TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.7K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ አርብ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እሁድ መስከረም 22/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

የሞተር እንቅስቃሴ የተከለከለው ከነገ ወዲያ ቅደሜ መስከረም 21/2015 ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ ነው።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማነጅመንት ኤጀንሲ ፤ " ለኢሬቻ በዓል በሁሉም የከተማድ መግቢያ በሮች የሚገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች ስለሚኖሩ ለጋራ ደህንነት፣ ሰላም እና ጸጥታ ሲባል ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴን መገደብ አስፈልጓል " ብሏል።

የተጣለውን ገደብ ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ የእርምት ርምጃ ይወሰዳል ሲልም አሳስቧል።

@tikvahethiopia
የተመድ ፀጥታ ም/ቤት በኢትዮጵያ ገዳይ መክሯል ?

ትላንት ለሊት የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ #ኢመደበኛ_ዝግ ስብሰብ ያደርጋል ተብሎ ነበር። ስብሳባው ስለመደረግ አለማደረጉ እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

ስለዚህ ስብሰባ የሚታወቀው ነገር የሚከተለው ነው ፦

- ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ መስከረም 2 (እኤአ) አይርላንድ ከአልባኒያ ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጋር በመሆን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ በክፍት እንዲሰብሰብ ጠይቃ ነበር። አይርላንድ " በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በግጭት ምክንያት በረሃብ እየተሰቃዩ በመሆናቸው ለሰብአዊ ዕርዳታ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በጣም ያሳስበናል " በሚል ነው ክፍት የሆነ ስብሰባ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርባ የነበረው፤ ሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና በአፍሪካ ህብረት (AU) ወደሚመራው የሰላም ንግግር እንዲመለሱ እንደምትፈልግ ነው የገለፀችው።

- የክፍት ስብሰባ ጥያቄው በ #A3 ሀገራት ማለትም #በኬንያ#በጋቦን እና #በጋና ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ሀገራቱ ይህን የስብሰባ ይዘት የተቃወሙ ሲሆን የተስማማቱ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) እንዲካሄድ ነው። ይህም ኢትዮጵያ የምትመርጠው አይነት የስብሰባ ይዘት እንደነበር ተነግሯል።

ℹ️ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) ማለት ምንድነው ? IID መደበኛ ያልሆነ ዝግ ስብሰባ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ያልሆኑትን እንዲሳተፉ የሚያስችልም ነው። የዚህ  የስብሰባ ይዘት የስብሰባ መዝገቦች የሌሉት ሲሆን በም/ቤቱ ወርሃዊ የስራ መርሃ ግብር ውስጥም አይካተትም።

- አይርላንድ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙ እና ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚጠይቅ ረቂቅ ጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭታ ነበር ሆኖም ግን #A3#ቻይና እና #ሩሲያ በረቂቅ ጽሑፉ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። ሀገራቱ መግለጫውን ከስብሰባው በኃላ ከግምት ውስጥ ማስገባትን ነው የመረጡት ተብሏል። በዚህም በመግለጫው ላይ የነበረ ውይይት ባለበት እንዲያዝ ተደርጓል።

- ትላንትና ይካሄዳል የተባለው እና እስካሁን ተካሂዶ ስለመሆን አለመሆኑ በይፋ ያልታወቀው የተ.መ.ድ. ፀጥታ ምክር ቤት የIID ስብሰባ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ተቴህ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆም አጭር መግለጫ እንዲሰጡ ተጋብዘው እንደነበር ታውቋል ፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍም ተጋብዛ ነበር።

- ትላንት ለሊት በተያዘው እቅድም መሰረት ኢመደበኛ ስብሰባው (IID) መካሄዱ ከተረጋገጠ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገረበት ነው የሚሆነው።

መረጃው ከSCR ፣ ከተመድ የአይርላንድ እና ኖርዌይ ተልዕኮ ፅ/ቤት የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
አሜሪካ ሱዳንን አስጠነቀቀች።

በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ጆን ጎድፍሬይ ፤ ካርቱም ሩሲያ በቀይ ባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር እንድትመሰርት ከፈቀደች ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው አስጠንቅቀዋል።

ከ25 ዓመታት በኋላ በሱዳን የመጀመርያው የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ጎድፍሬይ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ሱዳንን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መነጠል ብቻ ሳይሆን ጥቅሟን የሚጎዳ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

አምባሳደር ጎድፍሬይ ከሱዳን አል ታይያር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤ "ሩሲያ በቀይ ባህር ላይ የጦር ሰፈር ለመመስረት እ.ኤ.አ. በ2017 ከስልጣን ከተወገዱት ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው የሚሉ አንዳንድ ሪፖርቶች አሉ"  ብለዋል።

አልበሽር ለወራት የዘለቀን ተቃውሞ ተከትሎ ከስልጣን የተወገዱት በሚያዝያ 2019 እንደነበር ይታወቃል።

የአሜሪካው ዲፕሎማት " የሱዳን መንግስት የጦር ሰፈሩ (የሩስያ) እንዲቋቋም እንዲቀጥል ከወሰነ ወይም እንደገና ለመደራደር ከወሰነ ለሱዳን ጥቅም ጎጂ ነው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ሁሉም አገሮች ከየትኞቹ አገሮች ጋር አጋር እንደሚሆኑ የመወሰን ሉዓላዊ መብት አላቸው " ያሉት አምባሳደሩ " ነገር ግን እነዚህ ምርጫዎች በእርግጥም መዘዝ አላቸው " ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ አሜሪካ በሱዳን አዲስ በሲቪል የሚመራ መንግስት እና ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና የሚመልስ የሽግግር ማእቀፍ ለማየት ትፈልጋለች።

እ.ኤ.አ ህዳር 2017 ሱዳን እና ሩሲያ በወታደራዊ ስልጠና፣ የልምድ ልውውጥ እና የጦር መርከቦችን ወደ ሁለቱ ሀገራት ወደቦች ለማስገባት የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Sudan-Tribune-09-29

ምንጭ፦ ሱዳን ትሪቢዩን

@tikvahethiopia
የሚዘጉ መንገዶች - አዲስ አበባ !

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድን እንዲጠቀሙ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

- ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ

- ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

- ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ

- በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ 

- ከሳሪስ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ

- ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ

- ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

- ከልደታ በጌጃ ሰፈር፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ

- ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ

- ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ #ከዛሬ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

@tikvahethiopia
#NorthernEthiopia

አሜሪካ ፤ " ኤርትራ በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ ዋነኛውን ሚና በመጫወት ላይ ናት " ስትል ገልፃ ኤርትራ በአስቸኳይ ወደ ድንበሯ እንድትወጣ ጠይቃለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አሜሪካ ፤ ኤርትራ ወደ ድንበሯ እንድትወጣ መጠየቋን ገልፀዋል።

ፕራይስ ፤ " ለኤርትራ እና ለኤርትራ ባለስልጣናት በአስቸኳይ ወደ ድንበራቸው እንዲወጡና ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማባባሱን እንዲያቆሙ ግልፅ አድርገንላቸዋል። ይህ ግጭት ያስከተለው የሰብአዊ መብት ረገጣ በጣም አሳስቦናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ወደ ሰላም እና ደህንነት የሚመለሰው ብቸኛው መንገድ አሜሪካ የምትደግፈው በአፍሪካ ኅብረት (AU) የሚመራው የሰላም ሂደት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ወታደራዊ ግጭት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ሰላማዊ ድርድር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበናል  " ያሉት ፕራይስ " በዚህ የዲፕሎማሲ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከአህጉሪቱ አጋሮች ጋር ተቀራርበን ሰርተናል" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ባለፈው በመስቀል በዓል ዕለት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ " አዲ ዳዕሮ " እየተባለች በምትጠራ በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ከተማ በተፈፀመ የአየር ጥቃት 6 ሰዎች መሞታቸውን አንድ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኛን ዋቢ አደርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው " ህወሓት " ይህ ጥቃት የተፈፀመው በኤርትራ መሆኑንና በዕለቱ ተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን ቤቶችን ወደ ፍርስራሽነት መቀየራቸውን፣ ንፁሃንም ሰለባ መሆናቸውን ገልጿል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-Region-09-30

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ?

የሶማሊያ ፕሬዜዳት ሀሰን ሼክ ሙሃሙድ የሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር መክረዋል፤ የተለያዩ ተቋማትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የሁለት ቀን የስራ ጉብኝቱን ተከትሎ የሁለቱም ሀገራት መሪዎች የተስማሙባቸው ነጥቦችን የያዘ መግለጫ ለህዝብ ተሰራጭቷል።

የዚህ መግለጫ ሙሉ ቃል ከላይ በምስል ተያይዟል።

በዋነኝነት ፦

- የሁለቱን ሀገራት የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት በማክበር ላይ የተመሰረተ የሁለቱ ሀገራት እና ህዝቦች የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

- ለሶማሊያ ሰላም፣ መረጋጋትና ሀገር ግንባታ ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈለው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብራቸውን ገልፀዋል።

- የጋራ ጠላታቸውን፣ ሽብርተኝነትንና አክራሪነትን በመዋጋት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተባበር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸው ፤ የፀጥታ ተቋማት ያላቸውን የትብብር ስልቶች አጠናክረው እንዲቀጥሉ መመሪያ በመስጠት የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል።

- መሪዎቹ ፤ ሶማሊያ በአልሸባብ አሸባሪ ቡድን የሚደርሰውን የፀጥታ ስጋት በብቃት ለመቅረፍ እንድትችል በበቂ ሁኔታ እንድትታጠቅ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ ፌደራል መንግስት በሃገሪቱ ላይ ከ30 አመታት በላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ ያቀረበውን ጥያቄ እንዲያጤነው ጠይቀዋል።

- በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት በጋራ የሚያደርጉትን ጥረት እና ሽብርተኝነትን በብቃት ለመዋጋት የሚሰራውን ስራ ሊያበላሽ የሚችሉ ተገቢ ያልሆነ የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን ተፅእኖ መቀነስ ላይ ተስማምተዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#ግሸን_ደብረ_ከርቤ

የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግስ በዓል ነገ ይከበራል።

ይህንኑ የንግስ በዓል ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ እንግዶች ወደ ቦታው እየገቡ ነው።

የፀጥታው ዝግጅት ምን ይመስላል ?

- የፀጥታ ኃይሎች በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

- በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት የተጀመረው ቀደም ብሎ ሲሆን የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ ከደሴ ከተማ፣ ከኮምቦልቻ ከተማ እና ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ኦረንቴሽን በመስጠት ፈፃሚ አካላት እንዲሰማሩ አድርጓል።

- በዓሉ ላይ እጅግ በርከታ ምእመን የሚታደም በመሆን ይህንን የሚመጥን በቂ ዝግጅት  ተደርጓል ፤ በቂ የሆነ ስምሪት ተሰጥቷል ፤ ለበዓሉ ደህንነት ሰፊ የሰው ኃይል ተሰማርቷል።

ምእመናን ምን ጥንቃቄ ያድርጉ ?

1. ምእመናን ማንኛውም የተለየ ጥርጣሬ እና እንቅስቃሴ ሲመለከቱ አቅራቢያ ላለ ፖሊስ ሊያመለክቱ ይገባል።

2. ምእመእና ለስርቆት እንዳይጋለጡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። በተለይ አብሮት የሚሄደውን፣ አብሮ የሚያድረውን፣ ድንኳኑን የሚጋራውን ፣ ቤት የሚከራየውን፣ ቤት የሚገባውን ሰው መለየት እና ማወቅ / ማንነቱን ማጣራት ይገባል።

3. የእግር ጉዞ ስለለው ምእመናን ሲደክማቸው እቃ ተሸካሚ መስለው ለማገዝ በሚመስል ሁኔታ ሊሰርቁ የሚችሉ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ንብረትን በደንብ መጠበቅ ይገባል። ንብረት መስጠት ያለባችሁ ባጅ ላለው ፣ ባጅ ላለው የጉልበት ስራ ለተሰማራ ፣ ለበጎፍቃደኞች ብቻ መሆን አለበት።

4.ምእመናን በሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት ወቅት ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ስነሥርዓቱ በሚያደርጉበት ጊዜ እንዳይሰረቁ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎቻቸውን፣ ቦርሳቸውን በእይታቸው እና በቁጥጥራቸው ስር ማደረግ አለባቸው።

መረጃውን ከደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦

" ከባህር ዳር የተነሱ ወደ 9 ባስ ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከልክለው ቆመዋል።

በባሶቹ ውስጥ ተማሪዎች ይገኛሉ።

ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ጋር እየሄዱ ነው።

በየፈጠረው ሁኔታ ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ነው። አ/አ ለመድረስ 80 ኪ/ሜ ሲቀረን ነው የተከለከልነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦ " ከባህር ዳር የተነሱ ወደ 9 ባስ ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከልክለው ቆመዋል። በባሶቹ ውስጥ ተማሪዎች ይገኛሉ። ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ጋር እየሄዱ ነው። በየፈጠረው ሁኔታ ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ነው። አ/አ ለመድረስ 80 ኪ/ሜ ሲቀረን ነው የተከለከልነው። " @tikvahethiopia
" ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለን እየተንገላታን ነው ፤ ወደ መጣችሁበትም ተመለሱ ተብለናል " - መንገደኞች

መነሻቸዉን ከአማራ ክልል አድርገዉ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱ መንገደኞች በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኀይሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን ገለፁ።

በዚህ ምክንያትን እንግልት እየደረሰባቸው መሆን ጠቁመዋል።

ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸኖ ከተማ ጀምሮ ወደ አ/አ ለመግባት የሞከሩ መንገደኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፤ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ከነበረባቸው ሰዎች መካከል የህክምና ክትትል ያላቸው ዜጎች እንደሚገኙበት ገልፀዋል።

እራሳቸውን የሚገልፅ በቂ ማስረጃ፣ መታወቂያ ቢይዙም ወደ አ/ አ እንዳያልፉ መከልከላቸውን ጠቁመዋል።

ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የተለከለከሉት የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ እንዲሁም የአዲስ አበባ መታወቂያም ያላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ባወጣው ዘገባ ፤ ከመንገድ ተመልሰዉ በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ መንገደኞች የኢሬቻ በዓል እስኪያልፍ ድረስ አዲስ አበባ መግባት አትችሉም መባላቸዉን አስረድተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ የሆኑ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ለሚዲያው በሰጡት ቃል ፤ " እኛ ኢሬቻ በዓል ላይ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ ፍተሻ እያደረግን እንጅ መንገደኞችን አልመለስንም። "  ብለዋል።

ሚዲያው መንገደኞቹ እየተጉላሉ እንደሆነ መመልከቱን ገልጾ ላነሳው ጥያቄ  " ይህንን ጉዳይ አላዉቀዉም ችግሮች ካሉም እናስተካክላለን " ብለዋል፡፡

ም/ቢሮ ኀላፊዉ መንገደኞቹ ስለመመለሳቸዉና መንገዱ ስለመዘጋቱ እንደማያዉቁም ለክልሉ ሚዲያ ተናግረዋል።

ፎቶ ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
#Irreecha2015 #እንድታውቁት

ነገ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረውን የ2015 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ተከትሎ በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ከለሊቱ 11፡00 ጀምሮ ፦
- የአንበሳ
- የሸገር
- የድጋፍ ሰጪ
- የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

እንደ ቢሮው መረጃ ፦

👉 ከአባኪሮስ አደባባይ፣
👉 ከአያት አደባባይ፣
👉 ከቱሉዲምቱ አደባባይ፣
👉 ጎሮ አደባባይ፣
👉 አዲሱ ገበያ፣
👉 ከቁስቋም፣
👉 ከሳንሱሲ፣
👉 ከአየር ጤና አደባባይ
👉 ከጀሞ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia