#Woldia
በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል።
ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል።
ክልከላዎቹ ፦
- ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።
- ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ፤ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሥራ ከተመደቡ ተሽከርካሪዎች ውጭ በዚህ ምደባ ስምሪት ያልታቀፉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00 ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።
- የሰው እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሥራ ከተመደበው ሰው ውጭ ከምሽቱ 3:00 እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ለጸጥታ ሥራ ስምሪት ከተመደበ አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።
- አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።
- የመንግሥትን የታጠቀ ኀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ፣ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሰጠ፣ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል።
- የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ሕግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ ተጥሎበታል ፤ የማይተባበር በሕግ ይጠየቃል ተብሏል።
የኮማንድ ፖስቱ በአብዛኛውን በሌሎች ከተማዎች የተጣሉ ክልከላዎችን አይነት ይዘት ያለው ክልከላ ነው የጣለው። (#ሙሉ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)
ኮማንድ ፖስቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ምክንያቶች ፦ በከተማው የተጀመሩ ልማቶችን " አመጹን መቀላቀል ሲገባህ ልማትን እያስቀጠለክ " በሚል ዛቻ ልማትን የማደናቀፍ ፤ በሙስና፥ በሌብነት፥ እና በተለያዩ ብልሹ ወንጀሎች ስጋት ያለባቸው አካላት የዕለት ጉርስ ፈላጊዎችን በገዘብ በመግዛት ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠርና ለማባባስ የሚያደርጉት ሙከራ በመረጃ ደረጃ የተገኘ በመሆኑ ነው ብሏል።
ከዚህ ባለፈ የትንሳኤ እና የረመዳን ሃይማኖታዊ ሁነቶችን በሰላም ለማጠናቀቅ ለዕኩይ ዓላማ የተሰማሩ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ነው ሲል አሳውቋል።
(የወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia