TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለምንድነው በዩክሬን እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት የዓለምን የምግብ ዋጋ እንዲህ እንዲጨምር ያደረገው ?

🌾 ዩክሬን እና ሩስያ በአለም የስንዴ ኤክስፖርት 1/3 የሚሸፍኑ ሀገራት ናቸው።

🪖 በሁለቱ ሀገራት መካከል ጦርነቱ ሲቀሰቀስ የስንዴ ኤክስፖርት ሊቋረጥ ችሏል።

📈 በ2 ሳምንታት ውስጥ ብቻ የስንዴ ዋጋ በ28 በመቶ ከፍ ብሏል ፤ ይህም ሪከርድ የሆነ የዋጋ ጭማሪ የተመዘገበበት ነው።

🌍 በጦርነቱ ምክንያት የታየው የዋጋ ጭማሪ በተለይ ከውጭ ሀገር በሚገባ ምርት ላይ ጥገኛ የሆኑ ሀገራትን ክፉኛ ጎድቷቸዋል።

#WFP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ ከትላንት በስቲያ ወደ ትግራይ ክልል መቐለ እየተጓዙ እንደነበሩ የተነገረላቸው 74 የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ዛሬ መቐለ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፤ የዓለም የምግብ ፕሮግራም 2,000 ሜትሪክ ቶን ሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ 74 ተሽከርካሪዎች በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ መድረሳቸውን አረጋግጧል።

ተሽከርካሪዎቹ የጫኑትን የሰብዓዊ ዕርዳታ በመቐለ ከተማ በሚገኝ መጋዘን ሲያራግፉ ድርጅቱ በትዊተር የትዊተር ገፁ ላይ በቪዲዮ አጋርቷል።

ከሰብዓዊ ዕርዳታው በተጨማሪ ነዳጅ የጫኑ አምስት ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሳውቋል።

ምንጭ፦ WFP

@tikvahethiopia
የመን ውስጥ በ " ሁቲ ኃይሎች " ታስረው የቆዩ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጨምሮ 12 ሰዎች ከእስር መለቀቃቸውን ኦማን አስታውቃለች።

ታሳሪዎቹ የተለቀቁት የብሪታንያ፣ ኢንዶዥያ፣ ህንድ እና ፊሊፒንስ መንግስታት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የኦማን ባለሥልጣናት ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ነው የተነገረው።

ኢናቾ መኮንን የተባሉ ኢትዮጵያዊን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩት የብሪታንያ ፣ ፍሊፒንስ ፣ ማይናማር ፣ ኢንዶኔዥያ እና የህንድ ዜጎች ከየመን ሰነዓ ወደ ሙስካት መዘዋወራቸውን የኦማን ውጭ ገዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከታሳሪዎቹ አንዱ የሆነው የብሪታንያ ዜጋ በሁቲዎች በሀገር ክህደት ተጠርጥሮ ለ5 ዓመታት በእስር የቆያ ሲሆን ፤ የታሳሪው ቤተሰቦች በምርመራ ወቅት እጁ መሰረበሩን፣ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጤናው እንዲቃወስ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁቲዎች ኢትዮጵያዊውን ግለሰብ ለምን እና መቼ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ላይ የተገለፀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት

@tikvahethiopia
" ባይደን ታሪክን በደንብ መማር አለበት፤ ይህ ሳያውቅ ቱርክን ለመከራከር መሞከሩን ይቅር አንለውም " - ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ በ1915 በአርመን የተካደውን ክስተት ለሁለተኛ ጊዜ " የዘር ማጥፋት " ድርጊት ነው ብለው ገልፀው ነበር።

ይህንን አገላለፅ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ኮንነውታል።

ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በቱርክ በፕሬዝዳንት ቤተመንግስት የነበረውን ስብሰባ በመሩበት ወቅት ነው የባይደንን ንግግር የኮነኑት።

ኤርዶጋን ፤ በአርመኒያ ተደርጓል ስለተባለው ወንጀላ፤ በጥቂት ሀገራት እና ፓርላመንቶች የሚሰጠው አስተያያት በቱርክ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ለ1915 የአርመን ክስተት በውሸት እና በሃሰተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ኤርዶጋን " ባይደን ታሪክን በደንብ መማር አለበት፤ ይህ ሳያውቅ ቱርክን ለመከራከር መሞከሩን ይቅር አንለውም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአርመን ሰዎች በዚህ የአርመንን እና የቱርክ ህዝብን ለማጋጨት አላማው ባደረገው ግብዝ አመለካከት ሲጎዱ ነበር፤ ይጎዳሉም ብለዋል።

በቱርክ እና በአርመን መካከል ያለፈ ቁርሾ ከማጋነን ይልቅ ሰለማዊ ግንኙት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ኤርዶጋን የቱርክ ላሉት የአርመን ፓትሪያሪክ መልእክት መላካቸውን ተነግሯራ።

በቱርክ የሚገኙ አርመኖች በመጀመሪያው የአለም ጦርነት የደረሰባቸውን መጥፎ ሁኔታ በቱርክ ተሰባስበው አስበዋል፡፡

ምንጭ ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US_VISA አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በስቴት ዲፓርትመንት በተቀመጡና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች መሰረት Diversity Visa (ዲቪ) ን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኛ እና ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ሂደት ማስቀጠል መጀመሩ ዛሬ አሳውቋል። እስካሁን በትዕግሥት ለጠበቁም " ትዕግስታችሁን እናደንቃለን " ብሏል። የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ ቀጠሮ ለመያዝ ጊዜው ሲደርስ አመልካቾች መረጃ በኢሜል ይላክላቸዋል…
#US_VISA

የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ የ Diversity Visa (ዲቪ) ን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኛ እና ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ሂደቶች እያስቀጠለ መሆኑን ገልጿል።

ኤምባሲው አገልግሎቱን እየተጠባበቁ ያሉ ሁሉ ፤ በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 እና በኢትዮጵያ ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደኃላ የቀሩ ስራዎችን ለመስራት በሚደረገው ሂደት በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክቱ አስተላልፏል።

የቪዛ ቃለመጠይቆች ሂደት ሚከናወነው በስቴት ዲፓርትመንት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በመመስረት መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው ፤ አሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሁሉም የቪዛ መደቦች ላይ በተቻለ መጠን ብዙ ቃለ መጠይቆችን ለማድረግ በማቀድ በትጋት ስራቸውን እያከናወኑ ነው ብሏል።

በዚህም ሂደት ላይ ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች ይዘው ለቃለ መጠይቅ ዝግጁ ሆኖ በመምጣት የሁሉንም ሰው የጥበቃ ጊዜ እንዲቀንስ ለማድረግ ማገዝ ይችላሉ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በዚህ ሩጫ በበዛበት ዘመን የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ካሉበት ሆነው ለመክፈል የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ አይነተኛ አማራጭ ነው። በአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ የዲኤስ ቲቪ፣ የኢትዮ ቴሌኮም፣ የዌብ ስፕሪክስ ኢንተርኔት ክፍያ፣ የትምህርት ቤት እና የተለያዩ አይነት የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ ይክፈሉ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል።

ምርጫ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ ፦ ፓርቲው ከሚያዚያ 18 /2014 ዓ/ም ጅምሮ በ2 ወራት ጊዜ እስከ ሰኔ 18 /2014 ዓ/ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ ብሏል።

በተጨማሪም ፤ ፓርቲው በደንቡ መሰረት የሚቀርፃቸውን አጀንዳዎች ጨምሮ በጉባኤው የመነጋገር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ቀደም እልባት ያላገኘው " የአመራር ሪፎርም ወይም ለውጥ ማድረግ " የሚለው ለጉባኤው በአጀንዳነት ቀርቦ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥበት እና አግባብነት ያለው ምርጫ እንዲደረግ ብሏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አመሠራረት እና ሂደት ፣ ከኮሚሽነሮቹ እና ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በቀረበ ጥያቄ መሠረት የውይይት መድረኩ እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፋ ፤ ሀገራዊ ምክክሩ #ተስፋ_የተጣለበት እና #ለሀገራችን_ብቸኛ_አማራጭ በመሆኑ ቀጣይ በሚኖረው ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን መግለፃቸውን የህ/ተ/ምክር ቤት አሳውቋል።

የኮሚሽነሮቹን የአሰያየም ሂደት በተመለከተ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና በፍትህ ሚ/ሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር ) ማብራሪያ መሰጠቱ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በጎንደር አለመረጋጋት መኖሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እየጠቆሙ ይገኛሉ።

ችግር የተፈጠረው ፤ ዛሬ በነበረ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ነው ተብሏል።

ሸይኽ ከማል ለጋስ ለበርካታ አመታት የጎንደርን ህዝብ በሀገር ሽማግሌነት ያገለገሉ ትልቅ አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ሸይኽ ከማል ፤ ለበርካታ ዓመታት የጎንደርን ማህበረሰብ በባህል ህክምናና በሃገር ሽማግሌነት አገልግለዋል።

ሸይኽ ከማል የሙስሊምም የክርስቲያንም አባት የነበሩ ሲሆን በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ " አባ ለጋስ " ተብለው ይታወቃሉ ፤ የ " ሰሜኑ ኃያል (የአባሼይኽ ለጋሥ) " የበኩር ልጅም ናቸው።

ዛሬ በሸይኽ ከማል ስርዓተ ቀብር ላይ በተፈጠረው ችግር ምክንያት በጎንደር ከተማ የሰው ህይወት ማለፉ፣ ጉዳትም መደረሱን ለመስማት ተችሏል። አሁንም ከተማይቱ ወደመረጋጋት አልተመለሰችም።

በጉዳዩ ዙሪያ እና ዛሬ ስለተፈጠረው ክስተት ሁሉ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት አሰባስበን የምናካፍል ሲሆን ያለው ችግር ከዚህ ወደከፋ ሁኔታ ሳይሸጋገር የህዝብ ደህንነት ይመለከተናል የሚል አካል ሁሉ ችግሩ እንዲቀረፍ ርብርብ እንዲያደርጉ የጎንደር ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ " በጎንደር ከተማ ምን እየተካሄደ ነው ያለው ? እንደ ሃገር ያሳለፍናቸው የትላንት መጥፎ ጠባሳዎች ሳይሽሩ ዛሬም ለዘመናት የማይጠፉ ጥቁር ጠባሳዎችን መጣል ለምን አስፈለገ ? የክልሉ መንግስት ፣የፀጥታ ሃይሎች፣ የሐይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች የት አላችሁ? እየተፈፀመ የሚገኘውን ጥፋት ባስቸኳይ ማስቆም ይገባቹኃል " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት በጎንደር አለመረጋጋት መኖሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እየጠቆሙ ይገኛሉ። ችግር የተፈጠረው ፤ ዛሬ በነበረ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ነው ተብሏል። ሸይኽ ከማል ለጋስ ለበርካታ አመታት የጎንደርን ህዝብ በሀገር ሽማግሌነት ያገለገሉ ትልቅ አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ሸይኽ ከማል ፤ ለበርካታ ዓመታት የጎንደርን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጎንደር ምንድነው የሆነው ?

ትላንት በጎንደር ከተማ ላይ በተፈጠረው ችግር ሰዎች ሞተዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ የግለሰብ ቤቶቻ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

ችግሩ እንዴት ተፈጠረ ለሚለው የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ፤ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመበት መስጂድ ጥግ ቤተክርስቲያን እንዳለ ገልፀዋል።

ቦታው ህጋዊ በሆነ መንገድ ሽማግሌዎች በጋራ ተስማምተው ከፍለውታል፤ ተለይቶም ያደረ ነው ሲሉ አስታውሰዋል።

ትላንትና በመስጂዱ የታላቁ የሙስሊም አባት (ሸይኽ ከማል ለጋስ) የቀብር ስነስርዓታቸው እንደተፈፀመ ፤ ምእመኑ ለቀብር ስነስርዓት የሚያስፈልጉ ድንጋዮችን ለማንሳት በተንቀሳቀሰበት ወቅት ችግሩ መፈጠሩን ገልፀዋል።

አቶ ደሳለኝ ፤ " ድንጋይ አንስተው ወደ ቀብር ስነስርዓት የሚሄዱ ወገኖችን " ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ገብታችሁ ነው ድንጋይ የምታነሱት " በሚል ምክንያት ድንጋይ የሚያነሱትን ሰዎች ወረወሩባቸው እና ግጭት ተፈጠረ ፤ ይህ የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን የመሄድ ፍላጎት ነበረው " ብለዋል።

" ኦርቶዶክስም፣ ሙስሊሙም በጋራ የቀብር ስነስርዓት የሚፈፅም ፣ በማህበራዊም ፣ በኢኮኖሚም ችግር አብሮ የሚኖር ጨዋ ህዝብ ነው " ያሉት ኃላፊው " የሚታወቁ ሃይማኖቶች እጅግ ትልልቅ ክብር ያላቸው ሃይማኖቶች ናቸው ይሁን እንጂ ይህን ሀይማኖት ጥላሸት ለመቀባት የሚፈለጉ ቡድኖች ያን ግጭት ለማባባስ በቀባሪዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ተጀመረ " ብለዋል።

" ግጭቱን መልክ ለማስያዝ የፀጥታ ኃይል በቦታው ለመግባት ሞክሯል " ያሉ ሲሆን የተዛባ መረጃ በመስጠት በያለበት ያለው ወጣት ወደግጭት እንዲገባ ለማድረግ ግፊት ተፈጥሯል " ሲሉ ሁኔታው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጎንደር ምንድነው የሆነው ? ትላንት በጎንደር ከተማ ላይ በተፈጠረው ችግር ሰዎች ሞተዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ የግለሰብ ቤቶቻ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። ችግሩ እንዴት ተፈጠረ ለሚለው የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ፤ የሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመበት መስጂድ ጥግ ቤተክርስቲያን እንዳለ ገልፀዋል። ቦታው ህጋዊ በሆነ መንገድ ሽማግሌዎች በጋራ ተስማምተው ከፍለውታል፤ ተለይቶም…
#Gondar

በጎንደር ከተማ በሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ከተፈጠረ ግጭት በኃላ በተፈፀመ ጥቃት እስካሁን ባለው ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸው ፤ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ መስጂዶችም መጠቃታቸው ፣ ከዚህም አልፎ ንብረት መውደሙ ፣ የግለሰብ ቤቶች መጠቃታቸውን የጎንደር ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት በበኩሉ ፤ በጎንደር ሙስሊሙን የማጥቃት፣ መስጂዶችን የመድፈር እና ንብረቶቹን የማውደም የተደራጀ ጥቃት እናወግዛለን ብሏል።

ዛሬ የጎንደር ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ ትላንት በአራዳ ክ/ከተማ የተፈጠረው ሁኔታ በፍፁም የክርስትና እና እስልምና እምነት ተከታዮችን ሊወክል የማይችል ነው ብሎታል።

ምክር ቤቱ ጥፋቱ የተፈፀመው በጥቂት ጽንፈኛና አክራሪ ግለሰቦች የተከበሩትን የሁለቱን ዕምነት ተከታዮች ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ ለግጭት የማያበቃ ምክንያትን በመምዘዝ ጥፋት እንዲፈጠር የተቀነባበረና የተመራ ሴራ ነው ሲል ገልጾታል።

በዚህ እኩይ ተግባር ከሁለቱም የዕምነት ተከታዮች የህይዎትና አካል መጉደል እንዲሁም የንብረት መቃጠልና ዘረፋ አጋጥሟል ሲል አሳውቋል።

አሁን አካባቢው ሙሉ በሙሉ ከፀጥታ መዋቅርና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ትብብር በማድረግ የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ ስምሪትና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳውቋል።

ሙሉ መግለጫው በዚህ ተያይዟል ፦ https://telegra.ph/Gondar-04-27

@tikvahethiopia