TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle📍 በዛሬው ዕለት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ከባለፈው መስከረም ወር ወዲህ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የመጀመሪያውን የህክምና ቁሳቁስ ድጋፎችን ማድረስ መቻሉን አሳውቋል። አስፈላጊ መድሃኒቶችን ያካተተው የአስቸኳይ ህክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት በክልሉ በጣም ለተጎዱ የጤና ተቋማት ይደርሳል ተብሏል። ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጨማሪ በረራዎችን በማዘጋጀት…
#Tigray , #Mekelle 📍
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በረራ ዛሬ (ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም) ሁለተኛውን ዙር የአስቸኳይ ህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ አድርሷል፡፡
#ICRC
@tikvahethiopia
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በረራ ዛሬ (ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም) ሁለተኛውን ዙር የአስቸኳይ ህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ አድርሷል፡፡
#ICRC
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዩኤኢ ጥላው የነበረው እገዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ይነሳል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከ " ኦሚክሮን " ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ከተወሰኑ የአፍሪካ አገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ እገዳ ጥላ እንደነበር ይታወሳል። እገዳው ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኬንያ፣ ከናይጄሪያ እና ከሌሎች ስምንት የአፍሪካ አገራት ወደ ግዛቷ የሚጓዙ ተጓዦችን ያካትት እንደነበር አይዘነጋም። ይህንን…
" የዱባይ በረራ ቅዳሜ ይጀምራል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረውን በረራ ወደ ዱባይ እንደሚጀምር ዛሬ አሳውቋል።
ተጓዦች የጉዞ ምዝገባ ለመያዝ ይህንን 👉 https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ማስፈንጠሪያ መጠቀም እንደሚችሉ አየር መንገዱ ጨምሮ ገልጿል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረውን በረራ ወደ ዱባይ እንደሚጀምር ዛሬ አሳውቋል።
ተጓዦች የጉዞ ምዝገባ ለመያዝ ይህንን 👉 https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ማስፈንጠሪያ መጠቀም እንደሚችሉ አየር መንገዱ ጨምሮ ገልጿል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ምክንያታዊ ድርድር ይካሄዳል ብለውናል " - አቶ መስፍን ተገኑ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስታቸው ከህወሓት ጋር የተኩስ አቁምን በተመለከተ እንደሚደራደር መናገራቸውን አሶስየትድ ፕሬስ አንድ የዳያስፖራ ቡድን ሊቀ መንበርን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የዳያስፖራ ቡድን አባላት ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ባካሄዱት የግል ውይይት ከትግራይ ኃይሎች ጋር ተኩስ አቁምን…
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስለድርድር ምን አሉ ?
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህ መግለጫ ላይ ከሰሞኑን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዳይስፖራ አባላት ጋር በዝግ በመከሩበት ወቅት ከህወሓት ጋር ስለሚደረግ ድርድር ተናግረዋል በተባለው ጉዳይ አስተያየት ሰጥተዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፦
" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ ' ህወሓት ' እንደራደር ብለዋል ብሎ አንድ ሰው ተናገረ ያ ሰው የተናገረውንም አንድ ጋዜጠኛ ሪፖርት አደረገ ነው የተባለው ...እኛ ግን Officially በዚህ ረገድ የተባለ ነገር የለም ፤ አልተባለም።
ይሄ ድርጅት አሁንም በህግ designated የሆነ terrorist ድርጅት ነው።
የተባለው ግልፅ ነው፤ ለሰላም ተብሎ እኮ ኢትዮጵያ አንድ ብቻዋን አንድ ጊዜ ከትግራይ የመጣችበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን ከ terrorist ድርጅት ጋር እንነጋገራል የሚል አቋም የተገለፀበት አጋጣሚ የለም። "
ከቀናት በፊት የአሜሪካን ኢትዮጵያውያን ህዝባዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር መስፍን ተገኑ ለአሜሪካው የዜና ወኪል አሶሼትድ ፕሬስ (ኤፒ) የዳያስፖራ ቡድን አባላት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ባካሄዱት የግል ውይይት ወቅት ከህወሓት ጋር ተኩስ አቁምን የተመለከተ ድርድር ይካሄዳል ሲሉ ዶ/ር ዐቢይ እንደነገሯቸው ገልፀው ነበር፤ ዜና ወኪሉም የሳቸውን (አቶ መስፍን ተገኑ) ቃል ዋቢ አድርጎ ነበር ዜናውን ያሰራጨው።
የቡድኑ አባላት ከዶ/ር ዐቢይ ጋራ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ለ5 ሰዓታት መነጋገራቸውን የገለጹት አቶ መስፍን ተገኑ ዶ/ር ዐቢይ የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ምክንያታዊ ድርድር ይካሄዳል ማለታቸውን ነበር ለአሶሼትድ ፕሬስ የገለፁት።

#ETHIOPIA😷
የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 7,758
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 456
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 11
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,334
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 316
ዛሬ ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ አጠቃላይ 1,407 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 38 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

#MostInfluentialYoungAfricans
#አቫንስ_ሚዲያ_አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመትን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር የነበሩት ፊልሰን አብዱላሂ፣ ሳሙኤል አለማየሁ እንዲሁም ቢታኒያ ሉሉ ብርሃኑን በ2021 ከ100 ተፅእኖ ፈጣሪ የአፍሪካ ወጣቶች ዝርዝር ውስጥ አካቷቸዋል።
አቫንስ ሚዲያ 100ዎቹ 2021 ተፅእኖ ፈጣሪ የአፍሪካ ወጣቶች በተለያየ መስክ የተሰማሩ መሆናቸውን እንዲሁም ከ100ዎቹ መካከል 52ቱ ወንዶች 48ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል።
የተመረጡት 100 ወጣቶች 32 የአፍሪካ ሀገራትን እንደሚወክሉ አሳውቋል።
በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱ መካከል የጎረቤታችን ሀገር ሱዳን ኢንቬስተር ኢስላም ኤልቢቲ የምትገኝበት ሲሆን በእግር ኳሱ ዓለም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁት ሰኢዶ ማኔ፣ ሪያድ ማሃሬዝ ፣ ኩሉባሊ ፤ ፔየርኤምሪክ ኦባምያንግ ፣ ሞሀመድ ሳላ ይገኙበታል።
ምንጭ፦ https://t.co/SfVdxF0qD0

#Ethiopia #Sweden
የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አን ሊንዴ ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል።
የሁለቱ ወገኖች ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።
ምክት ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወናቸው ስላላቸው የሰላም ውጥኖች በተለይም በቅርቡ እስረኞች ስለመፍታታቸው እና ስለሀገራዊ ምክክሩ በዝርዝር ነግረዋቸዋል።
መንግስት ወታደሮቹ ወደ ትግራይ ክልል የሚያደርጉትን ግስጋሴ ለማስቆም ቢወስንም ሕወሃት በአጎራባች ክልሎች ለምሳሌ በአፋር ክልል ' አባአላ ወረዳ ' ላይ ጥቃት በመክፈት ወደ ክልሉ የሚደርሰውን ሰብአዊ ርዳታ ማደናቀፉን ገልፀዋል።
አቶ ደመቀ ስዊድን በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ሚዛናዊ አቀራረብን በመከተሏ አመስግነዋል።
የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አን ሊንዴ በበኩላቸው የመንግስትን የሰላም ተነሳሽነት አድንቀው ለመደገፍም ቃል ገብተዋል፤ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መንገድ እንደሚጠርግ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።
ስዊድን በኢትዮጵያ ለሚካሄድ ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ሂደት ድጋፍ እንደምታደርግ እና በልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር መስራቷን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

#UNSC #ETHIOPIA
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ በኢትዮጵያ ጉዳይ ዛሬ ስብሰባ ይቀመጣል።
ስብሰባው በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ስብሰባው እንደደረግ የጠየቁት ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ፣ አሜሪካ፣ አየርላንድ ፣ ፈረንሳይ እና አልቤኒያ ናቸው።
የፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ ጊዜ አንስቶ ከ12 ጊዜ በላይ ስብሰባ ተቀምጧል።

#Update
የገርጂ ሮባ-መብራት ኃይል መንገድ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።
በወሰን ማስከበር ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቆየው የገርጂ ሮባ ዳቦ -መብራት ኃይል አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቁ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት መደረጉን የአዲስ አበባ መንገዶችን ባለስልጣን አሳውቋል።
በፕሮጀክቱ የግንባታ ወሰን ውስጥ የነበሩ ቤቶች በፍርድ ቤት እግድ ምክንያት በወቅቱ ባለመነሰታቸው ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ሳየቻል መቆየቱ ተገልጿል።
ይህም በአካባቢው የትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ መቆየቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውሷል።
አሁን ላይም ችግሩ እልባት በማግኘቱ የፕሮጀክቱን ቀሪ የአስፓልት ማልበስ ፣ የእግረኛ መንገድ እና የቀለም ቅብ ስራዎች ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጿል።
መንገዱ ሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በተለይ ከመብራት ኃይል እስከ ሮባ ዳቦ ድረስ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ቀርፏል፡፡
መንገዱ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር ስፋት አለው፡፡

#NorthKorea ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማክሰኞ 2 ተጨማሪ የክሩዝ ሚሳዬሎችን በመተኮስ መሞከሯን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ፡፡ ይህ በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት አምስተኛው የሚሳዬል ሙከራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የደቡብ ኮሪያ ጦር ዝርዝሩ እየተጠና መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ ዓመት ውስጥ ብቻ ባደረገቸው 5 ሙከራዎች 8 ሚሳዬሎችን መተኮሷ ተገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1950 የተካሄደውን…
ለ6ኛ ጊዜ !
ሰሜን ኮሪያ ትላንት 2 የተጠረጠሩ የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ ተነግሯል።
ይህ የሚሳኤል ሙከራዋ በዚህ ወር ብቻ ለ6ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑ ነው።
#TheEphoTimes
@tikvahethiopia
ሰሜን ኮሪያ ትላንት 2 የተጠረጠሩ የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ ተነግሯል።
ይህ የሚሳኤል ሙከራዋ በዚህ ወር ብቻ ለ6ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑ ነው።
#TheEphoTimes
@tikvahethiopia
#HY_Online_Shopping
የጀርባ ፣ የወገብ መደገፊያ እና የውፍረት መቀነሻ
Call 0988102508 ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን።
የወገብ እና የጀርባ ችግር አለቦት?
- ሙሉ የወገብ 900 ብር ፣ የትከሻ 650 ብር
- የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣የጀርባ ዲስክ መንሸራተት
- የሰዉነትዎ ውፍረት መቀናሻ #Hot belt ከወገብ በላይ 950 ብር ፣ የቦርጭ 650 ብር
ቦሌ ሄድሞና ህንጻ HY Shop

#Amhara , #Kobo 📍
በአዲስ ጥቃት ምክንያት ቆቦ ላይ ተፈናቃዮች መስፈራቸውን ተሰምቷል።
ቆቦ ከተማ የሰፈሩት ከዋጃ ፣ ጥሙጋና አላማጣ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ናቸው።
ከተፈናቃዮቹ መካከል ከበርካታ ወራት በኃላ ወደ መኖሪያ ቄያቸው ሀገር ሰላም ነው ብለው የተመለሱ ይገኙበታል።
አንድ ከዋጃ የተፈናቀሉ ግለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ አካባቢው ነፃ ወጣ ከተባለ በኃላ የመንግስት ሚዲያዎችም ገብተው ዘግበው እንደነበር ነገር ግን በታህሳስ 29 የህወሓት ታጣቂዎች ተመልሰው እንደገቡ ከዛ በኃላ ህፃናት ፣ሴቶች፣ እናቶች ተፈናቅለው ወደ ቆቦ መምጣታቸውን ገልጿል። ህዝቡ ስቃይ ላይ ነው የሚዲያ ሽፋንም እያገኘ አይደለም ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
ተፈናቃዮቹ በአሁን ሰዓት ከባድ የሚባል የምግብ እንዲሁም የአልባሳት እጥረት እንዳለባቸው ተነግሯል።
የዋጃ ጥሙጋ ቀበሌ ዋና አስተዳደሪ ያሬድ አድማሱ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ የህወሓት ኃይሎች ከታህሳስ መጨረሻ ጀምሮ ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ እና እንደአዲስ በከፈተው ጥቃት ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አሳውቀዋል።
ተፈናቃዮች በቆቦ ከተማ በሁለት ካምፕ ውስጥ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ፤ ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በትግራይ አዋሣኝ ቦታዎች አብአላ፣ በርሃሌ ኤሬብቲና መጋሌ በከፈተው አዲስ ጥቃት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሙሉ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሳውቀዋል።

#USA #ETHIOPIA
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የክትባት ደጋፍ አደረገች።
አሜሪካ 1,680,120 ዶዝ የፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ አድርጋለች።
ይህ የክትባት ድጋፍ በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ አሳውቋል።

የአሜሪካ መግለጫ ፦
አሜሪካ በአፋር እና ትግራይ ክልል አዋሣኝ አካባቢዎች አዲስ የተቀሰቀሰው ጦርነት ያሳስበኛል አለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው" ብለዋል።
ፕራይስ ከቀናት በፊት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግጭቱ አካባቢ ላሉ ሰዎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ግጭቱ በድርድር እንዲጠናቀቅ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል።
ኔድ ፕራይስ በትላንትናው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት በመላው አገሪቱ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉ የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው ገልጸዋል።
"ይህ ውሳኔ [የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቃል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕራይስ ፤ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሰዎች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።
ቃል አቀባዩ ፤ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስቆም የሚቻለው በድርድር ግጭት ሲቆም፣ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ሲፈቀድ እና ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ መሠረት ሲጣል ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።