(ኢትዮ ቴሌኮም)
ቢዝነስዎን ከጊዜው ጋር ለማራመድ ኢንተርኔት፤ ስራዎን ለማሳለጥ ፈጣን ግንኙነት የግድ ሆኗል!
እኛም ለመፍትሄው ከጎንዎ ሁሌም አለን በገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እስከ 53% ቅናሽ አድርገን በተለያዩ አማራጮች ማቅረባችንን ስንገልጽ በልዩ ደስታ ነው!
አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ በሚገኝ የቢዝነስ አገልግሎት ማዕከላችን ጎራ ይበሉ!

#ትግራይ
" እስካሁን ወደ ህግ የቀረቡት 7 ብቻ ናቸው " - ግብረ ኃይሉ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰረቀ የሰብዓዊ እርዳትን ለማጣራት ያቋቋመው ግብረ ኃይል እስካሁን ሲሰራቸው የቆዩትን ስራዎች በተመለከተ ለክልሉ ቴሌቪዥን ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር።
በዚህም ወቅት በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ በኤርትራ ኃይሎች፣ በፌዴራል እና በትግራይ ክልል መንግስታት መዋቅር ዝርፊያ መፈፀሙን ለማወቅ ችሏል።
በተጨማሪም በግብረሰናይ ድርጅቶች ፣ የተፈናቃይ ወገኖች አስተባባሪዎች ለሰብዓዊ እርዳታ የመጣ ድጋፍን መዝረፋቸውን የሚያመላክት ማስረጃ ተገኝቷል።
የተዘረፈው ዘይት፣ ስንዴ፣ ክክ እና ሌሎች ድጋፎች ናቸው።
እስካሁን በተሰራው የማጣራት ስራ የኤርትራ ሰራዊት በሽራሮ 28,880 ኩንታል ስንዴ መዝረፉ፣ 43,200 ሊትር ዘይት፣ አተር ክክ 1440 ኩንታል መዝረፉን ግብረኃይሉ አሳውቋል። ይህ ኃይል የዘረፈውን ዘርፎ የተቀረውን እንዲባክን አድርጓል።
የፌዴራል መንግስት " አስተዳደር ብሎ ያስቀመጣቸው አመራሮች " 43,196 ኩንታል ስንዴ፣ 129,585 ሊትር ዘይት ፣ 4,184 ኩንታል የአተር ክክ እንደወሰዱ በጥናት ተረጋግጧል።
በትግራይ መዋቅር 14, 317 ኩንታል ስንዴ፣ 42,759 ሊትር ዘይት፣ 1,424 ኩንታል የአተር ክክ መዘረፉን ለማረጋገጥ ተችሏል።
እንደ ግብረ ኃይሉ መረጃ እስካሁን በክልልና በዞን ለማጣራት እንደተቻለው ከፌዴራል መንግሥት መዋቅር፣ ከትግራይ ክልል መንግሥት መዋቅር፣ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲሁም ከተፈናቃይ ወገኖች አስተባባሪዎች እስካሁን 186 ተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ በማጥፋት ተሳታፊ ሆነው መገኘታቸውን ለመወቅ እንደተቻለና 7 ሰዎች ወደ ህግ እንዲቀርቡ መደረጉን አሳውቋል።
የተጀመረው የማጣራት ስራ ገና የሚቀጥል ሲሆን በየጊዜውም መረጃውን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
@tikvahethiopia

#AAU
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።
ይኸው ድጋፍ ዛሬ ወደ ክልሉ መላኩን ተቋሙ ገልጿል።
ድጋፉ 11 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ቀሪው አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ኮምፒዩተሮችና የህክምና መሳሪያ ቁሳቁሶች መሆናቸው ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው መሰል ድጋፎችን በቀጣይነት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቆ በምርምርና ቴክኖሎጂዎች ረገድም በመልሶ ማቋቋሚያ ስራዎች ላይ የራሱን እገዛ እንደሚያደርግም ገልጿል።
#ኢዜአ
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
My Wish Enterprise
DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።
• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT
+251-913-356384 +251-912-710661 +251-910-626917 +251-928-414395
+251-911-606068 +251-922-475851 +251-935-409319 +251-911-602664

#ምርጥ_ዕቃ
እነዚህ ዕቃዎች በአስገራሚ ዋጋ እየተሸጡ ነው። ለበለጠ መረጃ፦ t.iss.one/MerttEka
☎️ 0944-22-23-24
☎️ 0904-94-48-48
🎯መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ 376

" የመሬት ደላሎችንና ህገወጥ አሰራራቸውን መታገል ራሱን የቻለ ጦርነት እንደ መምራት ነው " - የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዱባለ አብራሬ
የወልድያ ከተማ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍሎች በጉልህ ስማቸው ከሚጠቀሱ ከተሞች አንዷ ብትሆንም እስካሁን ከተማዋ ያላትን ስም የሚመጥን ልማት አለ ብሎ ለመናገር አያስደፍርም። ይበልጡኑ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት የነበረውን ጭላንጭልም ያደበዘዘ ነበር።
ከተማዋ በጦርነቱ ከደረሰባት ኪሳራ ተነቃቅታ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲፋጠኑ እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲፈጠሩ የከተማ አስተዳደሩ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ተናግረዋል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት ከንቲባው የእሳቸው አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ሁኔታዎችን ሲያጠና መቆየቱን ገልጸው በተለይ ከመሬት ጋር ተያይዞ የነበሩ ከፍተኛ ምዝበራዎችን አጥንቶ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ገልጸዋል።
"የመሬት ደላሎች" ለከተማዋ እድገት እንቅፋቶች ሆነው ቆይተዋል የሚሉት ከንቲባው ይህንን ተታግሎ ማለፍ ወይም ስልጣን መልቀቅ የሚል አማራጭ ይዘን ተነስተን ህገወጦችን በመታገል ወልዲያን ለማልማት ወስነን እየተንቀሳቀስን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በከተማዋ " ሀሰተኛ ሳይት ፕላኖች ይሰራሉ፤ በአንድ ቦታ ሁለት አይነት ሳይት ፕላን ይወጣል፤ የከተማ ከንቲባ ውሳኔ ይሸጣል ይለወጣል፤ ምትክ ቦታ እየተባለ በባዶይሰጥ ነበር " የሚሉት ከንቲባው ይህንን ህገወጥ ተግባር የሚፈጽሙ በቁጥር 41 የሚሆኑ ሰዎች የተለዩ መሆናቸውንና በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
"የአርሶአደር መሬት አርሶአደሩ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ ከተደረገ በኋላ ለኢንቨስትመንት እስከተመረጠ ድረስ ኢንቨስት ማድረግ አለበት" የሚሉት ከንቲባው "እነሱ [የመሬት ደላሎች] ግን አርሶአደሩን ከመንግስት የምታገኘው ጥቅም ትንሽ ነው እያሉ መሬት እየሸነሸኑ እየሸጡ ነው" ብለዋል።
ከተማዋን ያነቃቃል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመንገድ ፕሮጀከት ምን ላይ ይገኛል ?
የከተማዋ ነዋሪ ማለቁን በጉጉት ከሚጠብቀው ፕሮጀክት አንዱ የሆነው በከተማዋ የሚሰራው የአስፓልት መንገድ ግንባታ ነው።
ከጎንደር በር ፒያሳ እየተገነባ የሚገኘው ይህ የመንገድ ግንባታ ከዚህ ቀደም ጥሩ ሂደት ላይ የነበረ ቢሆንም በጦርነቱ ምክንያት ከዚያም ጋር ተያይዞ ተቋራጩ በተፈጸመበት ዝርፊያ መቀጠል ተቋርጦ ቆይቷል።
አሁን ላይ የመንገዱን ግንባታ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮምቦልቻ ዲስትሪክት ተረክቦት በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ከንቲባው ገልጸውልናል።
" የጎደሉ እቃዎችን እያሟላን፤ ከሌሎች ቦታዎች ጭምር ጥሬ እቃዎችን በማስመጣት በጥሩ ክትትል አብረን እየሰራን ነው። .... ከዝናብ ጋር ተያይዞ የመጣ መዘግየት እንጂ ዳግም ፕሮጀክቱ ከተጀመረ በኋላ በፍጥነት እየሄደ ይገኛል። " ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪም የ30 ሜትር ስፋት ያለውን የቀለበት መንገድ እንዲሁም ከስታዲየም አደባባይ የሚደርስ የአስፋልት ግንባታ በከተማዋ እየተከናወነ እኝደሚገኝ ከንቲባ ዱባለ አንስተዋል።
ወልድያ ከተማ ባለ አምስት በር እንዲሁም በተራራ የተከበበች እንደመሆኗ ለቱሪዝም እንዲሁም ለሥራ ፈጠራ እንዲውል እየተሰራ ይገኛል የሚሉት ከንቲባው ከዚህ ጋር ተያይዞም የሚያጠና ቡድን ተቋቁሞ 12 ተግባራት መለየታቸውንና ለዚህም 662 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ መለየቱን ጠቁመው የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራዎች በቴሌቶንና በሌሎች አማራጮች እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

የብድር ስርዓት . . . #ብሔራዊ_ባንክ
ባንኮች ብድር ለመስጠት መያዣ የሚጠይቁበት አሰራር እንዳለ ይታወቃል።
ከዚህ ቀደም ዜጎች ቋሚ የሆነ ማስያዣ ሳያቀርቡ ከባንክ እንዲበደሩ ለማስቻል ስራዎች ተጀምረው እንደነበር መነገሩ ይታወሳል።
አሁን ላይ ይህ ስራ ከምን ደረሰ ?
የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ #ለሸገር_ኤፍ_ኤም 102.1 ሬድዮ የሰጡት ቃል ፦
" ተንቀሳቃሽ ዋስትና ሲስተም ዘርግተናል።
ብዙ ነገሮች ከዚህ በፊት ተቀባይነት የሌላቸው ፦
- የቁም እንስሳት
- እህል
- በግምጃ ቤት ውስጥ እህል እናስቀምጥና ርሲት እንይዛለን
- የመሬት አጠቃቀም የምንለው አለ
- ሶፋ
- ፍሪጅ
- ቴሌቪዥን . . . ሌሎችም አሉ፤ አስይዘን የምንበደርበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
ከዚህም ባለፈ IP (Intellectual Property) ጭምር ሃሳብ (Idea) ፋይናንስ የሚደረግበት ስርዓት ነው ይሄ፤ ስለዚህ ሃሳቡን Patent ወይም የሆነ certified ነገር ይዞ ከመጣ ያንን ያሳያል እንደ Collateral ከዚያ በኃላ ብድር ይሰጡታል (ባንኮች) ማለት ነው። ያን ሂደት አሁን ተጀምሮ ወደ 70 ሺህ በMovable Collateral Registry ላይ ተመዝግቧል። ተንቀሳቃሽ ዋስትና አስይዘው ወደ 70 ተበዳሪ ተበድሯል።
ከእውቀት ጋር ፣ ከConsumer protection ጋር ተያይዞ የሚሰራ ስራ አለ፣ ለግብርና ... ወዘተ ከ5 % ያላነሰ ብድር እንዲሰጥ መመሪያ አውጥተን እሱንም ተግባራዊ እያደረግን እንገኛለን። አሁን ባለን መረጃ ከ5 % በላይ ሄዷል። "

ብርሃን ባንክ በሀገራችን የመጀመርያውን የ ’ኤም ፖስ’ ማሽን በስራ ላይ አዋለ !
ብርሃን ባንክ ከሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በጋራ በመሆን የመጀመርያ የሆነውን የኤም ፖስ ማሽን ለተጠቃሚዎች በስራ ላይ አውሏል።
ባንካችን ያስጀመረው ይህ የኤም ፖስ ማሽን ለታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች እና የዲጂታል ደረሰኝ ለሚፈልጉ ለተለያዩ አነስተኛ ቢዝነሶች መዋል የሚችል ነው።
እነዚህ ማሽኖች ለአጠቃቀም እና ለአያያዝ እጅግ ቀላል ከመሆናቸው በላይ የኔት ወርክ ፍጥነታቸው ቀድሞ በገበያ ላይ ካሉት የፖስ ማሽኖች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ስለሆነ ተመራጭ በመሆን በተሻለ የአገልግሎት ተደራሽነት በከተማችን ውስጥ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እና ለሌሎችም በማሰራጨት ላይ እንገኛለን፡፡
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
More : https://t.iss.one/berhanbanksc

#ትኩረት
ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር በሚያቀኑ የጭነት የተሽከርካሪ ሾፌሮች እና ረዳቶች ላይ " እገታ ተፈፅሟል " ሲሉ የታጋች ቤተሰቦች ገለፁ።
ድርጊቱ ዛሬ ንጋት 12 ሰዓት " አሊዶሮ " በሚባለው አካባቢ ስለመፈፀሙ አንድ ወንድሜ ታግቷል ያለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ጠቁሟል።
የታጠቁ አካላት " እስከ ሰላሳ / 30 የሚሆኑ ሰዎችን ከመኪናቸው አስወርደው አግተዋቸዋል ከነሱ ውስጥ ደግሞ አንዱ ወንድሜ ነው " ሲል አስረድቷል።
" ትላንት ነበር ከአ/አ የተነሱት ፤ በለሊት ጉዞ እየተደረገ ስላልሆነ መሃል ላይ መታደር ስላለበት አድረው ዛሬ ንጋት ላይ መኪናቸው እንዳለ እነሱን ግን እንደወሰዷቸው በስልክ ለእናቴ ደውሎ ነግሯታል " ሲል ይኸው የቤተሰባችን አባል ገልጿል።
" ከዛ በኃላም ቀን 6 ሰዓት ደውሎ ጫካ ውስጥ በእግር እየወሰዱን ነው ከእንግዲህ ከሌለውም ይቅርታ አድርጉልኝ ሲል የመሰናበቻ አይነት መልዕክት ተናግሮ ፤ እናቴን ጨምሮ መላው ቤተሰብ እያለቀሰ ፤ በጭንቀት ላይ ነው ፤ ምናልባት መፍትሄ ከተገኘ በሚል ነው ወደ ሚዲያ የወጣነው " ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።
ወንድሙ ሲደውልበት የነበረው ስልክ አሁን ላይ መስራት እንዳቆመ ጠቁሟል።
ወንድሙ በዚህ መስመር (ከአዲስ አበባ - ቻግኒ) ለረጅም አመታት መስራቱን ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለውን ነገር / እገታ አጋጥሞት እነደማያቅ ገልጾ ለቤተሰብ ጭንቀት እረፍት ይሆን ዘንድ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል።
ሌሎች የታጋች ሾፌር ቤተሰቦች ካላችሁም መልዕክታችሁን በ @tikvah_eth_BOT ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ (ከማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኮፒ የሚደረጉ መልዕክቶችን ባትልኩ ይመረጣል) ።
በዚሁ በ" ገብረ ጉራቻ "ቀጠና ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱ፣ እገታ ፣ እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ መነገሩ የሚዘነጋ አይደለም።
ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰጡት ማብራሪያ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።