TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ጥዋት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ በዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ #በመደርመሱ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ በተመለከተ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ለደ/ሬ/ቴ/ድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ፦
- አራት መቶ አስራ አምስት (415) ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ ተደርምሷል።
- የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው አልፏል።
- በድልድዩ መደርመስ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራት ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- ተጎጂዎች በሪፌራል፣ ያኔት፣ አላትዮን፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል ፤ የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።
የተማሪ ወላጆችም ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን ሁሉ እየተወጣ መሆኑን አስታውቋል።
በተጨማሪ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች በጥዋቱ ያልተጠበቀ አደጋ ምክንያት ለዛሬ የታቀዱትን ፈተናዎች መፈተን እንዳልቻሉ ገልጾ ፤ በሁኔታው ተደናግጠው ከግቢ የወጡም ሆኑ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደነበሩበት እንዲመለሱና ለነገ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳስቧል።
@tikvahethiopia

#Update የጥዋቱ የፈተና መርሀ ግብር ተጠናቋል። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት / በዩኒቨርሲቲዎች / ውስጥ መስጠት የጀመረው የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዛሬ ጥዋት መርሃግብር መጠናቀቁን አሳውቋል። ከሰዓት ብሔራዊ ፈተናው በተያዘለት መርሃግብር የሚቀጥል ይሆናል ብሏል። More : @tikvahuniversity
#Update
ትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቆ ተማሪዎች ለቀጣዩ ቀን ፈተና እየተዘጋጁ መሆኑን አሳውቋል።
በዛሬዉ እለት የተጀመረዉ 12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዕለት ፈተና መጠናቀቁን የገለፀው ሚኒስቴሩ " ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከተፈጠረዉ አሳዛኝ ክስተት እና በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ፈተና ሳይፈተኑ ከወጡ ተማሪዎች ሪፖርት ዉጪ አጠቃላይ ሂደቱ የተሳካ ነበር " ብሏል።
ፈተናው በመላው ሀገሪቱ ካሉት 130 የፈተና ጣቢያዎች በ128ቱ ጣቢያዎች ላይ ነበር ሲሰጥ የዋለው።
ትምህርት ሚኒስቴር የዛሬውን ፈተና ያጠናቀቁ ተማሪዎች በነገው ዕለት ለሚኖራቸዉ የሁለተኛ ቀን ፈተና ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል።

#HappeningNow የሀሳብ ቅኝት የተሰኘው በሀሰተኛ መረጃ እንዲሁም የጥላቻ ንግግርን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኮረው ልዩ የወጣቶች መድረክ በሸራተን አዲስ መካሄድ ጀምሯል። ዝግጅቱን ኦላይን መከታተል ለምትፈልጉ https://fb.watch/g3zmdGYwI6/ @tikvahethmagazine
#የሐሳብ_ቅኝቶች
የሐሳብ ቅኝቶች የተሰኘው የወጣቶች መርሐግብር የመጀመሪያ ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።
በመድረኩ " ሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር " ን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
እንዲሁም ልዩ ልዩ መርሐግብሮች ተከናውነዋል።
በነገው ዕለት የዝግጅቱ ሁለተኛ ክፍል የሚቀጥል ሲሆን በዕለቱ ለመገኘት #ከተመዘገቡ በተጨማሪ #ላልተመዘገቡ ተሳታፊዎች ጭምር እንዲሳተፉ እድሉ ተመቻችቷል።
ነገ ከጠዋቱ 3:00 ላይ በ " ሸራተን አዲስ ሆቴል " በመገኘት መሳተፍ ትችላላችሁ። ዝግጅቱ ምንም አይነት መግቢያ የሌለው (ነፃ) መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
በተጨማሪም ለተሳታፊዎች የተሳትፎ " ሰርተፊኬት " በማጠቃለያው መርሐግብር የሚሰጥ ይሆናል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
ይኸው የፈተና መርሀ ግብር ዛሬ ከሰዓት በኃላም ይቀጥላል።
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና መርሀግብር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ነገ ጥቅምት 2 / 2015 የሚጠናቀቅ ሲሆን ተማሪዎች ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 4 ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።
በሌላ በኩል ፤ ትላንት የድልድይ መደርመስ አደጋ ደርሶ የአንድ ተማሪ ህይወት በጠፋበት እና በርካታ ተማሪዎች በተጎዱበት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ተነግሯል።
የደቡብ ክልል ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሀዋሳ ዋናው ግቢ ብሄራዊ ፈተና እየተሰጠ መሆኑን ገልጾ ሁሉም በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው ብሏል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የፈተናውን ሂደት እየተመለከቱ መሆኑ ተነግሯል።
ትላንት ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችና ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዕድል ከት/ት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ጋር በመነጋገር እንደሚመቻችላቸው የሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ማሳወቁ አይዘነጋም።

#NEBE ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚያካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የጠየቀው በጀት 👉 541,270,104 ብር ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል መንግሥት ውስጥ በ6 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ማለትም ፦ - ጋሞ፣ - ጎፋ፣ - ወላይታ፣ - ጌዲዮ፣ - ኮንሶና፣ - ደቡብ ኦሞ ዞኖች - ቡርጂ፣ - አማሮ፣ - ደራሼ፣ - ባስኬቶ፣ - ኧሌ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ…
#Update
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በ6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል።
በዚህ ህዝበ ውሳኔ ከ3.1 ሚሊዮን በላይ መራጮች ይሳተፉበታል የሚል ቅድመ ግምት ተቀምጧል።
ለህዝበ ውሳኔው 3,756 ጣቢያዎች፣ 18,885 የምርጫ አስፈፃሚዎች እንደሚያስፈልጉ ቦርዱ ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ክንውኑን በተመለከተ እያካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ አስታውቋል።
ለህዝበ ውሳኔ ማስፈፀሚያ የሚውል 541.2 ሚሊዮን ብር በጀት ጥያቄ ለመንግስት ማቅረቡን ቦርዱ መግለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና " የማህበራዊ ሳይንስ " የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀግብር ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።
በነገው ዕለት የመጨረሻው ቀን የፈተናው መርሃ ግብር ተካሂዶ ቀድሞ በወጣው መርሀ ግብር ተማሪዎች ከነገ በስቲያ ጀምሮ ወደ የመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዛሬው የፈተና ውሎ ጋር በተያያዘ በተለይም በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች አንዳንድ ተማሪዎች ከፈተና ማዕከል ለቀው ስለመውጣታቸው ለመስማት ችለናል።
በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ምንድነው የሆነው ?
#DebreTaborUniversity
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥዋት በተወሰኑ " የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን አናከብርም ፤ አንፈተንም ! " ባሉ ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ተስተጓግሎ ነበር ሲል ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በተለይ " ካልተኮራረጅን አንፈተንም ! " በሚል እሳቤ ለመበጥበጥ የሞከሩ አካላት ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ፣ ከደብረ ታቦር አስተዳደር ፣ ከከተማው ሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶችና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ባደረገው ጥረትና ውይይት ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል ሲል አሳውቋል።
በከሰአቱ መርሀ ግብር የፈተና አሰጣጥ ፤ " ስርዓቱን አክብረን እንፈተናለን " ያሉ ተማሪዎች ተለይተው ፍጹም በሆነ መረጋጋት ፈተናቸውን እንደተፈተኑ ተቋሙ ገልጿል።
ዛሬ በደብረ ታቦር ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ አንድ የደብረ ታቦር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ምክንያቱ በምን እንደተነሳ ባያውቀውም በግቢው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ጩኸት እና ተኩስ ሲሰማ እንደነበር ገልጿል።
የዶቼ ቨለ ሬድዮ በበኩሉ አንድ የአይን እማኝ በግቢው በተፈጠረው ችግር ጉዳት መድረሱን እንደገለፁለት ዘግቧል።
ፈተናውን መፈትን የማይፈልጉ ግቢውን እንዲለቅቁ ፣ ፈተናው መፈተን የሚፈልጉ ደግሞ ወደ ፈተና አዳራሽ እንዲገቡ ተነግሮ ፈቃደኛ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ እየተፈተኑ እንደሆነ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ ግቢውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉን እኙሁ የአይን እማኝ ተናግረዋል።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ ስለጉዳት መጠን እና ዝርዝር ያለው ነገር የለም። ስለደረሰ ጉዳት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እንጥራለን።
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፤ የተማሪ ቤተሰቦች እንዲረጋጉ ያሳሰበ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።
በተቋሙ ያልተከናወኑ ጉዳዮች የተፈጸሙ በማስመሰል ኃላፊነት የጎደለው አሉባልታ በማሰራጨት ተማሪዎች ፈተናቸውን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ እንዳይፈተኑ ለማድረግ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እያሰራጩ የመገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አጥብቆ እሳስቧል።
የቲክቫህ ቤተሰብ የሆነ አንድ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኛ የግቢው መግለጫ ትክክለኛ መሆኑን ገልፀው " እደግፈዋለሁ " ብለዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ስለጉዳዩ ምንም ሳያውቁ የሚፅፉ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት ይበልጥ ትውልዱን በራሱ እንዳይተማመንና እራሱን እንዳይችል የሚያደርግ እና ሀገርንም በእጅጉ ሚጎዳ ተግባር መሆኑ ጠቁመዋል።
ዛሬ ፈተናውን ሳይፈተኑ ግቢውን ለቀው ወጡ ከተባሉ ተማሪዎች በኩል ምን እንደተፈጠረ እና እንዳጋጠመ ለማወቅ @officialtikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክታቸውን ማግኘት አልቻልንም።
#DebreMarkosUniversity
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው የወጡ ተማሪዎች እንደነበሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ፤ ለዶይቼ ቬሌ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ፤ " ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል። " ሲሉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ፈተና እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ሲሉ ገልፀዋል።
" ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬ እና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል " ያሉት አቶ ይትባረክ ፤ " ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው ተፈትነዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ " እንደተደበደቡ እና እንደተዋከቡ " ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነ ገልጸዋል።
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶክተር ተፈራ መላኩ ለአሐዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠቱ ቃል ደግሞ ፤ በዩኒቨርሲቲው ስር 4 የመፈተኛ ጣቢያች መኖራቸውን ጠቅሰው የዛሬውን ፈተናን አንፈተንም ብለው የወጡት በ " ጤና ካምፓስ " ውስጥ ሲፈተኑ የነበሩ ጥቂት ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።
የተማሪዎቹ ፈተና አቋርጦ በፈተና ማዕከል መውጣት ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በርካታ የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ ያሉት ዶክተር ተፈራ ፤ " ተማሪዎቹ ፈተናውን ያቋረጡበት ዋነኛው ምክንያት ከዝግጅት ጉድለት የመነጨ ነው። " ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ በበኩሉ ፈተና አቋርጠው የወጡት በዩኒቨርሲቲው ጤና ካምፓስ የሚፈተኑ እና "ፈተናው የከበዳቸዉ ጥቂት ተማሪዎች " ናቸው የሚል መረጃ አጋርቷል።
ፈተና ጥለዉ ከወጡ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ በ2013 ዓ.ም የጨረሱና ዳግም ፈተና የተፈቀደላቸው መሆናቸው ፖሊስ ያጋራው መረጃ ይገልጿል።
"ፈተና መፈተን ያልፈለጉ" ተማሪዎች በሰላም ግቢውን ለቀው ወጥተው እያለ ተቋሙ ውስጥ ብጥብጥ እንዳለ ተማሪዎችም እንደቆሰሉ ፣ እና እንደተደበደቡ ተደርጎ የሚሰራጨዉ ፍፁም መረጃ ሐሰት ነው ሲል አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በደብረ ታቦር እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ጉዳዩ ላይ እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም።

#Update የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ይኸው የፈተና መርሀ ግብር ዛሬ ከሰዓት በኃላም ይቀጥላል። እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና መርሀግብር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ነገ ጥቅምት 2 / 2015 የሚጠናቀቅ ሲሆን ተማሪዎች ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 4 ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ። በሌላ በኩል ፤ ትላንት…
#Update
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች #የመጨረሻ ቀን የፈተና መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ዛሬ ፈተናቸውን የሚያጠናቅቁት ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ወደየመጡበት አካባቢ የሚደረጉ ይሆናል።
የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ ከመደረጉ በላይ አንዳንድ ተቋማት ኩረጃን ለመከላከል ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ የደህንነት ካሜራዎችን ሲጠቀሙ እንደነበር ለማውቅ ተችሏል።
የደህንነት ካሜራዎችን ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ያላቸውን እንቅስቃሴ እና በፈተና ክፍል ያለው የፈተና ስርዓት ለመከታተል ነው ጥቅም ላይ እያዋሉ ያሉት።
ዘንድሮ ከታዩ በጎ በጎ ጅምሮች በተጨማሪ እንደ መጀመሪያ ጊዜም ስለሆነ #ክፍተቶች የነበሩ ሲሆን እነዚህን በቀጣይ የምናነሳቸው ይሆናል።
ትምህርት ሚኒስቴርም ፈተና እንዳለቀ አጠቃላይ የነበሩ አፈፃፀሞችን ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ተነግሮናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንዳይፈተኑ እና ጥለው እንዲወጡ የሚያበረታቱ የተለያዩ አክቲቪስት ነን የሚሉ አካላት ፣ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መኖራቸውን ተመልክተናል።
የተማሪዎችን ህይወትን የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ለማድረግ የሞከሩም ብዙ ናቸው ፤ ድርጊቱ በነገ የሀገር ተረካቢ ልጆች ላይ ትልቅ ተፅእኖ ስላለው ቢታታረም መልካም ነው።
ገና ፈተናቸውን ያልወሰዱና ወደ መፈተኛ ተቋማት የሚገቡ በርካታ ተማሪዎች በመኖራቸው ያሉ ክፍተቶች እንዲታረሙ ለማደረግ መረባረብ እንጂ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ተማሪዎችን መረበሽ ፍፁም ተገቢ አይደለም።
ፎቶ ፦ አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