TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትፈለጋለች በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ አንዲት እንጀራ እናት ሁለት ልጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደሏ እየተፈለገች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ስለጉዳዩ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ምን አሉ ? ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ፦ " ወንጀሉ የተፈፀመው ቅዳሜ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም. በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሦስተኛ…
ፎቶ ፦ በሸገር ከተማ ፤ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ/ም በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ " 3ኛ ቡራዩ " በሚባል ስፍራ ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ነጋሴ ከበደ የተባለችው ተጠርጣሪ መያዟ ተገልጿል።

ተጠርጣሪዋ የእንጀራ ልጆቿ የሆኑትን ሁለቱን ሕጻናት አንገታቸውን ቀልታ ፣ በተኙበት ብርድ ልብስ አልብሳ እሳት ለኩሳባቸው አምልጣ እንደነበርና ፍለጋው እየተካሄደ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ከቀኑ 10:30 ላይ " ሳንሱሲ " በሚገኝ ጫካ ውስጥ ራሷን ለማጥፋት ስትሞክር በተደረገው ክትትል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ነው የተገለጸው።

Photo Credit : Hachalu Lachesa

@tikvahethiopia
#big5construct

የማይገኝ አጋጣሚ ለሁሉም የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች !

ከግንቦት 10 እስከ 12፣ 2015ዓ.ም. በሚከናወነው ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት ላይ በሚካሄዱ ኢንደስትሪ ተኮር ንግግሮች እና ውይይቶች ላይ በመሣተፍ ብቻ ነፃ የሲፒዲ ነጥብ ማግኘት እንደሚቻል ያውቃሉ?

ይመዝገቡ https://bit.ly/3oI8P6L

የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/big5ethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች እና አካባቢያዊ ምርጫን በ2016 ዓ.ም ለማካሄድ መታቀዱን ዛሬ አሳውቋል።

ቦርዱ ይህን ያሳወቀው የ2015 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ፥ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተወሰኑ ክልሎች በሚገኙ አካባቢዎች 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አለመካሄዱን ገልጸዋል።

ይህንኑ ምርጫ ለማካሄድ በ2015 ዝግጅት ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር ተናግረዋል።

ነገር ግን የአካባቢ ምርጫ ለማካሄድ ቢታቀድም አለመሳካቱን ገልጸው፣ እነዚህን ምርጫዎች በ2016 ለማካሄድ ቦርዱ ዕቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ ባለፉት ወራት ከፖለቲካ ፓርቲዎች አሠራር ጋር በተያያዘ አንዳንድ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያካሂዱ በተለያዩ አካላት መከልከላቸውን ቦርዱ ማረጋገጡን እና አንዳንድ የፓርቲ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውን አቶ ውብሸት ገልጸዋል። ቦርዱ ለዚህ ችግር መፍትሔ ለመስጠት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፥ ከሀገር ውጭ የሚገኙትን ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌውን ፣ በቅርቡ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንደፈታ የተነገረለት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የሚዲያ ሰዎች እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ የሚዲያ ሰዎችን " ህገ መንግስታዊ…
" ክስ ከተመሰረተብኝ እመለሳለሁ " - አቶ ልደቱ አያሌው

መንግሥት በ "ሽብር ወንጀል እጠረጥራቸዋል" ያላቸውን በውጭ ሀገር ያሉና ተላልፈው እንዲሰጡ ማዘዣ ካወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው "ክስ ከተመሠረተባቸው" ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።

አቶ ልደቱ እስካሁን ክስ እንዳልተመሠረተባቸው በጠበቃቸው እንደተነገራቸውና ክስ ከተመሠረተባቸው ግን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመመለሱ ገልጸዋል።

ይህን የገለፁት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ምን አሉ ?

"...ከጠበቃዬ ጋር እየተነጋገርኩ ነው። እስካሁን ክስ አልተመሠረተብኝም። ዝም ብሎ በራድዮና በቴሌቪዥን ይነገራል እንጂ የቀረበ ክስ የለም። ክስ ሲመሠረት ነው የምሄደው።

ክስ ከመመሥረቱ በፊት መሄዴ ጥቅም የለውም። በጊዜ ቀጠሮ መጉላላት ነው እንጂ ምንም ፋይዳ የለውም። እስከዚያ ድረስ ሕክምናዬን እከታተላለሁ /አቶ ልደቱ ለልብ ህመም በአሜሪካ የህክምና ክትትል ላይ ናቸው/ ።

ክስ ሲመሠረት ዳኞቹ የሚቀጥለው ሕክምናዬ ድረስ እንድቆይ የሚፈቅዱ ከሆነ እቆያለሁ። የማይፈቅዱ ከሆነም የሕክምና ቀጠሮዬን አቋርጬ እሄዳለሁ። "

አቶ ልደቱ ስለ ሽብር ክስ...

" የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው እንጂ መጀመሪያም የመጣሁት እዚህ ለመኖር አይደለም። በቅርብ ጊዜ ወደ አገሬ እመለሳለሁ ብዬ እያሰብኩ ነበር። የዘገየሁት ያልተቋጨ የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው። የሽብርተኛነት ክስ ሲመጣ ካሰብኩት ጊዜ ፈጥኜ ነው የምሄደው አልኩ።

የሕግ ተፈላጊነት ካለ፣በሽብርተኛነት የመጠየቅ ጉዳይ ካለ፣እኔ ከፍ/ቤት ውሳኔ እና ጥያቄ ርቄ መኖር ስለማልፈልግ ነው ለመሄድ የወሰንኩት።

...አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ተመልሼ ለመውጣት ችግር ሊገጥም ይችላል ብዬ ነው እስካሁን የዘገየሁት። አሁንም የሕክምና ቀጠሮ አለኝ። ግን የሕግ ተጠያቂነት ከመጣ ምንም ማድረግ አይቻልም።

የተከሰስኩበት ወንጀል በፍጹም ከእኔ ታሪክ እና ማንነት ጋር የማይሄድ ነው። ሥርዓቱ ደግሞ ይሄንን ያደረገበት የራሱ ምክንያት አለው። አንደኛው ምክንያት እንደዚህ ዓይነት ክስ ፈርቼ ወደ አገሬ እንዳልመለስ ለማድረግ ስለሆነ ይሄንን በፈቃደኛነት ለመቀበል ዝግጁ አይደለሁም።

እኔ ሰላማዊ ታጋይ ነኝ። ሁልጊዜም በሕግ ነው የምተማመነው። ካሁን ቀደምም አምስት ስድስቴ ታስሬ በፍርድ ቤት ነው ነጻ የሆንኩት። አሁንም በዚያ መንገድ ሄጄ የግድ ሥርዓቱን መጋፈጥ አለብኝ በሚል ነው የምመለሰው።

ማናችንም ላለመታሰር፣ ዋጋ ላለመክፈል የየራሳችን ምክንያት ይኖረናል። ትግል ሲባል ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ጥሶ መከፈል የሚገባውን ዋጋ መክፈል ነው።

ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ስለሚገጥማቸው ችግር...

" ስሄድ የሚገጥመኝ ችግር ቀላል ነው ብዬ አይደለም። ከባድ እንደሚሆን አምናለሁ። ያ ችግር ምናልባት ሕይወቴንም ጭምር የሚያሳጣ ሊሆን ይችላል።

ግን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ፣ ሕዝቡ ያለበት ሁኔታ፣ ሰዎች በዚህ ደረጃ ዋጋ ለመክፈል ካልተዘጋጀንና ካልከፈልን ይለወጣል የሚል እምነት የለኝም። በእኔ ደረጃ ያለ ሰው ያን ዋጋ መክፈል እና ለትግሉ አርአያ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ።

ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በፖሊስ ሊያዙ ስለሚችሉበት ሁኔታ...

" ልምዱ አለኝ። መታሰር የመጀመሪያዬ አይደለም። በዚህ ዓይነት ትግል ውስጥ ላለፉት 31 ዓመታት ቆይቻለሁ። ወደ 6 ጊዜ ስለታሰርኩ ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም።

ከእኔ ጋር በመግለጫ የተጠቀሱ ግለሰቦች እየታደኑ እያተሰሩ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ኤርፖርት የሚጠብቀኝ ፖሊስ እንደሚሆንና እንደምታሰር አውቃለሁ። ለዚህ የሥነ ልቦና ዝግጅት አለኝ።"

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት የርክበ ካህናትጉባኤ ነገ ግንቦት 2 ቀን 2015  ዓ/ም ይከፈታል። በአሁን ሰዓት የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ የጸሎት ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሔድ ላይ ነው። ፎቶ ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ @tikvahethiopia
#Update

የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል።

ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል።

ምን አሉ ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው ብለዋል።

" በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል " ሲሉ ገልጽዋል።

" የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ " ጌታችን፡- ' እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ ' ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል " ብለዋል።

በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በተለይም #በትግራይ እና #በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል " ብለዋል።

" በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል " ሲሉም አክለዋል።

" እኛ ያጐደልነው ፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል " ያሉት ቅዱስ ፓትርያኩ " ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም " ሲሉ አሳውቀዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተከፍቷል። ይህን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል። ምን አሉ ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባቀረቡት ንግግር ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ በፈተና…
" በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ ባሰሙት የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ሀገራዊ የሰላም ጉዳይን በአፅንኦት አንስተዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ በሀገራችን ያለው የሰላም ሁኔታ በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው ብለዋል።

ይህም ሂዶ ሂዶ ቤተክርስቲያንንና ሕዝብን፣ ሀገርን ልማትን መጕዳቱ የማይቀር ነው ሲሉ አሳስበዋል።

" በመሆኑም ቤተክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣ በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መስራት ይኖርብናል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከዚህ ባለፈ ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " በተፈጠረው አላስፈላጊ ከባድ ጦርነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተፈናቀሉ ምእመናን ልጆቻችንን በፍጥነት ደርሰን የምናጽናናበትንና የምንደግፍበትን ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ማየት ይኖርብናል " ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜም አላስፈላጊ በሆነ የእርስ በርስ ግጭት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ግጭቱን አቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ አባታዊ ጥሪያቸውን በአፅንኦት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

We Are Hiring !

Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
1. Junior Customer Service Officer
Link; https://t.iss.one/berhanbanksc
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
0913356384 / 0912710661  0910626917 / 0928414395
0911606068 / 0922475851  0935409319 /0911602664
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግሥት የከለከለው ሰልፍ ... በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ በአደባባይ ሊከበር የነበረው የሰራተኞች በዓል (ሜይዴይ) በመንግስት መከልከሉ ይታወሳል። በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ? አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦ " የእኛ አላማ የነበረው የሰራተኛውን ጥያቄ ይዘን በመላው ከተማ ሳይሆን በመስቀል አደባባይ ብቻ ማክበር እና ጥያቄዎቻችንን በሰላም ማቅረብ…
" ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " - የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንገብጋቢ ባሏቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኮንፌዴሬሽኑን አመራሮች እንዲያነጋግሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በዘንድሮው የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎችን በማካተት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ እሳቸውን ማነጋገር ለሠራተኞች ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት እንደሚረዳ አስታውቋል፡፡

በየጊዜው እያሻቀበ በመጣው የኑሮ ውድነት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በደብዳቤው የጠቀሰው ኢሠማኮ፣ " ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " ብሏል፡፡

ኢሠማኮ የሠራተኞች አንገብጋቢ የሚባሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉንም በደብዳቤው ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም የሠራተኞች ጥያቄ የቀረበላቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄውን ወደ ጎን የመግፋት አዝማሚያ እያሳዩ በመምጣታቸው፣ የኢሠማኮ አመራር ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአነጋግሩን›› ጥያቄ ለማቅረብ መገደዱን በደብዳቤው አስረድቷል፡፡ 

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethmagazine