TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መነሻዬ

ሁሉም አይነት ትምህርታዊ መጫወቻዎችን በየትኛውም የእድሜ ክልል ላሉ ልጆችዎ
የሚሸምቱበት ምርጡ ስፍራ

አድራሻ፦
📍ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር 3ኛ ፎቅ
ይምጡ በመነሻዬ የልጅዎን መነሻ ያቅልሉ!

ይደውሉ 0989939393 ወይም 0930323334

Telegram > https://t.iss.one/meneshayeofficial
Tiktok > https://tiktok.com/@meneshayeofficial
Facebook > https://facebook.com/@meneshayeofficial
#AdigratUniversity

በጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስራ ዳግም ለማስቀጠል ሲደራ የነበረው ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎቹን በሙሉ (የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ጨምሮ) ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 01/2015 ዓ.ም እንደሚቀበል አሳውቋል።

በመሆኑም መደበኛ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በዋናው ግቢ በመገኘት እንዲመዘገሹ ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተማሪ መታወቂያ ካርድ
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላና ትራስ ጨርቅ
- ጉርድ ፎቶግራፍ (4)

የመደበኛ መርሃ ግብር ላልሆኑ ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው ጥሪ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በሸገር ከተማ ፤ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ/ም በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ " 3ኛ ቡራዩ " በሚባል ስፍራ ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ነጋሴ ከበደ የተባለችው ተጠርጣሪ መያዟ ተገልጿል። ተጠርጣሪዋ የእንጀራ ልጆቿ የሆኑትን ሁለቱን ሕጻናት አንገታቸውን ቀልታ ፣ በተኙበት ብርድ ልብስ አልብሳ እሳት ለኩሳባቸው አምልጣ እንደነበርና ፍለጋው እየተካሄደ እንደነበር…
" የእኔ ልጆች እንደ ጧፍ በርተው ለሌሎች ብርሃን መሆን ከቻሉ ተመልሼ የማዝንበት ምንም ምክንያት የለኝም " - አባት ጌታሁን በላቻ

በኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ በምትገኘው ሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከአራት ወራት በፊት ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው የእንጀራ እናት ነጋሴ ከበደ የሞት ፍርድ ተፈረደባት።

ጥፋተኛ ሆና በተገኘችው ግለሰብ ላይ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ሐምሌ 19/ 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው።

የቡራዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት እና ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ፤ "  እርሷን እና መሰሎቿን የሚያስተምር የሞት ቅጣት ውሳኔ ፍርድ ቤቱ በይኖባታል።  " ብለዋል።

የሟች ልጆች አባት አቶ ጌታሁን ባልቻ ምን አሉ ?

" አፈጻጸሙን ለሕግ አካላት እንተወዋለን። ለእኔ እንኳን ባይሆን ለሌሎች ህጻናት እና ለቀሪው ቤተሰብ፣ ይህ የተሰጠው ፍትህ ብርሃን ነው።

ብይኑ ለሌሎች ጥሩ ማስተማሪያ ይሆናል።

የተላለፈው የፍርድ ውሳኔ ያላጠበቁት ነበር።

ከበፊት ጀምሮ የነበረው የሕግ መላላት እንዳለ ሆኖ በዚህች ሦስት ወራት ውስጥ የፍትህ ሁኔታው መድረሱ ለእኔ ደስ ብሎኛል።

ሌሎች ህጻናት እንቅልፍ የሚያገኙበት፣ አሁን ትንሽ እፎይ የሚሉበት ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ።

የእኔ ልጆች እንደ ጧፍ በርተው ለሌሎች ብርሃን መሆን ከቻሉ ተመልሼ የማዝንበት ምንም ምክንያት የለኝም።

የውሳኔው ፍጥነት ደስ የሚል ነው። የሚመለከታቸው አካላትም ርብርብ አድርገውበታል።

አፈጻጸሙ ግን ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቃለሁ። "

የሞት ፍርድ መፈረዱ ብቻ ሳይሆን አፈጻጸሙ ያላለቀ ከዚህ በፊት ውሳኔዎችንም እየጠቀሱ ጥርጣሬያቸውን ስለሚያነሱ ግለሰቦች አሉ።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እና ሕጉን ለሕዝቡ ተዓማኒ እንዲያደርገው አፈጻጸሙ መሆኑንም አጽንኦት በመስጠት ያስረዳሉ።

ከዚህ ቀደም በሁለት ህጻናት ግድያ አንዲት ግለሰብ የሞት ፍርድ የተፈረደባት ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከማይደረግባቸው አገሮች አንዷ ናት።

ማስታወሻ ፦ ነጋሴ ከበደ ብሩ የተባለችው እንጀራ እናት የሁለት ህጻናትን አንገት ቀልታ በተኙበት ብርድ ልብስ በማልበስ ቤቱ ላይ እሳት ለኩሳባቸው አምልጣለች የተባለው ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም. ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ነበር።

በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ልጆች አንደኛው የ13 ዓመት ወንድ ሲሆን፣ ሌላኛዋ ደግሞ የ4 ዓመት ተኩል ሴት ናቸው።

ሁለቱም አንገታቸው ተቀልቶ መገደላቸውን ፖሊስ በወቅቱ አሳውቆ ነበር።

Via BBC AMAHARIC

@tikvahethiopia
#Russia #Africa

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ፤ በሁለተኛው የአፍሪካ ራሺያ የጋር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሩስያ፤ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ይገኛል።

ልዑካን ቡድኑ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በመገናኘት፣ በሁለቱ አገራት ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይም መክሯል።

ነገ ከሚጀመረው የሩስያ - አፍሪካ የጋራ ጉባኤ ጎን ለጎን ኢትዮጵያና ሩስያ 15 የሚደርሱ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ ገልጸውላቸዋል።

የትብብር ስምምነት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ፣ ኢትዮጵያ ከአቶሚክ ኃይል ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና ለመጠቀም የሚያስችላት የትብብር ፍኖተ ካርታ እንደሆነ ፕሬዝዳንት ፑቲን ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ አገራት በሳይበር ደህንነትና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ ለመተባበር ስምምነት እንደሚፈራረሙ ታውቋል።

" በሩስያ ቆይታዎ ወቅት የትብብር ስምምነት የምናደርግባቸውን የሰነዶች ፓኬጅ አዘጋጅተናል፤ ከነዚህም መካከል የመረጃ ደህንነት ስምምነት ፣ በአየር ትራፊክ ፣ በኢንፎርሜሽንና የግንኙነት ቴክኖሎጂዎች መስክ የመግባቢያ ሰነድ ፣ የአቶሚክ ኢነርጂን ለመጠቀም የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ፣ በጉምሩክ አገልግሎቶች ፕሮቶኮልና ሌሎች " ሲሉ ፕሬዚደንት ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ተናግርዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ በበኩላቸው ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

" ታሪካዊ ትሥሥራችንን መሠረት አድርገን ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ኢኮኖሚያዊ ትብብራችንን ማሳደግ እንቀጥላለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
" ችግር አላየሁበትም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ከአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ሲነሳ ለነበረው ቅሬታ " ገምግሜዋለሁ ምንም ችግር አላገኘሁበትም " ሲል ምላሽ ሰጠ።

የአካውንቲንግ እና የፋይናንስ የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ተፈታኞች እንዲሁም የትምህርት ክፍላቸው እንዲሁም ኮሌጆች ፈተናው ዳግም እንዲገመገም ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

የቀረበው ቅሬታ ፈተናው ከተዘጋጀው ብሉፕሪንት ጋር ተያያዥነት እንደሌለው፣ ይሸፍናል ከተባለው 15 ኮርስ የሸፈነው ከ4 የሚበልጥ እንዳልሆነ ፣ የመጡት ጥያቄዎችም በዲግሪ ደረጀ ለመረዳት የማይቻሉ ፣ ለፈተናው የተሰጠው ሰዓትም ከጥያቄው ጋር የማይገናኛ መሆኑ ይጠቀሳሉ።

ለዚህም ትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲያደርግ እና ፈተናውን እንዲገመግመው ተማሪውን የሚመጥን ፈተና ድጋሚ አዘጋጅቶ በፍጥነት እንዲፈትን ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ ስለተነሳው ቅሬታ እንደሚያውቅ ገልጾ ፈተናውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መገምገሙን ነገር ግን በፈተናው ይዘት ላይም ሆነ አቀራረብ ላይ ችግር እንዳላየበት አሳውቋል።

#ማስታወሻ፦ ከፈተናው ጋር በተያያዘ በተማሪዎች እንዲሁም በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍሎች / ኮሌጆች የቀረቡ ቅሬታዎች ፦
https://t.iss.one/tikvahethiopia/79870?single
https://t.iss.one/TikvahUniversity/7740?single
https://t.iss.one/TikvahUniversity/7739?single

@tikvahethiopia
#CBE
ግብርዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዴት ይከፍላሉ?
=======================
ለአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ሶማሌ ክልል ግብር ከፋዮች

ከግብር ሰብሳቢው ተቋም
• የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
• የገንዘብ መጠን እና
• የክፍያ ማዘዣ ቁጥር የያዘ መልእክት ሲደርስዎት

ወደ *889# በመደወል ወይም የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎን በመጠቀም ቅደም ተከተሉን ተከትለው በቀላሉ ይክፈሉ፡፡
***********
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፃችንን ይከተሉ፡
Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
#ሳፋሪኮም

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#UnlimitedSafaricom
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ምዕራባውያን በአንድ በኩል የእህልና የማዳበሪያ አቅርቦታችን እያስተጓጎሉ ነው። በሌላ በኩል በዓለም የምግብ ገበያ ለተፈጠረው ቀውስ ግብዝ ሆነው እኛን ይከሱናል " - ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ኤርትራ እና ሶማሊያን ጨምሮ ለስድስት የአፍሪካ አገሮች ስንዴ በነጻ ለማቅረብ ቃል ገቡ።

ፕሬዝደንቱ ይኸን ቃል የገቡት የአፍሪካ - ሩሲያ ጉባኤ በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ሲጀመር ባሰሙት ንግግር ላይ ነው።

ፑቲን ፤  " በመጪዎቹ ሦስት እና አራት ወራት ከ25,000 እስከ 50,000 ቶን እህል በነጻ ለቡርኪና ፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ኤርትራ ለማቅረብ ዝግጁ እንሆናለን " ብለዋል።

የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት የዩክሬን የእህል ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ ይፈቅድ የነበረው ሥምምነት እንዲያበቃ በመወሰኑ አሜሪካን ጨምሮ ከምዕራባውያን ብርቱ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በቱርክዬ አደራዳሪነት በተፈረመው ሥምምነት መሠረት 32.9 ሚሊዮን ቶን የምግብ እህል ከዩክሬን የእህል ጎተራዎች ለዓለም ገበያ ቀርቧል።

የሩሲያን ውሳኔ ኃላፊነት የጎደለው ሲሉ የሚተቹ የምዕራቡ ዓለም ፖለቲከኞች በደሐ አገሮች የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለረሐብ ይጋለጣሉ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ግን በሴንት ፒተርስበርግ በመካሔድ ላይ በሚገኘው ስብሰባ በሥምምነቱ ከዓለም ገበያ ከቀረበው እህል ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ከፍተኛ ገቢ ወይም ከአማካኝ በላይ ገቢ ላላቸው አገራት እንደቀረበ ተናግረዋል። 

" ምዕራባውያን አገሮች በአንድ በኩል የእህል እና የማዳበሪያ አቅርቦታችን እያስተጓጎሉ ነው። በሌላ በኩል አሁን በዓለም የምግብ ገበያ ለተፈጠረው ቀውስ ግብዝ ሆነው እኛን ይከሱናል" ሲሉ ተደምጠዋል።

በሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው የሩስያ አፍሪካ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምረ የሌሎችም ሀገራት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ፕሬዝደንት ፑቲን ትላንት ረቡዕ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከግብጽ ፕሬዝደንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
" ሁላችሁም የውጭ አገራት ጣልቃ እንዳትገቡ " - ኮሎኔል ሜጀር አማዱ

በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥት ሲደረግ በተደጋጋሚ ተሰምቷል።

አሁን ደግሞ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒጀር #ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት አውጀዋል።

ወታደሮሹ ሕገ-መንግሥቱን መበተናቸውን፤ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ለጊዜው ሥራ ማቆማቸውን እና የሃገሪቱ ድንበሮች መዘጋታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከረቡዕ ጀምሮ የኒጀር ፕሬዝደንት ሞሐመድ ባዙም በወታደሮች ቁጥጥር ሥር እንዳሉ ተነግሯል።

ተመድ እንዲሁም አሜሪካ ለፕሬዝደንቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

ረቡዕ ዕለት ዘጠኝ የወታደር መለዮ በለበሱ ሰዎች ተከበው በቴሌቪዥን መስኮት መግለጫ የሰጡት ኮሎኔል ሜጀር አማዱ አብድራማኔ ፤ " እኛ የመከላከያና የፀጥታ ኃይሎች የምታውቁት መንግሥት ከሥልጣን አውርደናል " ብለዋል።

የሃገሪቱ ሁሉም ተቋማት ለጊዜ ሥራ እንደሚያቆሙ የገለጹት ኮሎኔሉ ሚኒስትሮች የቀን ተቀን ሥራውን እንደሚመሩ ገልጠዋል።

" ሁሉም የውጭ አገራት ጣልቃ እንዳይገቡ እንጠይቃለን። ሁኔታዎች እስኪረጋጉ በምድርም ሆነ በአየር ድንበራችንን ዘግተናል " ብለዋል።

አክለው ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ ሰዓት እላፊ መታወጁንም ማሳወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኒጀር ጎረቤት የሆኑት ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ በቅርብ ዓመታት በተመሳሳይ በመፈንቅለ መንግሥት ምክንያት ታምሰው እንደነበር አይዘነጋም። #ቢቢሲ

@tikvahethiopia