#Update
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ዛሬ ጥዋት ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹ መረጃዎች ሰጥተወል ፦
- አጣየ እና አካባቢው ስጋት ቢኖርም ትላንት እና ዛሬ አንፃራዊ ሰላም/መረጋጋት አለ/የተኩስ ድምፅ የለም።
- ከሸዋሮቢት ወጥተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።
- በአጣየ ከተማ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪው ከመመለሱ በፊት ዳግም ጥቃት እንደማይከሰት ዋስትና ስለመኖሩ ከሚመለከታቸው አካላት ውይይት ይደረጋል ተብሏል።
- በአብዛኛው ከተቃጠለችው እና ከወደመችው አጣየ ከተማ ፣ ከሸዋሮቢት የሸሹ ዜጎች በደብረብርሃን፣ መሀል ሜዳ፣ የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ተጠልለዋል።
- ከአጣየ ከተማ ጥቃት የሸሹ በርግቢ፣ ይምሎ፣ መሀልሜዳ በሚባሉ አካባቢዎች ብቻ ከ10 ሺህ - 15 ሺህ ዜጎች ይገኛሉ።
- በአጣየ በርካታ የግለሰብ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ የመንግስት ተቋማት ፈርሰዋል፣ ውሃ መብራት የለም። እስረኞች ተለቀዋል።
- የከተማው አመራሮችም ከነዋሪዎች ጋር ከተማውን ጥለው ሸሽተዋል። አመራሮች እንዲመለሱ ፣ የውሃ እና መብራት ችግር እንዲፈታ እየተሰራ ነው ተብሏል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ዛሬ ጥዋት ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹ መረጃዎች ሰጥተወል ፦ - አጣየ እና አካባቢው ስጋት ቢኖርም ትላንት እና ዛሬ አንፃራዊ ሰላም/መረጋጋት አለ/የተኩስ ድምፅ የለም። - ከሸዋሮቢት ወጥተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው። - በአጣየ ከተማ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪው ከመመለሱ በፊት…
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ፦
"...የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲህ ያለ ግጭት ውስጥ ገብቷል ብለን አናምንም። እንዲህ ያለው ግጭት መከሰት የጀመረው ከቅርብ ዓመታት ጊዜ ጀምሮ ነው።
በተለይ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ እንደ ዓመታዊ ክብረ በዓል ችግሩ እየተከሰተ ነው ያለው በ2011 ፣ በ2012 አሁን በዚህ ዓመት።
ይሄን ግጭት በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የፈጠረው ነው ብለን አናምንም።
ስለዚህ ምንድነው የሚለውን ፥ ለምን ይሄ ግጭት ሊሆን ቻለ የሚለውን እኛ የምናነሳቸው ሃሳቦች እንደተጠበቀ ሆኖ ተጎጂው ማህበረሰብ በሁለቱም በኩል ያለው ህዝብ በኦሮሞ ብሄረሰብ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ያሉ ህዝቦች ችግሩን እና ያጣላቸውን ሰው በደንብ ስለሚለዩ ፣ ያጣላቸውን አካል ስለሚለዩ እዛ ላይ በደንብ ተወያይቶ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።
የህግ የበላይነት በቀጠናው ላይ መከበር አለበት ብለን እናምናለን፥ እንጂ እዛ አካባቢ ያለው ህዝብ በብዛት ሄዶ ቤት የሚያቃጥልበት፣ አረጋውያን የሚገልበት፣ ህፃናት የሚገድልበት ስነልቦና ፀባይም፣ ቁመናም የለውም።
ዘላቂ መፍትሄውን በተመለከተ በገለልተኛ ወገን ታይቶ ለግጭቱ አነሳሽ፣ አደራጅ፣ ቀስቃሽ እና ግብዓት አቅራቢዎች አካላት ያለ ምህረት መጠየቅ አለባቸው።"
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

በቻድ ያለው አረመረጋጋት :
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቻድ የሚገኙ ዲፕሎማቶች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ።
ዲፕሎማቶቹ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት አለመረጋጋት በመፈጠሩና የቦኮ ሃራም ቡድን ታጣቂዎች እንዳሉ በመገለጹ ነው።
የሰርጎ ገቦች ጥቃት ሊኖር እንደሚችል ያመለከተው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቻድ የሚገኙ አሜሪካውያን ከነቤተሰባቸው እንዲወጡ መክሯል።
“...መንግስታዊ ያልሆኑ የታጠቁ ቡድኖች ከሰሜናዊ ቻድ ወደ ዋና ከተማዋ ጃሜና እያቀኑ ነው። ወደ ከተማዋ በመቃረባቸው ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ስጋት በመኖሩ ወሳኝ ያልሆነ ተግባር ላይ የተሰማሩ አሜሪካውያን ሰራተኞች ለቀው መውጣት አለባቸው” ብሏል።
ወደ ቻድ ለመጓዝ ዕቅድ ያላቸው አሜሪካውያንም የጉዞ እቅዳቸውን እንዲሰርዙ አሳስቧል።
በተመሳሳይም UK ዜጎቿ ቻድን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። - ENA

መፍትሄው ምንድነው ? ሀሳብዎን ያካፍሉ :
በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እጅግ በተደጋጋሚ ጊዜ የንፁሃን ግድያ ፣ ጥቃት፣ ንብረት ውድመት እየደረሰ እንደሆን ይታወቃል።
በየጊዜው እንዲህ ያሉ ነገሮች ይፈጠራሉ ፥ አንዳንዱ ለራሱ አጀንዳ ያውለዋል ከሳምንታት በኃላ የተፈፀመው ሁሉ ይረሳና ሌላ አጀንዳ ይፈጠራል ፤ ይህ አዙሪቱ ላለፉት አመታት የነበረ ዛሬም የቀጠለ ነው።
በዚህ መሃል ልጆቻውን የሚያጡ እናቶች ፣ አባቶች ፤ ወላጆቻቸውን የሚያጡ ልጆች በመሪር ሃዘን ለዓመታት ይኖራሉ ነገር ግን በየጊዜው ሌላ አጀንዳ ስለሚኖር ማንም አያስታውሳቸውም።
ይህ አዙሪት ወይም በየጊዜው የሚፈፀመው ግድያ የሚሰማው ሞት በዜጎች መኃል የሚፈጥረው ክፍተት እጅግ አደገኛ/ሊቆም ካልቻለም ለነገ አብሮነት ጥሩ ያልሆነ አሻራ የሚያሳርፍ ነው።
የንፁሃን ሞት ፣ መፈናቀል፣ ጥቃት ማስቆም የመንግስት የመጀመሪያው ስራ መሆን እንዳለበት ብዙዎች ያምናሉ፥ የራሱን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ መንግስት መንግስትነቱ ምኑ ጋር ነው ብለው የሚጠይቁም አሉ ፤ በአንፃሩ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ አመራሮች እንዳሉበት የሚያምኑ አሉ።
ነገር ግን በየጊዜው አጀንዳ ሆኖ ሁሉም በሚያምንበት ሃሳብ በኩል ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ የቃላት ምልልስ ከማድረግ ውጭ የዜጎችን ሞት መታደግ አልተቻለም።
በአንድ በኩል ስሜታዊነት ተንፀባርቆ ፣ እውነተኛ ተቆርቋሪ ሆኖ ፣ ለህዝቡ አስቦ፣ ነገ የሱም እጣፋንታ እንደሆነ አምኖ ፍትህ የሚጠይቀው እንዳለ፤ በሌላ በኩል ፍፁም ግጭቶች እንዳይቆሙ ፣ እንዲባባሱ፣ በዚህም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሰራው ኃይል ብዙ ነው።
መፍትሄው ምንድነው ? ምን ቢደረግ የንፁሃ ሞት እና ስቃይ፣ ሰቆቃ ይቆማል ? ሀሳባችሁን በጨዋ ቃላት አካፍሉ።
@TikvahDiscussionandPoll

#Ethiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 5,833 የላብራቶሪ ምርመራ 1,603 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,330 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 243,631 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,392 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 180,645 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 972 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
@tikvahethiopia

2021.04.19_MUSE_REPORT.pdf
1.3 MB
#ሪፖርት
በሩዋንዳ በ100 ቀን ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ገደማ ቱትሲዎች በተጨፈጨፉበት የ1994ቱ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ፈረንሳይ የተባባሪነት ሚና እንደነበራት የሚያመለክት የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡
የምርመራ ሪፖርቱ ይፋ የሆነው በሩዋንዳ መንግስት ቀጣሪነት ምርመራውን ባካሄደው ‘ሌቪ ፋይር ስቶን ሚዩዝ’ በተባለ አሜሪካዊ የምርመራ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ እ.ኤ.አ ከ2017 ጀምሮ ላለፉት 5 ዓመታት ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ የመጨረሻ ውጤት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
ሪፖርቱ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በመሩት እና ዛሬ በተካሄደ ልዩ የሃገሪቱ ካቢኔ ስብሰባ ነው፡፡
ቦቢ ሚዩዝ የተባሉት የመርማሪው ተቋም ባልደረባም ፥ “A Foreseeable Genocide: The Role of the French Government in Connection with the Genocide against the Tutsi” በሚል ርዕስ የተካሄደውን ምርመራ የመጨረሻ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ከ600 ገጾች በላይ ጥንቅር በሆነ ሪፖርቱ ፈረንሳይ ቱትሲዎች ሰለባ በሆኑበት ጭፍጨፋ የ ‘ተባባሪነት ሚና’ እንደነበራት አስቀምጧል፡፡
“ተገማች የነበረው ጭፍጨፋ እውን እንዲሆን ፈረንሳይ ‘የጎላ ሚና’ ነበራት ነው ሪፖርቱ ያለው፡፡ ይህን ሪፖርት ለማጠናቀር በሚሊዬን የሚቆጠሩ የሰነድ ማስረጃዎች ተመርምረዋል፡፡ የ250 ምስክሮች ቃል ተደምጧል፡፡
#Republic_of_Rwanda #AlAIN

ያኔዝ ሌናርቺች ነገ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።
[www.ethiopiainsider.com]
የአውሮፓ ህብረት የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌናርቺች ፤ ነገ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ አስታወቁ።
የውይይታቸው ዋነኛ ትኩረት በትግራይ ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
ነገ አዲስ አበባ የሚገቡት ሌናርቺች ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።
“በትግራይ የተቀሰቀሰው ግጭት ቀድሞም በኢትዮጵያ አስቸጋሪ የነበረውን ሁኔታ አባብሶታል” የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ “ምግብ፣ የደህንነት ጥበቃ፣ ጤና እና መጠለያን ጨምሮ ሰብዓዊ ፍላጎቶች እየጨመሩ ነው” ሲሉ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ ባወጡት መግለጫ ላይ አንስተዋል።
“በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች ሁከት እየጨመረ ነው። በትግራይ ያለው ሁኔታ ጥቂት መሻሻል ቢያሳይም አሁንም የከፋ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዕርዳታ ይፈልጋሉ” ያሉት ሌናርቺች በተለይ በትግራይ ክልል ዕርዳታ ለሚሹ ሰዎች ድጋፍ የሚደርስበትን ሁኔታ ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ በዛሬው መግለጫቸው፤ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እጅግ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የሚውል ከ53 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ተጨማሪ ዕርዳታ ማጽደቁንም አስታውቀዋል።
ገንዘቡ በግጭት እና የከባቢ አየር ለውጥ ለችግር ለተጋለጡ ለተፈናቀሉ እና የተፈናቀሉትን ላስጠለሉ ማህበረሰቦች የሚውል መሆኑን ገልፀዋል።

#GERD 🇪🇹 #UNSC
ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ፅፋለች።
ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለወቅቱ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በላኩት ደብዳቤ ኢትዮጵያ ፦
- በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ያላትን የፀና አቋም አስረግጣ ገልፃለች።
- ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አስተዳደርን በማስመልክት ወደሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲመለሱ፤ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት እንዲያከብሩ ሊያስስቧቸው ይገባል ብላለች።
- በኢትዮጵያ በኩል ጥልቅ ፍላጎት ቢኖርም ፤ግብፅ እና ሱዳን ሁሉንም ሀገራት ተጠቃሚ ወደሚያደርገው መፍትሄ ለመምጣት በሚያስችል ቅን ልቦና እየተደራደሩ አይደለም ብላለች።
- ግብፅ እና ሱዳን ድርድሩን “በማኮላሸት” እና ጉዳዩን “ዓለም አቀፍ በማድረግ” በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደርን መምረጣቸውን ገልፃለች።
- ሃገራቱ በአስገዳጅ ስምምነት ስም ኢ-ፍትሐዊ ሁኔታዎችን ለማስጠበቅ እና በግድቡ ውሃ እንዳትጠቀም ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ገልፃለች።
- የሶስቱ ሃገራት መሪዎች እ.ኤ.አ በ2015 በሱዳን ካርቱም ለፈረሙት የመርሆዎች ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነትም ገልጻለች ግብጽ እና ሱዳን በስምምነቱ የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸውን ጠቁማለች።
