TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሹመዋል። ዶክተር አህመዲን መሐመድ  ደግሞ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ  ሆነው መሾማቸው ተን ከዚህ በተጨማሪ የባህር ዳር ከንቲባው ዶክተር ድረስ ሳህሉ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆነው…
" ኃላፊነቱን ከመቀበል ውጭ አማራጭ ባለመኖሩ ተቀብያለሁ " - አቶ አረጋ ከበደ

አዲሱ አማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አረጋ ከበደ ፤ ከሹመቱ በኃላ ባሰሙት ንግግር ወደ ኃላፊነት የመጡበት ወቅት ፈታኝ እና የጋራ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

" ክልሉ አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ ለሁሉም ግልጽ ነው " ያሉት አቶ አረጋ " ኃላፊነቱን ከመቀበል ውጭ አማራጭ ባለመኖሩ ተቀብያለሁ " ብለዋል።

በኃላፊነት ዘመናቸው ክልሉ አሁን ካለበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አውጥቶ የተሻለ እና የተረጋጋ ክልል ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

አቶ አረጋ ከበደ በንግግራቸው የህዝቡ የዘመናት ጥያቄና ጥቅም ላይ ያልተገባ ንግግር የሚያደርጉ ቡድኖች ድርጊታቸው ከትንኮሳ አይለይም ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ አረጋ ፤ " በክልሉ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር እንደአጋጣሚ በመውሰድ በክልሉ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ እና ጥቅም ላይ ተገቢ ያልሆነ ንግግር የሚሰነዝሩ ቡድኖች ድርጊታቸው ከትንኮሳ የማይለይ መሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል " ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ሕጋዊ የፌዴራል መንግሥት ውሳኔ የሚጠብቅ እንጂ ሕዝብ የጠየቀውን ጥያቄ የሚዘነጋ እንዳልሆነ ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት በንግግራቸው " የሚያደርጉትን ያልተገባ ንግግር ከትንኮሳ ለይተን አናያውም " ያሏቸው የትኞቹን ቡድኖች እንደሆነ #በግልፅ ስም ጠርተው አልተናግሩም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ትላንት ለሊት " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራ መጠጥ ቤት ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና ለጉዳት የዳረገው ተጠርጣሪ ግለሰብ ስሙ ሙሉጌታ እንደሚባል ታውቋል።

ፖሊስ ግለሰቡ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና " በቁጥጥር ስር ለማዋል " ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጾ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ተጠርጣሪው በመቐለ ከተማ በተለይ ቀበሌ 14 ፣ 15 ፣ 16፣ 17 በደንብ ይታወቃል ያሉን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፤  የቀድሞ ታጋይና የኮሌኔልነት መአርግ ያለው ጭምር ነው በማህበረ ረድኤት ትግራይ /ማረት/  ሹፌር ሆኖም ሲሰራ ነበር ብለዋል።

ተጠርጣሪው በ2013 ዓ.ም መልሶ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቱን በኃላም ከትግል መሰናበቱን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

ፖሊስ ተሰናባቹን የቀድሞ ታጋይና ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት ያጠፋውን እንዲሁም መከፍተኛ የአካል ጉዳት የዳረገውም " ሙልጌታ "ን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ጥልዬ ዛሬም ነገም እንወድሃለን የኢትዮጵያ ጀግና አትሌት ነህ፤ ሀቋ ግን የበሪሁ ስለሆነች ነው በሪሁን ያስሮጥነው " - ረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዜዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በ5000 ሜትር ውድድር እንደማይሮጥ ከሰማ በኃላ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ በተመለሰው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ጉዳይ ተጨማሪ አሰተያየቷን ለሪፖርተር ሰጥታለች።

ረ/ኮ ደራርቱ ፤ " ጥላሁን ኃይሌ ቢሮጥ ደስ ይለኝ ነበር አልሮጠም መሮጥ ያልቻለው ደግሞ ሀቁ የበሪሁ አርጋዊ ስለሆነ ነው " ብላለች።

" ከዚህ በፊት ኦሪጎን ላይ በሪሁ ጥሩ ስላልሮጠ እድል እንስጠው ብለን ለጥላሁን ሰጥተን ነበር ግን ፋይናል (ፍፃሜ) አልደረሰም ፤ አሁን ላይም በሪሁ አንደኛ ነው ከዛ ሀጎስ አለ፣ ዩሚፍ አለ ፣ ጥላሁን አራተኛ ነው ፤ አንደኛ በወርልድ ራንኪንግም በቅርቡም ተሸናንፈው ነው የመጡት " ስትል ደራርቱ አስረድታለች።

" እኛ አትሌቶቹ በደረጃቸው ነው ያስቀመጥናቸው ለበሪሁ ሀቁን ነው የሰጠነው እንጂ በሪሁን አቅርበን ጥላሁንን አርቀን አይደለም ፤ ሁለቱም ለኢትዮጵያ ነው የሚሮጡት ሁለቱም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን " ስትል ገልጻለች።

" ጥላሁን ከመናደዱ የተነሳ ደራርቱ ናት ያስቀረችኝ ብሏል ያን ለምን አለ ብዬ አልቀየመውም ፤ አትሌት ነውና ጥሮ ነው እዚህ የደረሰው ለመሳተፍ ብዙ ውጣ ውረድ አለው እኔም ያለፍኩበት ስለሆነ ይገባኛል ግን ደግሞ ሀቁ የበሪሁ ነው " ብላለች።

ደራርቱ ፤ " እኛ ጥዋት እሱንም አሰልጣኙንም አግኝተን በአግባቡ ልንነግረው ነበር " ያለች ሲሆን ግን ቀድሞ ከዓለም አትሌቲክስ ፔጅ ላይ  ተመለከተ በዚህም በጣም ተበሳጨ ፣ተናደደ አለቀሰ፤ እኔም በዚህ በጣም አዝኛለሁ እንደ እናትም እንደ አመራርም " ብላለች።

" በተፈጠረው ሁኔታ እኔ ይቅርታ ብያለሁ " ያለችው ደራርቱ " ይቅርታ ስል ደግሞ ሀቁ አሁንም የበሪሁ ነው ጥላሁን ለመሮጥ ስለጓጓ እንጂ ሀቁ የበሪሁ ነው " ስትል ገልጻለች።

" ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚታዩ አንዳንድ ነገሮች ፤ ' ሀገር ቢቀይር በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ ' እየተባለ ነው  " ያለችው የፌዴሬሽን ፕሬዜዳንቷ " ይህ ሀገር መቀየር ግን ቀላል አይደለም ይሄ ልጅ ሀገር ቀይሮ የሌላ ሀገር ዜግነት ወስዶ መቼ ነው ያንን ሀገር የሚወክለው ፤ መቼ ነው ወርልድ አትሌቲክስ ላይ የሚሳተፈው ያን ነገር ከግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል። " ብላለች።

" እድል ስጡት የሚሉ አስተያየቶችም ሲሰጡ ነበር ፤ እድል እንሰጠዋለን እሱን የሚያስሮጠው ውጤቱ ነው እንጂ የደራርቱን ፍቃድ ሆነ የሌላ ሰው ፍቃድ አይፈልግም ፤ ስለዚህ ማንም ሰው በችሎታውና በሰዓቱ ነው እየተመረጠ ያለው ነገም እንደዛው ነው የሚሆነው ዛሬ ይሄን ተናገረ ተብሎ ደራርቱ እዛ ጋር ተፅእኖ የምታደርግበት ምክንያት የለም ፤ ስብዕናዬም አይደለም ፤ ወደፊትም አላደርግም " ስትል አስገዝባለች።

አትሌቱን የሌላ ሀገር ዜጋ ይሁን እያሉ የሚመክሩ ሰዎች " እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ወይ ? እንደ ዜጋ ለምን አናስብም ? ይሄ ነገር ሌላ ጊዜ ባይደገም ጥሩ ይመስለኛል ለአትሌቱም መታሰብ አለበት ዛሬ እንደሄደ አይደለም ዜግነት ውስዶ ለዛ ሀገር የሚሮጠው ያም አብሮ መታሰብ አለበት እንጂ እንዲሁ ሀገር ስለቀየረ ብቻ ዛሬ ቀይሮ ነገ ይሮጣል ማለት አይደለም ፤ መቼ እዛ ሀገር ሄዶ ዜግነት ቀይሮ መቼ ነው የሚሮጠው የሚለውን ማሰብ ያስፈልጋል ስትል ገልጻለች።

ረ/ኮ ደራርቱ ፤ " ጥልዬ ዛሬም ነገም እንወድሃለን የኢትዮጵያ ጅግና አትሌት ነህ ሀቋ ግን የበሪሁ ስለሆነች ነው በሪሁን ያስሮጥነው " ስትል ተናግራለች።

@tikvahethiopia
#Oromia

የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ።

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

Via https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
#ዘይት

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት 88.1 ቶን ወይም 4,405 ካርቶን ባላ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ  የሱፍ ዘይት  ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በአዳማ መገቢያና መውጫ ኬላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳወቀ።

በአዳማ መገቢያ መውጫ ኬላ በኩል በቀን 15/12/2015 በተደረገ ቁጥጥር 88.1 ቶን ወይም 4405 ካርቶን ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ የሱፍ ዘይት ፦

- የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ይህም ማለት (የተመረተበት በቀን 04/05/22 የሚያበቃበት ጊዜ ደግሞ በቀን 04/05/2023)፤
- በባለስልጣን መ/ቤቱ ያልተመዘገበ፤
- ከስሪት ሀገሩ የጤና ሰርተፍኬት ያልተያያዘ፤
- የምርቱ ገላጭ በድጋሚ የተጻፈ (relabeled ) የተደረገ፤
- የምርት መለያ ቁጥር (batch number ) የሌለው፤
- በምርት ማሸጊያው ላይ ምርቱ መያዝ ያለበትን ንጥረ ነገር አለመገጹ የተረጋገጠ ነው ተብሏል።

በተደረገው ፍተሻ የተገኙትን ጉድለቶች መሰረት በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ጥቅም ላይ እንዳይውል በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ ላይ ይህ ዜጎች ጋር ቢደረስ የጤና ጉዳት የሚያስከትል ዘይት ማን ሊያስገባው እንደነበር / ይዞት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ ግለሰብ ይኖር እንደሆነ የገለፀው ነገር የለም።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ማንኛውንም ምርት ስትገዙ እባክችሁ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት መሆን አለመሆኑን አጣሩ።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል ከሚጠበቁበት ውድድሮች አንዱ የሆነው የሴቶች ማራቶን ውድድር በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ውድድር በዓለም ሻምፒዮናዋ ጎይተይቶም ገብረስላሴ ፣ ፀሀይ ገመቹ ፣ አማኔ በሪሶ እና ያለምዘርፍ የኋላው ተወክላለች።

ሁሉም አትሌቶቻችን ከፊት መስመር ከሚገኙት መካከል ናቸው። ጥሩ መቁመናም ላይ ናቸው።

የውድድሩን መረጃዎች በ @tikvahethsport በኩል ይከታተሉ።

ፎቶ፦ Tikvah Ethiopia Sport (Hungary , Budapest)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሴቶች ማራቶት ሊጠናቀቅ ጥቂት ኪሎሜትር ቀርቶታል።

በውድድሩ ብርቱ ሆነው ወደፊት እገሰሱ ያሉት 3 አትሌቶች ሲሆኑ 3ቱም የሀገራችን ልጆች ናቸው።

በከፍተኛ ጥንካሬ ወደፊት እየመጣች የነበረችው ፀሀይ ገመቹ ውድድሩን አቋርጣለች። ውድድሩን ከማቋረጧ በፊት የህመም ስሜት ተሰምቷት ነበር።

ፀሀይ ውድድሩን እስክታቋርጥ ድረስ በቡድን ስራ ከ3ቱ የሀገሯ ልጆች ጋር ከፍተኛ ስራ ሰርታለች።

የኢትዮጵያ ልጆች በጥሩ የቡድን ስራ ከፊት ሆነው እየተፈራረቁ ውድድሩን እያስኬዱ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቀ 6 ኪሎሜትር ብቻ ቀርቷል። ፉክክሩ የሶስቱ ኢትዮጵያውያን ሆኗል። 🇪🇹 አማኔ በሪሶ 🇪🇹 ያለምዘርፍ የኋላው 🇪🇹 ጎተይቶም ገብረስላሴ አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ኢትዮጵያ በጀግና ሴት አትሌቶቿ ወርቅ ፣ ብር፣ ነሃስ ማግኘቷ የማይቀር ነው። @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቅ ጥቂት ኪሎሜትር ብቻ ቀርቷል። አንደኛ ደረጃ የያዘችው አትሌት 40 ኪሎ ሜትር አጠናቃለች።

ውድድሩን አማኔ በሪሶ እየመራች ሲሆን ጎተይቶም ገብረስላሴ ሁለተኛ ነች።

1. አማኔ በሪሶ
2. ጎተይቶም ገብረስላሴ

ያለምዘርፍ የኃላው በሞሮኮ አትሌት ተቀድማ 4ኛ ደረጃ ላይ ሆናለች።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

አማኔ በሪሶ #ወርቅ አመጣች ❤️

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ጎተይቶም ገብረስላሴ #ብር አመጣች❤️

@tikvahethiopia