TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል። More : @tikvahuniversity #TikvahFamily @tikvahethiopia
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል።

እስካሁን ድረስ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኩል በታየው የጥቂት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ዝቅተኛው ውጤት 120 ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 666 ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከውጤት ጋር በተያያዘ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

More : @tikvahuniversity

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል። እስካሁን ድረስ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኩል በታየው የጥቂት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ዝቅተኛው ውጤት 120 ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 666 ነው። የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከውጤት…
#Update

" ብዙም አይርቅም "

የትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ትላንት ለሊት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ከውጤቱ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ መግለጫ ዛሬ ከሰዓት 8:00 በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

" የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ውጤታቸው ከ50 በመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከ28 ሺህ እንደማይበልጥ" በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ ይገኛል ፤ ይህን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች አሐዝ ከ28 ሺህ " #ብዙም_እንደማይርቅ " ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

እስካሁን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ያልተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ብዙም አይርቅም " የትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል። የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ትላንት ለሊት ይፋ መደረጉ ይታወቃል። ከውጤቱ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ መግለጫ ዛሬ ከሰዓት 8:00 በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል። " የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል…
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ50 % በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ50 % በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ…
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ ?

- በ2014 የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985 ሺህ 354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92 ነጥብ 2 % 908 ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77 ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም።

- በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50 ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

- በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

- በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30 ነጥብ 2 እንዲሁም ሴቶች 28 ነጥብ 09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

- በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31 ነጥብ 63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27 ነጥብ 79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

- በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት የሌለ ሲሆን አዲስ አበባ ፣ ሐረሪ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

- ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ።

- በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።

- ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል።

Credit : WMCC

@tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር ፦

- በሀገር ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ 666 ሲሆን በማህበራዊ ሳንይንስ ከ600 ፤ 524 ሆኖ ተመዝግቧል።

- በፆታ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ ወንድ 666 ሴት 650 ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 516 ፤ ሴት 524

- በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማህበራዊ ሳይንስ ከ500 እና በላይ ያስመዘገቡ 10 ተማሪዎች፤

- በአጠቃላይ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እና በላይ ያስመዘገቡ 263 ተማሪዎች ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር ፦ - በሀገር ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ 666 ሲሆን በማህበራዊ ሳንይንስ ከ600 ፤ 524 ሆኖ ተመዝግቧል። - በፆታ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ ወንድ 666 ሴት 650 ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 516 ፤ ሴት 524 - በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማህበራዊ ሳይንስ ከ500 እና በላይ ያስመዘገቡ 10 ተማሪዎች፤ - በአጠቃላይ…
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia