TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰሜን ሸዋ ዞን ፤ በኤፍራታና ግድም ወረዳ እና በቀወት ወረዳ እንዲሁም በኦሮም ብሄረሰብ ዞን አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የፌድራል መንገድ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ክፍት ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አሳውቋል። መንገዱ ወደ አገልግሎት የተመለሰው በሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮችና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች ፣ በፀጥታ አካላቶች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች በተሰሩ…
#AmharaRegion

በቅርቡ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች አስተዳደር አጎራባች አካባቢዎች የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር እና ሰላምን ለማጠናከር በአጣዬ ከተማ ትላንት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩ ሰላምን ለማጠናከር የሚጠቅሙ አንኳር ሀሳቦች የተነሱበት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በዋናነት ለግጭቱ መንስኤ የሆኑ አካላት በሕግ እንዲዳኙና ማኅበረሰቡም አሳልፎ እንዲሰጥ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የሃይማኖት አባቶች ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት የሕዝቦች ትስስር ዋልታ ነው፤ የሰው ልጅ ሁሉ ደሙ አንድ ነው፤ በሰውነቱ ሁሉም ከአንድ የተገኘ ነውም ብለዋል።

ምክክሩ የተጠናቀቀው ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ሲሆን የአቋም መግለጫው በዚህ ተያይዟል ፦ https://telegra.ph/Amhara-Region-04-27

ምንጭ፦ የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ

@tikvahethiopia
#GONDAR

ትላንት በጎንደር ከተማ ስለተፈጠረው ሁኔታ ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱን የአማራ ክልል ም/ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር ፣ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው እና የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ናቸው የመሩት።

ዶ/ር ጌታቸው ፤ ውይይቱ ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ያለመ ነው ብለዋል።

አክለው ፥ " ትናንት የተፈጠረው የፀጥታ ችግር አሳዛኝና የከተማዋን ሕዝብ አብሮነት ታሪክ የማይገልፅ ነው ፤ የፀጥታ ችግሩን የፈጠሩ አካላትን በመለየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የክልሉ መንግሥት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በጋራ ይሰራል " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፤ " የተፈጠረው ችግር ለጠላት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ችግሩን በውይይት ለመፍታት ሕዝቡ ባለቤት መኾን አለበት " ብለዋል።

" በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር ያሉትን ክፍተቶች ለማስተካከል ጠንካራ ሥራ ይሠራል " ሲሉም ተናግረዋል። የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችም ከመንግሥት ጋር በመሆን እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ጣሂር መሐመድ ፤ ችግሩን ለመፍታት በስክነት መወያየት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በከተማው የቆየውን አብሮነት ለመሸርሸር የሚሠሩ አካላትን ተከታትሎ በቁጥጥር ሥር በማዋል ሕግ የማስከበር ሥራ ሊሠራ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ ትላንትና ጎንደር ላይ የተፈፀመውን ድርጊት የሚያወግዝ ተቃውሞ ዛሬ በአዲስ አበባ እና ጅማ ከተማ የተለያዩ መስጂዶች ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ በኑር (በኒ) መስጂድ እና በአንዋር መስጃድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ድርጊቱን አውግዞ ፍትህ ጠይቋል። በተመሳሳይ በጅማ ፈትህ መስጂድ ምእመኑ በጎንደር የተፈፀመውን ድርጊት አውቆ የተቃውሞ ድምፅ አሰምቷል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ አውጥቷል።

ጉባኤው በመግለጫው " በጎንደር ከተማ በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም የተፈፀመው የግድያ፤ የመስኪድ ቃጠሎ የሙስሊም ግለሰቦች ንብረት ውድመትና ዘረፋ በሃይማኖት እጅግ የከፋ ሃጢያት ሲሆን በፈጣሪም ዘንድ የሚያስጠይቅ ፀያፍ ተግባር ነው፡፡ የሃገራችን ሕዝብ ልዩነትን በማክበር በጋራ ጉዳዮች ላይ በመደጋገፍና በመተባበር ለዘመናት የኖረበትን የተከበሩ እሴቶችና ታሪኮች የሚያጎድፍ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ነው፡፡ " ብሏል።

ጉባኤው " የሃገራችን ሕዝብ ልዩነትን በማክበር በጋራ ጉዳዮች ላይ በመደጋገፍና በመተባበር ለዘመናት የኖረበትን የተከበሩ እሴቶችና ታሪኮች የሚያጎድፍ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ነው፡፡ " ሲልም አክሏል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፤ የደረሰውን የሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ዜና የሰማው በታላቅ የልብ ስብራት መሆኑም ገልጾ ድርጊቱን አምርሮ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

(ዝርዝር መገለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Repost

ስለፊቼ ጨምባላላ ምን ያህል ያውቃሉ ?

- የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል።

- ፊቼ ጫምባላላ መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራል።

- በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል።

- ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል።

- 'የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው'፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ ነው።

- የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

- ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል።

- ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

- በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

- ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው።

- ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው። ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል።

- የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

ይህ መረጃ የቀረበው ከ2019 የቢቢሲ ድረገፅ ላይ ከወጣው ፅሁፍ ነው።

@tikvahethiopia
" ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡

ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡

‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡

አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡

ፑቲን ከዚህ በፊት በለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ወቅት ነው።

በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት አድርገው ነበር።

በዚህ ጉብኝታቸው ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡

በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#UNICEF #ETHIOPIA

ትላንት ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዩኒሴፍ ኤግዜኩቲቭ ዳይሬክትር የሆኑትን ካትሪን ራስል በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ በአገራችን በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ በርካታ ሕጻናትን ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ለማየትና ለመርዳት የሚያስችላቸውን የዓለም አቀፍ ከፍተኛ ድጋፍ ለማስገኘት ነው ተብሏል።

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የመስክ ሥራ ልምድ ያለው ሲሆን ግንኙነቱን በማሻሻልና በመጠናከር መሠራት እንዳለበት ፕሬዚደንቷ ገልጸዋል።

ካትሪን ራስል ከሶስት ወር በፊት ነው የዩኒሴፍ ኤግዜኩቲቭ ዳይሬክትር የሆነው የተሾሙት።

ምንጭ፦ የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በዚህ ሩጫ በበዛበት ዘመን የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ካሉበት ሆነው ለመክፈል የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ አይነተኛ አማራጭ ነው። በአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ የዲኤስ ቲቪ፣ የኢትዮ ቴሌኮም፣ የዌብ ስፕሪክስ ኢንተርኔት ክፍያ፣ የትምህርት ቤት እና የተለያዩ አይነት የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ ይክፈሉ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
" ትውልዱ የፊቼ ጨምበላላን ትርጓሜና እሴቶቹን መገንዘብ ያስፈልገዋል " - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል ለሆነው ለፊቼ ጨምበላላ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በሲዳምኛ ቋንቋ /Sidaamu Afoo/ ባስተላለፉት መልእክት ፤ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ የፊቼ ጨምበላላን ትርጓሜና እሴቶቹ ሰላም ፤ ፍቅር እና አንድነት መሆኑን ትምህርት መውሰድ ወይንም መገንዘብ እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia