TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የድጋሜ ህዝበ ውሳኔ . . .

ሰኞ በወላይታ ዞን የሚገኙ የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ሥራ ዝግ እንዲደሆኑ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ያስፈፅመል።

ይህንን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም መሠረት በዕለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉ እንዲሁም የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን ለማስቻል፤ የሚከተሉት ተግባራት ተፈጻሚ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የሥነ‐ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

እነዚህም ፦

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በዞኑ የሚገኙ የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ. ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣  

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጠት ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በዞኑ የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ. ም.  ዝግ እንዲያደርጉ፣

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ማለትም ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት … ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን የሚችሉ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም በዞኑ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እንዲሁም እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ አበረታቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የድጋሜ ህዝበ ውሳኔ . . . ሰኞ በወላይታ ዞን የሚገኙ የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ሥራ ዝግ እንዲደሆኑ ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ያስፈፅመል። ይህንን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መሠረት በዕለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉ እንዲሁም የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም…
የዎላይታ ዞን ሪፈረንደም . . .

ሁለት ፓርቲዎች ሰኞ በዎላይታ ዞን የሚካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ " እውቅና አንሰጥም " አሉ።

ሁለት ፓርቲዎች የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) እና የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ) የሰኞው ሕዝበ ውሳኔ ፍትሃዊነት የሌለው እንደሆነ በመግለፅ " እውቅና አንሰጥም " ብለዋል።

የዎሕዴግ ስራ አስፈፃሚ አባል እንደሆኑ የተገለፁት አቶ ሚልኪያስ ሳንጣ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ የሰኞው ህዝበ ውሳኔ " አማራጭ የሌለው ፤ የዎላይታ ህዝብን ድምፅ ያላከበረ ፣ የዎላይታ ህዝብን የዘመናት ጥያቄ ያላከበረ ፣ የራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግስታዊ መብትን ያላከበረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፓርቲያቸው ህዝበ ውሳኔውን " ህዝበ ውሳኔ ነው ብሎ እንደማይቀበል ገልጸው እስካሁን ሲያካሂዱት የነበረውን ሰላማዊ ትግል በመቀጠል  የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ህጋዊና ሰላማዊ ፣ ዴሞክራሲያዊ ትግል እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

የዎብን ፀሀፊ አቶ ጎበዜ አበራ በበኩላቸው " ' የዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ' የሚል አማራጭ ባልቀረበበት ሌሎች ስያሜዎች ተሰጥቶት የሚካሄድ ፣ አማራጭ በሌለበት ህዝበ ውሳኔ ብሎ ማምጣት በህዝብ ህልውና ላይ መቀለድ ነው " ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ፓርቲያቸው ለሕዝበ ውሳኔው / ሪፈረንደሙ እውቅና እንደማይሰጥ ፤ እንዳልተደረገም እንደሚቆጥረው ገለፀው " ኢፍትሃዊ ፣ ኢዴሞክራሲያዊ፣ ኢህገመንግስታዊ ነው " ያሉት አካሄድ እንዲስተካከል ለማድረግ በሰላማዊ ፣ ዴሞክራሲያዊና በህጋዊ መንገድ እንደሚታገሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#MoE #Tigray

የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ለኢፕድ ከሰጡት ቃል ፦

" ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል (ኣክሱም፣ ራያ፣ መቐለ፣ ዓዲግራት) ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ መቆየታቸውን ይታወሳል።

አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት #ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ይሰጧቸዋል። "

@tikvahethiopia
" የማህበራዊ ሚዲያው ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል " - ቮልከር ተርክ

ነገ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 የዓለም አቀፍ የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን ይከበራል።

ቀኑን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የጥላቻ ንግግርና አደገኛ መልዕክቶችን " ሰፊ ስርጭት " መከላከልን ጨምሮ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ጥረቶች እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ቀኑን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቮልከር ተርክ ፦

" ትልቅ ግብዓት ያለው ጥረት ዓለምን ከመከራ ሊያጸዳው ይችላል።

የጥላቻ መስፋፋት መለያየትን ለመዝራት፣ ለማፍረስ እና ከትክክለኛ ጉዳዮች ለማዘናጋት በሚፈልጉ አካላት እንደሚሰራጭ እናውቃለን።

የማህበራዊ ሚዲያው በተለይም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል።

ጥላቻ ትምክህተኝነትን ፣ አድልዎንና አመጽን ያነሳሳል፤ ዓለማችንን ከጥላቻ የሚያጸዳው ጥይት፣ ማብሪያ ማጥፊያ የለውም።ነገር ግን የታለሙ እርምጃዎች ላይ ቢሰራ የጥላቻ ንግግሮችን ስርጭት መገደብ እና የሚያሰራጩትን ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል።

በተጨማሪ ኩባንያዎች የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ለሚሰሩት እና ላልሰሩ ነገር ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ጥላቻን የሚያቋርጡ አውታረ መረቦችን መገንባት እና ድምጾችን ማጉላት አለብን። ለአብነትም የኃይማኖት መሪዎች ለጥላቻ እና ለአመጽ ማነሳሳት ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ አንዱ ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ በጋዜጠኞች እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ያለአግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉት ከጥላቻ ንግግር ጋር የተገናኙ ህጎች መስፋፋታቸውም የጥላቻ ንግግርን ከማስፋፋት ባልተናነሰ ጉዳት ያለው ነው። "

Credit : #አልአይን

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የ2023 የ " ሶልቭ ኢት " የፈጠራ ውድድር ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።

በ6 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ደሴ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር እና ድሬዳዋ ውድድሩ ይካሄዳል።

በዚህ አመት፣ የወጣቶችን የፈጠራ ሃሳቦች ወደ መሰረታዊ መፍትሄዎች ለመቀየር እንዲረዳ የ1,000,000 ብር ድጋፍ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ወጣቶች 1 ሚሊዮን ብር የሥራ መነሻ (Seed Funding) ተሸላሚ በሚያደርገው የ " Solve IT 2023 " የፈጠራ ውድድር እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

የፈጠራ ሃሳብ ያላችሁ ወጣቶች በዚህ https://solveit-et.com  መመዝገብ ትችላላችሁ።

ለበለጠ መረጃ ➭
Telegram Bot: @solveit_et_bot
Email: [email protected]
Phone No.: 0991440049

@tikvahuniversity
#አማራ_ባንክ

እንኳን ደስ አላችሁ! አማራ ባንክ አንድ ዓመት ሞላው! በዚህ አንደኛ ዓመት በዓላችን በውስጥ አቅም የበለጸገውን የሞባይል ባንክ መተግበሪያ ወደ እናንተ ስናቀርብ በደስታ ነው፥ ABa Mobile Banking ከፕሌይ ስቶር በማውረድ የባንካችንን ዲጂታል ዓለም ይቀላቀሉ።

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች
Website: https://amharabank.com.et/
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: https://t.iss.one/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g

#አማራባንክ #AmharaBank
" #ኢትዮጵያን በማስጠራቴ ትልቅ ክብር ይሰማኛል " - የወጣቱ የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ ትንሳኤ አለማየሁ

#ኢትዮጵያዊው የሕዋ ሳይንስ ተመራማሪ ወጣት ትንሳኤ አለማየሁ ዓለም አቀፉ የአስትሮኖቲካል ፌደሬሽን የ2023 ወጣት የህዋ መሪዎች ብሎ ከሰየማቸው አምስት ተመራማሪዎች አንዱ ሆኗል።

ፌደሬሽኑ ስያሜውን እውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለሌሎች ወጣቶች በማጋራትና ማህበረሰብ በመድረስ እንዲሁም በትምህርት እና ምርምር ለአስትሮኖቲክ መስክ አበርክቶ ላደረጉ ወጣቶች የሚሰጠው ዕውቅና ነው።

ፌደሬሽኑ ሽልማቱን በባኩ አዘርባጃን በመስከረም 2016 ዓ.ም በሚደረገው በ74ኛው የዓለም አቀፉ የአስትሮኖቲካል ኮንግረስ ለወጣት ተመራማሪዎቹ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በዓለም አቀፉ ፌደሬሽን በወጣቶች ዘርፍ የሚሰጠውን ትልቁን ሽልማት በማግኘቱ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማው ትንሳኤ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።

ሽልማቱን በማግኘት ኢትዮጵያን በማስጠራቱ ትልቅ ክብር እንደሚሰማውም ገልጿል።

በሜካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ከ #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ ያገኘው ትንሳኤ አለማየሁ ፤ ለህዋ ሳይንስ ባለው ራዕይ እና ለዘርፉ ላደረገው አበርክቶ በርካታ ሽልማቶችን አጊኝቷል። 

ካገኛቸው ሽልማቶች ውስጥ ፦

- እ.ኤ.አ. በ2022 ከዓለም አቀፉ የጠፈር ተመራማሪዎች ፌደሬሽን (አይኤኤፍ) የተበረከተውን ተስፋ የተጣለባቸው ስፔስ መሪዎች ሽልማትን፤

- ከ30 አመት በታች የአፍሪካ ስፔስ ኢንዱስትሪ ሽልማት፤

- በ2021 ከስፔስ ኢን አፍሪካ እና ከSGAC የግሎባል ግራንት ፕሮግራም ሽልማትን፤

- በ2019 ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የወጣት ሕዋ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሽልማቶችን እና እውቅናዎችን አግኝቷል።

ወጣቱ ተመራማሪ አሁን ላይ የዓለም ዐቀፉ የህዋ ጄነሬሽን አማካሪ ም/ቤት (SGAC) የአፍሪካ ቀጣናዊ አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

https://www.iafastro.org/news/the-iaf-is-proud-to-introduce-the-2023-iaf-young-space-leaders.html

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
" የማህበራዊ ሚዲያው ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል " - ቮልከር ተርክ ነገ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 የዓለም አቀፍ የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን ይከበራል። ቀኑን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የጥላቻ ንግግርና አደገኛ መልዕክቶችን " ሰፊ ስርጭት " መከላከልን ጨምሮ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዓለም…
#NoToHate

ዛሬ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 በዓለም አቀፍ ደረጃ  የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን እየተከበረ ይገኛል።

በተለይም በሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያዎች በፖለቲከኞች ፣ በታዋቂ ግለሰቦች፣ በጋዜጠኞች፣ በሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች ግጭቶች እንዲባባሱ  ፣ ሰዎች በማንነታቸው እንዲጠቁ፣ እንዲፈናቀሉ፣ እንዲሰደዱ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ከምንም በላይ የጥላቻ ንግግሮች በሌሎች በግለሰቦች ላይ ጥላቻ እንዲሰርፅ፣ ቂም እና በቀል እንዲያድር  እንዲሁም የማህበራዊ ህይወት ላይ መሸርሸር እንዲመጣ አድርጓል።

እንደ አንደ ሀገር ዜጋ በማንኛውም ጉዳይ ሀሳባችንን ስንገልፅ ከጥላቻ ቃላት በራቀ፣ በፍቅር፣ ለመግባባት፣ ለመተማመን በሚያግዙ ቃላት ሊሆን ይገባል።

ሁሉም ሰው የእኛን አይነት አመለካከት እንደሌለው በመገንዘብ አንድን ሀሳብ ስንቃወም ወይም በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ስንጠት ከጥላቻ በራቀ ሁኔታ መሆን አለበት። ይህን ስናደርግ አንድነት ይጠነክራል፣ የጋራ ችግሮች መፍትሄ ያገኛሉ፣ ሀገራዊ ፍቅር ይዳብራል፣ የማንግባባቸው ጉዳዮችን እየቀነሱ ይመጣሉ።

እያንዳንዳችን የጥላቻ ንግግሮችን ለመከላከል እንችላለን ፦

💗 የመቻቻል መልዕክቶችን በማካፈል የጥላቻ ንግግሮችን እንዋጋ።

💗በጥላቻ ንግግር የተጎዱ ሰዎችን እንደግፍ።

💗 በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጥላቻ ንግግር ስንመለከት ሪፖርት እናድርግ።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ እናተ ላይ ወይም ቤተሰቦቻችሁ ላይ የደረሰባችሁ ነገር ካለ ፤ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ የምትታዘቡትን በ @tikvah_eth_BOT ላይ አጋሩን

የጥላቻ ንግግር ፦ ማለት የግhሰቦች ወይም የቡድኖች ሀይማኖት ፣ ብሔር ፣ ዘር ወይም አካላዊ ሁኔታ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ንግግር ወይም የሚዲያ ውጤት ነው ፤ ይህም በሁለት ግለሰቦች መካከል ካለ የቃላት ልውውጥ ጀምሮ በትልልቅ መገናኛ ብዙሃ እስከሚሰራጭ ይዘት ሊዘልቅ ይችላል።

የጥላቻ ንግግር ይገድላል ፤ ከጥላቻ ንግግር እንቆጠብ !
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NoToHate ዛሬ እሁድ ሰኔ 11 / June 18 በዓለም አቀፍ ደረጃ  የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን እየተከበረ ይገኛል። በተለይም በሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያዎች በፖለቲከኞች ፣ በታዋቂ ግለሰቦች፣ በጋዜጠኞች፣ በሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች ግጭቶች እንዲባባሱ  ፣ ሰዎች በማንነታቸው እንዲጠቁ፣ እንዲፈናቀሉ፣ እንዲሰደዱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ከምንም በላይ የጥላቻ…
" ቃላት እንደሚያድኑት፤ እንደሚያፅናኑት ሁሉ ቃላት ለማጥፋትም ስሜትን መቀስቀስ ይችላሉ " - ዶክተር ፀደይ ወንድሙ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ #በ2011 ዓ.ም. ላይ እጅግ እየተባባሰ የመጣው የ " ጥላቻ ንግግር " በሀገሪቱ ላይ ስለሚያመጣው #የከፋ_ውድመት በመረዳት ፦
- በኦሮሚያ ፣
- በአማራ ፣
- በትግራይ ፣
- በሲዳማ፣
- በደቡብ ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ !! / STOP HATE SPEECH  " በሚል ዘመቻ አካሂዶ ነበር።

በወቅቱ ወደ ትግራይ ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ባደረጉት የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ጉዞ እንዲሁም በዛው በተቋሙ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ  የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህርት ዶ/ር ፀደይ ወንድሙ ንግግር አድርገው ነበር።

ዶክተር ፀደይ ወንድሙ  ፤ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መድረክ ላይ ፦

"... የጥላቻ ሀሳብ ንግግር መሆን የሚጀምረው በተለያዩ ሚዲያዎች መሰራጨት ሲጀምር ነው።

ንግግሩ ቀስ እያለ #ወደመጠፋፋት ደረጃ ያመራል። የቃላት ጉልበት የሚገለጠውም እዚህ ደረጃ ላይ ነው።

ቃላት እንደሚያድኑት፤ እንደሚያፅናኑት ሁሉ ቃላት ለማጥፋትም ስሜትን መቀስቀስ ይችላሉ።

ስለዚህ በእኔ እሳቤ መዋጋትና ማስቆም ካለብን የጥላቻን ሀሳብ ነው፤ የጥላቻ ንግግር ተብሰልስሎ ወደ ውጪ የወጣ የጥላቻ ሀሳብ መገለጫ ነው " ብለው ነበር።

(2011 ዓ/ም)

@tikvahethiopia