TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዛሬ ምሽት አሳውቋል። ባንኩ በቀጣይ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ አገልግሎቱን በማስፋትና በየደረጃው በሁሉም ቅርንጫፎች ላይ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሰራ ገልጿል። በሰሜን…
#Lion #Wegagen
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሽረ እንደስላሴና አካባቢው የሚገኙት ቅርንጫፎቹ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፤ ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በአላማጣና በራያ ጥሙጋ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።
ባንኩ ሰቲት ሁመራ፣ አዲ ረመፅ ፣ ዳንሻ እና ተከዜ ቅርንጫፎች ቀደም ብለው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውሷል።
በቅርቡም ፤ #በመቐለ እና #በሽረ ዲስትሪክቶች በሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።
በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማሳወቁ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

#ETHIOPIA
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የህዝብ እና ቤት ቆጠራ #የፊታችን መጋቢት 29 ይካሄዳል " ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።
ቃላቸውን ለመረጃ ማጣሪያው የሰጡት የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳፊ ገመዲ " የህዝብና ቤት ቆጠራ የፊታችን መጋቢት 29 ይካሄዳል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ ነው " ብለዋል።
የህዝብና ቤት ቆጠራ የሚካሄድበትን የጊዜ ሠሌዳ በፌዴሬሽንና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች እንደሚወስን ገልጸው ምክር ቤቶቹ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።
ም/ቤቶቹ 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ እንዲራዘም በተደጋጋሚ መወሰናቸው ይታወሳል።
#ኢትዮጵያቼክ

#USA #NorthKorea
አሜሪካ #ኑውክሌር_የመሸከም አቅም ያላቸውን " B-52 " ቦምብ ጣይ ጄቶቿን ዛሬ በደቡብ ኮሪያ አቅራቢያ ለልምምድ ማብረሯን ቪኦኤ ዘግቧል።
በረራው ከሰሜን ኮሪያ ሊመጣ የሚችልን ስጋት የመመከት አቅሟን ለማሳየት ነው ተብሏል። በተጨማሪም F-22 የተባሉትን ስቲልዝ ተዋጊ ጄትችንም ማብረሯ ተሰምቷል።
ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ F-35A እና F-15K ይተሰኙ ተዋጊ ጄቶቿን በልምምዱ ማሳተፏን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሀገራቱን ልምምዱን ያደረጉት በዚህ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚሳዬል ሙከራ ላደረገችውና በአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ላይ ዛቻዋ እየጨመረ ለመጣው ሰሜን ኮሪያ ጡንቻቸውን ለማሳየት እንደሆነ ነው የቪኦኤ ዘገባ የሚያስረዳው።
2ቱ አገሮች ወታደራዊ ልምምዳቸውን ለማጠናከርና በአሜሪካ በኩል የሚቀርቡትን የመሣሪያና ጄቶችን ቁጥር ለመጨመር፣ እንዲሁም አሜሪካ ደቡብ ኮሪያን ለመከላከል የገባቸውን ቃል በተግባር እንድታጠናክር ባለፈው ወር ተስማምተው ነበር።
የደቡብ ኮሪያው የመከላከያ ሚኒስቴር ፤ ያንን ስምምነት በመጥቀስ፣ ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌርና የሚሳዬል ዛቻ መልስ ለመስጠት ሁለቱ አጋሮች የመከላከያ ብቃታቸውን ማሳየታቸውን ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት ብቻ እጅግ ተደጋጋሚ ሚሳኤል ስታስወነጭፍ የነበር ሲሆን ከቀናት በፊትም መካከለኛ ርቀት ያላቸውን ባሊስቲክ ሁለት ሚሳዬሎች አስወንጭፋለች።
ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የስለላ ሳተላይት ለመላክ ወሳኝና የመጨረሻ ሙከራ ነው ማለቷን ዘግባው ያሳያል።

T-MAX FLASH
በጣም ፍጥነት ያለውን T-MAX USB Flash Disc ለገበያ አቅርበናል።
💎 ጫፉ የማይሸራረፍ ባለ ብረት
💎 ፍጥነቱ በጣም ጥሩ የሆነ
💎 ከተጠቀሙ በኋላ ወደ ውስጥ የሚሰበሰብ ዲዛይን
💎 ከጀርባው ህትመት/Logo ለማስቀመጥ ምቹ
🔔በፈለጉት መጠን በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን
➭ 8 GB /16 GB/32 GB /64 GB/128 GB
☎️ 0933111111 / 0911676767
🌟የ T-Max Electronics ምርቶችን ለማየት ተከታዩን ሊንኩን ይጠቀሙ፦
https://linktr.ee/tmaxelectronics
📍 አድራሻ፦ መርካቶ ይርጋ ኃይሌ ህንጻ ሱቅ ቁጥር G-96 Ground Floor
www.tmaxelectronics.com

#Woldia : የወልድያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በይፋ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቀረበ።
ጤና ጣቢያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው ደብዳቤ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ጦርነት ከተጎዱት ተቋማት መካከል አንዱ ይኸው የወልድያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አንዱ ስለመሆኑ ገልጿል።
በጦርነት ወቅት በደረሰው ጉዳት ተቋሙ ከህንፃው በቀር ምንም ነገር የሌለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑና ሁሉም ዜጋ በጨለማ የሚዋለዱትን እናቶችን ፣ የሞያተኞችንም ችግር በመመለከት በቻለው መጠን እገዛ እንዲያደርግ ይፋ ጥሪ አቅርቧል።
1. ለጥበቃ ምቹ የሆነ በር ስለሌለዉ በር ማሰራት የሚቻልበት፤
2. ዙሪያ ገባው አጥር የሌለዉ ስለሆነ አጥር የሚሰራበት፤
3. መብራት ሲጣፍ የላብራቶሪ አገልግሎት የወሊድ አገ/ት መስጠት ስለማይቸል ጄኔነተር የሚማላበት፤
4. የዉስጥ ለዉስጥ የዉሃ መስመር ከቆይታው የተነሳ የተበላሽ ስለሆነ የማደስ ስራ የሚሰራበት፤
5. የማዋለጃ ቁሳቁስ እና ሌሎች የቁስል መስፊያ መቀሶች ማጽጃ (Sterilizeation ማለትም Auto Clive መግዛት የምንችልበት (ልግሳ)፤
6. የጸሀፍት መሳሪያ ፣ ኮምፒዉተር እና ፕሪንተሮች ለማሟላት
7. ወንበርና ጠረጴዛዎች አጅግ አንገብጋቢ ችግሮች ስለሆኑ አቅም ያላችሁ ሁሉ የድጋፍ ትብብር ታደርጉ ዘንድ በጤና ጣቢያው ታካሚዎች እና በወልድያ ማህበረሰብ ስም ተጠይቋል።
የባንክ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000023835871
ይህ ጤና ጣቢያ ከ1964 ዓ/ም ጀምሮ ከሆስፒታል ባልተናነሰ መልኩ በዙሪያው ላለው የገጠር ቀበሌና ለከተማ አስተዳደሩ ህዝብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

" ... ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም " - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።
ዜጎች ፤ የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶችን ከመንግስት ተቋማት ማግኘት #ፈተና_እንደሆነባቸውም ተቋሙ ገልጿል።
የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ የሆኑት ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሠጡት ቃል ፤ " እንደ አጠቃላይ እንደ ሀገር የመልካም አስተዳደር ችግሩ እየሰፋ ተፈጥሮውም Complex (ውስብስብ) እየሆነ ነው የመጣው ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም ፤ ይሄንን መንግስትም የሚያውቀው ጉዳይ ነው " ብለዋል።
" የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙለት የሚቋቋሙበት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ነው " ያሉት ዶ/ር እንዳለ " ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ ከዜጎች የሚሰበሰብ ታክስ አለ፣ ከዜጎች ከሚሰበሰብ ታክስ ነው እያንዳንዱ የመንግስት ተቋም የሚተዳደረው ፣ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዙ የሚከፈለው ፤ ነገር ግን #ከህብረተሰቡ_በሚሰበሰበው_ታክስ ፣ ህብረተሰቡ ከሚያወጣው ወጪ አንፃር አገልግሎት እየተሰጠነው የሚል አጠቃላይ ግምገማ የለንም " ሲሉ ገልፀዋል።
ይህ ችግር ለዜጎች ሰፋ ያለ አገልግሎቶችን መስጠት በሚጠበቅባቸው የመንግስት ተቋማት የሚብስ ሲሆን ከተማ አስተዳደር፣ ወረዳ እና ቀበሌ ዋና ዋና ተጠቃሽ ናቸው።
ዶ/ር እንዳለ " በተለይ የከተማ አስተደሮች አካባቢ ፤ በተለይ ማዘጋጃ ቤቶች አካባቢ፣ ሰፋፊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አካባቢ እንደ #ወረዳ ፣ #ቀበሌ ፣ #ከወሣኝ_ኩነት ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለ መንግስትም ያምናል የኛም ግኝት ያን ያመለክታል " ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፥ " በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የመልካም አስተዳደር ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው ? " የሚለውን ካሉት 22 ሚኒስትር መ/ቤቶች ሰፋፊ አገልግሎት በሚሰጡ 15 መ/ቤቶች በቅርብ ቀን ጥናት በማድረግ ለህዝብ እናሳውቃለን ሲል ለሬድዮ ጣቢያው አሳውቋል።
#credit_ሸገር_ኤፍ_ኤም

" ... ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም " - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል። ዜጎች ፤ የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶችን ከመንግስት ተቋማት ማግኘት #ፈተና_እንደሆነባቸውም ተቋሙ ገልጿል። የተቋሙ ዋና ዕንባ…
" የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙለት የሚቋቋሙበት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ነው።
ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ ከዜጎች የሚሰበሰብ #ታክስ አለ፣ ከዜጎች ከሚሰበሰብ ታክስ ነው እያንዳንዱ የመንግስት ተቋም የሚተዳደረው ፤ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዙ የሚከፈለው።
ነገር ግን ከህብረተሰቡ በሚሰበሰበው ታክስ ፣ ህብረተሰቡ ከሚያወጣው ወጪ አንፃር አገልግሎት እየተሰጠ ነው የሚል አጠቃላይ ግምገማ የለንም "
/ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ /

" በነዚህ ወጣቶች ያለጊዜ ሕልፈት የተሰማኝን ሐዘን ገልፃለሁ " - ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ
ከትላንት በስቲያ ታህሳስ 10 /2015 በመዲናችን አዲስ አበባ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኛ አብራው የምትኖረውን እጮኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኃላ እራሱን ከ13ኛ ፎቶ ወርውሮ (መገናኛ አምቼ ፊት ለፊት ባለዉ የፌደራል ዳኞች መኖሪያ ጊቢ) ህይወቱን ማጥፋቱ በርካቶችን አሳዝኗል የመዲናይቱም መነጋገሪያ ሆኗል።
ዳኛው ትንሳኤ በላነህ የሚባል ሲሆን በዕለቱ እራሱን ከ13 ፎቅ ላይ ወርውሮ ከማጥፋቱ በፊት አብራዉ የምትኖረዉን እጮኛውን ህይወት አጥፍቷል።
ህይወቱ ከማለፉ ከሰዓታት በፊትም በ " ፌስቡክ ገፁ " ላይ ፅፎታል የተባለ አንድ መልዕክትም በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የብዙሃን መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ፤ ክስተቱ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ገልፀዋል።
" ባልተጠበቀ ሁኔታ እጮኛቸውን በመግደል ራሳቸውን ያጠፉት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኛ ተንሳይ በላይነህ ሞት በጣም አሳዛኝ ነው " ያሉት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ፤ " ዳኛው #መደበኛ_ያልሆነ ጠባይ ያሳዩ እንደነበረ ይህ ሁኔታ ከተከሰተ በኃላ ተጠቁሟል " ሲሉ ገልፀዋል።
" የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት መደበኛ ሥራ መሥራት የሚችሉ ሰዎች ሥራቸውን እያከናወኑ አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤንነት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ፤ " ያሉት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንቷ " እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲታዩ እገዛ ሊያደርግ ለሚችል ክፍል ማሳወቅ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።
በወጣቶቹ ያለጊዜ ሕልፈት ሐዘን እንደተሰማቸው የገለፁት ወ/ሮ መዓዛ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

#US
አሜሪካ መላ ዜጎቿን ለመግደል በቂ የሆነ " ፌንታሊን " የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ማያዟን አስታወቀች።
የአሜሪካ የዕጽ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እየተጠናቀቀ ባለው 2022 መላውን የአሜሪካ ዜጋ ለመግደል በቂ የሆነ " ፌንታሊን " የተሰኘ አደገኛ አደንዛዥ ዕጽ መያዙን አሳውቋል።
ባለስልጣኑ፤ በአንዴ እንዲወሰዱ ተደርገው የተዘጋጁ እያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊግራም የሚመዝኑ ገዳይ የሆኑ 379 ሚሊዮን ፌንታሊን የተሰኘ ዕጾችን ይዣለሁ ብሏል።
ይህ አደንዛዥ ዕጽ ከሄሮይን 50 እጥፍ በላይ ገዳይ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን "ፌንታኒል አሜሪካ በአሁኑ ወቅት የገጠማት ገዳይ ስጋት ነው " ሲል ገልጾታል።
ይኸው የዕፅ ተቆጣጣሪ መ/ቤት እንደሚለው፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ፌንታሊን ወደ አሜሪካ የሚገባው #ከሜክሲኮ ሲሆን ከ4 ሺ 500 ኪግ በላይ ፌንታሊንና 50.6 ሚሊዮን በእንክብል መልክ የተዘጋጁ ዕጾች ተይዘዋል።
በእንክብል መልክ የተዘጋጁት ዕጾች ህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች እንዲመስሉ መደረጋቸውን ተገልጿል።
እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት የተያዘው የዕጽ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል።
አንደ ባለስልጣኑ መረጃ፤ በአሜሪካ የሚያዙት ዕጾች " በሲናሎዋ እና ጃሊስኮ " ዕጽ አዘዋዋሪ ቡድኖች አማካይነት ሜክሲኮ ውስጥ በምስጢራዊ ስፍራ በሚገኙ ፋብሪካዎች ይመረታሉ።
"ፌንታሊን" እጅግ አደገኛ የሆነ ዕጽ ሲሆን የእርሳስ ጫፍ ላይ ልትቀመጥ የምትችል ትንሽ መጠን እንኳን የመግደል አቅም አላት።
ማጠቃለያ፦
- ባለፈው ዓመት 100 ሺ አሜሪካውያን ከመጠን በላይ ዕጽ ወስደው ሕይወታቸው አልፏል። ከዚህ ውስጥ ሁለት ሦስተኛው ሞት ከፌንታሊን ጋር የተገናኘ ነው።
- በዚህ ዓመት የተያዘው ፌንታሊን መጠን 330 ሚሊዮን የአሜሪካ ነዋሪዎች መግደል የሚችል ነው።
#BBC

#AddisAbaba
በRomal የክር ጥበብ(String Art) እና በአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የክር የስዕል ጥበብ አዉደ-ርዕይ ከታህሳስ 2 ጀምሮ ለተመልካች ክፍት ሆኖ እየተጎበኘ ይገኛል።
ይህን አውደ ርዕይ እስከ ፊታችን እሁድ ታህሳስ 16 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ በመሆኑ ታዳሚያን #በዲሊኦፖል ሆቴል ተገኝተው በነጻ እንዲጎበኙ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።
የክር ጥበብ(String Art) እንዴት ይሰራል ?
የክር ጥበብ ያለ ምንም ቀለም በተለያዩ የክር ውጤቶች፣ ጥቃቅን ሚስማሮችና መደብ የሚሆን እንጨተት (MDF) አማካኝነት የሚሰራ የጥበብ ውጤት ነው።
ለአብነት ያክል ከላይ በፎቶ የተያያዘው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ መልክ የተሰራው የጥበብ ሥራ ከ4000 በላይ ሚስማሮች(የባከኑትን ጨምሮ)፣ 9 አይነት የክር አይነቶች ጥቅም ላይ ውለዋል።
በተጨማሪም ሚስማሩን ቅርጽ አሲዞ ለመምታት ወደ 11 ሰዓታት የፈጀ ሲሆን ቀሪው በ4 ቀናት ውስጥ ሥራው ተጠናቋል።
ይህ የጥበብ ሥራ በዚህ የአውደ ርዕይ ወቅት የሚሸጥ ከሆነ አዘጋጆቹ 180 ሺ ብር ተመን አውጥተውለታል።
በአውደ ርዕዩ ከ50 በላይ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን ሁለት ወጣቶች በዋነኛነት፤ በአጠቃላይ አራት ወጣቶች በሥራው ላይ ተሳትፈውበታል። በቀጣይ የተለያዩ ሥራዎችን አካተው የአርት ጋላሪ የመክፈት እንዲሁም በዲጂታል አማራጭ ሥራቸውን የመሸጥ ትልም አላቸው።
NB: ከላይ በፎቶ የምትመለከቷቸው የጥበብ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በክር የተሰሩ ሲሆኑ ክሮቹ ተጠላልፈው ከፈጠሩት ቀለም ውጭ ምንም አይነት ቀልም አልተጠቀሙም።
More : @tikvahethmagazine