TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት የርክበ ካህናትጉባኤ ነገ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ/ም ይከፈታል። በአሁን ሰዓት የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ የጸሎት ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሔድ ላይ ነው። ፎቶ ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ @tikvahethiopia
#Update
የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል።
ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል።
ምን አሉ ?
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው ብለዋል።
" በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል " ሲሉ ገልጽዋል።
" የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ " ጌታችን፡- ' እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ ' ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል " ብለዋል።
በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም ሲሉ አስገንዝበዋል።
" በተለይም #በትግራይ እና #በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል " ብለዋል።
" በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል " ሲሉም አክለዋል።
" እኛ ያጐደልነው ፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያኩ " ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።
" የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም " ሲሉ አሳውቀዋል።
(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል። ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል። ምን አሉ ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና…
" በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ ባሰሙት የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ሀገራዊ የሰላም ጉዳይን በአፅንኦት አንስተዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ በሀገራችን ያለው የሰላም ሁኔታ በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው ብለዋል።
ይህም ሂዶ ሂዶ ቤተክርስቲያንንና ሕዝብን፣ ሀገርን ልማትን መጕዳቱ የማይቀር ነው ሲሉ አሳስበዋል።
" በመሆኑም ቤተክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣ በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መስራት ይኖርብናል " ሲሉ አስገንዝበዋል።
ከዚህ ባለፈ ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " በተፈጠረው አላስፈላጊ ከባድ ጦርነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተፈናቀሉ ምእመናን ልጆቻችንን በፍጥነት ደርሰን የምናጽናናበትንና የምንደግፍበትን ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ማየት ይኖርብናል " ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜም አላስፈላጊ በሆነ የእርስ በርስ ግጭት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ግጭቱን አቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ አባታዊ ጥሪያቸውን በአፅንኦት አስተላልፈዋል።

#ብርሃን_ባንክ
We Are Hiring !
Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
1. Junior Customer Service Officer
Link; https://t.iss.one/berhanbanksc

#MyWishEnterprise
DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።
• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT
0913356384 / 0912710661 0910626917 / 0928414395
0911606068 / 0922475851 0935409319 /0911602664

መንግሥት የከለከለው ሰልፍ ... በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ በአደባባይ ሊከበር የነበረው የሰራተኞች በዓል (ሜይዴይ) በመንግስት መከልከሉ ይታወሳል። በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ? አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦ " የእኛ አላማ የነበረው የሰራተኛውን ጥያቄ ይዘን በመላው ከተማ ሳይሆን በመስቀል አደባባይ ብቻ ማክበር እና ጥያቄዎቻችንን በሰላም ማቅረብ…
" ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " - የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንገብጋቢ ባሏቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኮንፌዴሬሽኑን አመራሮች እንዲያነጋግሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡
ኮንፌዴሬሽኑ በዘንድሮው የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎችን በማካተት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ እሳቸውን ማነጋገር ለሠራተኞች ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት እንደሚረዳ አስታውቋል፡፡
በየጊዜው እያሻቀበ በመጣው የኑሮ ውድነት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በደብዳቤው የጠቀሰው ኢሠማኮ፣ " ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " ብሏል፡፡
ኢሠማኮ የሠራተኞች አንገብጋቢ የሚባሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉንም በደብዳቤው ጠቅሷል፡፡
ከዚህ ቀደም የሠራተኞች ጥያቄ የቀረበላቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄውን ወደ ጎን የመግፋት አዝማሚያ እያሳዩ በመምጣታቸው፣ የኢሠማኮ አመራር ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአነጋግሩን›› ጥያቄ ለማቅረብ መገደዱን በደብዳቤው አስረድቷል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethmagazine

" ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረስ ክፍያ መጨመር አይቻልም " - የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን
ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረሱ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ት/ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ገልጿል።
በከተማው አንዳንድ ተቋማት የክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት መሆኑን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን የገለፀው ባለሥልጣኑ የክፍያ ጭማሪውን ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለ ሥልጣን መሰሪያ ቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ የጋራ አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ ወላጆች ከት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ መልዕክታችሁን በ @tikvah_eth_Bot ላይ አድርሱን። ልጆቻሁን የምታስተምሩባቸው ት/ቤቶች ምን ያህል ጨመሩ ?

#big5construct
አስደሳች ዜና ! አቴስፑል ኢንተርናሽናል ግሩፕ የተሰኘው የስፔን ድርጅት በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት ላይ በኤግዚቢተርነት እንደሚሳተፍ ስንገልፅ በደስታ ነው።
እጅግ የዘመኑ የሕንጻ ውስጥ ንድፎች እና የፊኒሺንግ ሥራዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች እና መሣሪያዎች፣ የኤምኢፒ አገልግሎቶች፣ የሶላር እና የከተማ ዲዛይን ላይ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን እና ምርቶቻቸውን ለመጎብኘት እና የቢዝነስ ትስስር ለመፍጠር ይዘጋጁ።
ለቀጣይ ፕሮጀክቶችዎ፣ ዘመናዊ እና ትክክለኛ መፍትሔዎችን ለማግኘት ይህ ዕድል እንዳያመልጦ። በከግንቦት 10 - 12 2015 በሚሊንየም አዳራሽ እንገናኝ !

#አባይ_ገበያ
ኑሮዎን የሚያቀሉ ማንኛውንም ኦንላይን ማርኬት ላይ አይተው የወደዷቸውን እቃዎች እኛ ጋር ያገኛሉ። ገፆቻችንን ይጎብኙ!!
Telegram፡ ABAY MART: https://t.iss.one/abaymart
ABAY KIDS : https://t.iss.one/amkids1
Website: https://abbaymart.com/
ይምጡና ይጎብኙን ተደስተው ይመለሳሉ !!
ቁጥር 1:- መገናኛ፤ ከአደባባይ ወደ ደራርቱ ሲሄዱ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
ቁጥር 2 :- ፒያሳ፤ ሰባራ ባቡር፤ አናኒያ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ
የመረጡትን እቃ ይዘዙ፤ ያሉበት እናደርሳለን!!
📞0980323232
📞0909858687
📞 0913892969

Photo
#AddisAbaba
ወላጆች ምን አሉ ?
ወላጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ወቅቱን ያገናዘበ ፤ የኑሮ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ልጆቻቸውን በተለያዩ ት/ቤቶች የሚያስተምሩ ወላጆች ት/ቤቶች እየጨመሩ ያሉት ከፍተኛ ክፍያ እጅግ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ መንግሥት ቁጥጥር ያድርግ ሲሉ አሳስበዋል።
አንድ ወላጅ " በየት/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ እየተደረገ ነው ይህ በጣም ያማል " ያሉ ሲሆን " ኑሮ ለእነርሱ ብቻ የተወደደ እስኪመስል ድረስ 7000 ከሆነ 14,000 እየተጠየቀ ነው " ብለዋል።
እሳቸው ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ት/ቤት ከጭማሪው ጋር በተያያዘ ወላጆች ሳይስማሙ ስብሰባ መበተኑን አመልክተዋል።
" መንግስት ይህንን ጉዳይ አንድ ሊለው ይገባል ፤ አንዴ ወልደናቸዋል ምን እናድርግ ? " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
አንደንድ ወላጆች ፤ ይደረጋል በተባለው አግባብነት እና ልክ የሌለው የዋጋ ጭማሪ ልጆቻቸው ከሚወዱት ትምህርት ቤት እንዲያስወጧቸው ሊያደርግ የሚችል መሆኑን አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ከ1,500 በላይ ወላጆች መልዕክታቸውን የተቀበለ ሲሆን ወላጆች በላኩት መልዕክት ት/ቤቶች ከ20 በመቶ እስከ 100 በመቶና #ከዚያ_በላይ ጭማሪ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ወላጆች ስለ ት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ምን አሉ ?
----
የካ አባዶ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትም/ ቤት ልጃቸውን የሚያስትምሩ ወላጅ የልጃቸው ወርሃዊ ክፍያ 1450 ብር እንደነበና 65.7 በመቶ በመጨመር 2500 ብር እንደተደረገ ገልጸዋል። " ወላጆች እንዲጨምርብን አንፈልግም ነበር ግዴታ ከሆነም ከ30 በመቶ በላይ እንዳይጨምሩ ተከራክረን ነበር። " ያሉት እኚሁ ወላጅ " ት/ቤቱ ግን 80 በመቶ እንጨምራለን ብለው ወላጅ ባይስማማም 65.7 በመቶ ወስነዋል " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
----
" መንግስት ካለ ለምን መጨመር የሚቻለውን ከፍተኛ ተመን አይወስንም ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ የተማሪ ወላጅ " እመኑኝ በዚህ ሁኔታ ብዙዎች ት/ት ሊያቆሙ ይችላሉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
----
በአንድ የግል ት/ቤት ውስጥ ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ት/ቤቱ መንግስት ምንም ሊያስገድደው እንደማይችል እና ነፃ ገበያ እንደሆነ ተናግሮ ምንም ለውጥ እንደማናመጣ ነገረን ያሉ ሲሆን " መንግሥት ስምምነት ሳይደረግ ዋጋ መጨመር አይቻልም ማለቱ ተስፋ ሰጥቶናል " ብለዋል ፤ እሳቸው ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 78% መጨመሩንና በተርም / በሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀን 7600 እንከፍል የነበረውን 13324 ነው ያደረጉብን ሲሉ ገልጸዋል።
----
አንድ ወላጅ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ት/ቤት የ65 በመቶ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን ገልጸው " በዚህ ኑሮ ውድነት ይህን ማድረግ ግፍ ነው ፤ የእኛ የወላጆች ገቢ ባላደገበት ይህ እንዴት ይድረጋል ፤ ለእኛስ አይታሰብም ወይ ? ሲሉ መልዕክታቸውን ልከዋል።
----
በኮ/ቀ በሚገኝ የአንድ የግል ትምህርት ቤት የወለጅ ኮሚቴ ነኝ ያሉ አንድ የቲክቫህ አባል " እንደ ኮሚቴ ተስማምተን የነበረው 200 እስከ 300 ጭማሪ ነበር ፤ ለምሳሌ በዚህ የት/ዘመን 1300 + 300 = 1600 ፤ 2016 ነበር የተስማማነው አሁን ግን 600 ጭማሪ አድርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል። " ይህ ለምን እንደሆና ምክንያቱን በግልፅ አላወቅንም " ያሉት እኚሁ የወላጅ ኮሚቴ " ለሚቀጥለው ዓመት 1900 ተብሎ በደብዳቤ አሰውቀውናል " ሲሉ አክለዋል። " ልጆቻችንን ከመስወጣተችን በፊት ትምህርት ቢሮ ክትትል ያድርግ !! " ሲሉ አደራ ብለዋል።
----
" መንግስት ውይይት ሳይደረግ መጨመር አይቻልም ብሏል ፤ ውይይት ሲባልስ #ስንት_ሠው_ተገኝቶ ነው ውሣኔ ማሣለፍ የሚችለው ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ ወላጅ " ይህ በራሡ #ክፍተት ያለው አገላለፅ ነው፤ እንዳሻችሁ እንደማለት ነውና መንግስት የኑሮ ጫና የሚፈታተንን ሳያንስ ሌላ ጫና ለመሸከም የሚችል ጫንቃ የለንምና ፤ የፈጠራትን ክፍተት መንግሥት ራሡ ይዝጋት እንላለን " ብለዋል። "
----
በአንድ የግል ት/ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ፤ ት/ቤቱ በቀጣይ አመት ከ1300 ባንዴ 2700 ጭማሪ ማድረጉን እና ያልፈለገ መልቀቅ ይችላል እንዳሏቸው ገልጸዋል። " በዛላይ ቀጣይ አመት በተርም ነው ምከፍሉት አሉን " የሚሉት ወላጅ " ሁለት ልጆቼን ለማስተማር 2600 ከፍዬም አንገዳግዶኝ ነበር የባሰው መጣና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ " ብለዋል።
----
" እኔ ልጄን የማስተምርበት ት/ት ቤት ወደ 120% ነው የጨመረው " ያሉ አንድ ወላጅ " ከአንድም ሁለት ጊዜ ከት/ት ቤቱ አሰተዳደር ጋር ብንሰበስብም መስማማት ላይ ግን መድረስ አልቻልንም። " ብለዋል። " እንደውም ት/ት ቤቱ መጀመሪያ 22ዐ% ነበር ያቀረበው ከብዙ ክርክር በኋላ ነው ወደ 120% የወረደው ሆኖም ግን ከዚህ በታች አሻፈረኝ ብሏል። ብዙ ወላጅም በጣም ተማሯል። " ሲሉ ገልጸዋል።
----
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነኝ ያሉ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 40 % ጭማሪ መደረጉን ገልጸው በዚህ ኑሮ ውድነት ፤ በዛ ላይ ሁለት / 2 / እና ከዛ በላይ ልጆች ያሏቸው ምን ይሆናሉ ? ሲሉ ሁኔታው እጅግ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።
----
አንድ ወላጅ ልጆቻቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ከጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች ጋር ስምምነት እንደሌለ ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ግን " የፈለገ ልጆቹ ያስቀጥል፤ ያልተስማማ ሌላ ት/ቤት ይቀይር " የሚል ምላሽ መስጠቱን አመልክተዋል " መንግስት የሰጠው አቅጣጫ ወላጆች ሳይስማሙ ማለት የሹፈት ውሳኔ ነው ፤ ሌላ ትም/ቤት ፈልጉ ከተባለ ለልጃችን ስንል ሳንስማማ እንቀጥላለን ፤ #መንግስት ነው ይህን #መቆጣጠር ያለበት፤ እውነቴ ነው በዚህ አካሄድ ብዙ ልጆች ከትምህርት ውጪ ይሆናሉ። " ሲሉ ስጋታቸውን አስረድተዋል።
----
የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ ወላጅ " ከክፍያ ጭማሪ በተያያዘ እኛ ወላጆች ምንም ባልተስማማንበት ሁኔታ ነዉ እየጨመሩ ያሉት ፤ በአካባቢያችን ከ50% በላይ ነዉ ጭማሪ የተደረገው እና የሚመለከተው አካል ከጊዜዉ ጋር ታሳቢ በማድረግ መፈትሔ እንዲሰጥ ። " ሲሉ ጠይቀዋል።
----
አንድ ወላጅ አምስት (5) ልጆቸውን በሚያስተምሩበት የግል ትምህርት ቤት በአመት አጠቃላይ 434 ሺህ ብር ሲከፍሉ እንደነበር አሁን ግን 100 % ጭማሪ (868,000 ብር) እንደሚደረግ እንደተነገራቸው ገልጸዋል ፤ መንግሥት በግል ት/ቤቶች እየተደረገ ያለውን ነገር እንዲከታተልና መፍትሄ እንዲፈልግ አደራ ብለዋል።
----
በአንድ የግል ትምህርት ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ትምህርት ቤቱ የ60,000 ሺህ ብር ጭማሪ ለማድረግ እንደወሰነና ለዩኒፎርም እና ለመሳሰሉት እስከ 30,000 ብር ጭማሪ እንደተደረገ አመልክተው የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
(ተጨማሪ ወላጆች የላኩይ መልዕክት በዚሁ ፅሁፍ ላይ #edit ተደርጎ ይካተታል)
በአጠቃላይ እጅግ በጣም በርካታ የተማሪ ወላጆች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መልዕክታቸውን ልከዋል።
የወላጆቹ ሃሳብ ሲጠቃለል ፤ በዚህ የኑሮ ጫና ወቅት እጅግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መንቀሳቀስ በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለውና ት/ቤቶችም ይህንን ተገንዝበው ማስተካከያ ማድረግ እንዳለብቸው የሚያሳስብ ነው።
ከምንም በላይ ደግሞ ፤ #መንግስት በሁሉም የግል ት/ቤቶች ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ወደ ምሬት ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን ማስቆም እንዳለበት የሚያገነዝብ ነው።

#CBEBirr
የሲቢኢ ብር ደንበኛ መሆን ቀላል ነው!
ባሉበት፣ በቀላሉ ይመዝገቡ!
=========
የነዳጅ ግዥ፣ የተለያዩ የአገልግሎት እና ሌሎች ክፍያዎችን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችለው የሲቢኢ ብር አገልግሎትን እስካሁን መጠቀም ካልጀመሩ፣ አሁኑኑ የተንቀሳቃሽ ስልክዎን ተጠቅመው ባሉበት በቀላሉ ደንበኛ ይሁኑ፡፡
ደንበኛ ለመሆን፡
• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራስዎ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
በሲቢኢ ብር በቀን ውስጥ የሚያንቀሳቅሱትን የገንዘብ መጠን ገደብ ከፍ ለማድረግ ወደ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ አሊያም የሲቢኢ ብር ወኪል መታወቂያ ይዞ በመሄድ ምዝገባዎን ያጠናቁ!
****
የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

ምንነቱ ያልታወቀ #ስራስር እና #ሰጋቱራ ከጤፍ ዱቄት ጋር ቀላቅለው ሲያከፋፍሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮችንና የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) በመቀላቀል ለህብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦችን በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ህገ-ወጥ ተግባሩ ሲፈፀም የነበረው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አጠራሩ ቆሼ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥ ነው።
በመጋዘኑ ውስጥ 47 ኩንታል ምንነቱ ያልታወቀ ስራስር፤ የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋ ቱራ) እና 167 ኩንታል የጤፍ ዱቄት ተከማችቶ የተገኘ ሲሆን ባዕድ ነገሩን ከዱቄቱ ጋር የሚደባልቅ መጋዘኑ ውስጥ እንዳይወጣ የተቆለፈበት ሠራተኛ በፍተሻ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።
ከአካባቢው ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የጅማ በር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በህግ አግባብ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በስራ ላይ የነበረውን ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረግው ተጨማሪ ምርመራ የንብረቱን ባለቤትን አፈላልጎ በመያዝ ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
Via @tikvahethmagazine