TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን #ለውጭ_ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል። የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን…
#ETHIOPIA
በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረግ ሂደት ውስን ቁጥር ባላቸው የውጭ ባንኮች ብቻ የሚጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆኖ የቆየው የባንክ ዘርፍ በቅርቡ ክፍት እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ለኢዜአ የሰጡት ማብራሪያ ፦
- የውጭ ባንኮች የካበተ ልምድ ይዘው ስለሚመጡ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ለማነቃቃት ትልቅ እድል ነው።
- የውጭ ባንኮች ይዘውት የሚመጡት ካፒታል በኢትዮጵያ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት በማቃለል ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
- መንግስት በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ ለመሳተፍ የሚመጡ የውጭ ባንኮችን በሙሉ ተቀብሎ ፈቃድ አይሰጥም። ለመነሻነት ውስን የውጭ ባንኮችን ብቻ ያስተናግዳል።
- የውጭ ባንኮችን ለማስተናገድ አራት ቅድመ ሁኔታዎች ተዘጋጅተዋል።
- ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት ባንኮች በኢትዮጵያ ንዑስ ባንክና ቅርንጫፍ ለማቋቋም የሚጠይቁና ከሀገር ውስጥ ባንኮች እስከ 40 በመቶ አክሲዮን የሚገዙ ናቸው።
- ከአገልግሎት አንፃር በተለይ ለግብርና፣ ለቤትና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታ እንዲሁም ለገጠር አካባቢዎች የተለያዩ አገልግሎት ለመስጠት አልመው የሚመጡ ባንኮች የሚኖራቸው ፋይዳ ጉልህ ነው።
- የውጭ ባንኮች መልካም እድል ይዘው እንደሚመጡት ሁሉ ስጋቶች ይኖራሉ ስጋቶችን ለመቀነስም በዘርፉ ያለው ልምድ እየዳበረ እስከሚሄድ ድረስ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ባንኮችን ቁጥር በመገደብና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በትኩረት ይሰራል።
(ኢዜአ)
@tikvahethiopia

Photo
#Update
ላለፉት ቀናት በኬንያ፣ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው የመንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር (ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና የፖለቲካ ተደራዳሪዎች የተገኙበት) የተደረሰበት ደረጃ እና ስምምነትን በተመለከተ በአሁን ሰዓት መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፣ ኡሁሩ ኬንያታ ፣ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በመድረኩ ላይ ተሰይመዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ።

#Update ላለፉት ቀናት በኬንያ፣ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው የመንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር (ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና የፖለቲካ ተደራዳሪዎች የተገኙበት) የተደረሰበት ደረጃ እና ስምምነትን በተመለከተ በአሁን ሰዓት መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፣ ኡሁሩ ኬንያታ ፣ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በመድረኩ ላይ ተሰይመዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ።…
#Update
በአሁን ሰዓት በናይሮቢ እየተሰጠ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ባለፈው በደቡብ አፍሪካ፣ ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ።
@tikvahethiopia
በአሁን ሰዓት በናይሮቢ እየተሰጠ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ባለፈው በደቡብ አፍሪካ፣ ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአሁን ሰዓት በናይሮቢ እየተሰጠ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ባለፈው በደቡብ አፍሪካ፣ ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BREAKING
በናይሮቢ ሳምንት ያህል የፈጀውን ውይይት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አዛዦች #ጦርነቱን_ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል ዛሬ ወታደራዊ አመራሮቹ በናይሮቢ ስምምነቱን ለማስፈጸም የሚያችል ስነድ ተፈራርመዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ይጠብቁ።
Video Credit : Ruud Elmendrop

#BREAKING በናይሮቢ ሳምንት ያህል የፈጀውን ውይይት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አዛዦች #ጦርነቱን_ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል ዛሬ ወታደራዊ አመራሮቹ በናይሮቢ ስምምነቱን ለማስፈጸም የሚያችል ስነድ ተፈራርመዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ይጠብቁ።…
#Update
የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ለሰብአዊ ርዳታ " ያልተገደበ እንቅስቃሴን ለማመቻቸት " መስማማታቸውን ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ለሰብአዊ ርዳታ " ያልተገደበ እንቅስቃሴን ለማመቻቸት " መስማማታቸውን ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
በሰላም ስምምነቱ መሠረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ መክረዋል።
በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቐለ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም #ተስማምተዋል። ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል።
ለዕቅዱ ተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ማሳሰቡን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ከናይሮቢው ስምምነት በኃላ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

#Update በሰላም ስምምነቱ መሠረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ መክረዋል። በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቐለ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም #ተስማምተዋል። ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል። ለዕቅዱ ተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት…
#Update
የአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የዛሬው ስምምነት ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት መጠበቅ፣ የትጥቅ መፍታትን እና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ጉልህ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
የአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የዛሬው ስምምነት ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት መጠበቅ፣ የትጥቅ መፍታትን እና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ጉልህ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የዛሬው ስምምነት ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት መጠበቅ፣ የትጥቅ መፍታትን እና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ጉልህ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። @tikvahethiopia
#Africa
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
" ዛሬ የተፈረመው ስምምነት #የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈታሉ የሚለውን እሳቤ እንዲጸና ያደረገ ነው ። "
#ENA
@tikvahethiopia
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
" ዛሬ የተፈረመው ስምምነት #የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈታሉ የሚለውን እሳቤ እንዲጸና ያደረገ ነው ። "
#ENA
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Africa አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦ " ዛሬ የተፈረመው ስምምነት #የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈታሉ የሚለውን እሳቤ እንዲጸና ያደረገ ነው ። " #ENA @tikvahethiopia
#Update
ዛሬ በናይሮቢ #በተፈረመው_ስምምነት መሰረት ፤ በሚቀጥሉት 7 ቀናት ወታደራዊ ሀላፊዎቹ ለወታደሮቻቸው ኦረንቴሽን እንደሚሰጡና ከዛም የፌደራል ባለስልጣናት በትግራይ ኃላፊነታቸውን እንደሚረከቡ ይገልፃል።
የከባድ መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትም በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ኃይሎች እና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ እንደሚፈፀም ይገልጻል።
የቀላል መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትን ለማሳለጥ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ኮሚቴ እንደሚቋቋምም የስምምነት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል።
(Credit : ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)