TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትንሳኤ

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊት እና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በዚህ የትንሳኤ በዓል ፤ በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የተቸገሩትን ፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ፤ በምድር ላይ ያሉ የሰው ልጆችን ሁሉ ይጠብቅልን።

መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
ፎቶ : የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጸሎት እና የምልጃ መርሃግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት ተካሂዷል።

በመርሀግብሩ ላይ ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ጸሎት ፣ ትንሣኤውን የሚያወድሱ ዝማሬዎች እና የእግዚአብሔር ቃል ተሰብኳል።

ምንጭ፦ የክርስቲያን ዜና

@tikvahethiopia
#Iftar

ዛሬና ትላንት ቅዳሜ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

ዛሬ በአፋር ክልል መዲና ሰመራ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን በጅማ ከተማም እጅግ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተገኘበት የኢፍጣር ስነሥርዓት ታካሂዷል።

በተመሳሳይ ዛሬ በአጋሮ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዳል።

ትላንት በአፋር ኤሊደአር ፣ ስልጤ ዞን ቃዋቅቶ እና በቂልጦ ከተማ፣ ሰሜን ምዕራብ ሸዋ ጎሮ ወረዳ፣ በአርሲ ነጌሌ፣ ባሌጎባ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ ፥ የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 18 በአዳማ ከተማ፣ ረቡዕ ሚያዚያ 19 ደግሞ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት እንደሚካሄድ ታውቋል።

በተጨማሪ ከጥቂት ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚካሄደው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶዎች ፦ telegra.ph/Iftar-04-24

@tikvahethiopia
#ትንሳዔ

ከሀገራችን ኢትዮጵያ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገራት የትንሳዔ በዓል ተከብሯል።

የትንሳዔ በዓል ልዩ በሆነ ሁኔታ ከሚከበርባቸው ሀገራት አንዷ ሩስያ ናት።

በሩስያ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት የሆኑት ቭላድሚ ፑቲን ሞስኮ በሚገኝ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ሻማ በማብራት በዓሉን ሲያከብሩ ታይተዋል።

በተመሳሳይ የትንሳዔ በዓል በዩክሬን ተከብሯል። በዓሉ በጦርነት ድባብ ውስጥ ነው የተከበረው።

ዛሬ በሁለቱም ሀገራት የተከበረው የትንሳዔ በዓል ያለተኩስ አቁም ነው ፤ በዛሬው ዕለትም በሩስያ በኩል ወታደራዊ ጥቃቶች ሲፈፀሙ እንደነበር ተገልጿል።

ከሩስያ እና ዩክሬን በተጨማሪ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ፣ በአፍሪካ ሀገራት የትንሳዔ በዓል ተከብሯል።

ፎቶ ፦ ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#ትንሳዔ

" መላው ዓለም ከስጋት ወጥቶ ፤ በሽታ በጤንነት ፣ ጦርነት በሰላም፣ ዘረኝነት በአንድነት ፣ ጥላቻ በፍቅር ተተክቶ እንድናይ ከልብ እመኛለሁ። በብርቱም እጸልያለሁ። "

" ክርስቶስ ተነስቷል እንኳን ደስ አላችሁ"

አባ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ::

ፎቶ ፦ EOTC TV / የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
#FRANCE

🗳 ማክሮን ፕሬዜዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ኢማኑኤል ማክሮን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጡ። ማክሮን ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

በፈረንሳይ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ቀኝ ዘመሙዋ ማሪን ለ ፐን ተፎካክረዋል።

በዛሬው ምርጫ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተቀናቃኛቸው ማሪን ሊ ፐንን በ58.2 % ለ 41.8 % በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን የFrance 24 ዘገባ ያስረዳል።

የማክሮንን ማሸነፍ ተከትሎ የሀገራት መሪዎች የ " እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት እያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም የደስታ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።

በሌላ በኩል ፤ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ፕሬዜዳንት ማክሮን በሚቃወሙ አካላት ተቃውሞ ተቀስቅሷል ፤ ለአብነት በፓሪስ በነበረ ተቃውሞ ማክሮንን ሊቃወሙ የወጡ ሰዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia