TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ከትግራይ ኃይሎች ጋር ርክክብ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ዶቼቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
የሰላም ሂደቱ አካል የሆነ ውይይት ዛሬ መቐለ እየተደረገ ነው።
መቐለ እየተካሄደ በሚገኘዉ ዝግጅት የ32 ሀገራት እና ተቋማት አምባሳደሮች፣ የኢጋድ፣ አፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሲቪልና ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች እየተሳተፉ ነው።
ፌደራል ፖሊስ ዛሬ መቐለ መግባቱ ተገልጿል። በቀጣይ ከትግራይ ሀይሎች ጋር ርክክብ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ።
ከዚህ በተጨማሪ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከመቐለ ቅርብ ርቀት ወዳለችው አጉላ ከተማ መግባታቸውን አንድ የትግራይ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን መግለፃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
Photo Credit : Tegrai Television , Demtsi Weyane
@tikvahethiopia

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፌዴራል ተቋማትን ለመጠበቅ መቐለ ገብቷል ፤ ስራም ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በትግራይ ክልል የሚገኙ በኢፌዲሪ መንግሥት የሚተዳደሩ ፦
- የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣
- የኤሌክትሪክ ኃይል፣
- የቴሌኮም አገልግሎት፣
- የባንክ እና ሌሎች ለኅብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ የፌዴራል ተቋማት ጥበቃ ያደርጋል።
Photo Credit : Ethiopian Federal Police

#ሽረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሽረ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ዛሬ ገልጿል።
አየር መንገዱ ፤ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሶስት ከፍ የሚያደርግ መሆኑንም አሳውቋል።
በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምርም ገልጿል።
አየር መንገዱ ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው ባድረ ገፀ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ ይችላሉ ተብሏል።
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

#Mekelle
- የሰላም የስምምነቱን አፈፃፀም የሚከታተለዉ የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር (monitoring, verification and compliance) ቡድን ዛሬ በይፋ ተቋቁሟል።
• የተልዕኮ ቡድኑ 3 አባላት ያሉት ሲሆን በሰላም ስምምነቱ መሰረት የሲቪልና ወታደራዊ ስምምነቱን አፈፃፀም የሚከታተል ይሆናል።
• ሜጀር ጀነራል ራዲና ስቴፈን ከኬንያ፣ ኮሎኔል ሩፋይ ኡመር ማይሪጋ ከናይጄሪያ ፣ ኮሎኔል ቴፎ ሰኮል ከደቡብ አፍሪካ የተልዕኮ ቡድኑ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።
• አባላቱ በዛሬው እለት የፌደራል ፖሊስ በመቐለ ከተማ ያሉ የመንግስት ተቋማትን የማረካከብ ሂደትን አስፈጽመዋል።
• የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ኮሚቴ ኣጉላዕ ተገኝቶ የትግራይ ኃይሎች የካባድ መሳርያ ትጥቅ የተሰበሰበበት አከባቢ ጎበኝቷል።
- የፌዴራል ፖሊስ መቐለ ከተማ ገብቶ ኃላፊነቱን መወጣት ጀምሯል።
- የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቀለ በቅርብ ርቀት ላይ ወዳለችው አጉዕላ ገብተዋል ፤ የትግራይ ኃይሎች የፈቱትን ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ይረከባሉ።
Photo Credit : ebc

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ፤ ገቢ የተሽከርካሪ ጭነቶችን በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ተሽከርካሪዎች በባቡር ሲጓጓዙ ደህንነታቸው ተጠብቆ ፣ በፍጥነት ፣ በብዛት እና በቀነሰ ወጪ ሀገር ውስጥ ለማድረስ እንደሚያስችል ድርጅቱ አመልክቷል።
ኢባትሎአድ ፤ #ለመጀመሪያው_ጊዜ ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ በባቡር ያጓጓዛቸው ተሽከርካሪዎች በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት " እንዶዴ ባቡር ጣቢያ " ተራግፈው ወደ ገላን የተሽከርካሪ ጊዜያዊ ማቆያ ተርሚናል መጓጓቸውን አሳውቋል።
ተሽከርካሪዎችም ሆኑ ሌሎች ጭነቶች ከ3 እስከ 4 ቀናት በፈጀ ጎዞ ነው ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ የሚደርሱት ጭነቶች በተለይም ተሽከርካሪዎች #በባቡር ሲጓጓዙ ደህንነታቸው ተጠብቆ ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ በሰዓታት ውስጥ ወደ ሀገር እንዲገቡ እንደሚያስችል አመልክቷል።
#ኢባትሎአድ