' ወጂዝ ሪል ስቴት ' በከፍተኛ የጥራት መመዘኛ እንደገነባቸው የገለፃቸውን 53 የአፓርታማና የንግድ ሱቅ ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች ማስረከቡን ገልጿል።
" በሪል ስቴት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እያከናወንኩ ነው " ያለው ወጂዝ ሪል ስቴት ፤ ግንባታቸው የተጠናቀቀላቸውን (የዋና መግቢያ በር ፣ የመስኮት መስታወት እንዲሁም የመጨረሻ የቀለም ቅብ) ብቻ የቀሩት በቤተል አካባቢ የሚገኙ በድምሩ 53 ባለ-ሶስት መኝታ አፖርታማ ቤቶችንና የንግድ ሱቆችን ለደንበኞቹ ማስረከቡን አመልክቷል።
በመኖሪያ አፖርትመንቶቹ ግንባታ ሂደት ወቅት በርካታ ደንበኞች በውል መሠረት በወቅቱ ክፍያቸውን ያለመፈፀምና ክፍያ የሟቀረጥ ክፍተቶች መፍጠራቸው እንዲሁም በኮቪድ ወረርሺኝ ወቅት በተፈጠረው የስራ መቀዛቀዝ የርክክብ ጊዜውን በመጠኑ መዘግየቱ ተመላክቷል።
ሪል ስቴቱ በቅርቡ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ በሚገኙ #ሌሎች ሳይቶቹ ለህጋዊና ውላቸውን በአግባቡ በመፈፀም ላይ ለሚገኙ ደንበኞቹ ቁልፍ የማስረከብ ስራ እንደሚሰራ አሳውቋል።
(ዋልተንጉስ ዘሸገር)
@tikvahethiopia

#መልዕክት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ልደትን አስመልክተው " የእንኳን አደረሳችሁ " መልእክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አንስተው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ቅዱስናታቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር አምላክ በአሁኑ ጊዜ #በሀገራችን የተከሠተው ችግር በከፊልም ቢሆን ረገብ ብሎ የሰላም ጭላንጭል እንድናይ አድርጎናል " ያሉ ሲሆን " ይህ ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና #ልንወደው #ልናከብረውና #ልንጠብቀው ይገባል " ብለዋል።
" ሰላም በጠፋ ጊዜ በወገኖቻችን ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ በዓይናችን አይተናል። " ያሉት ቅዱስነታቸው " ይህ ዓይነቱ ክሥተት ሊቆም እንጂ ሊቀጥል አይገባም " ሲሉ አስገንዝበዋል።
የተገኘው የሰላም ጭላንጭል ወደ ፍጹም አስተማማኝ ደረጃ በሙሉነት እንዲያድግ ሁሉም በኃላፊነት እንዲሰራ በአጽንዖት አደራ ብለዋል።
በተከሠተው አለመግባባት በአጠቃላይ በሕዝብ ላይ የደረሰው ስብራት ከባድ በመሆኑ የዓለም ማኅበረሰብ የተቻለውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ሕዝባችንን እንዲያግዝ መንግሥትና ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የተጀመረውን የሰላም ጉዞ እንዳይቀለበስ በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ቅዱስነታቸው ፤ " ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ ልጆቻችን በተለመደው የመተጋገዝ ቅዱስ ባህላችን መሠረት እርስ በርስ #በመረዳዳት ይህንን ፈተና እንድናልፈው በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን ከአደራ ጋር እናስተላልፋለን። " ብለዋል።
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያያዟል)

#እንድታውቁት
ከነገ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ #ጠጥተው በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።
ይህ ቁጥጥር ለ2 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የቆየው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ነበር።

በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተካሄደ ካለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ቅሬታ አቅርበው ነበር።
በዚህ መሰረትም የጉባኤው 3 የሰብዓዊ መብቶች ባለሞያዎች እና አንድ ሹፌር ታህሳስ 27 " ዓለም ባንክ " አካባቢ ጥቆማውን ለማጣራት ይሄዳሉ ፤ በፖሊስም ተይዘው ያሉበትን ማወቅ ሳይቻል ከቆየ በኃላ በተደጋጋሚ በተደረገ ጥረት አራቱም ሰራተኞችና የድርጅቱ መኪና ዓለምገና ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል።
በተጨማሪም ፤ ኢሰመጉ ባሉት ባለሙያዎች ላይ የተለያዩ #ጫናዎች፣ $ዛቻ እና #ማስፈራራትን ጨምሮ እየደረሰበት እንደሚገኝ አሳውቋል።
ኢሰመጉ ይህ አይነት ድርጊት ከህግ አግባብ ውጭ የሆነና ጉባኤው የተቋቋመበትን ዓላማ (ለሰብዓዊ መብት መከበር) እንዳያስፈፅም እንቅፋት የሚሆንና ባለሞያዎቹ በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ ለማድረግና #ለማሸማቀቅ የተደረገ ነው ብሎታል።
መንግስት በኢስመጉ ላይ የተለያየ አይነት #ህገወጥ_እስር እና የተለያዩ ጫናዎችን ከመፈፀም ይቆጠብ ያለው ጉባኤው ፖሊስ ሰራተኞቹን #በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ አሳስቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።
ከተማ አስተዳደሩ በ14 ኛ ዙር የ2080 የቤት ልማት ፕሮግራም 18 ሺ 930 ቤቶች፣ በ40/60 ደግሞ 6 ሺ 843 ቤቶች እንዲሁም ተጨማሪ 18 ስቱዲዮ ቤቶች በድምሩ 25 ሺ 791 ቤቶችን እጣ የማውጣት መርሃ ግብር በማካሄዱ የሚዘነጋ አይደለም።
ውል የመዋዋያ ቦታው #መገናኛ በሚገኝው የቦሌ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ

የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል…
20/80 እና 40/60 ውል ፦
የቤት እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ?
- እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤
- በውጭ የሚኖሩ ጉዳያቸውን በውክልና ለማስጨረስ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ (አውታንቲኬት) ሆኖ የመጣ ውክልና ማቅረብ፤
- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤
- የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤
- ያላገባ/ች ከሆነ/ች 6 ወር ያላለፈው የምስክር ወረቀት፤
- ያገባ/ች ከሆነ/ች የትዳር አጋር የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ 2 ኮፒ፤
- የምዝገባ ማረጋገጫ (print out) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤
- የምዝገባ የምስክር ወረቀት ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤
- የባንክ ምዝገባ ማረጋገጫ ከተመዘገቡበት ባንክ የሚቀርብ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤
- የባንክ የቁጠባ ደብተር ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ (ፎቶ ባለው በኩል)፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤
- ቅጽ -09 (ከወረዳ ተሞልቶ ታሽጎ የሚላክ) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤
- የጠፋ ሰነድ ካለ የፖሊስ ማስረጃ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤
- 4×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ 4፤
- ፍቺ ካለ በፍ/ቤት የፀደቀ ፍቺ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤
- የንብረት ክፍፍል ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤
- ባለ ዕድለኛው በሞት ከተለየ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤
- የወራሽነት ማስረጃ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ ባለ እድለኛው ወይም ወኪሉ ይዞ መቅረብ አለባቸው።
የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ የሚመጣ ማንኛውም ባለጉዳይ #እንደማይስተናገድ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጥብቅ አሳስቧል።
#በውጭ_ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊ ከላይ የተጠቀሱትን ማሟላት #የግድ_ሆኖ ፦
• የታደሰ ፓስፖርት ወይም ቢጫ ካርድ (yellow card) የታደሰ፤
• በውክልና ከሆነ የውክልና ወረቀቱ በጀርባው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተም የተረጋገጠ እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል ተብሏል።
ባለዕድለኞች / ወኪላቸው በ60 የስራ ቀናት ውስጥ ካልተዋዋሉ ምን ይፈጠራል ?
ባለእድለኞች ወይም ወኪላቸው ምዝገባ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ #ቤቱን_እንዳልፈለጉት_ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ የከተማው ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአጽንኦት አሳስቧል።
Credit : አዲስ ዘመን ጋዜጣ

የፖሊስ ማሳሰቢያ !
በማንኛው ሁኔታ ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ፖሊስ በተለያዩ ጊዚያት ባደረገው ቁጥጥር የጦር መሰሪያ የሚያዘዋውሩ ህገወጦች በዓላትን ጠብቀው ርችትን ሽፋን አድርገው ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን እንደሚተኩሱ አረጋግዝቻለሁ ብሏል።
ከዚህ ቀደም በአንድንድ ቦታዎች በርችት ምክንያት ጥፋትን ያስከተሉ አደጋዎች ማጋጣማቸውን ፖሊስ አስታውሶ ለህብረተሰቡ ሰላምና እና ደህንነት ሲባል እንዲሁም ርችት መተኮስ ለጦር መሳሪያ ለሚያዘዋውሩ ህገወጦች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህነንት ሲባል ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ርችት ባለመተኮስ አስፈላጊውን ትብብር እንዲሁም ርችት በመተኮስ የህብረተሰቡን ፀጥታ የሚያውኩ ሲያጋጥመው ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርግ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል ፤ በዓሉን ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ ተገልፆል፡፡
የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ታህሳስ 29 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ዘጠኝ ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የሀገር መከላከያ የኪነ ጥበባት ስራዎች ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡
#AddisAbabaPolice

ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ አርፈዋል።
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በውጪ ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው በተወለዱ 66 ዓመታቸው በታህሳስ 28/ 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3.56 ደቂቃ ከዚህ አለም ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ከአባታቸው አቶ ዘለቀ ሸንቁጥ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አሰለፈች አስፋው በሰኔ 21, 1948 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።
ክብር ሰውነታቸው በታህሳስ 29, 2015 ዓ.ም ከውጪ በአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ጠዋት አቀባበል ከተደረገለት በኋላ ወደ ቄያቸው መኖሪያ ቤታቸው ጉዞ ይደረጋል ተብሏል።
የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም እሁድ ታህሳስ 30, 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9.00 ሰዓት በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሀዋሳ ከተማ ህዝብ የሀይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት ወደ ዘልዓለም መኖሪያቸው ይሸኛሉ።
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ በተለይ በሀዋሳ ከተማ በሆቴል ዘርፍ (ሴንትራል ሆቴል) ከፍተኛ ስራን መስራት የቻሉ ለበርካታ ወጣቶችም የስራ እድል መፍጠር የቻሉ ነበሩ።
(ዶክተር ፍትህ ወልደሰንበት)