የደቡብ ሱዳን ፓርላማ ተበተነ !
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሀገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት (ፓርላማ) እና የክልል ምክር ቤቶች እንዲበተኑ ወስነዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ውሳኔውን ያሳለፉት እ.ኤ.አ. በ2018 በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሠረት ፣ የሀገሪቱ መንግስት ተቃዋሚዎች የተካተቱበት አዲስ ፓርላማ እንደገና እንዲዋቀር ለማድረግ ነው፡፡
የሀገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እንዲበተኑ የሚደነግገው የፕሬዝደንቱ ውሳኔ የተነገረው ቅዳሜ ምሽት ላይ በመንግስት ቴሌቪዥን በተላለፈው ፕሬዚዳንታዊ አዋጅ ነው፡፡
በመንግስት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ በይፋ ከጁባ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት የብሔራዊው ፓርላማ አባላት እና የክልሎች ምክር ቤት አባላት የአገልግሎት ጊዜ አብቅቷል፡፡
በ2018ቱ የሰላም ስምምነት የተሳተፉ ፓርቲዎች 400 አባላት የነበሩት ብሔራዊ ፓርላማው 550 አባላትን እንዲያካትት የተስማሙ ሲሆን በሳልቫ ኪር የሚመራው መንግስት 332 አባላት ሲኖሩት ፣ በሪክ ማቻር የሚመራው የታጠቀ የተቃዋሚ ቡድን ደግሞ 128 አባላት ይኖሩታል፡፡ ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ በ 50 አባላት ይወከላሉ፡፡
ፓርቲዎቹ በተጨማሪም የክልሎች ምክር ቤቶች በሰላም ስምምነቱ ለእያንዳንዱ ፓርቲ በተመደበው መጠን የሚከፋፈሉ 100 አባላትን እንዲያካትቱም ተስማምተዋል፡፡
እስካሁን የክልል ም/ቤት አባላት 50 የነበሩ ሲሆን በአዲሱ ስምምነት መሠረት የአባላቱ ቁጥር በእጥፍ አድጓል፡፡
የመንግስት የስራ አስፈፃሚ አካል ባለፈው ዓመት መመስረቱን ተከትሎ ሁለቱ ምክር ቤቶች ተበትነው እንደአዲስ መዋቀር የነበረባቸው ከአንድ ዓመት በፊት ነበር፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

'ኢፍጣር'
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ "መስቀል አደባባይ" በዓይነቱ ትልቅ የተባለ የኢፍጣር ዝግጅት ለማዘጋጀት የተለያዩ ስራዎች ባለፉት ቀናት ሲሰራ ቆይቷል።
ነገር ግን ይህን ታላቅ ነው የተባለው የኢፍጣር ፕሮግራም አልጋ በአልጋ ሆኖ ሊሳካ አልቻለም።
ህዝቡ ለኢፍጣር ወደ አካባቢው ቢሄድም የፀጥታ ኃይሎች እንዲመለሱ አድርገዋል። የአስለቃሽ ጭስም መተኮሱን በስፍራው የነበሩ አባላት ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ እጅግ በርካታ ነገር እየተባለ ቢሆንም አዘጋጆቹ ግን በመንግስት አካል ተገደው እንደሰረዙት ገልፀዋል።
የዛሬውን ፕሮግራም አዘጋጅተው የነበረው ሀላል ፕሮሞሽን ፣ ከነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመሆን ነበር።
“ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” በሚል ከተዘጋጀው ፕሮግራም ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ለዝግጅቱ ህጋዊ ፍቃድ ከሚመለከተው አካል አግኝቶ እንቅስቃሴ መጀመሩ አስታውሰዋል።
ሆኖም ከመንግስት አካላት ዘንድ የዝግጅት ቦታውን እንዲቀየር የተጠየቀ ሲሆን ይህም ፍፁም ተገቢ አለመሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት በማስረዳት ንግግር ሲደረግ ነበር።
ነገር ግን መንግስት በአቋሙ በመፅናቱ አዘጋጆቹም እንደተለዋጭ የተሰጠው ቦታ ላይ ፕሮግራሙን ማከናወን የማንችሉ መሆኑን በመግለፅ ዝግጅቱን ለመሰረዝ ተገደዋል።
ምንም እንኳን ዝግጅቱ ቢሰረዝ በርካቶችም ቀድሞ ወደተዘጋጀው ቦታ ለመሄድ ሞክረው ነበር። የፀጥታ ኃይሎች በየአካባቢው ሆነው ክልክላ ተፈፅሟል።
በዛሬው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ በታዳሚነት እንድንገኝ እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጥሪ ካርድ ተዘጋጅቶልን የነበረ ቢሆንም ፕሮግራሙን ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሰረዙን ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-09
@tikvahethiopia

"..ይህን ታሪካዊ ክስተት እንዲደናቀፍ እጅ የነበራቸው ሁሉ ተጠያቂ ሲሆኑ ማየት እንሻለን" - ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የዛሬው የአፍጥር ታዳሚ ቁጥር 100 ሽ እንደሚደርስ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ገልፀዋል።
ኡስታዝ ያሲን በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ፥ "ይህ ህዝብ ባሰበው እና በታቀደው መልኩ በሰላም አፍጥሮ፣ ለሀገሩ ሰላም ፀልዮ ፣ ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር ማዕድ ተካፍሎ ቢጠናቀቅ ለኢትዮጰያ ደማቅ ታሪክ ይሆን ነበር" ብለዋል።
ይህን ታሪካዊ ክስተት እንዲደናቀፍ እጅ የነበራቸው ሁሉ ተጠያቂ ሲሆኑ ማየት እንሻለን ሲሉም ገልፀዋል።
በ Hayat Regency በኩል ከነበረው በርካታ ምዕመናን ጋር አብረው እንዳፈጠሩ ተገለፁት ኡስታዝ ያሲን ፥ ምእመኑ ከእሳቸው ጋር አብሮ ሰግዶ በሰላም መለያየቱን አሳውቀዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

* Update
ዛሬ ማምሻውን ኡስታዝ አቡበክር አህመድ "ከተማ አቀፍ የጋራ ኢፍጣር ፕሮግራሙ ያጋጠመውን መስተጓጎል በኃላፊነት ስሜት በመወጣት ሰላማችንን እናስጠብቅ" በሚል በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiBOT

የ "ነሲሓ" ኢፍጣር ፕሮግራም !
«ነሲሓ» የተሰኘ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት፤ በዛሬ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ጎዳናዎች ላይ 12 ኪ.ሜ የሸፈነ ጾመኞችን የማስፈጠር መርሃ ግብር አካሂዷል።
የቦታዎቹ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው።
①) ዓለም ባንክ ከሚገኘው ኢማሙ አሕመድ መስጂድ አደባባይ ጀምሮ እስከ ቤተል ባለው መንገድ፣
②) ከቢላል ኮካ መስጂድ ወደ አብነት ባለው መንገድ በጭድ ተራ አልፎ እስከ ተክለ ኃይማኖት ድረስ፣
③) ዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር ከግራር እስከ ሰለፊያ መስጂድ ባለው መንገድ!
④) ከጦር ኃይሎች ወደ 18 አደባባይ በሚወስደው መስመር ሲታለፍ ከአባ ጅፋር መስጂድ በሸይኽ ደሊል (ዑሥማን ኢብኑ አፋን) መስጂድ አድርጎ በ01 እህል በረንዳ መዳረሻውን መሳለሚያ ቢላል መስጂድ ባለው መንገድ።
⑤) ኮልፌ ከሙስሊም መቃብር ሎሚ ሜዳ እስከ አስኮ መንገድ!
⑥) አስኮ አዲስ ሰፈር በድር መስጅድ መንገድ ናቸው።
መረጀውን ከድርጅቱ ነው የደረሰን።

' ኢፍጣር በባህር ዳር '
ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ታላቅ ነው የተባለ ኢፍጣር ስነ ስርዓት መካሄዱ ተገልጿል።
ፎቶ : ሀሩን ሚዲያ