- ጫና ለማድረግ የሚደረጉ የትኛውም ዓይነት ሙከራዎች እና ድርድሩን ከህብረቱ ውጭ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች በሃገራቱ መካከል ያለውን መተማመን የበለጠ እንደሚጎዱ ገልፃለች። [Al AIN]

የተቃውሞ ሰልፎች በአማራ ክልል :
አንድም ከሰሞኑ በአጣዬ እና አካባቢው ላይ በሌላ በኩል በተደጋጋሚ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች [በኦሮሚያ ወለጋ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል፣ ደቡብ ጉራፈርዳ] በአማራ ማንነታቸው ዜጎች ላይ የሚፈፀምን ግድያ ፣ ማፈናቀል ፣ ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰልፎቹ በባሕር ዳር ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ ፣ በኮምቦልቻ ፣ በወልደያ ከተሞች ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በሰልፎቹ ላይ መንግስት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ፣ እንዲሁም የችግሩ አካል ሆኖ በመገኘቱም ጭምር እየተወገዘ መሆኑን በሰልፉ ላይ የተገኙ አባላት አሳውቀዋል።
የዜጎችን ደህንነት መንግስት ሊጠብው ይገባል ፥ የንፁሃን ግድያ ፣ ማፈናቀል በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብለዋል።
ትላንት በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመሳሳይ ይዘት እና ሃሳብ ያለው ፣ ወገኖቻችን በማንነታቸው አይገደሉ፣ አይሳደዱ የሚሉ ሰልፎች መካሄዳቸውን በ @tikvahuniversity በኩል መገለፁ አይዘነጋም።

የትራፊክ ቅጣት በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ !
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ቅጣትን በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ።
መተግበሪያው የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣን እንዲሁም ቀልጣፋ በማድረግ አሽከርካሪዎችን ከእንግልት የሚታደግ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጅሬኛ ሄርጳ ተናግረዋል፡፡
የትራፊክ ደንብን የተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ባሉበት ቦታ ሆነው መክፈልም ይችላሉ ተብሏል፡፡
ክፍያውን በኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክና የኢ-ብር አገልግሎት በሚሰጡ የግል ባንኮች በኩል መፈጸም እንደሚቻልም መገለፁን ኢዜአ አስነብቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ቅጣትን በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ።
መተግበሪያው የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣን እንዲሁም ቀልጣፋ በማድረግ አሽከርካሪዎችን ከእንግልት የሚታደግ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጅሬኛ ሄርጳ ተናግረዋል፡፡
የትራፊክ ደንብን የተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ባሉበት ቦታ ሆነው መክፈልም ይችላሉ ተብሏል፡፡
ክፍያውን በኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክና የኢ-ብር አገልግሎት በሚሰጡ የግል ባንኮች በኩል መፈጸም እንደሚቻልም መገለፁን ኢዜአ አስነብቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በቻድ ያለው አረመረጋጋት : የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቻድ የሚገኙ ዲፕሎማቶች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ። ዲፕሎማቶቹ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት አለመረጋጋት በመፈጠሩና የቦኮ ሃራም ቡድን ታጣቂዎች እንዳሉ በመገለጹ ነው። የሰርጎ ገቦች ጥቃት ሊኖር እንደሚችል ያመለከተው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቻድ የሚገኙ አሜሪካውያን ከነቤተሰባቸው እንዲወጡ መክሯል። “...መንግስታዊ…
#BREAKING
የቻድ ፕሬዜዳንት ተገደሉ።
ላለፉት 30 ዓመታት ቻድን የመሩት ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺ ኃይሎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ማስታወቁን አል ዓይን ዘግቧል።
ፕሬዝደንቱ የመንግስት ኃይሎች ከአማጺያን ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ተመተው መገደላቸውን ነው መከላከያ ሠራዊቱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው፡፡
ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡
ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ፣ በቻድ ምርጫ እስካሁን ከተቆጠረው 80 በመቶ ድምጽ ከ79 በመቶ የሚሆነውን በማግኘት ማሸነፋቸው በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኖ ነበር፡፡
የቻድ አማጺያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና ከትናንት ጀምሮ በመቅረብ ላይ እንደነበሩ የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡

* የማይጣጣሙት የመንግስት አካላት መረጃዎች ፦
ከሳምንታት በፊት በተፈጠረው ግጭት ፦
የሰሜን ሸዋ ዞን :
ለተፈፀመው ጥቃት፣ ግጭት ንብረት ውድመት "ኦነግ ሸኔ" ን ተጠያቂ ነው።
በተፈፀመው ጥቃት በርካቶችን ተፈናቅለዋል ፣ ተገድለዋል ፣ ንብረት ወድሟል ፣ይህ ሲሆን ጥቃት ያደረሱት አካላት የተደራጁ እንዲሁም ዘመናዊ መሳሪያ ጭምር የታጠቁ ናቸው።
ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ፦
በተለይ ከሰሜን ሸዋ ጋር የሚዋሰነው ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ "ኦነግ ሸኔ" ጥቃት ፈፀመ የሚባለውን አይቀበልም ፥ በአርሶ አደሮች መካከል የተፈጠረ ግጭት ነው ይላል።
ወረዳው ፦ 68 ሰዎች መገደላቸውን ፣ 114 መቁሰላቸውን ፣ 815 ቤቶች ፣ ት/ቤቶች ፣ ጤና ተቋማት መቃጠላቸውን ሪፖርት አድርጎ ነበር፤ በተጨማሪ ከ40 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተፈናቅለው በ3 ጊዜያዊ መጠለያ ይፋ አድርጎ ነበር።
ልብ በሉ : ከሳምንታት በፊት በዚሁ አካባቢ የነበረውን ሁኔታ የሚገልፅ ዝርዝር ሪፖርት ሳይቀርብ፣ ምርመራ ሳይደረግ ነው፣ የገዳት መጠን ሳይታወቅ ነው ዳግመኛ የሰሞኑ ሁኔታ የተፈጠረው።
ከሰሞኑ የፈጠረውን ሁኔት በሚመለከት ፦
የአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ/የሰላም እና ህዝብ ደህንነት ቢሮ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር :
ሰሞኑን ዳግም በአካባቢው ለተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ "ኦነግ ሸኔ" ነው።
የሰላም እና ደህንነት ቢሮ ፥ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ እና አካባቢው "ኦነግ ሸኔ" ፈፅሞታል ባለው ጥቃት ከባድ ጉዳት መድረሱን በመግለፅ ፥ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ :
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጀማል ሁሴን ፥ የሰሞኑ በአጣዬ የተፈጠረው ችግር መነሻ አንድ የሱቅ ጠባቂ በአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል በመግደሉ ነው ብለዋል።
"ባለሱቁ ከተገደለ በኃላ ሁሉም ወደየቤቱ እየሄደ ጠመጃቸውን ይዘው ወጡ ግጭቱም በዚህ መልኩ ነው የተጀመረው" ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ጀማል ሁሴን ፥ ከአማራ ክልል የፀጥታ አካላት ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት ሲቪሎች መሆናቸውን በማመልከት ነው።
በአንድ የጤና ጣቢያ ውስጥ ብቻ 53 የቆሰሉ ሰዎች መመልከታቸውን 18 ሰዎች መገደላቸውን ገልፀዋል።
** ትዕግስታችን ተሟጧል የሚሉት የተቃውሞ ሰልፈኞች ፦
በተለያዩ የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች የአማራ ማንነትን ምክንያት አድርጎ በሀገሪቱ የሚፈፀሙ ግድያዎችን ፣ ማፈናቀል የሚያወግዙ ሰልፎች ከትላንት ጀምሮ እየተደረጉ ነው።
ሰልፈኞች ለንፁሃን ዜጎች ደህንነት አለመጠበቅ መንግሥትን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ትዕግስታቸው ተሟጦ ማለቁን እና የሚፈፀመው በደል ባለመቆሙ አደባባይ መውጣታቸውን ገልፀዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-20

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
እርስ በእርሱ የማይጣጣመው የመንግስት አካላት መረጃ ፦ ከሰሞኑን በአጣየ እና አካባቢው በተፈፀመው ጥቃት እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሞተዋል [ሲቪሎች እና የፀጥታ ኃይሎች] ፣ እጅግ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል፣ በተለይ በአጣየ ከተማዋ ወድማለች፣ ንብረት ተዘርፏል፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በእሳት ጋይተዋል። የሚፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶችን አስቆጥተው ወደ አደባባይ…
ሸይኽ ሁሴን በድንገተኛ የልብ ህመም አረፉ።
በታላቁ አንዋር መስጊድ ምክትል ኢማም የነበሩት ሸይኽ ሁሴን በድንገተኛ የልብ ህመም አርፈዋል።
የሶላተል ጀናዛ ነገ ሮብ ሚያዝያ 13 (ረመዷን 9) ዙህር ላይ አንዋር መስጊድ ይሰገዳል ፤ የቀብር ስርአታቸውም ኮልፌ በሚገኘው መቃብር ይፈፀማል።
መረጃው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በታላቁ አንዋር መስጊድ ምክትል ኢማም የነበሩት ሸይኽ ሁሴን በድንገተኛ የልብ ህመም አርፈዋል።
የሶላተል ጀናዛ ነገ ሮብ ሚያዝያ 13 (ረመዷን 9) ዙህር ላይ አንዋር መስጊድ ይሰገዳል ፤ የቀብር ስርአታቸውም ኮልፌ በሚገኘው መቃብር ይፈፀማል።
መረጃው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ኦንላይን_የመራጮች_ምዝገባ_ስርዓት_መምሪያ.pdf
2.2 MB
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁን ፥ ይህንንም ሂደት ለፓለቲካ ፓርቲዎች ማቅረቡ እና ምክክር እንደተደረገበት አስታውሷል።
በዚህም መሰረት ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እስከ ሚያዝያ 26/2013 ዓ/ ም ድረስ በኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
የመመዝገቢያ ሊንክ - https://www.nebe.org.et/ovrs
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁን ፥ ይህንንም ሂደት ለፓለቲካ ፓርቲዎች ማቅረቡ እና ምክክር እንደተደረገበት አስታውሷል።
በዚህም መሰረት ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እስከ ሚያዝያ 26/2013 ዓ/ ም ድረስ በኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
የመመዝገቢያ ሊንክ - https://www.nebe.org.et/ovrs
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በአንድ ቀን 47 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞቱ።
ባለፉት 24 ሰዓት 47 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 7,346 የላብራቶሪ ምርመራ 1,524 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,290 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 245,155 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,439 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 181,935 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 965 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦
[ በ Purpose የቀረበ ]
- ትላንት በመላው ዓለም 825,088 ሰዎች ለቫይረሱ ታጋላጭ መሆናቸው ሲረጋገጥ ፤ 13,914 ሰዎች ሞተዋል።
- ህንድ ከሰሞኑን በቀን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት እያደረገች የምትገኝ ሲሆን ትላንት ብቻ 294,390 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች፤ በ24 ሰዓት 2,020 ሰዎችም ሞተዋል።
- በብራዚል በ24 ሰዓት 3,481 ሰዎች ሲሞቱ፥ 73,172 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች።
- በ24 ሰዓት በርካታ ሰዎችን ከሞቱባቸው ሀገራት መካከል : አሜሪካ 863 ፣ ፖላንድ 601 ፣ ኢራን 395 ፣ ፔሩ 417፣ ዩክሬን 367 ፣ ሩሲያ 379 ፣ ፈረንሳይ 375 ፣ ጣልያን 390 ፣ ቱርክ 346 ይጠቀሳሉ።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች 143,577,735 ደርሰዋል፤ ከነዚህ መካከል 3,058,230 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል 121,953,574 አገግመዋል።
- በአፍሪካ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 4,489,169 የደረሰ ሲሆን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ኬዝ በማስመዝገብ ደቡብ አፍሪካ በ1,568,366 ቀዳሚ ናት፣ ሞሮኮ በ506,669 ፣ ቱኒዝያ በ289,230 ፣ ኢትዮጵያ በ245,155 ይከተላሉ።
- ክታባት : የኤስራኤል 56 በመቶ ህዝብ የኮቪድ-19 ክትባት ወስደዋል፣ በአሜሪካ ከአጠቃላዩ ህዝብ ውስጥ ከግማሽ የሚበልጥ ቢየንስ የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል፣ ቻይና በተያዘው ዓመት ከ3 ቢሊዮን በላይ ክትባት እንደምታመርት አሳውቃለች።

#ምርጫ2013 አጫጭር መረጃዎች ፦
- የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ምዝገባ ዙሪያ ዜጎች የሚኖራቸውን ጥያቄ የሚያቀርቡበትን ነፃ የስልክ መስመር ይፋ አድርጓል ፤ የነፃ የስልክ መስመሩ 778 ሲሆን ዜጎች በመራጮች ምዝገባ ዙሪያ ጥየቃያቸውን በአማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ማቅረብ ይችላሉ።
- የአውሮፓ ህብረት የውጭና የደህንነት ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ግንቦት ወር ለሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በሀገሪቱ የሚታየው የጸጥታ ችግር ተባብሶ እስካልቀጠለ ድረስ የምርጫ ታዛቢ ልዑካንን ለመላክ መወሰናቸውን ለህብረቱ ም/ቤት ገልፀዋልም። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት ከምርጫው በፊት ሀገራዊ ንግግር ለማድረግ ቁርጠኝነቱን ማሳየት አለበት ብለዋል።
- በአፋር ክልል በ1 ሺ 432 ጣቢያዎች ከላፈው አርብ ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
- የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ይቀረዋል። ምዝገባው ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ይጠናቀቃል። እስካሁን ምን ያህል መራጮች እንደተመዘገበ ዝርዝር መረጃ ባይኖርም የመራጮች ምዝገባው አሁንም ቀጥሏል።
- ምርጫ ቦርድ ምርጫውን መዘገብ ለሚፈልጉ ሚዲያዎች በ2ኛ ዙር ያቀረበው የማመልከቻ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀሩታል። አስፈላጊ ሰነድ ማሟላት የሚችሉና ምርጫውን መዘገብ የሚፈልጉ ሚዲያዎች ከሚያዚያ 7 ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት እንዲያመለክቱ ጥሪ መቅረቡ ይታወቃል። የማመልከቻ ቅፅ: bit.ly/3uTTxJW
- ደቡብ ክልል ለምርጫው ይመዘገባሉ ከተባሉ 7.9 ሚሊየን መራጮች መካከል ከ3.6 ሚሊየን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የክልሉ ፕሬዜዳንት ተናግረዋል።
ተጨማሪ :
አንድ ምርጫ ጣቢያ መመዝገብ የሚችለው 1500 ሰው ብቻ ነው ለምን ? ያንብቡ : telegra.ph/NEBE-04-21

Photo
ለሶስተኛ ቀን የቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ በአማራ ክልል :
በአማራ ክልል የ "አማራ ማንነትን" መሰረት ያደረገ ግድያ ፣ ማሳደድ ፣ ጥቃት፣ ማፈናቀል፣ ይቁም በሚል የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም ለ3ኛ ቀን ቀጥሏል።
ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ካስተናገዱ ከተሞች አንዷ የደብረብርሃን ከተማ ናት። በከተማይቱ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል።
ግድያዎችና ማፈናቀሎች እንዲቆሙ፣ የእናቶችና ህፃናት ሞት እንዲቆም ተጠይቋል። ሰልፈኞቹ መንግስትን ወቅሰዋል አውግዘዋል። ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው እየተካሄደ ያለው።
በተመሳሳይ ዛሬ በላሊበላ ዘር ተኮር የሆነ ግድያ ፣ ስቃይና መፈናቀል እንዲቆም የከተማዋ ማህበረሰብ አደባባይ ወጥቶ የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል።
በሰልፉ ላይ ገዢውን ፓርቲና መንግስት፣ አመራሮችን በእጅጉ የሚኮንኑ የሚያወግዙ መልዕክቶችም የተላለፉ ሲሆን በሌላ በኩል ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ህክምና መከልከላቸው የተቃወሙ ወጣቶች የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ባነሮችን ይዘው በመውጣት ድርጊቱን አውግዘዋል።