TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#MoE
ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።
ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።
ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን " ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
@tikvahethiopia

Photo
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፦
- በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ1 ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ብሔራዊ ፈተና አላለፈም።
- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል ነው 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ የታወቀው።
- ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል።
- 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦
👉 ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣
👉 ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣
👉 ባህርዳር ስቴም ት/ቤት ፣
👉 ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤
👉 የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው።
ምንጭ፦ WMCC
ፎቶ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@TIKVAHETHIOPIA

#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

19ኛው አለም አቀፍ የክር(የጨርቃጨርቅ) ኤክስፖ !
ከየካቲት15 እስከ 20 በቱርክ ሀገር ኢስታንቡል ከተማ ይካሄዳል ። ከፍተኛ ጥራት ያለው የክር እና ጨርቃጨርቅ አምራች ኢንደስትሪዎችን እንዲሁም ታላቁን የቱርክ የክር ኢንደስትሪ ይጎበኛሉ።
እንዲሁም ለድርጅትዎ አዳዲስ ፈጠራዎችን እና ግንዛቤዎችን ለማየት፤ ተወዳዳሪነቶን ለማሳደግ፤ የንግድ ግንኙነት የሚፈጥሩበት እና ልምድ የሚቀስሙበት ታላቅ ኤግዚብሽን ላይ እንዲሳተፉ ኢስታንቡል አዲስ አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ቅድመ ዝግጅቱን ጨርሶ እየጋበዞት ይገኛል።
አድራሻ ቦሌ ዲ ኤች ገዳ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ስልክ ቁጥር 0983568383፣ ወይም 0944000006 ላይ ይደውሉ

ሸዋሮቢት ውስጥ የሰውም ሆነ የባጃጅ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል። የከተማው አስተዳደር ፤ ለከተማው ሰላምና ጸጥታ ሲባል ማንኛውም የባጃጅና የሰው እንቅስቃሴ ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ የተከለከለ ነው ሲል አሳውቋል። ለተላለፈው ትዕዛዝ ሁሉም ትብብር እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል። ከሰሞኑን በዚሁ ቀጠና ዳግም ግጭት ተቀስቅሶ በርካቶች የደህንነት ስጋት ላይ ወድቀዋል። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፤ " ሰሞኑን በሸዋሮቢት እና በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በተደረገ ጦርነት በርካታ የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረትም ውድሟል " ሲል አሳውቋል።
የንብረት ውድመት የደረሰባቸው የከተማው የ05 ቀበሌ ነዋሪዎች #በመንግስት_ቸልተኝነት እና #የላላ_ህግ የማስከበር ተግባሩ የተነሳ በየአመቱ ለሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ ፤ ውፍጮ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ሙሉ በመሉ መውደማቸውን በመግለጽ መንግስት በዚህ ቀጠና ያለውን ጦርነትና የተደራጀ ቡድን ወይም ኃይል በማጥራት የመንግስት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ከሰሞኑን በደረሰው ጥቃት በርካታ ሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን የህዝብ መገልገያ ትምህርት ቤቶች ፣ ወፍጮ ቤቶች ፣ የጤና ክሊኒኮች ፣ ሱቆች ፣ የቀበሌ አስተዳደር ቢሮዎች ፣ የግለሰብ ቤቶች ወድመዋል።
ነዋሪዎች የሚመለከተው የበላይ የመንግስት አካል ልዪ ትኩረት ሰጥቶ ህይወታችንን ሊታደግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
Photo Credit : የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

#Singapore
የዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ሲንጋፖር ውስጥ በተፈጸመ ውስብስብ የፈተና ማጭበርበር እጇ አለበት የተባለችው ሴት እንድትያዝ ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ።
የ57 ዓመቷ ፖህ ዩዋን ኒይ ስልክ እና ኢርፎን በመጠቀም ተማሪዎች የፈተና ውጤት እንዲያጭበረብሩ የሚያደርግ መዋቅር ዘርግታ እንደነበር ተገልጿል።
የእሷ ሦስት ተባባሪዎቿ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብሏል።
ግለሰቧ ቀደም ሲል የአስጠኚዎች ማዕከል ኃላፊት ላይ የነበረች ሲሆን የተፈረደባትን የአራት ዓመት እስራት ካለፈው መስከረም ትጀምራለች ተብሎ ቢጠበቅም አስካሁን እጇን አልሰጠችም።
ግለሰቧ ከሴንጋፖር ኮብልላለች ተብሎ ይታሰባል።
የአገሪቱ ፖሊስ የእስር ማዘዣ ያወጣ ሲሆን ለኢንተርፖል ጥቆማ ካደረጉም በኋላ ኢንተርፖል " ቀይ ማስጠንቀቂያ " አውጥቷል። ያለችበትን የሚያውቁ እንዲያሳውቁ ጠይቋል።
‘ፖኒ’ በሚል ስም የምትጠራው ግለሰብ የወጣባት " ቀይ ማስጠንቀቂያ " በመላው ዓለም ያሉ የሕግ አካላት ያለችበትን እንዲፈልጉና እንዲይዟት ይሁንታ ይሰጣል።
እ.አ.አ. በ2016 በሲንጋፖር የተካሄዱ ሦስት ብሔራዊ ፈተናዎች ላይ ነው ማጭበርበር የተፈጸመው።
ተማሪዎች #ከቆዳቸው ጋር የሚመሳሰል ኢርፎን አድርገው በተለያዩ የፈተና ማዕከሎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ብሉቱዝ #ሰውነታቸው ላይ ተለጥፎ በልብስ እንዲሸፈን ተደርጎ ፈተና ወስደው ነበር።
ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-01-28-3
Credit : BBC

