TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በላከልን ባለ 7 ነጥብ የቋም መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ቆሞ ሰላማዊ ድርድር እንዲቀጥል ጠይቋል።

ምክር ቤቱ በሶስተኛ ወገን አማካኝነት ግጭቱን በድርድር ለመፍታት ሲደረግ የነበረውን ቅድመ ዝግጅት በቅርበት ሲከታተል እንደነበረ የገለፀ ሲሆን የድርድር ሂደቱ ተቋርጦ ግጭት መቀስቀሱ እጅጉን እንዳሳሰበው አመልክቷል።

ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነውን ጥቃት የጀመሩት የህዉሃት ኃይሎች መሆናቸው የገለፀው ምክር ቤቱ ፤ የህወሓት ኃይሎች የሠላም አማራጭ እንዳልተሟጠጠ አውቀው ቀደም ሲል በመንግስት የተወሰደውን የተኩስ አቁም እርምጃ በማክበር ወደ ሠላማዊ ውይይትና ድርድር እንዲገቡ ጠይቋል።

የትግራይ ህዝብም ህዉሃት ጦርነትን አቁሞ ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲገባ ተፅዕኖ እንዲፈጥር ጥሪ አቅርቧል።

ምክር ቤቱ በዚህ መግለጫው ፤ የውጪ ኃይሎች ከአገራችን የውስጥ ጉዳይ እጃቸውን እንዲሰበስቡና የሰላም መንገድን ብቻ አጥብቀው እንዲደግፉ የጋራ አጥብቆ እንደሚታገል አረጋግጧል።

የአለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብም የችግሩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ ጦርነቱ በሚቆምበትና ሰላማዊ ውይይትና ድርድር በሚጀምርበት ሁኔታ ላይ በፍትሐዊነትና በገለልተኝነት አጋርነቱን እንዲያሳይ አጥብቆ ጠይቋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ራይላ ኦዲንጋ በመግለጫቸው ምን አሉ ? የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና በወቅቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚደገፉት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱ ሕጋዊ ያልሆነ እና ተፈጻሚ የማይሆን ነው ብለዋል። ኦዲንጋ በመግለጫቸው  ፦ •  ውጤቱን አልቀበልም ብለዋል። • ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል። • የኮሚሽኑን ዋና ሰብሰቢ ዋፉላ ቼቡካቲን " አምባገነን " ሲሉ በመጥራት ተችተዋቸዋል። ይፋ…
#Update

ሩቶ እ.ኤ.አ. መስከረም 13 አምስተኛው የኬንያ ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ።

በዛሬው ዕለት የጎረቤት ሀገር ኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፍ አፅንቷል።

ፍርድ ቤቱ የነሀሴ 9 (እኤአ) ድምጽ ውጤት እንዲሰረዝ ለማድረግ የቀረቡ ሁሉንም ክሶች ውድቅ አድርጓል።

ሩቶ በመጪው መስከረም 13 (እኤአ) የኬንያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙ ተገልጿል።

በኬንያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሩቶ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BorisJhonson • ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን በገዛ ፍቃዳቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ለቀቁ። • አዲስ ጠ/ሚ እስኪሰየም ቦሪስ ጆንሰን ቦታው ላይ ይቆያሉ። ከምክር ቤት እና ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ድጋፍ ማግኘት ያልቻሉት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ከወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው መሪነት እንዲሁም ከጠ/ሚ ስልጣናቸው ለቀቁ። ለፓርቲው መሪነት የሚደረገው ፉክክር በቅርቡ የሚደረግ ሲሆን…
#Update

የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ተመረጡ።

የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል።

ትረስ እድሜያቸው 47 ሲሆን የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ሆነዋል።

ሶስተኛዋ የሀገሪቱ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትርም እንደሆኑ ተገልጿል።

ትረስ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሪሺ ሱናክን ሲሆኑ ያሸነፉት 57.4% ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
24 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ አቀረቡ። የሰላም ጥሪው ያቀረቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ ባሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በከባድ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች ሲሉ ገልፀዋል። - በትግራይ - በአማራ - በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ - በሶማሊ - በአፋር - በቤኒሻንጉል ጉሙዝ - በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በሚካሔዱ ግጭቶች ምክንያት በሺሕ የሚቆጠሩ…
" አስቸኳይ የሰላም ጥሪ "

የአገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በነገው ዕለት " አስቸኳይ የሰላም ጥሪ " ሊያቀርቡ ነው።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አሳስቧቸው የተሰባሰቡት አገር በቀል የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በጋራ በሚሰጡት መግለጫ " አስቸኳይ የሰላም ጥሪ " እንደሚያቀርቡ ተገልጾልናል።

ይህንን " የአቸኳይ የሰላም ጥሪ " መግለጫ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በቦታው ላይ ተገኝተው በመግለጫው የሚተላለፈውን የሰላም መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያደርሱ ተጋብዘዋል።

የአገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት " የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ " አቅርበው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል። በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው…
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለህክምና ከሄዱበት አሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲገቡ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሕክምናቸውን አጠናቀው ነገ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ይመለሳሉ።

ቅዱስ ፓትራርኩ ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው መመለሳቸውን ተከትሎ ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ታውቋል።

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጤና ወደ መንበራቸው መመለሳቸው የቤተ ክርስቲያን ደስታ ነው ያለ ሲሆን በዚሁ መጠን ይፋዊ አቀበበል ዝግጅት ተደርጓል ሲል አሳውቋል።

የቅዱስነታቸውን ወደ አገር ቤት መመለስን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የአቀባበል ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ የአቀባበል ቅድመ ዝግጅቱ #መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስነታቸው ወደ ሀገራቸውና ወቅዱስ መንበራቸው መመለስን ተከትሎ ነገ ለሚደረገው አቀባበል ሁሉም ሚዲያዎች ጥዋት 1 ሰዓት ላይ ቦሌ ኤርፖርት (VIP) እንዲገኙላት ጥሪ አቅርባለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ፓትርያርኩ ለህክምና ከሄዱበት አሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲገቡ አቀባበል ይደረግላቸዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሕክምናቸውን አጠናቀው ነገ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ይመለሳሉ። ቅዱስ ፓትራርኩ ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው መመለሳቸውን…
#HappeningNow

ቅዱስነታቸው በሰላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ተመልሰዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ ሲያደርጉ የነበረውን ሕክምናቸውን አጠናቀው ዛሬ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው በሰላምና በመልካም ጤና ተመልሰዋል።

የቅዱስነታቸውን ወደ ሀገርና ወቅዱስ መንበራቸው መመለስን ተከትሎ በአሁን ሰዓት የአቀባበል ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው።

የፎቶ ባለቤት : የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@tikvahethiopia