TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ
ትግራይ ክልል ውስጥ በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ከ900 በላይ ሰዎች ከምግብ እጦት እና ከመድሃኒት እጥረት ጋር በተያየዝ ሞተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።
የተቋሙ የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ረሃብ የሰው ህይወት መንጠቅ ከጀመረ ወራቶች መቆጠሩንም ገልጿል።
* በሽረ
* አክሱም
* በአብይአዲ
* በመቐለ
* ዓዲግራት ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች የሰው ህይወት በረሃብ እና በመድሃኒት እጥረት እያለፈ መሆኑን የሚገልጸው ተቋሙ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ምንም እርዳታ ያላገኘ ተፈናቃይ መኖሩንም አሳውቋል።
የዕንባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ከህዳር በፊት ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር ግን መንግሥት እርምጃ ባለመውሰዱ የከፋ ችግር ደርሷል ብሏል።
በሽረ የተፈናቃዮች ጣቢያ ፤ 309 አረጋዊያን እና 118 ህፃናት የሚገኙበት 849 ሰዎች ሞተዋል ይህ ሁሉ ሰው በአንድ IDP የሞተው በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ነው ሲል አሳውቋል።
በአክሱም 93 ሰዎች፣ በአብይአዲ 35 ሰዎች፣ በአይደር 4 ሰዎች፣ በሞሞና 2 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንም ተቋሙ አደረኩት ባለው ክትትል ማረጋገጡን ገልጿል።
በአጠቃላይ ክትትል በተደረገባቸው መጠለያዎች 980 ሰዎች ላይ ሞት ማጋጠሙን አክሏል።
ከመጠለያ ጣቢያ ውጭም ያሉ በርካታ ዜጎችም በድርቅ ምክንያት እየተሰቃዩና በተከሰተው የምግብ እጥረት ህይወት እየጠፋ ነው ብሏል።
ፅ/ቤቱ በረሃብ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው እንዲሰደዱ ፣ ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለመራው ጫፍ ላይ ደርሰዋል ሲል ይፋ አድርጓል።
" አሁንም በርካታ ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች ተሞልተዋል እዛ ያሉ ተማሪዎችም ድንኳን ሰርተው ለመማር ተገደዋል " ብሏል።
ምንም እኳን የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ረሃብ አልተከሰትም ቢልም የህዝብ ዕንባ ጠባቂ የመቐለ ቅርንጫፍ ረሃብ መከሰቱን አረጋጫለሁ ብሏል። በፌዴራልም ይሁን በክልል እየተሰጠ ያለው ትኩረትና ድጋፍም የሞተ በመሆኑ በቀጣይ አደጋው የከፋ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል። ህዝቡ ቀጣይ ክረምት አምርቶ እራሱን እስኪመግብ እርዳታ ማግኘት አለበትም ብሏል።
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ባለሃብቶች፣ድጋፍ አድራጊ ተቋማት፣ አቅም ያላቸው ክልሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ በድርቅ ምክንያት ረሃብ አንዣቧል ፌዴራል መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህግና የሞራል ግዴታቸውን ይወጡ ማለቱ ይታወሳል።
የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ደግሞ በትግራይ ረሃብ ስለመከሰቱ አለመከሰቱ በመዘኛ መስፈርቶች መዝኖ መናገር የሚችለው የፌዴራል መንግሥት ተቋም ነው "ረሃብ የሚባለው ሀሰት ነው" ማለቱ አይዘነጋም።
ከቀናት በፊት ደግሞ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤ 'ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረ ነው' የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ መሆኑን በማስረዳት ሠብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመቻልና የልማት ስራዎችን በማስፋፋት፣ ትርፍ አምራች ለመሆን ይሰራል ብሏል።
በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት ኮሚሽኑ በሰጠው ቃል በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ማረጋገጫ እንደሌለው አሳውቆ ነበር።
የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሀገሪቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሚፈቅድ እንዳልሆነም ነው የገለፀው።
የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በክልልና በፌዴራል መንግሥት መካከል አለመግባባት እንዳለ ጠቁመው፤ በድርቅ ምክንያት ስለደረሰ ጉዳት ቁጥጥር እንዳካሄዱና በቅርብ እውነቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሸገር FM ነው የወሰደው።
@tikvahethiopia

Photo ፦ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ አገዳ መፍጨት መጀመሩን በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፤ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ጽ/ ቤት አሳውቋል።
ፅ/ቤቱ ፤ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የ2016 ምርት ዘመን ስኳር የማምረት ሥራን ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት መጀመሩን ገልጾ በተያዘው የምርት ዓመት በአራት ሺህ 600 ነጥብ 5 ሄክታር ማሳ ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ በግብአትነት በመጠቀም 245 ሺህ 927 ነጥብ 5 ኩንታል ስኳር ለማምረት መታቀዱን ገልጿል።
የፋብሪካው አጠቃላይ የክረምት ጥገና ተከናውኖ ታህሳስ 26 ቀን 2016ዓ.ም ቦይለር መለኮሱም ታውቋል፡፡
ከማሳ የተቆረጠውን አገዳ ጭኖ ቀድሞ ፋብሪካ የደረሰውና በሴት አሽከርካሪዋ ዲቦራ ሞዲ ለሚመራው ጋሪ ሲሆን ለአሽከርካሪዋ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጥበቡ ማሞ በግል የማበረታቻ ሽልማት እንዳበረከቱላት ተነግሯል።
Via Ethiopian Sugar Industry Group

#GeneneMekuria አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን በማቅረብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ እውቀቶችን ያስጨበጠ ጋዜጠኛ ነበር። በተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች ፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ታሪኮችንና ወጎችን በማቅረብም በሚዲያው ላይ ከአርባ…
#Update የጋዜጠኛ ገነነ ሙኩርያ (ሊብሮ) የቀብር ሥነ ሰርአት በነገው ዕለት ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰአት በቅድስት ሥላሴ ካቴደራል እንደሚፈፀም አሻም ቴሌቪዥን አሳውቋል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም
ኩባንያችን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ እቅዱን በላቀ አፈጻጸም ማጠናቀቁን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው !
ኩባንያችን በበጀት አመቱ አጋማሽ የደንበኞቹን ብዛት 74.6 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዱን 98.3% እንዲሁም 42.86 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 98% ማሳካት ችሏል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 84.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 109% ያሳካ ነው፡፡
ኩባንያችን የገቢ አማራጮችን ለማስፋት ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረቶች በተጨማሪ ወጪን በአግባቡ ለመጠቀም ተግባራዊ ባደረገው (DO2SAVE) ስትራቴጂ በግማሽ አመቱ ብቻ ከብር 2 ቢሊዮን በላይ በመቆጠብ የዕቅዱን 113% አሳክቷል፡፡
ይህም ኩባንያችን ትርፋማ እንዲሆን ለምናደርገው የጋራ ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሠረት ከውጪ ኦዲት ምርመራ በፊት ያልተጣራ ትርፍ (EBITDA) ብር 19.77 ቢሊዮን (46%) በማግኘት የእቅዱን 137% ለማስመዝገብ ችሏል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ብር 11 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ የተመዘገበ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14% እድገት ሲኖረው የትርፋማነት መጠኑን ወደ 26% ያደርሰዋል፡፡
ውድ ደንበኞቻችን እና የስራአጋሮቻችን ለዚህ ስኬት ስላበቃን አብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን!
#Ethiotelecom #telebirr #GSMA #ITU

Tecno Spark 20 pro +
አስገራሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ያካተተው አዲሱ Tecno spark 20 pro+ ለአስደሳች እና ዘመናዊ አኗኗር የሚመርጡት ልዩ ስልክ!
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia

ትላንት ከላሬ ወረዳ ወደ ጋምቤላ እየተጓዘ ባለ የህዝብ ማመላለሻ #ባስ ላይ ኢታንግና አቦል መካከል ጥቃት ተፈፅሞ ነበር።
በዚህ ጥቃትም በተወሰኑ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።
ጥቃት አድራሾቹ እስካሁን ያልተያዙ ሲሆን ክልሉ " በቁጥጥር ስር ላውላቸው ክትትል እያደረኩ ነው ፤ ህብረተሰቡ በማጋለጥ ይስጠኝ " ብሏል።
በክልሉ ትላንት ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደርስ የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ ተነግሯል።
በክልሉ ወንድማማች ህዝቦችን ወደ ማያባራ ግጭት ለማስገባት የሚሰሩ " ፅንፈኛ አካላት " አሉ ያለው የክልሉ አስተዳደር ፤ ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አልታገስም እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።

#ትኩረት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን፤ ባድዋቾ ወረዳ እና በሾኔ ከተማ በተቀሰቀሰ የኩፍኝ ወረሽኝ የ4 ህጻናትን ጨምሮ የ8 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው የኩፍኝ ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ መዛመቱንና ህይወት መቅጠፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገልጹት በሾኔ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የኩፍኝ ወረሽኝ ቁጥጥር አስተባባሪው ዶክተር ፋብዬ ግርማ " ችግሩ ከዚህ በላይ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት የሚመለከተዉ አካል ሁሉ አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ ይኖርበታል " ሲሉ አሳስበዋል።
አሁን ላይ ከሰላሳ በላይ ተጠቂዎች በሆስፒታል ዉስጥ ተለይተዉ ክትትል ላይ የሚገኙ መሆኑን ገልጸው የተወሰኑ ሰዎች በተሰጣቸዉ ህክምና ድነዉ ወደቤታቸዉ መሸኘታቸውን አስረድተዋል።
ዶ/ር ፋብዬ ፤ " አሁን ባለን መረጃ መሰረት በሽታዉ እየተስፋፋ ነው " ያሉ ሲሆን " ማህበረሰቡ ለበሽታዉ ባለዉ ዝቅተኛ አመለካከትና ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠዉን ምክር በአግባቡ ባለመረዳቱ ምክኒያት ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኗል " ብለዋል።
" በሽታው በዚህ ሰአት 4 ህጻናትን ጨምሮ 8 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረግ በዚህ ምክኒያትም የአካባቢዉን ማህበረሰብ ለከፍተኛ ጭንቀትና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እያጋለጠ ነው " ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ማህበረሰቡ የህክምና ወጪዉን ራሱ እንዲሸፍን መደረጉ ወደሆስፒታል የመምጣቱን ሁኔታ ዝቅ ማድረጉን የሚገልጹት ዶክተር ፋብዬ አሁን ላይ ሆስፒታሉ በነጻ የሚሰጠዉ አልጋና ኦክስጅን ብቻ ሲሆን የፌደራል መንግስቱ ድጋፍ ሲጀምር መድሀኒቶች በነጻ የመታደል ተስፋ ይኖራቸዋል ብለዋል።
ዘገባዉን ያደረሰን የሀዋሳዉ የቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

" የጾታዎች ሁለትነት እና አንዳቸው ከሌላቸው መጣመራቸው ማኅበራዊ ግኝት ሳይሆን #ከፈጣሪ_የመጣ_ነው " - የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻም ሆነ እንዲህ ያሉ ጥንዶች ልጆች በጉዲፈቻ ማሳደጋቸውን በሚመለከት የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን በይፋ ተቃወመች።
ረቂቅ አዋጁ በመጪው ሳምንት አጋማሽ ላይ በሀገሪቱ ፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ሊሰጥበት ታቅዷል።
ሆኖም የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኒን ቅዱስ ሲኖዶስ ረቂቅ ሕጉ ልጆች አባት ወይም እናት ሳይኖራቸው በተምታታ የመኖሪያ ከባቢ ውስጥ እንዲያድጉ የሚያደርግ ነው፤ እንዲህ ላሉ ጥንዶች ልጆችን ለማርገዝ ማሕጸናቸውን የሚያከራዩ ሴቶችንም የሚበዘብዝ ነው በማለት ውግዞታል።
በጉዳዩ ላይ ለአራት ሰዓት የተወያየው የግሪክ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ " የጾታዎች ሁለትነት እና አንዳቸው ከሌላቸው መጣመራቸው ማኅበራዊ ግኝት ሳይሆን ከፈጣሪ የመጣ ነው " ብሏል።
የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቀጳጳስ ኢሮኒሞስ በበኩላቸው " ረቂቅ ሕጉ በሀገሪቱ ማኅበራዊ ትስስር ለማበላሸት ያለመ አዲስ ነገር ነው " በማለት ተቃውመዋል።
በግላቸው ጉዳዩን ይደግፋሉ የሚባሉት ወግ አጥባቂው የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ ግን ረቂቅ ሕጉ በመጪው ሳምንት ይቀርባል ብለዋል።
ሆኖም ከምክር ቤቱ አባላት አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ሊቃወሙት እንደሚችሉ አዣንስ ፍራንስ ፕረስን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።