅበት በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ ጉዳዩን መከታተል እንደጀመረ ጠቁመዋል።

" የእኛን ዲፕሎማቶች ስለ ስራቸው ማስታወስ አያስፈልግም " ሲሉም ዛካሮቫ አክለዋል።

ቴሌግራም ሩስያ እንዲሁም በዩክሬን አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለስልጣናትም ተመራጭ መልዕክት መለዋወጫ አድርገውታል።

ዱሮቭ የሩስያ እና የፈረንሳይ ዜግነት አለው።

@tikvahethiopia
" የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀምሪያለሁ " - ፌዴራል ፖሊስ

ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቐለ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፦
👉 ዮሀንስ ዳንኤል
👉 አማኑኤል መውጫ
👉 ናትናኤል ወንድወሰን
👉 ኤልያስ ድሪባ
👉 ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ " እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል " ብሏል።

" የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው " የገለጸው።

የምርመራ መዝገቡ ፥ " በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ብለዋል " ሲል ገልጿል።

" ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ነው " ብሏል

" እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎች በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ " ሲል ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀምሪያለሁ " - ፌዴራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቐለ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ፦ 👉 ዮሀንስ ዳንኤል 👉 አማኑኤል መውጫ 👉 ናትናኤል ወንድወሰን 👉 ኤልያስ ድሪባ 👉 ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።…
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል በማለት በቁጥጥር ስር አውሎ የሽብር ወንጀል ምርመራ የከፈተባቸውን 6 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ማንነት የሚያሳይ ፎቶ ይፋ አድርጓል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው በሀገራችን ካለው የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት " ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ አውሮፕላን መብረር አይችልም " ያሉ የበረራ ባለሙያዎችን በማስገደድ በረራውን ለማስቀጠል በፈጠሩት አምባጓሮ እና ግርግር ወንጀል ተጠርጥረው ነው ሲል አስረድቷል።

ነገ ፍርድ ቤት አቀርባቸዋለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia