TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የአስቸኳይ የሰላም ጥሪ መግለጫው እንዳይሰጥ ተከልክሏል " - የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች

የአገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዛሬው ዕለት ሊያቀርቡት የነበረው " አስቸኳይ የሰላም ጥሪ " እንዳይደረግ ተከልክሏል።

ይህንን " የአቸኳይ የሰላም ጥሪ " መግለጫ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በቦታው ላይ ተገኝተው በመግለጫው የሚተላለፈውን የሰላም መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያደርሱ ጥሪ የቀረበ ቢሆንም የተገኙ ሚዲያዎች እንዲመለሱ ተደርጓል።

መግለጫው በሚሰጥበት ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በርከት ያሉ ሲቪል የለበሱ ደኅንነቶች እንዲሁም የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ አካላት በቦታው ተገኝተው ነበር።

ጋዜጣዊ መግለጫው ይሰጥበታል ከተባለው ከጠዋቱ 3:30 እስከ 4:00 ድረስ መግለጫውን ያዘጋጁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም ጋዜጠኞች በስፍራው የነበሩ ቢሆንም ጋዜጣዊ መግለጫውን ማካሄድ አልተቻለም።

በመጨረሻም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮቹ ለጋዜጠኞች መግለጫው በመንግስት አካል ስለመሰረዙ ጠቁመዋል። በስፍራው የነበሩት እና መግለጫው እንዳይሰጥ የከለከሉ አካላት በየትኛው የመንግስት አካል እንደተከለከለ ለመናገርም ፈቃደኞች አለመሆናቸውን ተወካዮቹ ገልፀዋል።

ክልከላውን ከፌደራል ይሁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ለጊዜው ማወቅ አልተቻለም ሲሉም አክለዋል።

የአገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት " የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ " አቅርበው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በላከልን ባለ 7 ነጥብ የቋም መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ቆሞ ሰላማዊ ድርድር እንዲቀጥል ጠይቋል። ምክር ቤቱ በሶስተኛ ወገን አማካኝነት ግጭቱን በድርድር ለመፍታት ሲደረግ የነበረውን ቅድመ ዝግጅት በቅርበት ሲከታተል እንደነበረ የገለፀ ሲሆን የድርድር ሂደቱ ተቋርጦ ግጭት መቀስቀሱ እጅጉን እንዳሳሰበው አመልክቷል።…
#Ethiopia

" ጥቃቱን የጀመሩት የህወሓት ኃይሎች ናቸው " - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ዳግም ያገረሸው ግጭት አሁንም ቀጥሎ በተለያዩ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች ግጭቶች ስለመኖራቸው የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ።

ይህ ግጭት ዳግም እንዲያገረሽ ያደረገው ህወሓት በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት በመክፈቱና ሰላም አሻፈረኝ በማለቱ እነደሆነ የኢፌዴሪ መንግስት መግለፁ ይታወሳል ፤ ህወሓት ግን ይህ ከመገለፁ ቀደም ብሎ ፌዴራል መንግስት ጥቃት እንደፈፀመበት እና የተኩስ አቁሙን እንደጣሰ በመግለፅ ክስ አቅርቦ ነበር።

ጥቃቱን መጀመሪያ ማን ፈፀመ ? በሚለው ላይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ዳግም ላገረሸው ጦርነት ምክንያት የሆነውን ጥቃት የከፈተው ህወሓት / TPLF እንደሆነ ያለውን አቋም አሳውቋል።

ለዚህም አሳማኝ ነው ያለውን ምክንያት አቅርቧል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሰቢ ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለቪኦኤ ሬድዮ የሰጡት ቃል ፦

" እሱ / #ህወሓት ባይጀምር እንዴት እስከ ቆቦ ድረስ ይወሩታል፤ እንዴት እስከ ወልዲያ ድረስ ይመጣሉ። በጋራ ምክር ቤቱ በኩል ብዙም እምነት ያለው ነገር አይደለም (ህወሓት ጦርነት ተከፈተብኝ የሚልው ክስ) ምክንያቱም መንግስት የሰላም አማራጭ አቅርቧል። መንግስት ብዙ ፈተናዎች አሉበት ፣ የሀገር ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ ፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ፣ ከሸኔ እንቅስቃሴ ጋር በተለያዩ ቦታዎች ካሉ ክፍተቶች ጋር ተያይዞ ወደ ጦርነት ሊያስገባ የሚችለው ምንም ፍላጎት የለውም መንግስት። ስለዚህ ህወሓት በራሱ ጊዜ የቀሰቀሰው ነው እኛ እንደ ጋራ ምክር ቤት እይታችን። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow ቅዱስነታቸው በሰላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ተመልሰዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ ሲያደርጉ የነበረውን ሕክምናቸውን አጠናቀው ዛሬ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው በሰላምና በመልካም ጤና ተመልሰዋል። የቅዱስነታቸውን…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተናገሩት ፦

" ... ቅዱስ አባታችን በዚህ ባሳለፍነው ወቅት እኛ ልጆችዎ ከአየሩ ጠባይ የተነሳ ተፈትነን ቆይተናል። እንደሚታወቀው የአየሩ ጠባይ ተቀያያሪ ነው። በቅሎ ወለድም የሚነገርበት ነው።

ስለዚህ ቅዱስነቶ ደግሞ ለዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ክብር እና አንድነት ምሳሌ ሆነው በተናገሩት ቃል መሰረት ማዕበሉ ንፋሱ ወደ አጠገብዎ ሳይቀርብ ወደ ቅድስት ሀገርዎ ፣ ወደ መንበረ ክብርዎ ስለመጡ ደግመን ደጋግመን ደስታችንን እንገልፃለን። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-09-06

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተናገሩት ፦ " ... ቅዱስ አባታችን በዚህ ባሳለፍነው ወቅት እኛ ልጆችዎ ከአየሩ ጠባይ የተነሳ ተፈትነን ቆይተናል። እንደሚታወቀው የአየሩ ጠባይ ተቀያያሪ ነው። በቅሎ ወለድም የሚነገርበት ነው። ስለዚህ ቅዱስነቶ ደግሞ ለዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ…
ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፦

" ስሄድ እንደተናገርኩት ቤተክርስቲያንን ጥሎ ለመሄድ ሳይሆን ስላመመኝ ብዙ ዘይግይቼበታለሁ እንደውም በመላወል በዚሁ በአሁኑ ጊዜ እንዴት ብዬ ሄዳለሁ ብዬ ብዙ ጊዜ አስቤ ባሰብኩት ወቅት አልሄድኩም።

ለምን ሁለቱ እግሮቼ አብጠው ህመም የለውም ቁስል የለውም ነገር ግን ያብጣል ጫማዬ ሁሉ ተጥሎ አንዲት ጫማ ብቻ ነበረች የምጠቀምባት።

የጫማዬ ቁጥር በውጭው ሀገር ከውጭ ሀገር ነው የሚመጣው በአሜሪካውያን የጫማ ቁጥር 11 ቁጥር ነበር ከዛ አልፎ 15 ተኩል ቁጥር ነበረ አሁን አንዲት ጫማ ብቻ ስጠቀም የነበረው።

እና ይሄ ምንም ህመም ባይኖርበትም ይሄ እብጠት ከላይ እስከ ታች ከጉልበቴ ጀምሮ እስከ እግሬ ጥፍር ድረስ የነበረው ችግር ውሎ አድሮ ምን እንደሚያመጣ አይታወቅምና ይሄን ጉዳይ ዝም ብዬ ባየው ኃላ ይፀፅታል ስለዚህ ሄጄ መመርመር አለብኝ ብዬ ነው እንጂ የሄድኩት ይሄ ሁሉ አሁን የሚባለው የሚነገረው ነገር ሁሉ በህሊናዬ የለም በእውነቱ ጭራሽ።

ያም ደግሞ በብፁአን አባቶች ፀሎት፣ በካህናቱም፣ በምእመናኑም፣ በኢትዮጵያ ካህናትና ምህመናን ፀሎት ያ ጉዳዬ ተሳክቶልኝ ተሽሎኛል ተመልሼ መጥቻለሁ።

በዚሁ ቀን እመጣለሁ ባልኩት ቀን ተመልሼ መምጣቴ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች የለም ለህመሙ አትቸኩልበት፣ሰንብት ጥቂት እንደው 1 ሳምንት 2 ሳምንት ሰንብት የሚሉ ሰዎች ነበሩ አይ አይደለም ይሄ ሰውን ያጠራጥራል አልቆይም ብዬ ነው በዛች በወቅቷ የመጣሁትና በእናተ በፀሎታችሁ፣ በአባቶች ፃሎት፣በሊቃነ ጳጳሳቱ ፀሎት፣ በቤተክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን በኢትዮጵያ ህዝብ ፀሎት ጥሩ ህክምና አግኝቼ ተመልሻለሁና በጣም ደስ ብሎኛል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአስቸኳይ የሰላም ጥሪ መግለጫው እንዳይሰጥ ተከልክሏል " - የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዛሬው ዕለት ሊያቀርቡት የነበረው " አስቸኳይ የሰላም ጥሪ " እንዳይደረግ ተከልክሏል። ይህንን " የአቸኳይ የሰላም ጥሪ " መግለጫ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በቦታው ላይ ተገኝተው በመግለጫው የሚተላለፈውን የሰላም መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያደርሱ ጥሪ የቀረበ ቢሆንም…
#Update

ዛሬ ጥዋት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አዲስ አበባ " የሰላም ጥሪ " ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ከመንግስት መጣን ባሉ አካላት የተከለከሉት የአገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መግለጫቸውን ዛሬ ከሰዓት በኦንላይን ሰጡ።

አጠቃላይ መግለጫውን የሰጡት 35 ድርጅቶች ሲሆኑ ለጠዋቱ መግለጫ መከልከል የመንግሥት አካል ነን ያሉት ግለሰቦች ግልፅ ምክንያት እንዳልሰጧቸው ገልጸዋል።

ክልከላውን ያዘዘ አካል ማን እንደሆነ ብንጠይቅም መልስ አላገኘንም ብለዋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ " ለመንግሥት የፀጥታ አካላት ቅድሚያ ማሳወቅ የሚጠይቁት የአደባባይ ሰልፎች ብቻ ናቸው " ያሉ ሲሆን " ይህ ዓይነቱ አሠራር የሕግ የበላይነትን የሚፃረር ከመሆኑም ባሻገር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም ሊጫወቱ የሚገባቸውን ድርሻ ይነፍጋል። " ሲሉ አስገዝበዋል።

በድርጊቱ ማዘናቸውንም የገለፁ ሲሆን እንዲታረም አሳስበዋል። ከላይኛው የመንግሥት አካላት ይቅርታ ሊጠየቅበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ጥዋት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አዲስ አበባ " የሰላም ጥሪ " ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ከመንግስት መጣን ባሉ አካላት የተከለከሉት የአገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መግለጫቸውን ዛሬ ከሰዓት በኦንላይን ሰጡ። አጠቃላይ መግለጫውን የሰጡት 35 ድርጅቶች ሲሆኑ ለጠዋቱ መግለጫ መከልከል የመንግሥት አካል ነን ያሉት ግለሰቦች ግልፅ ምክንያት እንዳልሰጧቸው ገልጸዋል። ክልከላውን…
#Update

" አስቸኳይ የሰላም ጥሪ "

35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዛሬ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ጦርነት እና ግጭቶች ቆመው፣ ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ ጠይቀዋል።

ጦርነት እና ግጭት ህዝቡን በብዙ መልኩ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው ያሉት ድርጅቶቹ በአዲሱ አመት ያሉ ችግሮች ተቀርፈው ለማየት መፍትሄ ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦች አቅርበዋል።

- በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልል ያለው ጦርነትና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ ቆመው፣ ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ፤

- በትግራይና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ የተቋረጡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲጀመሩና ዕርዳታ ያለ እንቅፋት እንዲደርስ፤

- የፆታ ጥቃትን የፈፀሙ የተዋጊ አካላትን ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ያደረሱ አካላት ላይ ተጨማሪ ምርመራ ተደርጎ እርምጃ እንዲወሰድ፤

- ብሔር ተኮር ጥቃቶችና አግላይ ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ። በፌዴራሉ እና ክልል መንግሥታት በቁጥር አነስተኛ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና ግፉዓን ዜጎች የልዩ ጥበቃ ስርዓት እንዲዘረጋ፤ 

- ተፋላሚ አካላትና ደጋፊዎቻቸው ከማንኛውም የጦርነት ፕሮፓጋንዳና የግጭት አባባሽ ንግግሮች እና ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፤

- በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያሉ መገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የእምነት ተቋማት፣ የፖለቲካ ኃይሎችና አክቲቪስቶች ድምፃቸውን ለሰላምና ለእርቅ ብቻ እንዲያውሉ፤

ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-09-06-2

(ከላይ ሙሉ መግለጫ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " አስቸኳይ የሰላም ጥሪ " 35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዛሬ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ጦርነት እና ግጭቶች ቆመው፣ ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ ጠይቀዋል። ጦርነት እና ግጭት ህዝቡን በብዙ መልኩ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው ያሉት ድርጅቶቹ በአዲሱ አመት ያሉ ችግሮች ተቀርፈው ለማየት መፍትሄ ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦች…
#ጥያቄ

35ቱ የአገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ካቀረቡት " የአስቸኳይ ሰላም ጥሪ " ጋር በተያያዘ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች አንዱ " ጦርነቱ ካገረሸ ቀናት አልፈዋል እስከዛሬ የት ነበራችሁ ? ለምን አሁን ? ህወሓት ላይ እርምጃ ሲወሰድበት ነው ወይ ዛሬ መግለጫ የምትሰጡት ? " የሚል ሲሆን ድርጅቶቹን ወክለው አቶ አመሃ ደስታ ፦

" የሰላም ጥያቄ ሊነሳ የሚችለው ምን ጊዜም ሰላም በተጓደለበት ሰዓት ነው። እንዲያውም ትክክለኛው ሰዓት ነው ብለን ነው የምናስበው።

ጦርነቱ ጋብ ብሎ የንግግር፣ ድርድር ፍላጎቶች ስሜቶች እየታዩ ባለበት ሰዓትና በዛም ተስፋ አድርገን እየጠበቅን እያለ ነው ይሄ ጦርነት እንደገና ያገረሸው እንደገና እልቂት፣ ስደት፣ ውድመት የቀጠለው ስለዚህ ትክክለኛ ሰዓት ነው።

2ኛ እንዲህ አይነት የሰላም ጥሪ ስናደርግ በሲቪል ማህበራት ስብስብ ይሄ 4ኛው ወይም 5ኛው ነው። ከእኛ በፊት ሌሎች አካላት ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ይዘት ያለው የሰላም ጥሪ አቅርበዋል፤ ዋናው ነገር የሰላም ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ተገቢ ነው። " ሲሉ መልሰዋል።

ድርጅቶቹ የሰላም ግልፅ ጥሪውን ለማቅረብ ግጭቱ ያገረሸበት ጊዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተነጋግሮ፣ አስቦ ለመወሰን፣ ደብዳቤ ለማዘጋጀት ጊዜ መውሰዱን ጠቁመዋል።

አምና ጳጉሜ ላይም የአዲስ አመት የሰላም ጥሪ አቅርበናል፣ ሰብዓዊነትን መሰረት ያደረገ ተኩስ አቁም ሲደረግ የሰላም ጥሪም አቅርበን ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

" የዛሬው ጥሪ የመጀመሪያችን አይደለም " ያሉት ድርጅቶቹ እንደ ሲቪል ማህበረስብ ስራችንና የሚጠበቅብን ኃላፊነታችን እንዲህ ያለ ጥሪ ማቅረብ ነው ያንን ነው ያደረግነው ሌላ አንዳችም ትርጉም የለውም ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አጋምሳ ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ፤ ሆሩ ጉዱሩ ወለጋ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተገናግረዋል። በአጋምሳ ከተማ በተፈፀመው ጥቃት በርከታ ሰዎች መገደላቸውን የሚገልፁት የአይን እማኞች ለተለያዩ ሚዲያዎች ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን በትንሹ ከ55 በላይ ንፁሃን ሰዎች እየደተገደሉ የአይን እማኞቹ ገልፀዋል። ለእነዚህ የንፁሃን ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት ያደረሱት " የፋኖ…
* ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ፤ ኡሙሩ ወረዳ ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች የተገደሉ፣ የቆሰሉ እና ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ወደ ኦቦራ ከተማ መፈናቀላቸውን ገለፀ።

አካባቢው ላይ ተሰማርተው የነበሩ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሌላ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው በኡሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃት የተፈፀመው ብሏል።

በነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ/ም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ የሚጠራ) ታጣቂዎች የወረዳው ዋና ከተማ የሆነችውን ኦቦራ ከተማን ለመያዝ ባደረጉት እንቅስቃሴ 3 የአማራ ብሔር ተወላጆች ገድለዋል።

ይህን ተከትሎ ከኡሙሩ ወረዳ፣ ሀሮ አዲስ ዓለም ከተባለ ቀበሌና አጎራባች ከሚገኘው የአማራ ክልል ቡሬ ወረዳ የተውጣጡ ታጣቂዎች በኡሙሩ ወረዳ በሚገኙና አገምሳ፣ ጆግ ምግር፣ ታም ኢላሙ፣ ጀቦ ዶባን፣ ጦምቤ ዳነጋበ፣ ጃዋጅ፣ ኛሬ፣ ለገ ሚቻ፣ ሉቁማ ዋሌ በሚባሉ ቀበሌዎች የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ነዋሪዎች ላይ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቃት ፈጽመዋል ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል።

በእነዚህ ሁለት ቀናት  በተደረጉ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ፤ ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ፣ የነዋሪዎች የቤት ንብረቶችና የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውን ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው በኦቦራ ከተማ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ጥቃት ከተፈጸመባቸው ቀበሌዎች መካከል አሁንም ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ተጠቁሟል።

(ኢሰመኮ የላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ " አማኑኤል ሆስፒታል " አካባቢ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ሁለት ልጆቻቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች ባለ 2 መኝታ ቤትና የ150 ሺ ብር ድጋፍ እንዳደረገላቸው ገልጿል።

የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ " አስተዳደራችን በሚችለው ሁሉ ከጎችሁ ነው ፤ የሞቱ ልጆቻችሁን መመለስ ባንችል እንኳን መፅናኛ ይሆናችሁ ዘንድ ይህንን ድጋፍ አድርገናል " ብለዋል።

መረጃው ፦ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia