TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Share

"የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት ምንም ዓይነት የኮቪድ 19 ቅድመ ላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ አያስፈልግም" - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ምሽት ባሰራጨው መልዕክት የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር በታቀደው መሰረት በመላው ኢትዮጵያ መሰጠት መቀጠሉን ገልጿል።

እስካሁን ባለው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች ተከትበዋል።

እድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከ55-64 ዓመት ሆነው የሚታወቅ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የኮቪድ 19 ክትባትን ማግኘት ይጀምራሉ፡፡

ጤና ሚኒስቴር ክትባቱን ለመውሰድ የኮቪድ- 19 የቅድመ ላብራቶሪ ምርመራ ያስፈልጋል እና ሌሎች ክትባቱን በተመለከተ የሚነገሩት ነገሮች ማህበረሰቡ ትክክል እንዳልሆኑ በመገንዘብ የክትባቱን እንዲወስድ ፥ ከአላስፈላጊ ወጪ አልፎም ከሚፈጠረው ትርምስ እንዲሁም አካላዊ ንክኪ እንዲቆጠብ ብሏል።

@tikvahethiopia
"ለእናቶች ደም እንለግስ" - የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒተል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ 'ለእናቶች ደም እንለግስ' በሚል ከፊታችን መጋቢት 30 እስከ ሚያዚያ 2 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የደም ልገሳ መርሃግብር ማዘጋጀቱን አሳውቆናል።

የደም ልገሳው መጋቢት 30 ፣ ሚያዚያ 1 እና ሚያዚያ 2 ሲሆን 5ኛ በር አካባቢ ነው የሚደረገው።

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የአ/አ ቲክቫህ አባላት በተባሉት ቀናት እና ቦታ በመገኘት ለእናቶች ደግም እንድትለግሱ መልዕክት አስተላልፎላችኃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ከዛሬ ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በማኅበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸው በአማራጭ ጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምዝገባ ይጀምራል። የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ መመዝገብ ትችላላችሁ። aahdab.gov.et በሚለው የቢሮው አድራሻ በኦንላይን ነው መመዝገብ የሚቻለው። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...በ4 ቀናት 3000 ነዋሪዎች ተመዝግበዋል" - የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ በቅርቡ በ20/80 እና በ40/60 ፕሮግራም ሙሉ ክፍያ ከፍለው ቤት ለማግኘት እየተጠባበቁ ላሉና 70 በመቶ መክፈል የሚችሉ ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው መኖሪያ ቤት መገንባት እንዲችሉ አማራጭ አቅርቦ ነበር።

ቢሮው ፥ ለግንባታው የሚሆን መሬት በ5 ክፍለ ከተሞች እነዚህም በአዲስ ከተማ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በኮልፌ ቀራንዮና በቦሌ ክፍለ ከተሞች መዘጋጀቱን አሳውቋል።

የመጀመሪያ ዙር ከ100 እስከ 130 ማህበራት ለማደራጀትና 10 ሺ የሚደርሱ ቤት ፈላጊ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው የተባለ ሲሆን ምዝገባው በተጀመረ ባሉት አራት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ3,000 በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል ተብሏል።

የቤት ግንባታው የሚከናወነው በ2 አይነት መንገድ ነው ፦ አንደኛው እስከ 9 ፎቆች፣ ሁለተኛው ደግሞ 13 ፎቆች መሆኑ ተገልጿል፤ የግንባታ ሥራው በ18 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ማህበራቱ በፈለጉት ኮንትራክተር ማስገንባት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ መግለፁን ኢፕድ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅሌ ጥሙጋ የሰዓት እላፊ ገደብ ታወጀ።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት፥ የአካባቢውን ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥ እንዲቻል በወረዳ ደረጃ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አሳውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ የሰው እና የባጃጅ እንቅስቃሴ የምሽት የሰአት አለፊ ገደብ አስቀምጧል።

በዚህም መሰረት ባጃጅ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ሲሆን ሰዎች ደግሞ እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ብቻ መንቀሳቀስ የሚችኑ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።

ከተጠቀሰው ሰአት ውጭ የሚንቀሳቀስ ሰውም ሆነ ባጃጅ ካለ የህግ እርምጃ እደሚወሰድበት የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጢስ ዓባይ ባህር ዳር የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ስርቆት ተፈፀመበት ! ከጢስ ዓባይ የውሃ ኃይል ማመንጫ ወደ ባህር ዳር የተዘረጋው ባለ 132 ኮሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ላይ ስርቆት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ። ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በተፈፀሙ ስርቆቶች 8 ምሰሶዎች ወድቀዋል፡፡ ይሁንና በአካባቢው ኃይል እንዳልተቋረጠ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ምሰሶዎቹ በመውደቃቸው…
ዘራፊዎቹ ተያዙ።

ከጢስ ዓባይ - ባህር ዳር በተዘረጋው የባለ 132 ኮሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ምሰሶዎች ላይ ስርቆት የፈፀሙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ከሰረቁት ንብረት ጋር እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተሰምቷል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ኃይሎች በሰጠው ጥቆማ ምሰሶውን በመቆራረጥ በማዳበሪያ ጠቅልለው ከመሸጣቸው በፊት በአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች የተያዙ ሲሆን ከወንጀሉ ጋር የተገናኙ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ምርመራ ቀጥሏል ተብሏል።

በጢስ ዓባይ - ባህር ዳር ባለ 132 ኮሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ምሰሶዎች ላይ የተፈፀመው ስርቆት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ኪሳራ ዳርጎታል።

ከዘረፉት ንብረት ጋር እጅ ከፍንጅ የተያዙት ግለሰቦች ምን አይነት ቅጣት ይጠብቃቸው ይሆን ? የኢነርጂ አዋጁ ምን ይላል : telegra.ph/Ethiopian-Electric-Power-04-03

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በመራጭነት ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል? መምረጥ የማይችሉ ዜጎች አሉ ?

ለመራጭነት ለመመዝገብ ፦

- ኢትዮጵያዊ ዜግነት

- እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ

- 6 ወራት ነዋሪነት

- ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ ወይም ነዋሪነት የሚያውቁ ምስክሮች

በመራጭነት መመዝገብ የማይችሉ ፦

- በአዕምሮ ሕመም ሳቢያ የመወሰን አቅም ውስንነት ያለባቸው

- የእስር ፍርደኞች

- የመምረጥ መብታቸው በሕግ የተገደበባቸው

#CARD

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በአንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ የዘረፋ ሙከራ ተደርጓል" - ወ/ሪት ሶሊያና

የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ከሰሞኑን አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ምርጫ ጣቢያ ላይ የዘረፋ ሙከራ መደረጉን ተናግረዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና እንደተናገሩት ፥ የምርጫ ጣቢያው ቢሮው ተከፍቶ "ብሉ ቦክስ" / እቃዎች ታሽገው የተቀመጡበት ሳጥን ተወስዶ 100 ሜትር ርቀት ላይ ተገኝቷል።

በሙከራው ምንም የተወሰደ ንብረት የሌለ ሲሆን ሳጥኑ እንደታሸገ ነው የተገኘው። እቃው ተመልሶ ምርጫ ጣቢያው ስራውን ቀጥሏል።

በዚህ ጉዳይ ምርጫ ቦርድ ከከተማው አስተዳደር እና ከፖሊስ ጋር የተነጋገረ ሲሆን እንዲህ ያለ ነገር ዳግም እንዳይፈጠር ምርጫ ጣቢያ አካባቢ ጥበቃ እንዲጠናከር አሳስቧል።

በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደመና ተስፋዬ ፥ ከሰሞኑን አንድ ምርጫ ጣቢያ በሩ ተከፍቶ ንብረት መወሰዱን እና የተወሰደውን ንብረት ሁሉንም ማግኘች መቻሉን እና ወደምርጫ ጣቢያው ምንም ቁሳቁስ ሳይጎድል እንዲመለስ ማድረግ መቻሉን አሳውቀዋል።

በምርጫ ጣቢያው ላይ ይተፈፀመው ተራ ዘረፋ ? ወይስ ሌላ ተልዕኮ ያለው ? በሚል የተጠየቁት የመምሪያው ኃላፊ ፥ "ዘረፋ ነው አይደለም፤ ሌላ ነገር ሆኖ ምርመራ ጀምረን እውነት የሚመስሉ ነገሮችን አግኝተናል" ብለዋል። ይህን ሊሉ የቻሉት ምርመራው በሂደት ላይ ስለሆነ እርግጠኛ መሆን ስላልተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

አሁን ላይ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የጥበቃው ሁኔታ መጠናከሩን አሳውቀዋል።

መረጃውን ያገኘነው ከሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"... በሁለት ተርባይኖች በአመቱ መጨረሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ስራ እንዲጀመር እየተሰራ ነው" - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምስረታ 10ኛ ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች በዓመቱ መጨረሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት እንዲጀምሩ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ፥ ግድቡ 79 በመቶ ያህል መድረሱን ገልፀው ፥ በዚህ ዓመት የውሃ ማስተላለፊያ ፥ ወደ ታችኛው ተፋሰሶች የሚያስተላፍ የውሃ ማስወጫ ስራዎች በስፋት የሚሰራበት ነው ብለዋል።

በተጨማሪ ይህ ዓመት 11ዱን ተርባይኖች ማንሳት የሚችሉ የብረት ስራዎች እየተሰሩ ያሉበት መሆኑንና የግድቡን ቁመት ለማሳደግ የኮንክሪት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራሉ ሰራዊት በ8 ግንባሮች ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረጉ ፤ መስዋእትነት እየከፈሉ ነው" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሩቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን አይችሉም ብለው የሚያስቡ ኃይሎች ሽፍቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያን ለመከፋፈል እየሰሩ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ምርምር ማእከል ደመናን ወደ ዝናብ የመቀየር ቴክኖሎጂን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ጠ/ሚሩ ፥ "በሩቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን አትችሉም ስለዝናብ ስለ ግድብ አታስቡ እናተ በበሬ እያረሳችሁ የጎደላችሁን ስንዴ እኛ እየረዳናችሁ መኖር ብቻ ነው የተፈቀደላችሁ የሚሉ ኃይሎች ከውስጥ ከተገዙ ሽፍቶች ማንነታቸውን የማያውቁ ሽፍቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን እርስ እርስ ለማባላት እና ለማከፋፈል ቀን ከሌት እየሰሩ ይገኛሉ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው 'ሽፍቶችን' እየተጠቀሙ ነው ያሉትን እና ኢትዮጵያውያን አይችሉም የሚሉት ኃይሎች እነማን እንደሆኑ ስም ጠቅሰው አልተናገሩም።

ነገር ግን ተላላኪ የተባሉትን ኃይሎች እና አሸባሪዎችን ጠራርጎ ማጥፋት ከተቻለ ዋናው የላከውን ኃይል መጋፈጥ እና ፍላጎቱን መገንዘብ የሚቻልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ባደረጉት ንግግር የሀገር መከላከያ እና የፌዴራል ሰራዊት በ8 ግንባሮች ፀረ አርሶ አደረ፣ ፀረ ንፁሃን ዜጎች የሆኑ በሰሜን በምዕራብ ተሰልፈው ኢትዮጵያን ሊያባሉ ከተነሱ ኃይሎች ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረጉ እና መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ ሲሉ ተደምጠዋል።

More : telegra.ph/PM-Dr-Abiy-Ahmed-04-03

@tikvahethiopia
ፔካ ሐቪስቶ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።

By : www.ethiopiainsider.com

የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የፊንላንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሐቪስቶ “በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተለይ የትግራይ ክልል ቀውስ እና በቀጠናው ባለው አንድምታ ላይ ለመወያየት” በድጋሚ ወደ አ/አ እንደሚያቀኑ የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል

ሚኒስትሩ ከሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኋላ ፤ የተመለከቷቸውን ጉዳዮች የያዘ ሪፖርት በሚቀጥለው ወር ለሚካሔደው የአውሮፓ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያቀርባሉ ተብሏል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ፤ ሐቪስቶ “ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ተገናኝተው የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም ያለውን ስጋት” ያስረዳሉ።

በዚሁ ጉዟቸው “ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ፣ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እና የስደተኞች መብቶች ጥበቃ ህግጋት እንዲያከብሩ እንዲሁም ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ገለልተኛ ምርመራ እንዲከናወን እንዲፈቅዱ ” ጥሪ እንደሚያቀርቡ በመግለጫው ተመልክቷል።

ሐቪስቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሚያነሱት ሌላው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣት የተመለከተ እንደሆነ መግለጫው ላይ ጠቅሷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Attention😷

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት 21 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,392 የላብራቶሪ ምርመራ 1,997 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,297 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 213,311 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,936 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 161,226 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 818 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ግልገልበለስ ከተማ እንቅስቃሴ ቆሟል።

የግልገልበለስ ቲክቫህ አባላት በአካባቢያቸው ስላለወቅታዊ ሁኔታ ሪፖርት ልከዋል።

ከትላንት ጀምሮ ገልገልበለስ ጭር እንዳለች መሆኑን ገልፀዋል ፤ አልፎ አልፎ ከሚታይ የሞተር እንቅስቃሴ ውጭ ፤ የንግድ ተቋማት ዝግ ናቸው ፣ገበያ የለም ቆሟል ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፣ ከከተማ የሚወጣ ሆነ የሚገባ የህዝብ ትራንስፖርት የለም ፤ ክፍት የስራ ቦታም የለም በአጠቃላይ የከተማዋ እንቅስቃሴ ቆሟል።

ባንክ ቤቶች ስጋት ስላለባቸው ተዘግተዋል ፤ ATM አገልግሎት ግን አልቆመም።

ነዋሪው እንቅስቃሴ ያቆመው ጥያቄ ስላለው ነው ያሉት የግልገልበለስ አባላት ፥ "ሞት በቃን፣ ስደት በቃን፣ ግድያ በቃ፣ የሰላም እጦት በቃን ዘላቂ መፍትሄ ይፈለግልን" የሚል ነው።

በዚህ እንቅስቃሴ ማቆም ዋነኛው ማህበረሰቡ ማስተላለፍ የፈለገው እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎች አለመቆማቸው፣ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ፈተና መሆኑ፣ እንደዜጋ የመከበር እና በሰላም የመኖር ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳሰብ እንደሆነ የግልገልበለስ አባላት ገልፀዋል።

ከግልገልበለስ አባላት መካከል በስልክ ያገኘናቸው አባል ፥ "ጥያቄያችን ሰላማዊ ነው ፥ ስለምን ሞት ፣ ግድያ ፣ መፈናቀል አይበቃም ? ለዚህ ሰላማዊ ጥያቄያችን ደግሞ መልስ እንፈልጋለን ፤ ዛሬ አንዳንድ ተቋማትን የፀጥታ ኃይሎች በኃይል ለማስከፈት ሞክረው ነበር ግን ነዋሪው ጥያቄውን የሚመለከተው አካል ተረድቶት መፍትሄ እንዲሰጠው ይፈልጋል" ብለዋል።

ከላይ የተያያዙት 3 ፎቶዎች የዛሬውን የግልገል በለስ ውሎ የሚያሳዩ ሲሆን በአባላችን BR ተነስተው በ @tikvahethiopiaBOT የተቀመጡ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የG7 ሀገራት መግለጫ ፡ የካናዳ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ጃፓን ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩኤስኤ የሚገኙበት የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የትግራይን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ የጋራ መግለጫ አወጡ። በመግለጫው የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ፣ በቅርቡ ሪፖርት የተደረጉ በትግራይ የተፈፀሙ…
የኢፊድሪ መንግስት ለG 7 መግለጫ ምላሽ ሰጠ !

የትግራይ ክልልን አስመልክቶ በቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የወጣው መግለጫ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ ጉልህ እርምጃዎችን ያላገናዘበ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ትላንት ባወጣው መግለጫ መንግስት በክልሉ የተከሰተውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ በርካታ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ሆኖም የቡድን 7 አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሰጠው ማግለጫ ይህን ከግንዛቤ ሊያስገባ አልቻለም ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡

ሚኒስቴሩ ፣ “ባለፈው ሳምንት እንደተገለጸው በሕወሓት ቀስቃሽነት ድንበር አቋርጠው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች አሁን ለቀው መውጣት የጀመሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይል ብሔራዊ ድንበሩን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል” ብሏል፡፡

መንግስት የሚዲያ ተቋማትን ጭምሮ ለሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለተገደብ እንቅስቃሴ ፈቃድ ቢሰጥም ከአለም አቀፉ ማሕበረሰብ እየቀረበ ያለው እርዳታ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመልክቷል፡፡

በክልሉ ተፈጽሟል ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ምርመራ እነዲያደርጉ ፈቃድ የተሰጣቸው ሲሆን ሥራቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስፍሯል፡፡

እንዲሁም መንግስት ከ4.2 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ተረጂዎች እረዳታ ማቅረቡን ያስታወሰው መግለጫው ከዚህ ውስጥ ከአለም አቀፍ ማሕበረሰብ የተገኘው የዕርዳት መጠን ከአንድ ሶስተኛ በታች መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም በክልሉ ያለው ችግር ሙሉ በሙሉ እና በወቅቱ እንዲቀረፍ ከተፈለገ በቂ የእርዳታ አቅርቦትን ማሰባሰበ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ መግለጫው ማመልከቱን ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT
የተማሪዎችን ቅበላ እና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል !

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጅቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ዋና ዳይሬክተር ተሻለ በሬቻ ለኢፕድ እንደገለፁት፣ ዩንቨርሲቲው የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት አዘጋጀቶ ለኢፊድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲፀድቅ አቅርቧል።

በዚህም በቅርቡ ፀድቆ ዩንቨርሲቲው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምር ገልጿል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ፤ ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መቀበል የሚጀምር ሲሆን ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሚሰጥ የመግብያ ፈተናም እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።

በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ ዲግሪ እንደሚያስተምርም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። #EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ዛሬ ማምሻውን በላከልን መልዕክት ነባር ተማሪዎቹ ከመጋቢት 28-30/2013 ድረስ ወደዩኒቨርስቲው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል። ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ፦ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የሆናችሁ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲው በወሰነው መሰረት የመግብያ ቀን መጋቢት 28-30/2013 ዓ/ም መሆኑ ኣውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው…
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ተራዘመ።

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በ1 ሳምንት መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው መግቢያው የተራዘመው ፥ "አንዳንድ ያልተሟሉ ግብዓቶችን በበቂ ለማቅረብ ሲባል" ነው ብሏል።

መጋቢት 28-30 የነበረው ወደ ዩኒቨርስቲው የመግቢያ ቀን ወደ ሚያዝያ 5-7/2013 ነው የተራዘመው።

መረጀው የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ረጂስትራር እና MoSHE ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT