TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጎረቤት ሀገራት እንዲሁም የሌሎችም በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ይገኛሉ።

መሪዎቹ ሳዑዲ ዓረቢያ ያቀኑት በመጀመሪያው የ " ሳዑዲ-አፍሪካ ጉባዔ " ለመሳተፍ ነው።

በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ላይ እየተካፈሉ ከሚገኙት መሪዎች መካከል፦
🇪🇹 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
🇪🇷 የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
🇩🇯 የጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ
🇸🇴 የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇰🇪 የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ይጠቀሳሉ።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሳዑዲ - አፍሪካ ጉባኤ ጎን ከጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዳደረጉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን ተሻግረው የጣሊያን ወረራን አልፈዋል እንዲሁም በየዘመናቱ በተፈጠሩ የእርስበርስ ጦርነቶች ጉዳት ሳያደርሱባቸው እዚህ ደርሰዋል ብላለች።

ይሁን እንጂ አሁን ባለበንበት ዘመን በአካባቢው  በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት  ምክንያት ከፍተኛ  የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን በይፋ አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን ገልጸው ፤ ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት በቅድሚያ ጠቁመዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና   የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ  የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ  ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ  ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም  የቅዱሱ ቅርስ  የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ  በጉዳዩ ላይ  በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው።

@tikvahethiopia
በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወዳጅነትን ይበልጥ የሚያጠብቅ ጥቅል!

ተጨማሪ ዳታ ተጨማሪ ደስታ እና ፌሽታ!!!

እንደፍላጎትዎ በተለያየ የአገልግሎት ጊዜ አማራጮች ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር ወይም በማይ ኢትዮቴል እና *999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸው በስጦታ ያበርክቱ።

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
* ወንጀል

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ የተፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች ከሰሞኑን የበርካቶች መነጋገሪያ ሆነዋል።

የመጀመሪያው የወንጀል ድርጊት የተፈፀመው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ነው።

በዚህም ዞን አንድ ባል ከሚስቱ ጋር የተፈጠረን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ የባለቤቱን መራቢያ አካል ሆን ብሎ በጭካኔ በእሳት በማቃጠል በቀረበበት ክስ በጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

የወረዳ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳው ድርጊቱ የተፈፀመው ባለፈው ዓመት ሐምሌ 4/2015 ዓ.ም. ነው።

ግለሰቡ ጥቃቱን ለመፈጸሙ ምክንያት ነው የተባለው ከባለቤቱ ጋር " አብረሺኝ ተኚ፣ አልተኛም " በሚል ከተጨቃጨቀ በኋላ ነው።

በዚህ ሳቢያ ተከሳሽ የሚስቱን የመራቢያ አካል እና ከፊል ጭኗን እና ከኋላዋ በኩል በእሳት በማቃጠል ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባታል።

በገጠር አካባቢ በቤት ውስጥ ፍልጥ እንጨት ማንደድ እና እሳቱ ተዳፍኖ እንዲቆይ ማድረግ የተለመደ ሲሆን ተከሳሹም አለመግባባቱ ሲፈጠር እሳት የያዘ ፍልጥ እንጨት ከእሳት ውስጥ አውጥቶ የአካሏን የተለያዩ ክፍሎች አቃጥሏል።

በባለቤቱ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰው የ21 ዓመቱ ወጣት ወንጀሉን ከፈጸም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በአካባቢው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ምርመራ ተደርጎበት ጉዳዩ በአካባቢው ፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል።

የወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በ5  ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፈርዶበታል።

ጉዳት የደረሰባት ሴት ባለፉት ወራት የሕክምና ድጋፍ እና ክትትል አግኝታ አሁን ላይ በጤናዋ ላይ መሻሻል እያሳየች መሆኑን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘግቧል።

ሌላኛው የወንጀል ድርጊት የተፈፀመው በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳ ሲሆን በውርስ ምክንያት አባቱን በመግደል የተጠረጠረ የ25 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ተጠርጣሪው ኢብራሂም ሐሰን ይባላል።

የኤላ ጣጤሳ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩትን ወላጅ አባቱን ሐሰን አብደላ " አስቦ እና ተዘጋጅቶ " በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ታስሯል።

በዕድሜ መግፋት ምክንያት አባቱ የእርሻ መሬታቸውን በውርስ ለልጆቻቸው ያከፋፈሉበት ሁኔታ ያላስደሰተው ተጠርጣሪው በአባቱ ላይ ግድያ ፈጽሟል ብሏል ፖሊስ።

አባቱን የገደለው ተዘጋጅቶ፤ ሰው የሌለበትን አሳቻ ሰዓት ጠብቆ እና አባቱን ተከታትሎ ነው። በድርጊቱ ባለቤቱም ተባባሪ እንደነበረች ተገልጿል።

ተጠርጣሪው አባቱን ከገደለ በኋላ አስክሬናቸውን ከሌሎች ሰዎች ጋር በመተባበር ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የጣለ ሲሆን ሟች አድራሻቸው ሲጠፋ ተጠርጣሪው ከሌሎች ወንድም እና እህቶቹ ጋር " አባቴ ጠፍቷል " በሚል ፍለጋ ሲያደርግ ነበር።

በሦስተኛው ቀን ላይ ግን ለእህቱ የአባቱን አስክሬን ያሳያታል። እርሷ መጮኽ ስትጀምር እሱ በሩጫ ከአካባቢው ይሰወራል። ፖሊስ ባደረገው ክትትል እዛው መንደር በተባባሪው ቤት ውስጥ ተደብቆ ተገኝቷል።

ከተጠርጣሪው ባለቤትና ከሸሻጊው ሰው በተጨማሪ የቀበሌው ሊቀ መንበር የወንጀሉ ተባባሪ ናቸው በሚል በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሊቀመንበሩ ከተጠርጣሪው ጋር የጥቅም ትስስር ስላላቸው የአካባቢውን ሰዎች አስገድደው የሟች አስክሬን እንዲቀበር ማስደረጋቸውን ፖሊስ ገልጿል።

አስክሬኑ ለምርመራ መላክ አለበት በማለት የተከራረኩትን ሊቀመንበሩ እስከ ማሰር ደርሶም ነበር።

የወረዳው ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ጉዳዩን በመመርመር አስክሬን ከተቀበረበት ወጥቶ ለምርመራ ወደ ሐረር ከተማ ተልኳል።

ከተጠርጣሪው በተጨማሪ የተጠርጣሪውን ባለቤትና ሊቀ መንበሩን ጨምሮ 5 ሰዎችን በወንጀል ተባባሪነት በመጠርጠር መታሰራቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
* የ10 ዓመቷን ህፃን ልጅ የደፈረው ግለሰብ 14 ዓመት እስራት ተፈረደበት።

አዲስ አበባ ውስጥ የ10 አመት ህፃን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

ድርጊቱ የተፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ ሁለት  ፋና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

የ22 ዓመቱ ሳምሶን ሸመነ የተባለው ተከሳሽ የአስገድዶ መደፈር ወንጀሉን የፈፀመው #በጎረቤቱ ህፃን ልጅ ላይ ነው።

ግለሰቡ የህፃኗን ቤተሰቦች በቤት ውስጥ አለመኖር አጋጣሚ ጠብቆ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከፈፀመባት በኋላ ለጊዜው ከአካባቢው ተሰውሮ ቆይቷል፡፡

ፖሊስም ባደረገው ምርመራና ክትትል ወንጀል ፈፃሚውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ያውለዋል።

በተከሳሽ ሳምሶን ሸመነ ላይም ክስ ከተመሰረተ በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ምድብ ችሎት ተከሳሹን ያስተምራል፣ ሌሎችን ያስጠነቅቃል በማለት በ14 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ፖሊስ ፤ በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በአብዛኛው በቅርብ ዘመድና በሚያውቋቸው ሰዎች መሆኑን ገልጾ ከወላጆች ባሻገር ህብረተሰቡ ተገቢውን ከለላ እና ጥበቃ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ፤ ወንጀል ፈፃሚዎችም በህግ እንዲጠየቁ ጥቆማና መረጃ መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ከ ' ጠላት ተባብራችኃል' በሚል ግምገማና ክስ ከስራና ከሃላፊነት ውጭ ሆነው የቆዩት 19 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸውና የሃላፊነት ቦታቸው እንዲመለሱ ፍርድ ቤት ወሰነ።

በፍርድ ቤት ውሳኔ ወደ ሰራቸው ከተመለሱት መካከል 10 ጋዜጠኞች ፣ 7 የቴክኒክ ባለሙያዎች ፣ 2 የፕሮሞሽን ክፍል ሰራተኞች ባጠቃላይ 19 እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።

የፍርድ ቤት ወሳኔ ተከትሎ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም በትግራይ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሻለ በቀለ ተፅፎ ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ ፦

" ለስቪል ስርቪስ ኮሚሽን ፍርድ ቤት ባቀረባችሁት አቤቱታ መሰረት በቀን 03/12/2015 ዓ.ም በደብዳቤ ይ/ፍ/መ ቁጥር 001650/2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ወደ ስራ ምድባችሁ እንድትመለሱ ተወስኗል። " ይላል።

ጉዳዩ መቼና ? እንዴት እንደተጀመረ ?

የቀድሞው የትግራይ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አስተያየቱ አጋርተዋል።

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ህዳር 19/2013 ዓ.ም የፌደራል መንግስት መቐለን ሲቆጣጠር በክልሉ ከነበሩ ድምፂ ወያነ ትግራይና የትግራይ ቴሌቪዥን ጣብያዎች መሃል ድምፂ ወያነ ባጋጠመው ውድመት እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም ሰርጭት ሲያቆም ከ8 ወራት ጦርነት በኃላ ሰኔ 21 /2013  ዓ.ም የትግራይ ሃይሎች መቐለን መልሰው ሲቆጣጠሩ ስራ አስኪያጁ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ጨምሮ 46 ባለሙያዎችና ደጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ' ከጠላት ተባብራቹሃል ' የሚል ግምገማና ክስ ቀርቦባቸው ታስረዋል፣ ከስራ ተባረዋል ፣ ትግራይ ለቀው የወጡም አሉ።

' ከጠላት ተባብራቹሃል ' የሚል ክስ ቀርቦባቸው ከታሰሩና ከስራ ከተባረሩት  መካከል 19 ጋዜጠኛችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ለሁለት አመታት ሲከላከሉና ሲከራከሩ ቆይተው ፍርድ ቤት አዘግይቶም ቢሆን ወደ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ መወሰኑ የቀድሞ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ 'ሕጊ ስዒሩ ' 'ህግ አሸንፈዋል ' ሲል ገልፆታል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፣ ከመቐለ ከሚገኙ ቤተሰቡ ተለያይቶ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የቀድሞ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ወደ ስራው ይመለስ እንደሆነ ላቀረብንለት ጥያቄ ' ከነበርኩበት የሃላፊነት እርከን ሁለት ደረጃ ወደ ታች ወርደህ ስራ በመባሌ እና አሁን በተቋሙ ካለው ማኔጅመንት ለመስራት ፍላጎት ስለሌለኝ አልመልስም ' ብሏል።

በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወደ ስራ ምድባቸው እንዲመለሱ ከተወሰነላቸው 19 ጋዜጠኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በተጨማሪ በ2013 ዓ.ም በቀጥታ  (በሃንቲንግ) የተቀጠሩ 8 ጋዜጠኞች ወደ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ ወደ ክልሉ እንባ ጠባቂና ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አመልክተው መልስ በመጠበቅ ላይ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ለማወቅ ችሏል።    
                        
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን !

አንድ ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ፦

- በተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ)

- የተሸከርካሪዉን የመጫን አቅም (የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣

- ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም ClF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

#ተገጣጥመው_ወደ_ሀገር_ውስጥ_የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 13ዐዐ ከሆነ 75.67% ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ18ዐዐ በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሸከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው #ያገለገሉ (USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

የተሽከርካሪው ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡

እንደ ተሽከርካሪው አይነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የተሸከርካሪዎች ላይ እስከ #አራት_ዓይነት የቀረጥና ታክስ ዓይነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከአምራች ድርጅቶች ውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ደግሞ በተጨማሪነት #የዊዝሆልዲንግ_ታክስ ይሰበሰባል፡፡

የቀረጥ እና የታክስ ማስከፈያ መሠረት (Tax base) የሚሆነው የእቃው ዋጋ (CIF) እና በቅድም ተከተል የሚሰላው የቀረጥ ወይም ታክስ መጠን ፦
* የጉምሩክ ቀረጥ፣
* ኤክሳይዝ ታክስ፣
* የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣
* ሱር ታክስ ድምር ይሆናል፡፡

የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት ተደርጎ እንደሚታሰብ ለምሳሌ ሁሉም ዓይነት ታክስ በሚመለከተው በቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በምሳሌነት እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 4ዐዐ,ዐዐዐ፣ የሲሊንደር አቅሙ 13ዐዐ የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ሲገባ ፦

🚘 በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 400,000 × 3ዐ%(ከፍተኛው መጣኔ) = 12ዐ,ዐዐዐ ይሆናል፡፡

🚘 ቀጥሎ ኤክሳይዝ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (400,000 + 120,000) 5%= 26,000 ብር ይሆናል፡፡

🚘 በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት thn (400,000 + 120,000 + 26,000) 15% = 81,9ዐዐ ብር ይሆናል፡፡

🚘 በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000 +81,900) 10% = 86,190 ብር ይሆናል፡፡

🚘 ተሽከርካሪው በመደበኛ አስመጪ (ከአምራች ድርጅት ውጪ...) የሚመጣ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 4ዐዐ, 000 × 3%= 12,ዐዐዐ ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት 120,000 + 26,000 + 81,900 + 86,190 + 12, 000= 326,090 ብር ይሆናል፡፡

#ማሳስቢያ ፦ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው መሠረት በማድረግ የተለያየ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል።

ይህ መረጃ የገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
"ብልሆች ወደ ህልማቸው ለመድረስ ይቆጥባሉ!" ከባንካችን ጋር አብረው ሲሰሩ ለስኬትዎ ብርቱ አጋር በመሆን የድርሻችንን እንወጣለን ፡፡

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123    

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!

#globalbankethiopia #GBE #banksinethiopia #fintech #bank #finance #ethiopia #ethiopian #digitalbanking #Globaldigital