TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ🚨

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳውቋል።

በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል #ጥንቃቄ እንዲደረግ ተብሏል።

የማዕከሉ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሀ/ማርያም ለሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ " በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተሰራው ትንበያ እንደሚያሳየው በቀጣይ 10 ቀን ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል የሚል ነው " ብለዋል።

" በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚጠበቁት በሰሜኑ ላይ #ከድሬዳዋ ጀምሮ #በጭናቅሰን እስከ #ጅግጅጋ ድረስ ነው " ብለዋል።

" በብዛት በኦሮሚያ ሃይላንድ በቀርሳ ፣ በቁልቢ ከፍታ ቦታዎች ላይ ከሚዘንበው ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይ #ድሬዳዋ ላይ ብዙ ዝናብ ከተማው ላይ ሳይዘንብ ጎርፍ የመምጣት እድል አለው። በተመሳሳይ #ጅግጅጋ ላይ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል " ሲሉ ገልጻዋል።

ዋቢ ሸበሌ፣ ከኢሚ፣ ጎዴ፣ ቀላፎ፣ ሙስታይል ወደታች ያለው አካባቢ ጎርፍ ሊመጣ የሚችልበት እድል ስላለ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#MesiratEthiopia

📢 በሐዋሳ እና በድሬዳዋ ለምትገኙ ወጣቶች በሙሉ!

የመስራት የወጣቶች መማክርት ቡድን (M-YAG) አባል በመሆን ለለውጥ ድምጽ ሁኑ !

M-YAG ከቡድን በላይ ነው፤ በመስራት ፕሮግራም ውስጥ የወጣቶችን ድምጽ ለማሰማት የተዘጋጀ እንቅስቃሴ ነው።
ከ 15 እስከ 35 እድሜ የሆኑ ለመምራት፣ ለማነሳሳት እና በማህበረሰቦቻቸው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማሳደር ዝግጁ የሆኑ ወጣቶችን እየፈለግን ነው። በM-YAG በኩል በዋጋ ሊተመን የማይችል የግል እና ሙያዊ ክህሎቶችን ታገኛላችሁ፣ ጠንካራ አመራር ላይ ቁርጠኛ የሆነ ቡድን አካል ትሆናላችሁ።

ተጽዕኖ ለማሳደር ዝግጁ ከሆናችሁ እዚህ ተመዝገቡ፥ https://forms.gle/pd3JLtHM1u1fDD4D6

#MYAG #መስራት #Hawassa #ሐዋሳ #DireDawa #ድሬዳዋ
#ድሬዳዋ

በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ የመተማ መስመር በመዘጋቱ፣ በድሬዳዋ በኩል የሚደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ።

ይህንን የገለጸው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው።

ቢሮው ፤ " የመተማ መስመር በመዘጋቱ ድሬዳዋ እንደ መተላለፊያነት ስለምታገለግል ከፍተኛ የዜጎች ፍልሰት በከተማዋ ታይቷል " ብሏል።

ከተማዋ በምሥራቅ አቅጣጫ ድንበር መተላለፊያ በመሆኗ ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚሻገሩ ሰዎች ፍልሰታቸው እየጨመረ መሆኑን ገልጿል።

ፍልሰተኞቹ ድንበር ለመሻገርም ሆነ በአጋጣሚ ያሰቡት ሳይሳካላቸው ሲቀር ተመልሰው ድሬዳዋ ውስጥ የሚቀሩ መኖራቸው ተመላክቷል።

በፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በበኩሉ ፥ ከተማዋ የመተላለፊያ በር በመሆኗ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ይፈልሳሉ ብሏል።

በቀን ከ80 አስከ 100 ያህል ከ14 እስከ 35 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ ለመውጣት ጥረት እንደሚያደርጉ ጠቁሟል።

የሰላም ዕጦት

ሥራ አጥነት

በደላሎች መታለል ለዚህ ገፊ ምክንያት መሆናቸውንም ጽ/ቤቱ ጠቁሟል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በድሬዳዋ በኩል የሚደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው፣ አዘዋዋሪዎች በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በሌሎች ማኅበራዊ የትስስር ገጾች ማስታወቂያዎች ነው ተብሏል።

ችግሩን ለመፍታት ዘመኑን የሚመስሉ የወንጀል ምርመራ ሒደቶችን በመከተል በፍርድ ቤት ከማስረጃ ምዘና በተያያዘ ችግሮች እንዳይፈጠሩ፣ የወንጀል አፈጻጸም ዘዴ ግምት ውስጥ ያስገቡ የሕግ ማሻሻዎች ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የተቋማት ግንባታን በሚገባ ማጠናከርና ያላቸውን ግንኙነት ማሻሻል ይገባል ያለው ጽ/ቤቱ ወንጀሉ በአንድ ቦታ ብቻ የሚያበቃ ባለመሆኑ በክልሎች፣ በወረዳዎችና በቀበሌዎች የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሊተባበሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ አዘዋዋሪዎች የሰውነት ክፍሎቻቸውን እያወጡ መሸጥና ሌሎችም ወንጀሎችን ስለሚፈጽሙባቸው ለመከላከል፣ የአገሮች ቅንጅት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑም ተጠቁሟል።

ዜጎች ከሚነሱባቸው አካባቢዎች ያሉ የሕግ አካላት እስከ መዳረሻ አገሮች ድረስ ከፀጥታ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሠራሮችን ማሻሻልና ማዘመን ይገባል ተብሏል።

ድንበር ላይ የተያዙ ዜጎች ወደ መጡበት ለመመለስ የትራንስፖርትና የጊዜያዊ ማቆያ ችግሮች አሉ የተባለ ሲሆን ካለው ብዛት አኳያ ግን በቂ አለመሆኑን ተገልጿል።

በተለይ የባህር ላይ ወጀብ በማይኖርበት ወቅት ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚጨምር ተመላክቷል።

ከድሬዳዋ ጂቡቲ ርቀቱ 300 ኪሎ ሜትር በመሆኑ ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ድሬዳዋ አመቺ ከተማ በመሆኗ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ከተማዋ እንደሚፈልሱ ተነግሯል።

መረጃው ከሪፖርተር ጋዜጣ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

" አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር። ነግሬያችኃለሁ
!! " - ኮሚሽነር ዓለሙ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዓለሙ መግራ ድሬ ውስጥ ሰዎች ቤት ሲቀይሩ " ጫኝ አውራጅ ነን እያሉ የሚከተሉ ጎረምሶች እንዳይኖሩ " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

ይህን እጅግ ጠንካራ ትዕዛዝ የሰጡት ከከተማውን የፀጥታ አመራሮች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።

በህዝብ ላይ እንግልትና ዘረፋ በሚፈፅሙ ጫኝና አውራጆች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

ኮሚሽነር ምን አሉ ?

" ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

በየቀጠናችን ያለው የጫኝ አውራጅ ስቃይ ህዝቡን ብታዩ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም።

ይሄን ያደራጀ ሰው ካለ ኃላፊነቱን አናውቀውም።

አንድም ጫኝ እና አውራጅ በየትኛውም ቀጠና የውሃ ፋብሪካ ምናም ካልሆነ በስተቀር ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

ይሄ ከተገኘ እወቁ ! አንድም ቦታ ሰውዬው ሲፈልግ ተሸክሞ ያውርድ ሲፈልግ ይስበረው።

በቀደም አንዱ መጥቶ ነገረኝ ትንሽ እቃ ነው በዳማስ ሄዶ ቀስ ቀስ እያለ አወረደ ... ከዛ ሮጠው መጡና አንኳኩ ' ክፈቱ ' አሉ ግር ብለው ገቡ ፤ እቃው ወርዷል ከዛ ' ስጡን (ብር) ' አሉ ለምን ? ' የደንቡን ' የምን ደንብ ? እኛ አውርደናል እቃችንን አላቸው ' ሊሰጠን ይገባል አታውቅም እንዴ ይሄ የሰፈሩ ደንብ ነው ' አሉ።  ሰውዬው ወደ ፖሊስ ሲደውል ከግቢ ወጥተው በር ላይ ቁጭ አሉ። ትንሽ ሲቆይ አንድም ሁለትም እየሆኑ ሄዱ።

እኚህ ወጣቶች ሌላ ቀን ወንጀል ከመስራት ወደኃላ አይሉም። ለዚህ ነው ሰግቶ የነገረኝ።

ሰው በፍርሃት ነው ያለው።

አይቻልም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል !! ነግሬያችኃለሁ።

ቤት ሲቀየር ገና ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ነው ሰው የሚደራጀው ስራ ?

አይቻልም !

ብሎኬት ማውረድ ከፈለገ ሰውየው ቤት ሲሰራ እዛው ጋር የሚሰሩትን ሰዎች ማስወረድ ይችላል ፤ ሌላ ሰው ጠርቶ ዋጋ ተደራድሮ እሱ ባለው ዋጋ ማስወረድ ይችላል አለቀ።

' እኔ ማህበር ነኝ ፤ እኔ እንደዚህ ነኝ ' ማን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ።

አንድም እንዳይኖር ይሄን ሰፈራችሁ ላይ አወያዩ ፤ ማህበረሰቡ ይሄን ይወቅ ለናተ መረጃ ይስጣችሁ። ሰፈር መድረስ ማለት ይሄ ነው።

ጫኝ እና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።

ይሄ የጫኝ እና አውራጅ ስቃይ የድሬዳዋ ብቻ አይደለም። በአዲስ አበባ በየሰፈሩና በክልል ከተሞች ተመሳሳይ ነው።

ገና ሰው እቃ ይዞ ሲመጣ " እኛ ካላወረድን ማንም ማውረድ አይችልም " በሚል አምባጓሮ የሚፈጡ አሉ።

አውርዱ ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው የሚጠሩት ብር ደግሞ አስደንጋጭ ነው።  ሰው በስንት ድካም ገንዘቡን እንደሚያገኝም አይረዱም።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ በስንት መከራና ጭቅጭቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ እቃውን ያስወርዳል። " ነገ የት እኖራለሁ " ብሎ በመፍራት።

እራሱና ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ በጋራ የገዛ እቃቸውን እንዳያወርዱ ዛቻ ሁሉ ሊፈጸምባቸው ይችላል።

ይህንን ስርዓት አልበኝነትና ድንፋታ እንዲያስቆሙ የሚጠሩ አንዳንድ የፀጥታ አባላት ነገሩን ለማስተካከል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የሚሉት ' ከነሱ ጋር ተስማሙ ' ነው።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃውን ይዞ ይገባል። በገዛ ሀገሩ በገዛ ከተማው በገዛ እቃው ተሳቆ ነው የሚኖረው። ስቃዩ ብዙ ነው !

#TikvahEthiopiaFamily

#DirePolice #ድሬ

@tikvahethiopia