#FDREDefenseForce
የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን በአሁኑ ሰዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮች የተሰጣቸውን ስልጠና አጠናቀዋል።
ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሠራዊቱ ጋር በመቀላቀልከ ውስጥ እና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopia

28 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ተመለሱ።
በህገወጥ ስደት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ ጉዞ ከአገር ወጥተው የታንዛኒያን ድንበር ጥሰው ሲገቡ በአገሪቱ ፖሊስ ተይዘው የነበሩ 28 ታዳጊዎች በትላንትናው እለት ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
ታዳጊዎቹቹ ከሌሎች 36 እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ከሆኑ ስደተኞች ጋር በአንድነት ተይዘው የነበሩ ሲሆኑ፤ የታንዛኒያ መንግስት እድሜያቸው አነስተኛ የሆኑትን ለማሰር የማይችል በመሆኑ በአፋጣኝ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ኤምባሲው ሁኔታውን እንዲያመቻች ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የተመለሱ ናቸው ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአገራችን ዜጎች በታንዛኒያ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ያሉ በመሆኑ ሁሉንም ዜጎች ወደ አገር ቤት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ3 ሽህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ዩኒቨርስቲው በ9 የትምህርት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 40 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡
ምንጭ፦ አሚኮ

''...ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው'' - አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ የዘፈን አልበም ምርቃትና የአንደኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተው ነበር።
አርቲስቱ በህይወት እያለ ያዘጋጀው ሶስተኛው የዘፈን አልበም፤ 'ማል መሊሳ' በሚል ርዕስ ታትሞ ለአድማጮች ቀርቧል። የዘፈኑ 300 ሺህ ቅጂ በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጀ ሲሆን አልበሙም 14 ዘፈኖችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።
ትናንት ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ለአርቲስቱ ሙት ዓመት መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአርቲስቱ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ''ሀጫሉ በህይወት ቢለይም ትውስታውና ስራዎቹ ህያው ናቸው'' ብለዋል።
ከአርቲስቱ ህልፈት ቦኃላ ከቤተሰቡ ጎን ሆነው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የአርቲስቱን ስም ባልተገባ መንገድ ለመጠቀም የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ''ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው'' ብለዋል። ''የልጄ ገዳዮች ህግ ፊት ቀርበው ፍትህ እንዲያገኙ ሁሉም እንደየ ሀይማኖቱ ጸሎት ያድርግልኝ'' ሲሉም ጥ አቅርበዋል።
በመርሃ-ግበሩ የጥበብ ስራዎችን የሚያግዝና በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመ ፋውንዴሽን ተቋቁሟል።
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22 በአዲስ አበባ በሰው እጅ በጥይት ተመቶ መገደሉ አይረሳም።
#ENA

ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈረደባቸው።
የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።
የ79 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ በአገሪቱ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ፍ/ቤት መገኘት ሲኖርባቸው ባለመገኘታቸው ከህግ ተቋማት ትችቶች ሲቀርብባቸው ነበር።
ይህ እውነትን አፈላላጊ ኮሚሽን አቋቁሞ የዙማን ጉዳይ እየተመለከተ የነበረ ሲሆን ጃኮብ ዙማ ግን በዚህ ፍርድ ቤት አልቀርብም ሲሉ በይፋ ተቃውመው ነበር።
ዙማ በዚህ የኮሚሽኑ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ፍቃደኛነት ባለመሆናቸው ባለፈ ፈርድ ቤቱ ገለልተኛ አይደለም በማለታቸው ፍርድ ቤት ተዳፍረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
የዙማ ድርጊት ፍርድ ቤቱን መናቅና መድፈር በመሆኑ ሕግ አለማክበርን ያበረታታል፤ ሌሎችን ለህግ ተገዢ እንዳይሆኑ ያደርጋል የሚሉ ሀሳቦች ሲነሱ ቆይቷል።
የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በቀድሞው ፕሬዘዳንት ድርጊት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።
ዙማ እስሩ የተላለፈባቸው በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ቀጣይ የፍርድ ክርክር ላይ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አላከበሩም በሚል ነው።
ምንጭ፦ አል ዓይን

ችሎት !
በእነ አቶ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ጉዳዩን በዋነኛነት የያዘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የምስክር አቀራረብ ሒደት ላይ የግራና ቀኝ የህግ ክርክር በመመርመር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ እንዲመሰክሩ ያዘጋጃቸው 16 ምስክሮች #በግልጽ_ችሎች እንዲመሰክሩ ወስኗል ።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ውሳኔውን ያሳለፈው፤ ምስክሮች “ለደህንነታቸው” ሲባል በዝግ ችሎት ከመጋረጃ ጀርባ እንዲሰሙ በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን ጥያቄ በተከሳሾች እና በደጋፊዎቻቸው በኩል ለዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ምንም አይነት በቂ የሆነ በምክንያት እና በእውነት አስረጂ የሆኑ የደህንነት ስጋት አላገኘሁም ፤ በማለት ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕግ የመጋረጃ ጀርባ ምስክርነት ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሐምሌ 8 እና 9 እንዲሁም ሐምሌ 14 ፣15 እና 16 በአምስት ቀናት ውስጥ እንደሚሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
መረጃው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ባልደራስ) ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ነው።

#Update
ከሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 777 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ::
ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን የማስወጣት የተጠናከረ ዘመቻ እያደረገች መሆኑ ይታወቃል::
በዚህ መሰረትም በትናትናው ዕለት 1 ሺህ 777 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል::

የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !
የፊታችን እሁድ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም "መንገድ ለሰው” ከተሽከረካሪ ነፃ መንገዶች ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት በእለቱ ፕሮግራሙ የሚካሄድበት እና ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው ፡-
1. ከልደታ ኮንደሚኒያም ጌጃ ሰፈር፣
2. ቤተል ወይራ ሰፈር ፊት ለፊት፣
3. ቤተል ከወረዳ 5 እስከ ታክሲ ተራ፣
4. ቤተል ከኪዳነምህረት እስከ ቤተል አደባባይ፣
5. ከሜክሲኮ አደባባይ በሸበሌ እስከ ብሄራዊ ትያትር፣
6. ከስድስት ኪሎ እስከ ሚኒሊክ ፣
7. በስፔን ኤምባሲ መነን ት/ቤት፣
8. መካኒሳ ከአምጎ ካፌ እስከ ቆሬ አደባባይ፣
9. ገላን ኮንደሚኒየም አካባቢ፣
10. ከለቡ ጀሞ፣
11. ከፊጋ ሳሚት መብራት፣
12. ሳሚት ኮንደሚኒየም፣
13. የካ አባዶ፣
14. ቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣
15. ጎተራ ኮንደሚኒየም
#AMN