TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል።

ምርጫ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ ፦ ፓርቲው ከሚያዚያ 18 /2014 ዓ/ም ጅምሮ በ2 ወራት ጊዜ እስከ ሰኔ 18 /2014 ዓ/ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ ብሏል።

በተጨማሪም ፤ ፓርቲው በደንቡ መሰረት የሚቀርፃቸውን አጀንዳዎች ጨምሮ በጉባኤው የመነጋገር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ቀደም እልባት ያላገኘው " የአመራር ሪፎርም ወይም ለውጥ ማድረግ " የሚለው ለጉባኤው በአጀንዳነት ቀርቦ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥበት እና አግባብነት ያለው ምርጫ እንዲደረግ ብሏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አመሠራረት እና ሂደት ፣ ከኮሚሽነሮቹ እና ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በቀረበ ጥያቄ መሠረት የውይይት መድረኩ እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፋ ፤ ሀገራዊ ምክክሩ #ተስፋ_የተጣለበት እና #ለሀገራችን_ብቸኛ_አማራጭ በመሆኑ ቀጣይ በሚኖረው ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን መግለፃቸውን የህ/ተ/ምክር ቤት አሳውቋል።

የኮሚሽነሮቹን የአሰያየም ሂደት በተመለከተ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና በፍትህ ሚ/ሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር ) ማብራሪያ መሰጠቱ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በጎንደር አለመረጋጋት መኖሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እየጠቆሙ ይገኛሉ።

ችግር የተፈጠረው ፤ ዛሬ በነበረ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ነው ተብሏል።

ሸይኽ ከማል ለጋስ ለበርካታ አመታት የጎንደርን ህዝብ በሀገር ሽማግሌነት ያገለገሉ ትልቅ አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ሸይኽ ከማል ፤ ለበርካታ ዓመታት የጎንደርን ማህበረሰብ በባህል ህክምናና በሃገር ሽማግሌነት አገልግለዋል።

ሸይኽ ከማል የሙስሊምም የክርስቲያንም አባት የነበሩ ሲሆን በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ " አባ ለጋስ " ተብለው ይታወቃሉ ፤ የ " ሰሜኑ ኃያል (የአባሼይኽ ለጋሥ) " የበኩር ልጅም ናቸው።

ዛሬ በሸይኽ ከማል ስርዓተ ቀብር ላይ በተፈጠረው ችግር ምክንያት በጎንደር ከተማ የሰው ህይወት ማለፉ፣ ጉዳትም መደረሱን ለመስማት ተችሏል። አሁንም ከተማይቱ ወደመረጋጋት አልተመለሰችም።

በጉዳዩ ዙሪያ እና ዛሬ ስለተፈጠረው ክስተት ሁሉ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት አሰባስበን የምናካፍል ሲሆን ያለው ችግር ከዚህ ወደከፋ ሁኔታ ሳይሸጋገር የህዝብ ደህንነት ይመለከተናል የሚል አካል ሁሉ ችግሩ እንዲቀረፍ ርብርብ እንዲያደርጉ የጎንደር ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ " በጎንደር ከተማ ምን እየተካሄደ ነው ያለው ? እንደ ሃገር ያሳለፍናቸው የትላንት መጥፎ ጠባሳዎች ሳይሽሩ ዛሬም ለዘመናት የማይጠፉ ጥቁር ጠባሳዎችን መጣል ለምን አስፈለገ ? የክልሉ መንግስት ፣የፀጥታ ሃይሎች፣ የሐይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች የት አላችሁ? እየተፈፀመ የሚገኘውን ጥፋት ባስቸኳይ ማስቆም ይገባቹኃል " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት በጎንደር አለመረጋጋት መኖሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እየጠቆሙ ይገኛሉ። ችግር የተፈጠረው ፤ ዛሬ በነበረ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ነው ተብሏል። ሸይኽ ከማል ለጋስ ለበርካታ አመታት የጎንደርን ህዝብ በሀገር ሽማግሌነት ያገለገሉ ትልቅ አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ሸይኽ ከማል ፤ ለበርካታ ዓመታት የጎንደርን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጎንደር ምንድነው የሆነው ?

ትላንት በጎንደር ከተማ ላይ በተፈጠረው ችግር ሰዎች ሞተዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ የግለሰብ ቤቶቻ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

ችግሩ እንዴት ተፈጠረ ለሚለው የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ፤ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመበት መስጂድ ጥግ ቤተክርስቲያን እንዳለ ገልፀዋል።

ቦታው ህጋዊ በሆነ መንገድ ሽማግሌዎች በጋራ ተስማምተው ከፍለውታል፤ ተለይቶም ያደረ ነው ሲሉ አስታውሰዋል።

ትላንትና በመስጂዱ የታላቁ የሙስሊም አባት (ሸይኽ ከማል ለጋስ) የቀብር ስነስርዓታቸው እንደተፈፀመ ፤ ምእመኑ ለቀብር ስነስርዓት የሚያስፈልጉ ድንጋዮችን ለማንሳት በተንቀሳቀሰበት ወቅት ችግሩ መፈጠሩን ገልፀዋል።

አቶ ደሳለኝ ፤ " ድንጋይ አንስተው ወደ ቀብር ስነስርዓት የሚሄዱ ወገኖችን " ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ገብታችሁ ነው ድንጋይ የምታነሱት " በሚል ምክንያት ድንጋይ የሚያነሱትን ሰዎች ወረወሩባቸው እና ግጭት ተፈጠረ ፤ ይህ የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን የመሄድ ፍላጎት ነበረው " ብለዋል።

" ኦርቶዶክስም፣ ሙስሊሙም በጋራ የቀብር ስነስርዓት የሚፈፅም ፣ በማህበራዊም ፣ በኢኮኖሚም ችግር አብሮ የሚኖር ጨዋ ህዝብ ነው " ያሉት ኃላፊው " የሚታወቁ ሃይማኖቶች እጅግ ትልልቅ ክብር ያላቸው ሃይማኖቶች ናቸው ይሁን እንጂ ይህን ሀይማኖት ጥላሸት ለመቀባት የሚፈለጉ ቡድኖች ያን ግጭት ለማባባስ በቀባሪዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ተጀመረ " ብለዋል።

" ግጭቱን መልክ ለማስያዝ የፀጥታ ኃይል በቦታው ለመግባት ሞክሯል " ያሉ ሲሆን የተዛባ መረጃ በመስጠት በያለበት ያለው ወጣት ወደግጭት እንዲገባ ለማድረግ ግፊት ተፈጥሯል " ሲሉ ሁኔታው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጎንደር ምንድነው የሆነው ? ትላንት በጎንደር ከተማ ላይ በተፈጠረው ችግር ሰዎች ሞተዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ የግለሰብ ቤቶቻ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። ችግሩ እንዴት ተፈጠረ ለሚለው የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ፤ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመበት መስጂድ ጥግ ቤተክርስቲያን እንዳለ ገልፀዋል። ቦታው ህጋዊ በሆነ መንገድ ሽማግሌዎች በጋራ ተስማምተው ከፍለውታል፤ ተለይቶም…
#Gondar

በጎንደር ከተማ በሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ከተፈጠረ ግጭት በኃላ በተፈፀመ ጥቃት እስካሁን ባለው ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸው ፤ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ መስጂዶችም መጠቃታቸው ፣ ከዚህም አልፎ ንብረት መውደሙ ፣ የግለሰብ ቤቶች መጠቃታቸውን የጎንደር ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት በበኩሉ ፤ በጎንደር ሙስሊሙን የማጥቃት፣ መስጂዶችን የመድፈር እና ንብረቶቹን የማውደም የተደራጀ ጥቃት እናወግዛለን ብሏል።

ዛሬ የጎንደር ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ ትላንት በአራዳ ክ/ከተማ የተፈጠረው ሁኔታ በፍፁም የክርስትና እና እስልምና እምነት ተከታዮችን ሊወክል የማይችል ነው ብሎታል።

ምክር ቤቱ ጥፋቱ የተፈፀመው በጥቂት ጽንፈኛና አክራሪ ግለሰቦች የተከበሩትን የሁለቱን ዕምነት ተከታዮች ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ ለግጭት የማያበቃ ምክንያትን በመምዘዝ ጥፋት እንዲፈጠር የተቀነባበረና የተመራ ሴራ ነው ሲል ገልጾታል።

በዚህ እኩይ ተግባር ከሁለቱም የዕምነት ተከታዮች የህይዎትና አካል መጉደል እንዲሁም የንብረት መቃጠልና ዘረፋ አጋጥሟል ሲል አሳውቋል።

አሁን አካባቢው ሙሉ በሙሉ ከፀጥታ መዋቅርና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ትብብር በማድረግ የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ ስምሪትና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳውቋል።

ሙሉ መግለጫው በዚህ ተያይዟል ፦ https://telegra.ph/Gondar-04-27

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ለተመረቁ ተማሪዎች #መደበኛ_ዲግሪ ለመስጠት እንደሚቸገር አሳውቋል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ማግኘት ባለመቻላቸው ሥራ ለመቀጠር መቸገራቸውን ይገልጻሉ።

በተማሪዎቹ ቅሬታ ዙሪያ በሪፖርተር ጋዜጣ የተጠየቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) " የተማሪዎቹ ሙሉ መረጃ ሳይገኝ መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንደሚቸገሩ " ገልጸዋል።

" ሰላምና መረጋጋት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሰፍን ከመጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቆሙበት መረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ዲግሪው ይሰጣቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡

እስከዚያው ግን በተሰጣቸው ጊዚያዊ ሰርተፊኬት ሥራ መፈለግ እንደሚችሉ ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ተማሪዎች ግን " ትምህርት ሚኒስቴር በአንድ ሴሚስተር የውጤት መግለጫ ወረቀት/Grade Report አሰናብቶናል " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ይህ ወረቀት በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠር እንደማያስችላቸው በመጥቀስ ሚኒስቴሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል፡፡

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar በጎንደር ከተማ በሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ከተፈጠረ ግጭት በኃላ በተፈፀመ ጥቃት እስካሁን ባለው ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸው ፤ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ መስጂዶችም መጠቃታቸው ፣ ከዚህም አልፎ ንብረት መውደሙ ፣ የግለሰብ ቤቶች መጠቃታቸውን የጎንደር ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት በበኩሉ ፤ በጎንደር ሙስሊሙን የማጥቃት፣ መስጂዶችን…
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በጎንደር የተፈፀመው " ጭፍጨፋ እና የሽብር ጥቃት " ነው ሲል ገለፀ።

ም/ቤቱ በጎንደር ስለተፈጠረው ሁኔታ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው በሼኽ ኤልያስ ጥንታዊ የሙስሊም መካነመቃብር ላይ ለቀብር በወጡ ሙስሊሞች ላይ የታጠቁ አክራሪ ክርስቲያኖች በቡድን እና በነፍሥ ወከፍ ትጥቅ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል ብሏል።

ም/ቤቱ፤ ሼይኽ ኤልያስ ጥንታዊ የሙስሊም መካነመቃብር ቦታን በተለያየ መንገድ ለመውረር ሰፊ እርምጃ ተካሂዷል ቢሆንም ቦታው በታሪክ አንድና አንድ የሙስሊሞች ታሪካዊ የመካነ መቃብር ቦታ ነው ሲል ገልጿል።

ነገር ግን እንደልባቸው በተባሉና በመንግስትም መዋቅር በሚደገፉ ኃይሎች ወንዝ ተሻግረው በእለቱ ያረፉትን ታዋቂ የህዝብ ባለውለታ የሆኑትን አባት ቀብር አናስቀብርም በማለት ቀድሞ ባዘጋጁት ማሳሪያ ለቀብር በወጡት መስሊሞች ላይ በተኮሱት የመትረየስና የቦንብ ውርጅብኝ የሙስሊሞች ህይወት አልፏል፤ በርካቶች በከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል ገብተዋል ሲል ም/ቤቱ ሁኔታውን አስረድቷል።

በቀብር ቦታ መነሻ ያደረገው የተደራጀው ኃይል የጥቃት እንቅስቃሴውን በቀጥታ ወደ ከተማው በማድረግ በንግድ ተቋማት ላይ በማነጣጠር በርካታ የሙስሊም ህ/ተሰብ ሱቆች ዘርፏል፤ መስጂዶችን እና የሙስሊሞችን ቤት እየለዩ በመደብደብ አገር የማተራመስ አላማውን ቀጥሎ አምሽቷል ሲል ገልጿል።

ቀድሞ በዚህ ቦታ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ እየተነገረው በቸልታ የተመለከተው የከተማው አስተዳደር የትላንቱን ችግር ፈጥኖ ለማርገብ ባለመቻሉ ም/ቤቱ መረጃው ከደረሰው ሰዓት አንስቶ እስከ ፌዴራል ድረስ ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ገለልተኛ ኃይል ወደቦታው እንዲደርስ በማደርግ የአጥፊ ኃይሎች እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲገታ ተደርጓል ብሏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ትላንት በጎንደር ከተማ የተካሄደው ቀድሞ የታቀደበት ጭፍጨፋ ነው ሲል ገለፀ።

ምክር ቤቱ ፤ የሸይኽ ከማል ለጋስ (ረሂመሁላህ) የቀብር ስነ ስርአት እንደ መንስኤ በመጠቀም ቀድሞ በታቀደ መልኩ በሙስሊሙ ላይ በተፈፀመውን ጭፍጨፋ፣ 21 ሰዎች በግፍ መገደላቸውን እና መስጂዶችና ቁርአን መቃጠሉን ገልጿል።

በሙስሊሙ ላይ የተቃጣን አጥፊ የሆነና በፅንፈኞች ወገን ቀድሞ የተቀነባበረን ግልፅ የሆነ የወንጀል ድርጊት ፦ የክልሉ ሚዲያዎች፣ መንግስት እና አንዳንድ የፖለቲካ ፓሪቲዎች በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ የተፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት የማይመጥን ነው ሲል ምክር ቤቱ አውግዟል።

እነዚሁ አካላት በመስሊሙ ላይ የተቃጣውንና የ21 ሙስሊሞችን ህይወት የቀጠፈውን ወንጀል የእርስ በርስ ግጭትና በሀሰት በድንበር ምክንያት የተፈጠረ ነው በማለት ያወጡት መግለጫ ሀገርን ለማፈራረስ ላቀዱ ሰዎች ሽፋን ከመሆኑም ባሻገር ምክር ቤታችንንም ሆነ ህዝበ ሙስሊሙን በከፍተኛ ደረጃ አሳዝኗል ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፊቼ_ጨምበላላ

የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮው 1 ሺህ 500 ወጣቶች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አሳውቋል።

የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከሲዳማ አልፎ የአለም ቅርስ በመሆኑ በዓሉ ባህልና እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የህብረተሰቡን ደህንነት መጠበቅ ቀዳሚ ስራው መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ለስራው መሳካት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም ከሁሉም የፌዴራልና የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ጋር በጋራ ሰፊ ስራ እየሰሩ መቆየታቸውን እና ተግባሩ እስከ በዓሉ መባቻ ድረስ እንደሚዘልቅ ተገልጿል።

ለሰላም መጠበቅ የህብረተሰቡ ሚና ግንባር ቀደም ቦታ እንዳለው የተግለፀ ሲሆን ማንኛውም አጠራጣሪ ነገር ከተመለከቱ በቶሎ በአቅራቢያቸው ላሉ የጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ ደሬቴድ

@tikvahethiopia