TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ይጠብቁ

ላለፉት ቀናት በኬንያ ፤ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (የወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮች የተሳተፉበት) የሰላም ንግግር የደረሰበት ደረጃ እና ስምምነት ይፋ ይደረጋል።

@tikvahethiopia
#ENDF

የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ለህ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ተወሰነ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አሁን በሥራ ላይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል።

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔ ካሰለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ነው።

ምክር ቤቱ ፤ መከላከያ ሠራዊቱ የሪፎርም ስራ ውስጥ እንደሚገኝ አስታውሶ ይህን ሪፎርም የበለጠ ለማጎልበት እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ከመከላከያ ሠራዊቱ ወቅታዊ እና የወደፊት ግዳጆች ጋር የሚጣጣም የህግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ በሥራ ላይ ያለውን አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ መቅረቡን አመልክቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል #ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሙሉ ድምጽ እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

(የዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ENDF የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ለህ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ተወሰነ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አሁን በሥራ ላይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል። የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔ ካሰለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ የመከላከያ…
" ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን "

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦

" በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩት ግጭቶች #በሰላማዊ_መንገድ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በተደራጀ ኃይል ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ፣ በአገሪቱ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲሳተፉ ለማስቻል ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ "

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ከንጋቱ 11:30 አንስቶ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ በአዲስ አበባ ፤ በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል።

ሩጫው መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሲሆን ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦

- ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን  ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአጎና ሲኒማ  ወደ መስቀል አደባባይ
- በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
- ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
- ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
- ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
- ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ
- ከትንባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
- ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
- ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
- ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
- ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
- ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
- ከሐራምቤ ሆቴል  ወደ መስቀል
- ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
- ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በውድድር መስመር  ግራ እና ቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው።

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ #ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይጠብቁ ላለፉት ቀናት በኬንያ ፤ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (የወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮች የተሳተፉበት) የሰላም ንግግር የደረሰበት ደረጃ እና ስምምነት ይፋ ይደረጋል። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

በኬንያ ፤ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረውን የሰላም ውይይት ተከትሎ የተደረሰበትን ስምምነትና ደረጃ በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ዝርዝር መግለጫ ከተባለበት ሰዓት ዘግይቷል።

የዘገየበት ምክንያት አይታወቅም።

ዝርዝር መግለጫው እየተጠበቀ ነው።

የኬንያው #CitizenTV ከስፍራው ያቀረበውን ዘገባ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኬንያ ፤ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረውን የሰላም ውይይት ተከትሎ የተደረሰበትን ስምምነትና ደረጃ በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ዝርዝር መግለጫ ከተባለበት ሰዓት ዘግይቷል። የዘገየበት ምክንያት አይታወቅም። ዝርዝር መግለጫው እየተጠበቀ ነው። የኬንያው #CitizenTV ከስፍራው ያቀረበውን ዘገባ ይመልከቱ። @tikvahethiopia
Photo : ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ በኬንያ ፤ ናይሮቢ ቆመው ሲነጋገሩ።

Photo Credit : ጋዜጠኛ ዳይላን ጋምባ (ኤኤፍፒ) ፣ ጋዜጠኛ አየናት መርሴ (ሮይተርስ) ፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን #ለውጭ_ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል። የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን…
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረግ ሂደት ውስን ቁጥር ባላቸው የውጭ ባንኮች ብቻ የሚጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆኖ የቆየው የባንክ ዘርፍ በቅርቡ ክፍት እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ለኢዜአ የሰጡት ማብራሪያ ፦

- የውጭ ባንኮች የካበተ ልምድ ይዘው ስለሚመጡ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ለማነቃቃት ትልቅ እድል ነው።

- የውጭ ባንኮች ይዘውት የሚመጡት ካፒታል በኢትዮጵያ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት በማቃለል ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

- መንግስት በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ ለመሳተፍ የሚመጡ የውጭ ባንኮችን በሙሉ ተቀብሎ ፈቃድ አይሰጥም። ለመነሻነት ውስን የውጭ ባንኮችን ብቻ ያስተናግዳል።

- የውጭ ባንኮችን ለማስተናገድ አራት ቅድመ ሁኔታዎች ተዘጋጅተዋል።

- ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት ባንኮች በኢትዮጵያ ንዑስ ባንክና ቅርንጫፍ ለማቋቋም የሚጠይቁና ከሀገር ውስጥ ባንኮች እስከ 40 በመቶ አክሲዮን የሚገዙ ናቸው።

- ከአገልግሎት አንፃር በተለይ ለግብርና፣ ለቤትና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታ እንዲሁም ለገጠር አካባቢዎች የተለያዩ አገልግሎት ለመስጠት አልመው የሚመጡ ባንኮች የሚኖራቸው ፋይዳ ጉልህ ነው።

- የውጭ ባንኮች መልካም እድል ይዘው እንደሚመጡት ሁሉ ስጋቶች ይኖራሉ ስጋቶችን ለመቀነስም በዘርፉ ያለው ልምድ እየዳበረ እስከሚሄድ ድረስ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ባንኮችን ቁጥር በመገደብና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በትኩረት ይሰራል።

(ኢዜአ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ላለፉት ቀናት በኬንያ፣ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው የመንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር (ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና የፖለቲካ ተደራዳሪዎች የተገኙበት) የተደረሰበት ደረጃ እና ስምምነትን በተመለከተ በአሁን ሰዓት መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፣ ኡሁሩ ኬንያታ ፣ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በመድረኩ ላይ ተሰይመዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ።

@tikvahethiopia