TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥምቀት

የኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።

የበዓሉ ታዳሚዎችና እንግዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆንና በዓሉን በሰላም እንዲከበር ግብረ ኃይሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ስምሪት ወስዶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጿል፡፡

ግብረኃይሉ ፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ የፀጥታ አካላት ማሰማራቱን ገልፆ በታቦታት ማደሪያ ስፍራዎችና በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት አካባቢ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የተከላከሉ ተግባራት ፦

• ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ ነው።

• በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ አይችሉም።

• ምንም አይነት የጦር መሳሪያ፣ ተቀጣጣይም ሆነ ስለታማ ቁሳቁስ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም።

የበዓሉ ታዳሚዎች ለደህንነት ሲባል ፍተሻ የሚደረግ መሆኑን ከወዲሁ በማወቅ እና በመረዳት ትብብር እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በፍጥነት ለጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥቆማ ለመስጠት በስልክ ቁጥር ፦
• +251115-52-63-03፣
• +251115-52-40-77፣
• +251115-54-36-78 እና
• +251115-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀምና በአካባቢው ላለ የፀጥታ ኃይል መረጃውን በአካል ማድረስ ይቻላል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ሰሜን_ኮሪያ

ሰሜን ኮሪያ ሁለት የተጠረጠሩ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን (SRBM) በመዲናዋ ፒዮንግያንግ ከሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር ማሳወቁን ሮይተርስ ዘግቧል::

ጃፓን በተመሳሳይ መወንጨፉን ሪፖርት አድርጋ ድርጊቱን የሰላም እና የፀጥታ ጠንቅ ነው ስትል አውግዛለች። ቻይና በበኩሏ ሁሉም ወገኖች የቀጠናውን መረጋጋት እንዲያስጠብቁ ስትል አሳስባለች::

ዛሬ ሰሜን ኮሪያ እንዳስወነጨፈች የተነገረው የሚሳኤል ሙከራ በዚህ ወር 4 ኛው ነው ተብሏል:: ኒውኩሌር የታጠቀችው ሰሜን ኮሪያ ከዛሬ በፊት ከ2 ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 3 የሚሳኤል ሙከራዎች አድርጋለች:: ይህም ያልተለመደ ፈጣን ተከታታይ ሙኩራ ነው ተብሏል::

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሚወጣው ምዕመን ግጭት ቀስቃሽ ጽሑፎችን እና አርማ የሌላቸውን ባንዲራ ይዞ መውጣት እንደማይችል አስታወቀ::

ፖሊስ ኮሚሽኑ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ምዕመኑ ከበዓሉ አላማ ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ከማድረግ ተቆጥበው በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል::

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል::

በዓሉ የአደባባይ በመሆኑ በሁሉም አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር በግልጽና በስውር የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩን ጠቅሰዋል።

በዓሉ በሚከበርባቸው ሁለት ቀናት ወደ ማክበሪያ ቦታው መግባት የሌለባቸው ግጭት የሚቀሰቅሱ ጽሑፎች ፣ አርማ የሌለው ባንዲራ እንዲሁም ስለታማ ነገሮች ይዞ መግባት እንደማይቻልም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል::

ምንጭ : አሀዱ ሬድዮ (ፎቶ - ከኢዜአ)

@tikvahethiopia
#GoodayOn Mobile App

የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!

አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም

ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
800,000💵

ትላንትና ምሽት በታላቁ ቤተ-መንግስት " በገበታችን ሀገር እንገንባ ፤ በትብብር ወገን እናግዝ " በሚል መርህ በተካሄደ የእራት መርሀ ግብር ከትኬት ሽያጭ ብቻ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ መገኘቱ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በትላንት ምሽቱ የእራት መርሀ ግብር ከትኬት ሽያጭ በቀጥታ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።

በመረሐግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ? ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦ " ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው። አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ…
“አንድም መንግስት ‘እነዚህ ሰዎች ታስረዋልና ፍታ ብሎ የጠየቀኝ የለም” - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትላንት በቤተ መንግስት በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ፤ በቅርቡ ከእስር የተፈቱ እስረኞችን በተመለከተ “ጉዳዩን እኛም መጀመሪያ ስንሰማ ደንግጠን ነበር” በሚል ለተናገሩት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እስረኞችን ለመፍታት ከውሳኔ ላይ የተደረሰው ከወር በፊት እንደነበር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሆኖም የሚፈቱ የእስረኞች ዝርዝር እርሳቸውን ጨምሮ ለካቢኔ አባላት የቀረበው የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ የህዳሴው ግድብ በሚገኝበት ስፍራ በተደረገ የሚኒስትሮች ስብሰባ ወቅት እንደነበር አስረድተዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ “እውነቱን ለመናገር ፖለቲካሊ እስረኞችን ለመፍታት ‘እነዚህን ጉዳዮች እናሳካ ነው’ ያልነው እንጂ፤ እነማን ይፈቱ የሚለውን በቀደም ህዳሴ [ግድብ] የሚኒስትሮች ስብሰባ እስካደረግንበት ቀን ድረስ እኔም አላውቅም። እንፍታ ብለን ወስነናል። ዐቃቤ ህግ ሲያጠና ቆይቶ፤ ዝርዝር አመጣልን። ‘እነ እንትናማ አይቻልም፤ እነ እንትና ይቻላል’ ተጨቃጭቀን የተወሰኑ ሰዎች ላይ ወስነን መጣን” ሲሉ ስለ ሂደቱ ገለጻ አድርገዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ እስረኞችን ለመፍታት ሲወሰን የንግግሩ ማዕከል “ ግለሰቦች አልነበሩም ” ያሉ ሲሆን የውይይቱ ማጠንጠኛ “የበጎ ፍቃድ ምልክት (gesture) እና ሆደ ሰፊነት (magnanimity) ያስፈልጋል” የሚል እንደነበር ገልጸዋል። “ሀሳቡ፤ ዝም ብሎ ድርቅ ያለ ነገር አድርገን ሀገራችንን እንዳንጎዳ የሚል ነው” ሲሉ አክለዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከውሳኔው ጀርባ “ የሌላ ሀገር ግፊት አለ ” በሚል ለሚቀርቡ አስተያየቶችም በትላንቱ ንግግራቸው ምላሽ ሰጥተዋል። እስረኞቹ እንዲታሰሩም ሆነ እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረበ “አንድም መንግስት” እንደሌለ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “አንድም መንግስት ‘እነዚህ ሰዎች ታስረዋልና ፍታ ብሎ የጠየቀኝ የለም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የእስረኞች ፍቺ ጉዳይ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ውይይት የተደረገበት ከአንድ ወር በፊት መሆኑን የጠቆሙት አብይ፤ ውሳኔው “እስከ ታች ድረስ” ውይይት የተደረገበት እንጂ “እንግዳ ጉዳይ” እንዳልነበር ገልጸዋል።

“ሁሉም ክልል ተወያይቶበታል። አሁን ድንገት ደርሶ ‘ድንገት ሆነብኝ’ የሚለው ተቀባይነት የለውም። ከወር በላይ ተወያይተንበታል። አዲስ ነገር አይደለም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

Credit : ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሊቀ ጳጳስ ዘኢሉባቡር አረፉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነሥርዓት እና ቀብራቸው የሚፈጸምበት ቦታን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ይገለፃል ተብሏል።

መረጃው የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
በቀን 22 በረራ ወደ ጎንደር !

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለጥምቀት በዓል አከባበር ለሚጓዙ ደንበኞቹ ክብረ ወሰን ሆኖ የተመዘገበ በቀን 22 በረራዎች ማድረጉን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ምድቧን የማለፍ እድል አላት ? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ ሀ ሦስተኛ የጨዋታ መርሐ ግብር ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር ዛሬ ምሸት 1 ሰዓት ላይ በባፎሳም ስታዲየም ያካሂዳል። ለመሆኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ምድቧን የማለፍ እድል አላት ? ትላንት መግለጫ የሰጡት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተከታዩን ተናግረዋል ፦ " ሁለት ቡድኖች በቀጥታ ከምድቡ ያልፋሉ። ጥሩ ሶስተኛ ሆኖ…
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናበተች።

ሀገራችን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆናለች።

ብሄራዊ ቡድናችን ዛሬ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ እኩል ቢለያይም በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

በዛሬው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምት ለሀገራችን ብቸኛዋን ጎል በ52ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

@tikvahethiopia
#Hosaena

ቤተ-ክርስቲያኒቱ ለ40 ዓመታት ስታቀርብ የነበረው ጥያቄ ተመለሰላት።

የሆሳዕና ከተማ የጥምቀት እና የመስቀል ደመራ ማክበሪያ ቦታ ምላሽ ማግኘቱን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከጥንት ጀምሮ ስትጠቀምበት የነበረውን የባህረ ጥምቀት እና የመስቀል ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲያገኝ ከ1974 ዓ/ም ጀምሮ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግስት አካላት ጥያቄ ስታቀርብ መቆየቷን ፅ/ቤቱ አስታውሷል።

ነገር ግን ጥያቄው ምላሽ ባለማግኘቱ እና ቦታውም ለሌላ ማህበራዊ አግልግሎት እንዲውል በመደረጉ በቦታው ላይ የአደባባይ በዓላቶች ማክበር የማያስችሉ በርካታ ችግሮች በመፈጠራቸው ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የአደባባይ በዓላቶቿን ማክበር ሳትችል መቅረቷ ተገልጿል።

በመጨረሻም ለ40 ዓመታት ሲቀርብ የነበረው ጥያቄ የደቡብ ክልል መንግስት ፣ የሀዲያ ዞን እና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ለችግሩ ትኩረት በመስጠት ባደረጉት ጥረት ለጥያቄው ተገቢው ምላሽ መሰጠቱን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት ዛሬ አሳውቋል።

ቤተክርስቲያኒቱ ፥ የ2014 ዓ/ም የጥምቀት በዓልን ምዕመናን በጋራ እንዲያከብሩ ጥሪዋን አቅርባለች።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 6,094
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 881
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 15
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,731
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 420

ዛሬ ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ አጠቃላይ 3,647 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 45 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሱዳን 2 ሰዎች ተገደሉ። ጎረቤት ሀገር #ሱዳን በተቃውሞ መናጧን የቀጠለች ሲሆን ትላንት እሁድ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን ለማወቅ ተችሏል። በኦምዱርማን እንዲሁም በካርቱም በሀገሪቱ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል። የሱዳን የዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ በትላትናው ሰልፍ የሁለት ሰዎች ማለፉን ሪፖርት ያደረገ ሲሆን አንደኛው ሟች ትላንት አንዱ ደግሞ ዛሬ…
#SUDAN

ዛሬ በጎረቤት ሀገር ሱዳን 7 ሲቪሎች ተገደሉ።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ በዛሬው እለት በተካሄደ የፀረ መፈንቅለ መንግስት ሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ 7 ንፁሀን ዜጎች በፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን አሳውቋል።

ኮሚቴው ፥ " የጁንታው ኃይሎች ጭፍጨፋቸውን ቀጥለውበታል፣ ሰላማዊ የሱዳን ተቃዋሚዎች ገዳይ ከሆነ ሃይል ጋር እየተጋፈጡ ነው " ብሏል።

በዛሬው ሰልፍ በቀጥታ በተተኮሱ ጥይቶች ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ሪፖርት መደረጋቸውን እና ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጿል።

ኮሚቴው ፤ መላው ዓለም በሰላማዊ መንገድ ለ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊት አገር ወደፊት እየተጓዘ ያለውን የሱዳን ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀሎች በቅርበት መከታተል እና ለማስቆምም ከበድ ያለ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል ሲል አስገንዝቧል።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ፥ ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ወዲህ የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 71 እንደደረሰ ሪፖርት አድርጓል።

@tikvahethiopia
#UAE

ዛሬ UAE ውስጥ በድሮን መሆኑ በተገመተ ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 6 ሰዎች ቆስለዋል።

የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE) ባለሥልጣናት የደሃቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካል በሆነው ስፍራ የሚገኙ 3 የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንከሮች በድሮን መሆኑ የተገመተ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የአገሪቱ መንግሥት ዜና አገልግሎት ባለሥልጣናቱን ጠቅሶ እንዳስታወቀው በደረሰው ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡

ከሟቾቹ መካከል 2 ህንድ እና 1 የፓኪስታን ዜጋ እንደሚገኙበት ተነገሯል፡፡

ፖሊስ ሁኔታው እየተጣራ መሆኑን ቢገልጽም የየመን ሁቲዎች ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት (UAE) ጠልቆ የሚገባ ጥቃት የሰነዘሩ መሆናቸውን ቢያስታውቁም ስለ ሁኔታው ግን ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም፡፡

ሁቲዎች ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉም አስጠንቅቀዋል።

የዩናይትድ አረብ ኤምሬት (UAE) እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ የየመን ሁቲዎችን የሚወጋውና በሳኡዲ አረብያ የሚመራው የጦር ህብረት አባል መሆንዋ ይታወቃል፡፡

ዘገባውን ቪኦኤ አሶሼይትድ ፕሬስ እና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀው ሲሆን በተጨማሪ የአልጀዚራ መረጃ ተካቶበታል።

@tikvahethiopia