ንግድ ባንክ አገልግሎት መቋረጡን ገለጸ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦
- በቅርንጫፎች፥
- በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው አሳውቋል።
አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በርብርብ እየተሰራ ነው ያለው ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።
ለተፈጠረው መጉላላትም #ይቅርታ ጠይቋል።
ከአንድ ወር ገደማ በፊት በፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ሁሉም አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደነበር እና በሰዓታት ውስጥ ችግሩ መፈታቱ አይዘነጋም።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ፕሮጀክት እና ተያያዥ የልማት ሥራዎች ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መስመር የማዛወር ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
በዚህም ሥራው ሲከናወን ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም አደጋ እንዳይከስት ሲባል ሥራው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ ወይም አልፎ አልፎ ለተወሰኑ ሰዓታት #እየተቋረጠ እንደሚገኝ አመልክቷል።
" የመስመር ማዛወር ሥራዎቹ በጥንቃቄና በፍጥነት ለማከናወንና አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው " ያለ ሲሆን ነዋሪዎች ይህን ተረድተው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።
በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ለአገልግሎት መስተጓጎሎችም #ይቅርታ ጠይቋል።
በሌላ በኩል፥ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ በተለይ በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
በዚህም፦
➡ ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
➡ ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።