ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 7 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,775 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 298 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily
@tikvahethiopia

ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ - አዲስ አበባ !
ሰሞኑን አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ተክለኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን ውስጥ በአስክሬን ሳጥን ተደርጎ የጦር መሳሪያ ተቀብሮ ተያዘ በሚል በተለየዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ወሬ ትክክለኛ መረጃ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ከልደታ ክ/ከተማ በተገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ ከኢትዮጲያ ውጭ በመሞቱ ምክንያት ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሟቹን የሚያውቁት ነዋሪዎች አስፈላጊውን ህጋዊ ሂደት ተከትለው ከውጭ እንዲመጣ በማድረግ አሰክሬኑ በተክለ ሐይማኖት ቤ/ክርስቲያን እንዲያርፍ አደርገዋል፡፡
ቀብሩ ሲፈፀም ጥቂት ሰዎች በተገኙበት መሆኑና የአስክሬን ሳጥኑ ከመደበኛውና ከሚታወቀው አይነት ውጪ መሆኑ ያጠራጠራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለፖሊስ መረጃ ሰጥተዋል፡፡
ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ኮሚቴ አዋቅሮና ከቤተ-ክርስቲያኗ አባቶች ጋር በመሆን ፍተሻ በማድረግ በተቀበረው የአስክሬን ሳጥን የሰው አስክሬን እንጂ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ልተገኘ መሆኑን ተረጋግጧል፡፡
ፖሊስ ባስተላለፈው መልዕክት ማነኛውንም አጠራጣሪ ነገሮች ሲታዩ መረጃውን ለፀጥታ አካላት የማድረሱ ተግባር የሚደነቅና ሊበረታታ የሚገባው ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያጎለብት ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

#ማሳሰቢያ
ቤት የሚገዙ፣ የሚሸጡ ሁሉ ስራቸው ህገወጥ ስለሆነ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት አሳስቧል።
የቋሚ ንብረት ሽያጭ የቆመ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎቱ ሳይጀመር ሽያጭ እና ማስተላልፈ በመንደር ውል እና በውክል እየተሰራ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።
የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ፤ በውክልናም ሆነ በመንደር ውል የቤት ሽያጭ ማከናወን ህጉ እንደማይፈቅድ ገልፀዋል።
አገልግሎቱ የሚጀምርበትን ጊዜ እናሳውቃለን ብለዋል።
" ቤት ሽያጭ ውል ሰነድ የማረጋገጥ አገልግሎት ነው " ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ " ይህ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል። ተቋሙ በተለይ ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ህገወጥ ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ እየሰረ ስለሆነ ከዛ ጋር ተያይዞ ላልተገባ ሰዎች ያልተገባ ውል ውስጥ እንዳይገቡ ያን የማረጋገጥ ስራ እስኪጠናቀቅ በጊዜያዊነት አገልግሎቱን መስጥ ቆሟል " ሲሉ አስረድተዋል።
ይሄ ህገወጥ ይዞታዎችን የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰ ጊዜ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም መኖሪያ ቤት ሽያጭ / በስጦታ የማስተላለፍ ውሉ አሁንም ለጊዜው እንደተቋረጠ ይቀጥላል ሲሉ አሳውቀዋል።
ተቋሙ የተቋረጠውን አገልግሎት በሚጀምርበት ሰዓት በግልፅ በተለያየ ሚዲያ መረጃውን የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።
በተለይ የተጠራቀመ አገልግሎት ካለ ተገልጋዮች በሰልፍ ብዙ ሳንይገላቱ ለመስራት አሰራር ተዘርግቶ ይኬዳል ሲሉ ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡ ላልተገባ የመንደር ውል ሆነ ባልተገባ መረጀ ላይ ተመስርቶ ከሚደረጉ ውሎች እንዲቆጠብ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ለሸገር ራድዮ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

#Oromia
በኦሮሚያ ክልል መንግስት የሰዓት እላፊ ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎች ተላልፏል።
የክልሉ መንግስት ውሳኔውን ያሳለፈው በአገሪቱ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በማለም ነው።
በዚህም መሰረት ፦
• በክልሉ የሰዎችና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ለሊት 11፡30 ድረስ እንቅስቃሴ ማድረግ ተከልክሏል።
• ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከለሊት 11፡30 እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ሲሆን ተሸከርካሪዎች ግን መንቀሳቀስ የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ብቻ ነው።
• በመንገድ ላይ ፍተሻዎች ይኖራሉ። ድንገተኛ ፍተሻ ይካሄዳል፤ በኬላዎችም ላይ ፍተሻ ይደረጋል። በመንግሥት መስሪያ ቤቶችና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎችም ፍተሻዎች ይካሄዳሉ። አብዛኛዎቹ ፍተሻዎች ምሽት ላይ የሚካሄዱ መሆናቸው ተጠቁሟል።
• በክልሉ የሚገኙ አከራዮች የተከራዮቻቸውን መታወቂያ በመያዝ በቀበሌና በአቅራቢያቸው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እየሄዱ ማስመዝገብ አለባቸው።
• አከራዮች አዲስ ተከራይ፤ ያለመታወቂያ ቤት ማከራየት የሌለባቸው ሲሆን መታወቂያ የሌላቸው ተከራዮች ካሉ መታወቂያ እንዲያወጡ ጊዜያዊ አሰራር ተዘርግቷል።
ተጨማሪ ፦ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች በ10 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ታዟል።
መረጃው የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳ ለቢቢ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዱኛ አሕመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነው።
@tikvhaethiopia

#GONDAR
በጎንደር ከተማ በፋሲል ክፍለ ከተማ በአንድ ሪስቶራንት ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሬስቶራንቱ ወደመ።
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኢስፔክተር ስማቸው ፈንታ እንደገለፁት በከተማዋ በፉሲል ክፍለ ከተማ ከቀኑ 8 ስዓት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የሪሴቶራንቱ ቁሳቁስ የወደመ ሲሆን የእሳት አደጋው ምክኒያት እየተጣራ መሆኑን እንስፔክተር ስማቸው ገልፀዋል።
ከሪስቶራንቱ የተነሳው የእሳት አደጋ በዙሪያው ያሉ ቤቶች መጠነኛ ጉዳት ቢደርስም በፀጥታ አካላትና በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ የእሳት ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻሉን ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል።
በእሳት አደጋ መከላከል ስራው ላይ የነበረ አንድ ግለሰብ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እየተደረገለት መሆኑ ጠቁመዋል።
መረጃው የጎንደር ኮሚኒኬሽን ነው።

#Somali
በሶማሊ ክልል ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ፡፡
ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታ ክትባት ዘመቻ በቀብሪ በያ ወረዳ በገብሪ እና በጊሎ ቀበሌዎች የፌደራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ዛሬ በይፋ የተጀመረው።

በዩጋንዳ ካምፓላ ሊካሄድ የነበረው ጉባኤ ተላለፈ።
የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት (IGAD) አባል ሀገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት በሰላም ስለሚያበቃበት መንገድ ለመነጋገር ለዛሬ ይዘዉት የነበረዉ ቀጠሮ ተሰረዘ።
በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነት የኢጋድ አባል ሐገራት መሪዎች ዛሬ ካምፓላ-ዩጋንዳ ዉስጥ ተገናኝተዉ እንዲነጋገሩ የጠሩት የዩጋንዳዉ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴ ቬኒ ነበሩ።
ነገር ግን የዛሬው ጉባኤ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ አስነብቧል። ጉባኤዉ የተላለፈበትን ምክንያትም ሆነ የሚደረግበት ቀን አልተጠቀሰም።

#Uganda: ዛሬ በኡጋንዳ በደረሱ 2 የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡
ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡
በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡
በካምፓላ ሁለት የገበያ ማዕከላት ላይ ደረሰ የተባለው ይህ የዛሬ ረፋድ የሽብር ጥቃት በአገሪቱ ፓርላማ መግቢያ አካባቢ ነው የተፈጸመው፡፡
የአገሪቱ ፖሊስ በበኩሉ አደጋው በሁለት የአገር ውስጥ የሽብር ቡድን አባላት አማካኝነት በተመሳሳይ ሰዓት በተለያዩ ቦታዎች ፍንዳታው መድረሱን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ይሁንና እስካሁን በሽብር ድርጊቱ ዙሪያ ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን የአገሪቱ ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመርኩ ነው ብሏል፡፡
ከ1 ወር በፊት በካምፓላ ከተማ ባለ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ በደረሰ ተመሳሳይ የሽብር አደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሀላፊነቱን አይኤስ አይ ኤስ ለድርጊቱ ሃላፊነት ወስዶ ነበር፡፡
በዚሁ ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ ቀናት ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት እራሱን ገድሎ በርካቶችን ማቁሰሉ አይነጋም
Credit : Al AIN

የዳሰሳ ጥናት በአማራ ክልል :
(ዶቼ በለ)
የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ህወሓት በክልሉ ላይ በከፈተው ጦርነት እና ወረራ በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የዳሰሳ ጥናት አድርጓል።
በዚህም ፦ ህወሓት በወረራ በያዛቸው እና ነፃ በንብረት ብቻ 280 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ማውደሙንና መዘረፉን ኮሚሽኑ አሳውቋል።
አብዛኛው ዝርፊያና ውድመት በግብርናው ዘርፍ የተፈፀመ ነው።
ጥናቱ የተካሄደው ወረራ በተካሄደባቸው 45 ወረዳዎች ሲሆን የደሴና ኮምቦልቻ አካባቢዎችን አላካተተም።
የደሴንና የኮምቦልቻ አካባቢ ውድመት በጥናት ሲረጋገጥ የውድመቱና የዘረፋው ሁኔታ የከፋና ግዙፍ እንደሚሆን ተገልጿል።
በዳሰሳ ጥናቱ በከፊልና በሙሉ ተቋማትን የዳሰሰ ሲሆን የግብርናው ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ደግሞ የወደመውንና የተዘረፈውን የግብርና ምርት ለማካካስ 100ሺህ ማሳ በመስኖ በማልማት 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማልማት አውጃለሁ ብሏል።
በጦርነቱ ምክንያት በተለይ በምስራቅ አማራ ዞኖች ከፍተኛ የምርት ቅናሽ ይኖራል። የማካካሻ ሥራ እንደሚሰራ ተገልጿል።
በጥናቱ መሰረት በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና ውስጥ ከ6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፋ የኑሮ ጉስቁልና መዳረጉና ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ናቸው፡፡

ፎቶ : የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ለመጀመር ዛሬ ኬንያ ገብተዋል።
ብሊንከን ኬንያ ሲደርሱ በአምባሳደር ሬይሼል ኦማሞ (የውጭ ጉዳይ ካቢኔ ጸሃፊ) አቀባበል ተደርጎላቸዋል።