TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NationalExam

ከነገ ሐምሌ 19 ጀምሮ በሚጀምረው ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ከፈተና ደንብ ውጭ ማንኛውም እንቅስቃሴ ካደረጉ / ጥፋት ከፈፀሙ ውጤታቸው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ #ሊሰረዝባቸው ይችላል።

ፈተና በከፊል የሚያሰርዙ ጥፋቶችን አጥፍተው የተገኙ ተፈታኞች ጥፋቱ የተመዘገበባቸው ፈተና ውጤት ብቻ ነው የሚሰረዝባቸው።

ተፈታኞች በፈተናው ወቅት የፈፀሙት ጥፋት ሙሉ በሙሉ ፈተናቸውን እንዲያሰርዝ የሚያደርግ ከሆነ  ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ ይሰረዝባቸዋል።

ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ።

@tikvahethiopia
" እንደ አስፈላጊነቱ የሚታጠፉና የሚዘጉ የትምህርት ክፍሎች፣ ፕሮግራሞች ሊኖሩ ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ በቀጣዩ ዓመት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ይደረገል ብሏል።

ይህን ያፋ ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በሰጡት መግለጫ ነው።

ሚኒስትር ዴኤታው ፤ መንግስት በ2014 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት እንዲለዩ በማድረግ ወደ ተለዩባቸው የትምህርት መስኮች የማሸጋገር ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር አንስተዋል።

በዚህ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሻለ አፈጻጸም አሳይተዋል ብለዋል።

በ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለዩበት ተልዕኮና የትምህርት መስክ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

የልየታ ስራው ከባቢያዊ ጸጋዎችን የማሳደግ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች የሚስተዋለውን የትምህርት ክፍሎች መደጋገምና የፕሮግራሞች መደራረብን የሚያስቀር መሆኑን ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል።

በዋናነት የሚከፈቱ የትምህርት መስኮችና ፕሮግራሞች አገራዊ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በተልዕኮና በትኩረት ሲለዩ እንደ አስፈላጊነቱ የሚታጠፉና የሚዘጉ የትምህርት ክፍሎች፣ ፕሮግራሞች ሊኖሩ ይችላሉ ሲሉ ጠቁመዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ከመማር ማስተማር ሂደት ወደ ኋላ የቀሩ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ወደ ልየታው እንደሚገቡ ገልጸዋል።

ለዚህም የማካካሻና የማስተካከያ ስራዎች በልዩ ሁኔታ እንደሚከናወንላቸው አመልክተው ልየታው ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ሚኒስቴሩ እየሰራ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ከጊዜው ጋር እየተሽቀዳደመ ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመነ የመጣው አዋሽ ባንክ ት/ቤቶች ትውልድን ለመቅረፅ ያለባቸው ትልቅ ሃላፊነት በመረዳትና የትምህርት ጥራትን ለማሳካት በማሰብ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ሥርዓት ወይም የኢ-ስኩል ሲስተም ቴክኖሎጂን አቀረበልዎ!
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!

Learn More- https://eschool.awashbank.com/
#AwashBank #Awash #ESchool #Management #System #Ethiopia #ኢትዮጵያ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 https://t.iss.one/awash_bank_official
217 ፍሬ አልባሳትን በ40 ሚሊየን 67 ሺህ 748 ብር የገዙት አመራር እና ሰራተኞች ላይ የሙስና ተከስ ተመሰረተ።

በሀገራችን ብዙ የሙስና ወንጀል ክስ ሰምተናል።  በሰማናቸው በብዙዎቹ የሙስና ክሶች አፋችንን ይዘን ተገርመናል፤ ደንግጠናል።

ዛሬም በርካቶችን ያስገረመ አንድ የሙስና ወንጀል ክስ ተሰምቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው . . .

የሙስና ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፦

1ኛ. የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ሰለሞን ፍስሃ፣
2ኛ. የተቋሙ የመንግስት የግዢ ዳይሬክተር ግሩም ወልዴ፣
3ኛ. የኮሚሽኑ የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ደረጄ ተፈራ፣ 
4ኛ. የኮሚሽኑ የሎጀስቲክስ ምዝገባና ቁጥጥር ባለሙያ ወንድሜነህ ምስጋናው፣
5ኛ. የአደጋ ስጋት ትግበራ ቡድን መሪ እዮብ ታደሰ ካሳ ፣
6ኛ. በኮሚሽኑ የህክምና ባለሙያዋ ሲስተር  አልማዝ ጌቶ፣
7ኛ. የአደጋ መረጃ ሀርድ ዌርና ሶፍትዌር ባለሙያ መስፍን ለገሰ 
8ኛ. ነጋዴ የሆኑት ንጉስ አማን ይባላሉ።

የቀረበባቸው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ከሆነ ፤ በሰኔ ወር  በ2014 ዓ.ም በጀት አመት ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች የግዢ ጨረታ ሂደት ውስጥ ይሳተፋሉ።

ግለሰቦቹ በሂደቱ በስውር በመመሳጠር በወቅቱ በተደረገ የገበያ ዳሰሳ ጥናት የአልባሳቱ ዋጋ 46 ሺህ 923 መሆኑ የተረጋገጠ ተከሳሹቹ ግን " ብልዶዘር " የተሰኘ የእሳት አደጋ መከላከያ ልብስን  ከፍተኛ በሆነ ዋጋ በፍሬ 184 ሺህ 644 ብር ከ8ኛ ተከሳሽ ተጫራች ድርጅት ግዢ እንዲፈጸም ያፀድቃሉ።

አጠቃላይ 217 ፍሬ አልባሳትን በ40 ሚሊየን 67 ሺህ 748 ብር በመግዛት በመንግስት ላይ በልዩነት 29 ሚሊየን 885 ሺህ 441 ብር ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግም በተከሳሾቹ ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ የከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

ክስ የተመሰረተባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ከተከሳሾቹ መካከል 1ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ያልቀረቡ ሲሆን ቀሪ ስድስት ተከሳሾች ግን ክሱ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

መረጃው ከጋዜጠኛ ታሪክ_አዲኛ / ኤፍቢሲ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
@berhanbanksc

የወላጆችን ጊዜ ቆጥቦ፤ ተማሪዎችን ከእንግልት ገላግሎ፤ የትምህርት ቤቶችን አሰራር ያዘመነውን ዘመናዊ ፤ቀላል እና ቀልጣፋ የብርሃን ስኩል ፔይ (school pay) አገልግሎት ይጠቀሙ!

#schoolpay #berhanbank #bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia

#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፦ @berhanbanksc
#MyWish

አስተማማኝ የሆነውንና ቱርክ ሰራሹን ኢሳን ሲልድ ባትሪን በተለያዩ አማራጮች ማለትም በ12V35AH፣ በ12V45AH፣ በ12V55AH፣ በ12V60AH፣ በ12V70AH፣ በ12V90AH፣ በ12V100AH፣በ12V120AH እና በ12V150AH በጅምላና በችርቻሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
0910041280  0911135133  0921612272  0911159234   0984733988  0941473413
ዋና መስሪያ ቤት፡ ሀይሌ ጋርመንት ወደለቡ መብራት በሚወስደው መንገድ ቅርንጫፍ፡ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ አጠገብ
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ 
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.iss.one/MYWISHENT
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

በሁለት ዙር የሚሰጠው ፈተና ዛሬ በማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ተጀምሯል።

ዛሬ በጥዋቱ መርሀ ግብር የእንግሊዝኛ ፈተና እየወሰዱ ሲሆን በከሰዓቱ መርሃግብር የሒሳብ ፈተና ይወስዳሉ።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና እስከ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
ቴሌግራም ተገደበ።

በኢትዮጵያ የቴሌግራም መተግበሪያ በድጋሚ ተገድቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ማረጋገጥ እንደቻለው አገልግሎቱ ከጥዋት አንስቶ ተገድቧል።

በጉዳዩ ላይ በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም እንደታየው የቴሌግራም መገደብ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጀመር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።

ባለፈው ዓመት ፈተናው ሲሰጥ ተመሳሳይ እርምጃዎች እንደነበሩ አይዘነጋም።

ምንም እንኳን " የቴሌግራም " አገልግሎት ቢገደብም ሌሎች እንደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ትዊተር የመሳሰሉ መተግበሪያዎች ያለ ገደብ እየሰሩ ናቸው።

ቴሌግራም መተግበሪያ ከየካቲት ወር አንስቶ ተገድቦ በቅርቡ ገደቡ ከተነሳላቸው መተግበሪያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethiopia