TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'ሺዎች ታድመውታል የተባለው ኢፍጣር ስነስርዓት በቃሉ ወረዳ '

ዛሬ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ እና በሃርቡ ከተማ የተፈናቀሉና ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን ያሳተፈው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂድል።

ስነስርዓቱ በተሳካ መልኩ በሰላም መጠናቀቁን ከወረዳው ኮሚኒኬሽን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ወረዳው ፥ "ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከሃብት ማሰባሰብ፣ ከፅዳትና ከማስተባበር እስከ ፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ድረስ በአንድነትና በአብሮነነት በማከናወን መላው ሙስሊም ማህበረሰብ ከእምነት ባሻገር የነበረውን የወሎየነት እሴት፣ ወግና ባህል ያንፀባረቀ ፕሮግራም እንደነበረ በተግባር ታይቷል" ብሏል።

አጭር መረጃ ስለገርባ ከተማ ኢፍጣር ፦

- ከ4,000 በላይ ፆመኞችን፣ የተፈናቀሉና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ነበር።

- የአፍጢር ፕሮግራሙ በዋናነት አንድነትንና አብሮነትን ለመግለፅ ያለመ ነበር።

- ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከአፋር ክልል አዳይቱ፣ ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ፣ ከደቡብ ክልል ጉራፈርዳና ቤንች ሸኮ፣ ከቤኒሻንጊል ጉምዝ ክልል መተከልና ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አጣዬና አካባቢው ተፈናቅለው በገርባ ከተማና በቻይና ካምፕ ተጠልለው የሚገኙ እና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ነበር።

@tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት 17 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 5,303 የላብራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,716 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 262,702 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,888 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 206,870 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 740 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,295,723 ደርሷል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
'ኢፍጣር' ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ "መስቀል አደባባይ" በዓይነቱ ትልቅ የተባለ የኢፍጣር ዝግጅት ለማዘጋጀት የተለያዩ ስራዎች ባለፉት ቀናት ሲሰራ ቆይቷል። ነገር ግን ይህን ታላቅ ነው የተባለው የኢፍጣር ፕሮግራም አልጋ በአልጋ ሆኖ ሊሳካ አልቻለም። ህዝቡ ለኢፍጣር ወደ አካባቢው ቢሄድም የፀጥታ ኃይሎች እንዲመለሱ አድርገዋል። የአስለቃሽ ጭስም መተኮሱን በስፍራው የነበሩ አባላት ተናግረዋል። በዚህ…
የመስቀል አደባባይ 'ኢፍጣር' እና የመንግስት መግለጫ !

ቀደም ሲል በሰጠነው መረጃ ላለፉት በርከታ ቀናት ሰፊ የሆነ ዝግጅት ሲደረግበት ነበር የተባለው የአ/አ መስቀል አደባባይ ኢፍጣር ስነስርዓት አዘጋጆቹ እንዳሉት 'ተገደው' ሊሰረዙት ችለዋል።

ምዕመኑ ግን ወደስፍራው በብዛት የሄደ ቢሆንም የከተማው የፀጥታ ኃይሎች ወደቦታው እንዳይገቡ አድርገዋቸዋል።

በተላኩልን የፎቶ ማስረጃዎችም በርካታ የፀጣታ ኃይሎች አካባቢው ላይ ሰፍረው ሰዎችን ሲመልሱ ታይተዋል።

የአስለቃሽ ጭስ መተኮሱንም በስፍራው የነበሩ አባላት ገልፀዋል።

በተለይም ምዕመኑ እንዲሁም የሃይማኖት መምህራን ሁኔታው ወደሌላ እንዳይሄድ በማድረግ ፤ የነበረው ሁኔታ ረግቦ ሁሉም ምዕመን ወደ ቤቱ ሄዷል ተብለናል።

ስነስርዓቱ መከልከሉ በርካቶችን ያስቆጣ ነበር።

የአ/አ ከተማ ስለጉዳዩ ምን አለ?

የአ/አ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ባሰራጨው መልዕክት አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ አደባባይ የኔ ያንተ ብሎ አይጣላም ሲል ገልጿል።

በአንድ በኩል የአደባባዩ የመጨረሻ የግንባታ ሥራዎች አለመጠናቀቁ ፤ ከሥነ - ሥርዓቱ መከናወን ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ የደብዳቤ ልዉዉጥ ካደረጉት አካላት ጋር በመወያየት በጋራ ግንዛቤና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተና ያለንበትን አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ ፕሮግራሙ በታቀደዉ መሠረት የኢፍጣር ቦታዉ ስፋቱ እና ርዝመቱ እንዲያሳትፈዉ ከታሰበዉ የታዳሚ ብዘት አንጻር እንቅፋት እንዳይፈጠር እዛዉ በዉስን አካባቢ እንዲካሔድ እንደመፍትሔ ተወስዶ ነበር ብሏል።

አዘጋጆቹ የኢፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ ውስንነት ላይ ስላልተሰሙ የመሰረዝ አማራጭን ወስደዋል ሲል ገልጿል።

ሙሉ መግለጫው: telegra.ph/AAPS-05-09

@tikvahethiopia
*Update

የኮቪድ-19 ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ :

- ትላንት በዓለም አቀፍ ደረጃ 649,149 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ 10,206 ሰዎች ሞተዋል።

- ህንድ ውስጥ ትላንት 366,499 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ 3,748 ሰዎች ሞተዋል።

- ብራዚል ትላንት 34,162 ዜጎቿ ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን እና 934 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች።

- ትላንት ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባቸው ሀገራት ስንመለከተ፦

• ኮሎምቢያ 495
• አርጀንቲና 283
• ሩሲያ 334
• ቱርክ 283 ይገኙበታል።

- የአፍሪካ አቀፍ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ፦ ትላንት 7,320 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 220 ሰዎች ሞተዋል። ደቡብ አፍሪካ 1,596,595፣ሞሮኮ 513,864 ፣ቱኒዝያ 320,813፣ ኢትዮጵያ 262,702 ታማሚዎችን ሪፖርት በማድረግ የቀዳሚዎችን ቦታ ይዘዋል።

ክትባት ፦

የዓለም ጤና ድርጅት ለ "ሲኖፋርም" በቻይና ኩባንያ የተዘጋጀ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጥቶታል።

ይኸ ሲኖፋርም የተባለው ኩባንያ በቤጂንግ ባዮሎጂካል ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የቻይና ክትባት ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ይኸን ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት በበርካታ አገሮች ሥራ ላይ የዋለው ክትባት በሁለት ዙር የሚሰጥ ነው።

ከዚህ ቀደም ፋይዘር-ባዮንቴክ፣ ሞዴርና፣ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን እንዲሁም አስትራዜኔካ በተባሉ ኩባንያዎች የተሰሩ ክትባቶች በአስቸኳይ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውሉ ፈቃድ ሰጥቶ ነበር።

#Purpose

@tikvahethiopia
"....በቂ ዝግጅት ተደርጎ 2ኛው ዙር የግድቡ የውኃ ሙሌት የሚከናወንበት ጊዜ እየተጠበቀ ነው" - ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ

[ ኢፕድ ]

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውኃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ፥ ሱዳን በቅርቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መሬት የእኔ ነው የሚል ያልተገባ ትርክት ይዛ መምጣቷ ኢትዮጵያ ትኩረቷን ከግድቡ እንድታነሳ ለማድረግ የተቀየሰ ሴራ መሆኑን ገልፀዋል።

ፕ/ር ያዕቆብ ፥ ሱዳን በቅርቡ የቤኒሻንጉል መሬት የእኔ ነው የሚል ያልተገባ ትርክት ይዛ መጥታለች ፤ ትርክቱ በሀገራቱ መካከል ያለውን የድንበር ችግር የበለጠ በማወሳሰብ ኢትዮጵያ ትኩረቷን ከግድቡ እንድታነሳ ያለመ የሱዳን እና የግብጽ ምኞት ነው ብለዋል።

የአንድን ሉዓላዊ ሀገር መሬት የእኛ ነው በማለት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስተጓጎል መጣር ከንቱ ምኞት ነው ያሉት ፕሮፌሰር ያዕቆብ ኢትዮጵያ ባቀደችው መሠረት ግድቧን ሰርታ ትጨርሳለች፤ ለዚህም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቂ ዝግጅት ተደርጎ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት የሚከናወንበት ጊዜም እየተጠበቀ ነው ያሉት፡፡

እንደ ፕሮፌሰር ያዕቆብ ገለጻ፤ ቀደም ሲልም ግብጽና ሱዳን የግድቡን ግንባታ ሊከለክሉትና ሊያስጓጉሉት የሚችሉበት ምንም መንገድ አልነበረም። አቅምም አልነበራቸውም። በዚህ የተነሳ ከኢትዮጵያ ጋር ስለግድቡ አሞላል እና ስለግድቡ የውኃ አያያዝ ውይይት ሲያደርጉ ነው የቆዩት።

እነርሱ የሚሠሩት ሥራ ሁሉ ኢትዮጵያ ግድቧን ጨርሳ፣ ውሃ ሞልታ፣መብራት የምታገኝበትን መንገድ ሊያደናቅፍ የሚችል አይደለም ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-05-10

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ተገደለ።

የኦቢኤን ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ትናንት ከቀኑ 11፡30 ላይ ከሰርግ ቤት ሲመለስ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሁለት ታጣቂዎች መገደሉን በቄለም ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ሰላም አስከባሪ ምክትል ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር አህመድ ያሲን ገለፁ።

ኢኒስፔክተር አህመድ ፥ ግድያውን የፈፀሙት የ 'ሸኔ' ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

የወንጀሉ ፈፃሚዎች ማንነት እንደተደረሰበትና ክትልል እየተደረገባቸው መሆኑን ኢንፔክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ኦቢኤን (OBN) ፥ "ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ህዝባዊ ወገንተኝነትን እንዲሁም መልካም ስነ-ምግባርን የተላበሰ ጠንካራ ጋዜጠኛ ነበር" ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የመስቀል አደባባይ 'ኢፍጣር' እና የመንግስት መግለጫ ! ቀደም ሲል በሰጠነው መረጃ ላለፉት በርከታ ቀናት ሰፊ የሆነ ዝግጅት ሲደረግበት ነበር የተባለው የአ/አ መስቀል አደባባይ ኢፍጣር ስነስርዓት አዘጋጆቹ እንዳሉት 'ተገደው' ሊሰረዙት ችለዋል። ምዕመኑ ግን ወደስፍራው በብዛት የሄደ ቢሆንም የከተማው የፀጥታ ኃይሎች ወደቦታው እንዳይገቡ አድርገዋቸዋል። በተላኩልን የፎቶ ማስረጃዎችም በርካታ የፀጣታ ኃይሎች…
ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይቅርታ ጠይቁ !

ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ 'መስቀል አደባባይ" የኢፍጣር ስነስርዓት መስተጓጎሉ መግለፁ ይታወሳል።

ወደስፍራው ሰዎች እንዳይሄዱም የፀጣታ ኃይሎች ክልከላ ሲያደረጉ እንደነበረም ሲገለፅ ነበር።

የአ/አ ከተማ መግለጫ አውጥቶ የተፈጠረው ሁኔታ ላይ ማብራሪያ መስጠቱ አይዘነጋም።

ዛሬ ጥዋት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሙስሊም ማህበረሰብን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ም/ከንቲባዋ ለሙስሊም ወገኖች ባሰራጩት የይቅርታ መልዕክት ላይ "የኢትዮጵያ አደባባዮች የሁሉም ኢትዮጵያዊን ናቸው" ብለዋል።

አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ፤ አደባባይ "የኔ፣ ያንተ" ብሎ አይጣላም ሲሉም አክለዋል።

ትላንት በጎዳና ላይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የአፍጥር ስነስርአት መስተጓጎሉን በተመለከተ ተከታዩን ብለዋል ፦

"ይህ የሆነው ወቅታዊ የደህንነትና የጸጥታ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የቦታው ስፋት እና ርዝመት ዉስን እንዲሆን ባቀረብነው ሀሳብ አዘጋጅ ኮሚቴው ባለማመኑ ብቻ መሆኑ ግልጽ እንዲሆን እንፈልጋለን።

የትላንት ምሽት ሁኔታ የሁላችንም ሰላም እና ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊ ጥንቃቄ ለማድረግ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ለማድረግ ብቻ የተንቀሳቀሱት እንጂ በፍፁም የአፍጥር ክልከላ አይደለም።

በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች የአፍጥር ስነስርዓት መካሄዱን አይተናል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ይህን ጉዳይ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመዉሰድ በማህበራዊ ሚዲያ ሊያራግቡት ሞክረዋል።

በዚህ ሁኔታ ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰማውን ቅሬታ የገለጸበት መንገድ ጨዋነት የተሞላበት እና ሰላማዊ መሆኑ ሊደነቅ ይገባል።"

ም/ከንቲባዋ ትላንት ለተፈጠረው ነገር በራሳቸውና በከተማ ስተዳደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል

@tikvahethiopia
ፊልትማን ኢትዮጵያ ናቸው።

ከሰሞኑን በግብፅ ፣ በሱዳን እና በኤርትራ ቆይታ የነበራቸው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጀፍሪ ፊልትማን ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ይገኛሉ።

የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጀፍሪ ፊልትማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ለልዩ መልዕክተኛው በግድቡ ግንባታ እና የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ በሚኒስትሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ክልል ጉዳይ የተናገሩበት ቪድዮ ፦ ይህ ከ14 ደቂቃ በላይ ርዝማኔ ያለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ጉዳይ የሚናገሩበት ቪድዮ የተቀረፀው በሞባይል ነው። ቪድዮው Dennis Wadley በተባሉና የሳቸው የቅርብ ወዳጅ በሆኑ ሰው በሞባይል የተቀረፀ መሆኑ ነው የተገለፀው። Dennis Wadley በአሜሪካ መቀመጫነቱን…
"... ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የተገሩት መልዕክት ሲኖዶሱን አይወክልም" - የሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ

ከቀናት በፊት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 15 ደቂቃ በሚረዝም የቪድዮ ንግግር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።

ብፁዕነታቸው በቪድዮው፥ በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሸዋሮቢት በሌሎችም ቦታዎች ችግር እንዳለ ገልፀው የትግራይ ግን እጅግ የከፋ ፣ ጭካኔ የተሞላበት መሆኑን ተናግረው ነበር።

ትግራይ ውስጥ ይሰራል ያሉት አረመኒያዊ ስራ እንዲቆም ያቀረቡት ጥይቄ አለመሳካቱን ፤ ፍቃድም እንዳልተሰጠ ገልፀው፤ የሚናገሩት ሁሉ በተደጋጋሚ እንደሚመለስ እና ፍቃድ እንዳላገኙ ተናግረው ነበር።

በተጨማሪ ያሉበትን ሁኔታ እሳቸው ብቻ እንደሚያውቁ በመናገር በትግራይ እየተፈፀመነው ያሉትን አረመኒያዊ ስራ ለመቃወም ብዙ ጊዜ እነደሞከሩ ነገር ግን ስላልተፈቀደ "እየታፈነ" እየቀረ መሆኑን አስረድተው ነበር።

ሚያዚያ 7 ቀን 2013 ያደረጉት ቃለምልልስም ታግዶ መቀረቱን በወቅቱ ገልፀው የትግራይ ግጭት አሁን ላይ 6 ወር እንደሆነውና እስካሁን ግድያ/ግፍ መቀጠሉን በመናገረ ይህን ሁኔታ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመልሰው የራሱ ዳኝነት አለው ሲሉ ተደምጠውም ነበር።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የቪድዮ ንግግር ጋር በተያያዘ ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ እኔን አይወክለኝም ሲል መግለጫ ሰጥቷል።

የቤተክርስትያኒቱ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የትኛውም መልዕክት ከመተላለፉ በፊት በሲኖዶስ በሚደረግ ስብሰባ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

በመሆኑም ፓትሪያኩ ያስተላለፉት የግል አቋም እንጂ የሲኖዶሱ ውሳኔ አይደለም ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

ዛሬ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክን በመኖሪያ ቤታቸው ተቀብለው እንዳነጋገሯቸው አሳውቋል።

አምባሳደሯ እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ በተለይ ደግሞ በትግራይ ስላለው የሰብዓዊ ቀውስ እንዲሁም ሰሞኑን ስላስተላለፉት መልዕክት ተወያያተዋል።

አምባሳደሯ ፥ ፓትርያርኩ ወደፊትም በኤምባሲው በሚካሄዱ የሃይማኖቶች / የእምነት ማኅበረሰብ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እንዲሁም ውይይታቸውን እንዲቀጥሉ ጋብዘዋቸዋል።

ምንጭ፦ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የምርምር፤ አፕላይድ ሳይንስ፣ ኮምፕሬሄንሲቭ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ቴክኒካል በሚል ከለያቸው ውስጥ የትኞቹ የቅድመ ምዘና ፈተና ይሰጣሉ ?

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመባል ከተለዩት ፦
- ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ውጪ ምንም አይነት የቅድመ ምዘና ፈተና እንደማይሰጥ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለ @tikvahuniversity ገልጿል።

ሚኒስቴሩ አሁን ላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ እንደሚገቡ ነው የገለፀው፤ ሆኖም የመጀመሪያ ዓመት (freshman) ትምህርታቸውን አጠናቀው የትምህርት ክፍል ምርጫ ሲያደርጉ የምዘና ፈተና ሊወስዱ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በተጨማሪ መረጃ ፦ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኩሪያ ንጋቱ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጠዋል።

"የምንሰጠው ስልጠና 50 በመቶው የተግባር ስልጠና በመሆኑ ብዙ ተማሪዎችን መቀበል አንችልም" ያሉት ኃላፊው፤ ስልጠናው ብዙ ሰርቶ ማሳያ ማዕከላና ከፍተኛ ሃብት እንደሚጠይቅ ነው የገለፁት።

#CARD #TikvahUniversity

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#Update

በጋምቤላ ክልል #የሙቀት_መጠኑ_በመቀነሱ የመንግስት የስራ ሰዓት ወደ መደበኛው የስራ ሰዓት እንዲመለስ መደረጉን የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታውቋል።

የመስተዳድር ምክር ቤቱ እንዳመለከተው የሙቀት መጠኑ በመቀነሱ ላለፉት ሶስት ወራት በሙቀት መጨመር ምክንያት ተቀይሮ የነበረው የመንግስት የስራ ሰዓት ከግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ቀድሞ መደበኛ የስራ ሰዓት እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት ከጧቱ አንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል የነበረው የስራ ሰዓት ከአንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል እንዲሆን ተወስኗል፡፡

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከአስር ሰዓት እስከ አስራ ሁለት ተኩል የነበረው የስራ ሰዓት ከዘጠኝ እስከ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን አመልክቷል፡፡

በተጠቀሰው የስራ ሰዓት ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ገበታው ላይ በመገኘት የተለመደ ስራቸውን እንዲከናውኑ ጥሪ ስለመቅረቡ ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ.pdf
38.7 KB
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ !

ዛሬ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በአክሱም ከተማ የወንጀል ምርመራ ተግባራትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ሠርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት የ9 አመት ልጅ በጥይት ተመቶ ቆሰለ።

በደብረ ማርቆስ ቀበሌ 07 ልዩ ቦታው ዳሊጋው ጊዮርጊስ እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በነበረው የሠርግ ፕሮግራም ላይ የወንድሙን ሽጉጥ ሰርጉ ላይ አምጥቶ ሲተኮስ የ9 አመት ልጅ አቁስሏል።

ህብረተሰቡም ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሠረት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ አስፈላጊው የምርመራ ስራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

መረጀውን ይፋ ያደረጉት የ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ገናነው ፥ እንደገለጹት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሰርግ ፕሮግራሞች ላይ ሮኬት በማፈንዳት እና አስመስለው ጥይት በመተኮስ የአካባቢያቸውን ሠላም እና ጸጥታ ከማደፍረስ አልፎ የሠው ህይወት መጥፋት እና የአካል ማጉደል ወንጀል እንደሚፈጸም አስረድተዋል።

ኮማንደሩ አክለው ፥ "ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች ላይ ከተያዘላቸው አላማውጭ በህገወጥ መንገድ አጉል ጀብደኝነትን ለመፍጠር እንዲሁም በሰፈር መሀል እታታይ የሚሉ እና ዛፍ በሌለበት እንቧጮ አድባር ነው እንደሚባለው በሠርግ ላይ ተኩሶ ጀግናነኝ ለማለት የሚደረጉ ህገ ወጥ ድርጊቶች ማህበረሰቡንም ሆነ ጥይት ተኳሹን ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ" ሲሉ አሳስበዋል።

በተጨማሪ ኮማንደሩ የመሣሪያ ፍቃድ ያላቸው ግለሠቦች ለማንም ሰው አሳልፈው መስጠት የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው ይህ ሆኖ ሲገኝ ፖሊስ ለህዝብ ሠላም እና ደህንነት ሲል አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድን አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia