ፎቶ፦ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በመላው ኢትዮጵያ በ2022 ፤ 11 ሚሊዮን ሰዎችን በምግብ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ ጠንክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከላይ በፎቶው የምንመለከተው ፥ በዛሬው ዕለት ረቡዕ #ከመቐለ የተሰነሳ ሲሆን በWFP የመቐለ መጋዘን ውስጥ ከመከፋፈላቸው በፊት በጥንቃቄ የተከማቹ የአትክልት ዘይት እና ስንዴ ክምችትን ያሳያል።
የአትክልት ዘይቱ እና ስንዴው በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ኤይድ (UAE AID - በፎቶው ላይ የUAE ባንዲራ ይታያል) እና በአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የተበረከተ ስለመሆኑ ተገልጿል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ከ19 ወራት በኃላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን መንገደኞችን ጭኖ መቐለ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረው የመንገደኞች እና የቤተሰቦች ስሜት። #Peace #ETHIOPIA Photo Credit : Tigrai Television @tikvahethiopia
#Update
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአርብ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ #ሁለት ከፍ ማድረጉን አስታውቋል።
በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ እንደሚጨምር ገልጿል።
አየር መንገዱ ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ላይ ሆነው በድረገፅ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን አሳውቋል።
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

#Update #Tigray #ነዳጅ
ዛሬ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ ነዳጅ አዳዮች ከጅቡቲ #ነዳጅ እንዲጫንላቸው ውሳኔ እንዳስተላለፈ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ዘግቧል።
የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ በቀለች ኩማ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ፤ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ትግራይ ክልል ነዳጅ መጫን ተከልክሎ መቆየቱን አስተውሰው ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የኩባንያዎችን ትዕዛዝ እየተቀበለ ነዳጅ መጫን እንዲጀምር ፈቃድ መሰጠቱን አሳውቀዋል።
ይህንንም ተከትሎም ድርጅቱ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ የሚፈልጉትን የነዳጅ መጠን እንዲያሳውቁ መጠየቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " በድረገፁ አስነብቧል።

#AddisAbaba
ሃሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ እያዘጋጁ ሲሸጡ የነበሩ 3 ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
መታወቂያዎቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው ማህተሞችና ወረቀቶችም በብርበራ ተይዘዋል፡፡
እንደ ፖሊስ መረጃ ፤ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አውቶብስ ተራ አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ለዚሁ ህገወጥ ተግባር ማስፈፀሚያ የሚውሉ በአዲስ አበባ አስተዳደር " የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት " እና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ጎንደር ዞን " ደባርቅ ከተማ የቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት " የሚሉ ሃሰተኛ ክብ ማህተሞችን እንዲሁም የግለሰብ የስም ቲተር በማስቀርፅ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርማ ያረፈበትን የመታወቂያ ወረቀት አመሳስለው በማሳተም ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደነበር ተገልጿል።
ማህተሞቹንና ወረቀቶቹን በአንድ የሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ደብቀው በማስቀመጥ የነዋሪነት መታወቂያ ለሚፈልጉ ሰዎች ሃሰተኛ መታወቂያዎችን እያዘጋጁ እንደሚሸጡ ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ ነው።
ግለሰቦቹ ፤ ሃሰተኛ መታወቂያውን ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው ወረቀቶችና ማህተሞች ከተደበቁበት በብርበራ እንደተገኙም ፖሊስ አስታውቋል።
https://telegra.ph/Addis-Ababa-Police-12-29
(አዲስ አበባ ፖሊስ)

ፎቶ ፦ ዛሬ የ32 ሀገራት አምባሳደሮች መቐለ መግባታቸውን ድምፂ ወያነ ዘግቧል።
መቐለ የገቡት ፤ የኢንግሊዝ አምባሳደርን ጨምሮ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት አምባሰደሮች ናቸው ተብሏል።
ከአምባሳደሮቹ ጋር የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የሚገኙ ሲሆን አምባሳደሮቹ በመቐለ ቆይታቸው በሰላም ስምምነቱ ዙርያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Photo Credit : Demtsi Weyane
@tikvahethiopia
መቐለ የገቡት ፤ የኢንግሊዝ አምባሳደርን ጨምሮ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት አምባሰደሮች ናቸው ተብሏል።
ከአምባሳደሮቹ ጋር የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የሚገኙ ሲሆን አምባሳደሮቹ በመቐለ ቆይታቸው በሰላም ስምምነቱ ዙርያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Photo Credit : Demtsi Weyane
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ዛሬ የ32 ሀገራት አምባሳደሮች መቐለ መግባታቸውን ድምፂ ወያነ ዘግቧል። መቐለ የገቡት ፤ የኢንግሊዝ አምባሳደርን ጨምሮ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት አምባሰደሮች ናቸው ተብሏል። ከአምባሳደሮቹ ጋር የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የሚገኙ ሲሆን አምባሳደሮቹ በመቐለ ቆይታቸው በሰላም ስምምነቱ ዙርያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። Photo Credit : Demtsi Weyane…
ፎቶ ፦ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት እና የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎች የሰላም ስምምነቱን ሲያሳልጡ የነበሩ አካላት ዛሬ መቐለ ገብተዋል።
የሰላም ስምምነቱን የመሩት አካላት አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት ቡድን መቐለ የገባው በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማቆም በተደረሰው ስምምነት መሠረት የተቋቋመውን የጋራ የክትትልና የማረጋገጫ ሥርዓት ለማስጀመር እንደሆነ ታውቋል።