#EOTC #አሁን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጠች ነው።
ቤተክርስቲያኗ ፤ ከሃያ (20) ዓመታት በላይ በጅማ የም ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የሚያገለግሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ዛሬ በጅማ ዞን ፖሊስ ታስረው መዋላቸውን ገልጻ ድርጊቱን በፅኑ አውግዛለች።
በአሁኑ ሰዓት ሊቀ ጳጳሱ #በግዳጅ ከጅማ እንዲወጡ መገዳቸውን እና ከሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያን የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ጋር ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ መሆናቸውን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ፤ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከክልል የተሰጠ ትዕዛዝ ነው በማለት በነገው እለት በጅማ የቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጻ ቤተመቅደስ ቡራኬ ቤተክርስቲያን ሳያከናውኑ በፀጥታ ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ የተገደዱት ብሏል።
በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ " በሕገ ወጥ ከተሾሙ አባቶች መካከል ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱትና ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታቸውን የተቀበለው መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ ከመንበረ ፓትርያርክ ማረፊያ ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል " ስትል ገልፃለች።
በመግለጫው መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀች ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚገኙበት ግቢ አፈና መፈጸሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ነው ብላለች።
#Update : መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ታፍነው ከተወሰዱበት ተለቅቀዋል።

ቅናሽ ካለማ…
አዲሱን የአቢሲንያ ባንክ አፖሎ የዲጂታል መተግበርያ ሲጠቀሙ በሲኒማ ትኬት፥ በምግብ እና መጠጥ ትዕዛዝዎ ላይ ቅናሽ ያገኛሉ። አፖሎን አውርደው ዛሬውኑ ይጠቀሙ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollo #OurNewProduct #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank, #poweredbybankofabyssinia, #thechoiceforall

#Afar
የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለሰላምና ግንባታ የመጠቀም ልምድ ደካማ በሆነበት ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ጉዳታቸው ትልቅ ነው።
በተለይ እነዚህ አደገኛ መረጃዎች በከተማም ሆነ ከተማ ወጣ ባሉ አከባቢዎች የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከፍ ያለ ነው።
ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከጥር 13 ጀምሮ ለ4 ቀናት በዲጂታል ሰላም ግንባታ እንዲሁም መሰረታዊ የሚዲያ ክህሎት ላይ ትኩረቱን መሰረት ያደረገው የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሂዷል።
በስልጠናው 20 ወጣቶች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ 4 ወረዳዎች (አሚባራ፣ አፋንቦ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ) ለተወጣጡ ሰልጣኞች የዲጂታል ሚዲያ ክህሎትን ስለማሳደግ፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ስለመስራትና ከሀሰተኛና ጥላቻ ንግግሮችን ራስንና ማኅበረሰብን ስለመከላከል በዚህም ምክንያት የሚደርስን ጉዳት መቀነስ በሚቻልበት አግባብ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
በቀጣይም ወጣቶቹ በወሰዱት ሥልጠና መሰረት ወደ ማኅበረሰባቸው ተመልሰው ለሌሎች እኩዮቻቸው ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን እንዲሰጡ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በአከባቢያቸው አወንታዊ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ታቅዷል።
በተለይ የመረጃ ተደራሽነቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተገደበባቸው አከባቢዎች መሰል የአቻ ሥልጠናዎች ትርጉም ያለው ለውጥ ከማምጣቱም በዘለለ ወጣቱን አሳታፊ ያደረገ የመፍትሔ ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ እድሉን በሰፊው ያመቻቻል።
ይህንን ስልጠና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ Mercy Corps Ethiopia ጋር በጋራ በመሆን ለሥልጠናው ከሚያስፈልገው የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ጀምሮ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።
በቀጣይ በድሬደዋና በጅጅጋ ከተሞች መሰል ሥልጠናዎችን የሚሰጡ ይሆናል።