TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ያልተገደበ ወርሃዊ የኢንተርኔት ጥቅልን በM-PESA App ላይ እንግዛ !

ፈጣንና ያልተገደበ ወርሃዊ ጥቅልን በ999 ብቻ በመግዛት እንደልብ እንንበሽበሽ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
Telegram: https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia
Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm
#እንድታውቁት

ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና ፦

- የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው።

- በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል::

አጋላጮች ፦
▫️የአቻ ግፊት
▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች
▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል
▫️የማንነት ጥያቄ
▫️የሚዲያ ተጽዕኖ
▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው።

- በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው።

ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች ፦
* ከልክ በላይ ጭንቀት
* የስሜት መዋዠቅ
* ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም #በህይወት_መቆየት_አለመፈልግ

የባህሪ ችግሮች ፦
° ትኩረት ማጣት፣
° ለነገሮች መቸኮል፣
° የፀባይ ለውጥ መኖር

የአመጋገብ ችግር ፦
ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር ነው።

የስነ-ልቦና ቀውስ ፦
• ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል።
• ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ።
• ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ  ተጽዕኖ ያሳድርበታል።

- ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ ?
▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት።
▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ  በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።።

#WHO #የዓለምጤናድርጅት

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
በርከት ያሉ ዝርፊያ የፈፀሙ ግለሰቦች በሌሉበት #ከሞት ፍርድ እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው ፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

ግለሰቦቹ ከ1 ሚሊዮን 375 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶችን እንደሰረቁ ነው የተነገረው።

ግለሰቦቹ ፦
1ኛ አቤል ኢሳስ ተስፋዬ ዜግነቱ ኤርትራዊ፣
2ኛ አቤል አዋየው አሊ፣
3ኛ አቤል ግደይ በረኸ፣
4ኛ ሀብታሙ ወንድሙ ገብረየስ፣
5ኛ ዳንኤል ጎይቶም ተስፋዬ ዜግነቱ ኤርትራዊ፣
6ኛ ናትናኤል ግደይ በረኸ፣
7ኛ ዳንኤል ዮሐንስ ገ/መድን፣
8ኛ ዮናስ ፍፁም ከበደ፣
9ኛ ናትናኤል ረዳኢ ኪሮስ የተባሉ ዘጠኝ ተከሳሾች በሁለት ክሶች ተከሰዋል።

በ1ኛ ክሳቸው ተከሳሾች ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 9፡30 ሰዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 መሪ 20 ሜትር ጎላጉል አጠና ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ካልተያዙ ግብረ-አበሮቻቸው ጋር በመሆን ፦
* ሽጉጥ፣
* ጩቤ፣
* ገጀራ ይዘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ግቢ በር ገንጥለው በመግባት ተበዳዮችን በማስፈራራት አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 365 ሺ ብር የሚያወጣ የተለያዩ ንብረቶችን ዘርፈዋል የሚል ነው።

ሁለኛው ክሳቸው ከላይ በአንደኛ ክስ በተገለፀው ቀንና ቦታ ከሌላኛው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ የግቢውን የአጥር ሽቦ በከተር ቆርጠው ዘለው በመግባት በማስፈራራት አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 1 ሚሊዮን 13 ሺ 200 ብር የሚያወጣ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን በመውሰድ ተከሰል።

ግለሰቦቹ ዝርፊያውን ከፈፀሙ በኃላ ከአካባቢው ተሰውረው ፖሊስ ባደረገው ክትትል የተያዙ ሲሆን በፍትህ ሚኒስቴርም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የከባድ ውንብድና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

የክርክር ሂደቱ የታየውም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ነበር።

ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው እንዲያሰሙ ቀጠሮ ቢሰጣቸውም የመከላከያ ምስክር ባለማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ የመከላከል መብታቸው ታልፎ በተከሳሾች ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦
- 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በሌሉበት #በሞት እንዲቀጡ፣
- 2ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በሌሉበት በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣
- 9ኛ ተከሳሽ በሌለበት በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣
- 3ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች በሌሉበት በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሁም 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች ቀርበው በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

ይህ መረጃ በፍትህ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገፅ ላይ የተመለከቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፦
° አብዛኞቹ ፍርደኞች #አለመያዛቸው ግር እንዳሰኛቸው
° ፍርዱ እስከሞት የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ በዝርዝር እንዳልተብራራላቸው
° በገዘንብ የማይተመን የሰው ነፍስ በአሰቃቂ መንገድ ያጠፉ ፣ ህፃናትን የደፈሩ የተወሰነ አመት ሲፈረድባቸው እዚህ ጋር የተገለፀው ፍርድ እስከ ሞት መሆኑ ደግሞ ለመረዳት እንዳስቸገራቸው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው እና የምግብ ዘይት ላይ አደረኩት ባለው የገበያ የቅኝት ስራ የገላጭ ጽሁፍ እና የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶች መኖራቸውን ገልጿል።

ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል።

የምግብ ዘይት እና በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ እንዲያሟሉ ደረጃ የወጣላቸው ሲሆን በነዚህ ምርቶች ላይ የደረጃ ምልክት አለመለጠፍ ከፍተኛ የህግ ጥሰት መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈ አምራች ድርጅቱ ከምርት ጥራት ችግር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች ኃላፊነት ላለመውሰድ የሚያደርገው ጥረት ነው ተብሏል።

አንድ ምርት ፦
* አገዳጅ የደረጃ ምልክት
* የምርት መለያ ቁጥር
* የአምራች ስም
* የአምራች አድራሻ
* #የተሰራበት_ግብዓት
* የተመረተበትና የመጠቀሚያ ጊዜው የሚያበቃበት ቀን ሊኖረው ይገባል።

(ህብረተሰቡ አይጠቀማቸው የተባሉት ምርቶች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም #አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል ብሏል። በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ያላለፉ…
የመውጫ ፈተና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 /2016 ድረስ ባሉት 5 ቀናት ይሰጣል።

ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በከፍተኛ ትምህርት የመውጫ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ በሚደነግገው መሰረት፦

- በመንግሥት ወጪ ሙሉ ድጋፍ ትምህርታቸውን የሚከታተሉና ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በወጪ መጋራት ውስጥ በማካተት ተቋማት ወጪውን እንደሚሸፍኑ፣

- በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችም ሆነ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን በግል የሚከታተሉ የመውጫ ፈተና ወጪያቸውን በግላቸው እንዲፈፅሙ ተቀምጧል።

ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች በነፍስ ወከፍ 500 ብር እንዲከፍሉ በተወሰነው መረሰት ሁሉም አዲስ ተፈታኝ ተማሪዎች ተቋማት በሙሉ በላኩት መረጃ መሰረት የተቀመጠውን የክፍያ መጠን በሚያስፈትኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ተባዝቶ ለዚህ ተብሎ በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000553176097 ገቢ እንዲያደርጉ ተብሏል።

ሁሉም ተቋማት (የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች) ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ያለባቸው እስከ ጥር 25 ቀን 2016 ዓ/ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም #አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል ብሏል። በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ያላለፉ…
" የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ መራዘሙን አስታወቀ።

በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመፈተን የምዝገባ ጊዜው ጥር 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 15/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ መጠቀሱ የሚታወሰ ነው።

ይሁን እንጂ ትምህርት ሚኒስቴር በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት የምዝገባ ጊዜው እስከ ጥር 20/2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ሌሎች ሁኔታዎች ግን ቀደም ሲል በተገለጸው አግባብ የሚከናወኑ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/84290?single

@tikvahethiopia
Attention all aspiring entrepreneurs in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹!
Join us for an in-person information session to share knowledge about the Jasiri Talent Investor program offerings, the application process, and answers to any questions you might have

📅 26th January 2024 at 6:00pm.
📍 To be shared with those who RSVP
RSVP Link- https://bit.ly/421zcEd

Make sure to mark your calendars! We are excited to get to know you and answer any questions you may have about the program.

#Jasiri4Africa
#JasiriTalentInvestor
#highimpactentrepreneurship
#marketcreatinginnovations
ወደ ሚቀርብዎ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቅርንጫፎች ጎራ ብለው የቁጠባ ሒሳብ በመክፈት የአገልግሎቶቻችን ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ 
ለጋራ ስኬታችን!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋግኽምራ " ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም" - ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ በዞኑ ስላሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? - ድርቁ በጣም #እየባሰ ነው። ባለፈው ጥናት ካጠናን በኋላ ሊደረግ የሚገባው ግን ያልተደረገ በጣም በስፋት…
#አማራ #ዋግኽምራ

በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሃላ ሰየምትን ጨምሮ ድርቅ በተከሰተባቸው ሌሎችም ወረዳዎች ላይ እንስሳት በመኖ እጥረት #እየሞቱ ፣ አካባቢያቸውን ለቀው #እየተፈናቀሉ መሆኑን አስተዳደሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የአስተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ ከ10,000 በላይ የተለያዬ እንስሳት በውሃና በመኖ እጥረት ሞተዋል።

በአበርገሌ፣ በሮቢና፣ በበለቃ በላይኛው ተከዜ ተፋሰስ በተለይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ነጻ ያልወጡ፣ መንግሥት የማይቆጣጠራቸው ቀበሌዎች ላይ ሰፋ ያለ ችግር እንዳለ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በድርቁ ቀጥተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ እንስሳትን በሚመለከት ኃላፊው ፤ በሦስቱም ወረዳዎች ፦
* ሰሃላ ሰየምት፣
* ዝቋላ፣
* አበርገሌ በጣም የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የለተለዩ ወደ 791,000 አካባቢ እንደሆኑ አስረድተዋል።

ከ791,000ዎቹ ውስጥ በተለይ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ላይ ያሉት ክርቲካሊ የዕለትም አቅርቦት ስላጡ 171,000 ወደ ደሃና ወረዳ ተፈናቅለው እንዲሄዱና ተጠግተው ለጊዜው እንዲቆዩ መደረጉን ተናግረዋል።

" ይህን ይህል ተፈናቅሎ ከሄደ ቀሪው 620,000 ደግሞ ከዚያው #እየተላወሰ ነው ያለው " ሲሉ አክለዋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-24

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ   ዛሬ ጥር 13/2016 ዓ.ም በትግራይ በርካታ ከተሞች  ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተሰምቷል። ሰልፎቹን ያካሄዱት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው ተብሏል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የተደረጉት ፦ * በሸራሮ * በሽረ * በአክሱም * በዓድዋ * በተምቤን * በዓዲግራት * በጉሎመኸዳ * በኢሮብ * በመቐለና ልሎች ከተሞች ሰሆን ከጠዋት ጀምሮ በተካሄደ ሰልፍ የተለያዩ መፈክሮች ሲሰሙ ነበር።…
#ትግራይ

" ... እዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የወደቃችሁት ሥራችንን መሥራት ስላልቻልን ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዛሬም የትግራይ ተፈናቃዮች ሰልፍ መቀጠሉ ተሰምቷል።

ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ተፈናቅለው በመቐለ የተለያዩ የመጠለያ ጣብያዎች የሚኖሩ ተፈናቃዮች ካለፈው የቀጠለ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተነግሯል።

ሰልፈኞቹ ዛሬ ጥር 15/2016 ዓ.ም በመቐለ ዋና መንገዶችና አደባባዮች ባካሄዱት የተፈቀደ ሰልፍ ፤ " መሶባችንና ሆዳችን ባዶ ሆኖ ኬሻና ፕላስቲክ ለብሰን የመከራ ህይወት መኖር ይብቃን። ድምፃችን ይሰማ ወደ ቤታችን መልሱን " ሲሉ ድምፅ አሰምተዋል።

በተጨማሪ ሰልፈኞቹ ፤
* ሰርተው መኖር እንዲችሉ ወደ መሬታቸው እንዲመለሱ፣
* የፕሪቶሪያ ውል ሙሉ በሙሉ እንዲተገበት ፣
* በትግራይ ውስጥ ያሉ ኃይሎች ከመሬታቸው እንዲወጡ፣
* በተፈናቃዮች ላይ የሚፈፀመው በደል እንዲቆም
* ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ጠይቀዋል።

" የሚታረስ መሬት እያለን በረሃብ እያለቅን ነው " ያሉት ሰልፈኞቹ ፤ " በእርዳታ እጦት እያለቅን ነው፤ ምግባረሰናይ ድርጅቶች ድረሱልን " ብለዋል።

የተፈናቃዮቹ ጥያቄ በፅ/ቤታቸው ደጃፍ ደረስ በመምጣት ያዳመጡትና የተቀበሉት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ እንዳሉት ፤ " ስቃይችሁ ስቃያችን ነው። ወደ መሬታችሁ እንድትመለሱ ከሁሉም ስራዎቻችን በላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን " ብለዋል።
 
ተፈናቃዮቹ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ላለመለሳቸው አንዱ ተጠያቂ አስተዳደራቸው እንደሆነ አምነዋል።

" እዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የወደቃችሁት ሥራችንን መሥራት ስላልቻልን ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወስድ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው የፌዴራል መንግሥትም ስራውን እንዳልሰራ ሳይናገሩ አላለፉም።

ጥር 13/2016 ዓ.ም በሸራሮ ፣ ሽረ፣  አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ተምቤን ፣ ዓዲግራት ፣ ጉሎመኸዳ ፣ ኢሮብ ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ተመሳሳይ ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል።

መረጃው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                       
@tikvahethiopia